Sunday, 13 October 2019
Sunday, 6 October 2019
ሾላኮቹ (የመጨረሻ ክፍል)
Please read in PDF
ምን እንድርግ?
በባለፉት ጊዜያት እጅግ መልካም ነገሮችን በማንሣት በዚህ ርእስ ሥር ስናጠና
ቆይተናል፤ ሾላኮችን ጠባያቸውንና ኹለንተናዊ ባሕርያቸውን አንስተንም ተመልክተናል፤ ከዚህ በመቀጠል ደግሞ እኛ ምን ማድረግ እንደሚገባን
በማንሣት የእግዚአብሔርን ቃል እንጫወታለን።
1.
ወደ ቃሉ
እንመለስ፦ የሾላኮቹ ያላሳለሰ ተግባራቸው እኛን ከቃሉ መነጣጠል ነው፤ ወደ ቃሉ ልንመለስና ዘወር የምንልባቸውን ማናቸውንም
ምክንያቶችና መንገዶችን ጨርሰው ነው የሚዘጉት። ብንመለስ እንኳ ለገዛ ራሳቸው እንዲመች አድርገው ቃሉን ያጣምማሉ እንጂ በትክክል
እንድንመለስ አያደርጉም፤ አይፈልጉምም።
Friday, 4 October 2019
እሬቻን የማላከብርበት ክርስቲያናዊ ምክንያቴ
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ “የፖለቲካው ጡዘት አገራዊ መልኩን በመልቀቁ፣ ብሔርና ሃይማኖት ተደጋፊ” ከመኾን ጋር ተያይዞ፣
የበአላትን ፉክክር ሃይማኖታዊ መልክ ሲያለብሱ እየተመለከትን ነው። ይህ ደግሞ ውል አልባ የኾነ መጠዛጠዝንና መገፋፋትን፣ “እኔ
እበልጥ እኔ እበልጥ!” የሚል ሥጋዊ መቀናናትን ሲያስከትልና ትውልድ የሚመርዙ ተግባራት “ሃይ ባይ” ማጣታቸውንም እንድንመለከት
አድርጎናል። ልክ እንደ ዘመነ መሣፍንት፣ “በዚያም ዘመን በእስራኤል ዘንድ ንጉሥ አልነበረም፤ ሰውም ሁሉ በፊቱ መልካም መስሎ
የታየውን ያደርግ ነበር።” (መሣ. 16፥7) ተብሎ እንደ ተነገረው፣ የትኛውም ሰውና ብሔር መልካም መስሎ የታየውን ከማድረግ
ከልካይ የሌለበትና እግዚአብሔር የተገፋበት የተናቀበት ዘመን ላይ ነን።
Friday, 27 September 2019
Lallaba gowwummaa (1Qoro. 1:21)
Please read in PDf
Waaqayyoon ilma namaa
cubbuudhaan bade jiru gara qulqullumaa fi qajeelumaatti deebisuuf; ilma isaa
tokkicha Goofta Yasuus Kiristoos gara biyya lafaatti ergee jira. Ilmi isaa
tokkichaan haalli inni gara biyya lafaatti ittiin dhufe bayyee kan nama
haawachisuufi gammachiisu miti. Tasumaa karaan itiin dhufe kabajaa fi
jaalatamummaa biyya lafaa barbaadu hundaaf faallaa ta’eti.
Wednesday, 25 September 2019
Monday, 23 September 2019
ሾላኮቹ (ክፍል ፬)
Please read in PDF
ባለፈው በተመለከትነው ክፍል ሾላኮቹ ማንን ያስታሉ? ብለን በቀዳሚነት
ከቅዱሳት መጻሕፍት ጠቅሰን “እውነትን ማወቅ የማይወዱ
ሞኞች ሴቶችን” እንደሚያስቱ ተመልክተናል፤ ዛሬ ደግሞ የዚኹን ቀጣይ ክፍል እንዲህ እንድታነቡት ጋብዛችኋለሁ፤ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ፤
አሜን።
2.
አዳዲስ አማኞችን፦ አዳዲስ
አማኞች ለቃለ እግዚአብሔር ጥማት የተጋለጡ ናቸው፤ ከቃለ እግዚአብሔር ጋር የተያያዘ ማናቸውንም ትምህርቶች ለመስማት ይቸኩላሉ።
በተለይም ሾላካ መናፍቃን የሚጠቅሷቸውንና እውነተኛ መምህራን የሚጠቅሷቸውን እውነተኛ ትምህርት ከመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ጋር በማነጻጸር
የትኛው እውነተኛና የትኛው ደግሞ ሾልኮ እንደ ገባ የመለየትና የማስተዋል እንከን አለባቸው።
Wednesday, 18 September 2019
ሾላኮቹ (ክፍል ፫)
Please read in PDF
በባለፉት ኹለት ክፍሎች የመናፍቃንን የሾላካነት ጠባይ መመልከታችን አይዘነጋም፤ ከዚያ በመቀጠል ዛሬም
እንመለከታለን፤ የጌታ ጸጋና ሰላም ከኹላችሁ ጋር ይኹን፣ አሜን፡፡
4.
ልዩነትን ወይም
እንግዳ ዘርን ለመዝራት፦ ጌታችን ኢየሱስ እንክርዳድ ዘሪው ክፉ፣ ማንም ሳያየው በሌሊት ወይም ጨለማን ለብሶ በመሹለክ
ተግባር እንዳደረገው ነግሮናል፤ ጠላት እንክርዳድ የዘራው በዚያው መልካሙ ዘር በተዘራበት እርሻ ላይ ነው፤ አበቃቀሉም ኹለቱም በአንድነት
በቀሉ፤ የስንዴውም የእንክርዳዱም አበቃቀላቸው ተመሳሳይና አንዱን ከሌላው ለመለየት እጅግ አዳጋች እንደ ኾነ፣ “እንክርዳዱን ስትለቅሙ ስንዴውን ከእርሱ ጋር እንዳትነቅሉት አይሆንም” (ማቴ. 13፥29) ከሚለው ከጌታችን ኢየሱስ
ንግግር እናስተውላለን።
Wednesday, 11 September 2019
Monday, 2 September 2019
ሐዋ. 2 ላይ የብሔርተኞቹ ሸቃጭነት!
በቃሉ ውስጥ
ባዕድ ዐሳብ ቀላቅሎ ማቅረብና መሸቀጥ ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነት የማይታዘዙ ሰዎች ኹነኛ መገለጫ ነው (2ቆሮ. 2፥17፤ 4፥2)፤
ከሰሞኑ የተነሡት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም፣ ዝቅ ብለውና ወርደው “በክልል ደረጃ፣ በአንድ ብሔር
ስም” ክርስትናን “እንመስርት” ባዮቹ አካላት፣ እጅግ ድፍረት በተሞላበት ንግግር መጽሐፍ ቅዱስን ጠቅሰው፣ ይህን እኩይና እቡይ
ድርጊታቸውን እንደሚደግፋቸው ሲጠቅሱ ሰምተናቸዋል፤ በቋንቋና በብሔር ክርስትናን ለመደራጀት እንደሚፈቅድላቸው ከጠቀሱት ጥቅስ
አንዱ ደግሞ የሐዋርያት ሥራ ኹለትን ነው።
Friday, 30 August 2019
የቄሳር ተላላኪ “ቀሳውስት” - ሠርግና ምላሽ
ቤተ ክርስቲያን ከመንግሥት ጋር “ተቃራኒ” በነበረችባቸው ዘመናት፣ ማለትም
ነገሥታት ጸረ ክርስትና አቋም ይዘው ተነሥተው በነበሩባቸው ዘመናት፣ ቤተ ክርስቲያን ከሩቅ የሚታይ አብረቅራቂ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋን
ተጐናጽፋ ነበር፤ ከአንድ መቶ ሃምሳ ዓመታት በላይ ከኔሮን ቄሣር እስከ ዲዮቅልጥያኖስ የዘለቀው ጽኑ የመከራ ዘመን ቤተ ክርስቲያን
እንደ ቦኸር በዐለት ላይ ተከላት እንጂ፣ ፈጽሞ ካመነችው እውነትና ከመንፈስ አንድነቷ አላነወጣትም፤ አልከፋፈላትም፡፡ መከራ ማጥሪያዋ
ብቻ ሳይኾን መጽናኛዋም ጭምር ነበር፡፡
Tuesday, 27 August 2019
ሾላኮቹ (ክፍል ፪)
Please read in PDF
2.
ለመስረቅ፦ ጌታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ወደ በጐች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው፤” በማለት ሲናገር ሾላኮቹ ራሳቸውን በማመሳሰልና በመደበቅ የተካኑ መኾናቸውን
እየነገረንም ጭምር ነው፤ (ዮሐ. 10፥1)። ሌባ በባሕርይው ተደብቆ ወይም ሾልኮ እንጂ በግልጽ መግባትን አያውቅም። ይህንም የሚያደርገው
ተቀዳሚ ዐላማው የእርሱ ያልኾነውን ነገር፣ ለራሱ ጥቅምና ፍላጎት ለመስረቅና ለመውሰድ ነው።
Monday, 19 August 2019
Monday, 12 August 2019
ሾላኮቹ (ክፍል ፩)
Please read in PDF
መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ
ቃል ሐራጥቃ[1] የኾኑ መናፍቃንን
ጠባያቸውን ሊገልጥ በሚችል መንገድ፣ ሾላኮች ወይም ወደ ቤቶች ሾልከው የሚገቡ በማለት ይጠራቸዋል፤ (ገላ. 2፥4፤ 2ጢሞ. 3፥6፤
ይሁ. 4)። ቅዱስ ጳውሎስ ወደ እግዚአብሔር አደባባይና ወደ አማኞች የሚገቡት እንደ ሰላይ ነው ይለናል፤ ጌታችን ኢየሱስ ደግሞ
ከአማኞች ጋር ልዩነት የሌላቸው እስኪመስሉ ድረስ “እንደ ተኩላ” (ማቴ. 7፥15) ነው ይለናል፤ ሰላይ መመሳሰልን ገንዘብ ያደርጋል፤
ተኩላም ኹለ ነገሩ ከበግ ጋር አንድ ዓይነት መኾንን ይመርጣል፤ ይህን ተፈጥሮአዊ ተመሳስሎታቸውን የሚጠቀሙት ግን የሚፈልጉትን ለማግኘት
ወይም በጭካኔያቸው ለመንጠቅና በግን በሕይወቱ ቦጫጭቀው ለመብላት ነው።
Saturday, 3 August 2019
የእምነት እንቅስቃሴ አማኞች መጽሐፍ ቅዱስን በዐውድ አያውቁትም!
Please read in PDF
ዐውድ አንድን
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ለመረዳት ወሳኝ ነው፤ ዐውድን አለመረዳት ጠቅላላ የመጽሐፉን ዐሳብ አለመረዳት ነው፤ መንፈስ ቅዱስ ቀድሞ
የተናገረውን ያብራራልናል ይገልጥልናል እንጂ፣ አዲስ መገለጥም ኾነ ኢየሱስ ከተናገረው የተለየ የሚነግረን ምንም ነገር የለውም፤
ይህም በዐውድ ውስጥ ልንረዳው እንችላለን ማለት ነው፡፡ ከመንፈስ ቅዱስ ቀጥሎ፣ ዐውድ የቀደመው መልእክት ለዝንተ ዓለም ዘመን ዘለቅ
ኾኖ እንዲሻገር ኹነኛ አጥር ነው ማለት እንችላለን፡፡
Monday, 29 July 2019
Subscribe to:
Posts (Atom)




