ምንጭ - https://www.mahibereahaw.org.et/
በቅዱሳን አማኞች መካከል ጨርሶ
እንዳይሰማ ወይም ስሙ እንኳ እንዳይነሳ የሚገባ ነገር አለ፤ ኀጢአት፡፡ በዚያው ትይዩ ደግሞ፣ “ርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁ
ተናዘዙ።” እንዲል፥
ቅዱሳን አማኞች ርስ በርስ ኀጢአታቸውን መናዘዝ የሚገባቸው ጊዜ አለ። ኀጢአታችንን በግልጥ ለእግዚአብሔር የምንናዘውን ያህል፥ ደግሞም፥ ለበደልናቸውም ሰዎች በደልና
ስህተታችንን በግልጥ መናዘዝ ይገባናል።
የኤፌሶን መልእክት የተጻፈው፥ ላመኑና ጌታን ይከተሉ ለነበሩ ቅዱሳን
ነው። ያመኑ ቅዱሳን ከነርሱ ሊሰማ የሚገባ ነገር አለ፤ የጌታን ቤዝዎት፣ ማዳኑን፣ ስቅለቱንና ትንሣኤውን በመናገር ከነርሱ
የምሥራች ሊሰማ ይገባል።
ዳሩ ግን ባመኑ ቅዱሳን መካከል ሊሰሙ የማይገባቸው ነገሮችም ደግሞ አሉ። “ለቅዱሳን እንደሚገባ ግን ዝሙትና ርኵሰት ሁሉ ወይም
መመኘት በእናንተ ዘንድ ከቶ አይሰማ፤ የሚያሳፍር ነገርም የስንፍና ንግግርም ወይም ዋዛ የማይገቡ ናቸውና አይኹኑ፥ ይልቁን
ምስጋና እንጂ።” (ኤፌ. 5፥3-4)
ምክንያቱም፣
በአማኝ ሕይወት ኀጢአት ሊገኝ
አይገባውም፤ ወይም በቀዳሚ ተግባር አማኝ ኀጢአትን ሊያደርግ አይገባም። ቅዱስ ዮሐንስ፣ “ልጆቼ ሆይ፥ ኃጢአትን እንዳታደርጉ
ይህን እጽፍላችኋለሁ።” (1ዮሐ. 2፥1)፤ አማኞች፥ ኀጢአት ጨርሶ እንዳያደርጉ እያስተማረም፤ እያስጠነቀቀም ነው። ለአማኝ
ኀጢአት አለማድረግ ምርጫው ሳይኾን ግዴታው ነው፤ በምናለብኝ ሕይወት እንዲኖር አልተጠራምና። ሐዋርያው በመቀጠል እንዲህ ይላል፣
“ይኽን እወቁ፤ አመንዝራም ቢኾን ወይም ርኵስ ወይም የሚመኝ እርሱም ጣዖትን
የሚያመልክ በክርስቶስና በእግዚአብሔር መንግሥት ርስት የለውም።” (ኤፌ. 5፥5)
እንዲህ ያሉ ኀጢአቶች በአማኞች መካከል
እንኳን ሊፈጸሙ፥ ስማቸው እንኳ ሊነሣ አይገባም። ምክንያቱም፥ እኒህ ኀጢአቶች ለተከታይ ኀጢአቶች የሚጋብዙ ናቸው፤ ለምሳሌ፦
ስድብ፣ ክፋት፣ መራራ ቁጣና ንዴት ወደ መግደል ያደርሳሉ፣ ርኵሰት፣ ክፉ ምኞትና ስግብግብነት ወደ ዝሙትና አመንዝራነት
ያደርሳሉ፤ ስለዚህ ኀጢአት በአማኞች መካከል ሊሰማ አልያ ስሙ እንኳ ሊነሣ አይገባውም።
ነገር ግን፥ ከዚህ እውነት ሊያርቋችሁ
ወይም በኀጢአት ምክንያት
ከእግዚአብሔር መንግሥትማ ርስት ልታጡ አትችሉም ለሚሉአችሁ፣ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይላል፣
“…ከዚህ የተነሣ በማይታዘዙት ልጆች ላይ የእግዚአብሔር ቊጣ ይመጣልና ማንም
በከንቱ ንግግር አያታልላችሁ።”።
“እንግዲህ
እንደ ተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን ምሰሉ፤ ክርስቶስ እንደ ወደደን ራሱንም ስለ እኛ መልካም መዐዛ ያለው መባና መሥዋዕት
አድርጎ ለእግዚአብሔር እንደ ሰጠ እናንተም በፍቅር ተመላለሱ።” (ኤፌ. 5፥1-2)። ጸጋው ይደግፈን፤ አሜን።
“ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በማይጠፋ ፍቅር
ለሚወድዱ ሁሉ ጸጋ ይሁን።” (ኤፌ. 6፥24)።

🙏🙏🙏🙌👏👏👏❤️❤️❤️❤
ReplyDelete