“... በኹለት ዐመቱ ጌታችን በእናቱ እቅፍ መጥቶ ባረካት[ዋልድባን]። ዋልድባ በአራቱ ወንዞች ትከበብ ብሎ፣ የሰው
ብቻ ሳይኾን የእንሰሳ ሴት አይግባባት ብሎ ጌታችን ኢየሱስ የውግዘት ቃል አሳልፎባታል። ሴቶች እንዳይገቡ በግዝት ቃል ተነግሮባታል።
... ስውር ቅዱሳን ክንድ ከስንዝር ከፍ ብለው የቀደሱበት ስፍራ ነው።... ዳልሻ ዋልድባ ቤተ ደናግል የሚባል የሴቶች ገዳም ጨርሶ የለም። ... ገዳሙ ጨርሶ የእርሻ ስፍራ እንዳይኾን እንኳ ተከልክሎአል።...
በዋልድባ ጳጳስ እንኳ ቢመጣ 40 ቀን ቋርፍ ሳይጨብጥ በዋልድባ ቀጥታ መቁረብ አይቻልም።…” የሚሉ አያሌ “ተረቶች” በገዳሙ “አባቶች”
ሲነገር መደመጡ እንግዳ ነገር አይደለም።
ከዚህም በተጨማሪ፣ “በገዳሙ ስውራን ቅዱሳን አሉ፤ ያልተገባ ተግባር ሲፈጸም
ይቀስፋሉ።” ቢሉም በነርሱ ሚዛን፣ እሸቱ መለሰ የተባለ “ኮሜዲያን” በገዳሙ ያልተገባ ተግባር ሲፈጽም ግን አልተቀሰፈም። ያ ብቻ
ሳይኾን ሊገደል እንደሚችል፣ ሀብቱን የማጣት ዕጣ እንደሚወጣበትም መነኮሳቱ በድፍረት ተናግረዋል። ከዚህ በዘለለ በዘረኝነት፣ በግድያ፣
የሌሎችን በዐት በማፍረስ የተካኑ መነኮሳት ያለበት ገዳም እንደ ኾነ እዚያው ዋልድባ አከባቢ ያሉ የቤተ ጣዕማ መነኮሳት ምስክርነት
ሰጥተዋል።
የግል መደምደሚያዬ!
ገዳሙ “ከስሙ” በተቃራኒ የቆመ ነው። “ጻድቃን ስውራን” የሚል ንግግር በተደጋጋሚ
ይነገራል፤ እውነታ ግን “ስውራን” የተባሉ ጨርሶ አለመኖራቸውን ምክንያቶቼን
ከዚህ በታች ላስረዳ፣
1.
“ኹለት አበምኔት በአንድ ገዳም
አለ፤ ይህም የኾነው ፍቅረ ንዋይ ስለሚያጣላን ነው” ይላሉ የገዳሙ መነኮሳት። እውን ስውራን ቢኖሩበት ይህን ማስተካከል እንዴት
ተሳናቸው?!
2.
አንዳንዶቹ የሴቶች ገዳም አለ
ሲሉ፣ ሌሎቹ ግን ዋልድባ ሴት የምትባል የእንሰሳም የሰውም ፍጥረት አይገባባትም ይላሉ። እውን የሴት ፍጥረት ሰውና እንሰሳ ብቻ
ነውን? የዛፍ የአትክልት፣ የአዝርእት፣ የአእዋፋት፣ የጥቃቅን ነፍሳት … “ሴቶች” የሉምን? እኒህ ሁሉ በዋልድባ የማይገቡ ኾነው
ነው? ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ ያነጋገራቸው “ሴት መነኮሳት” ለምን “ዋልድባውያን” አይደሉም ተባለ?
3.
“አንዱ ሌላውን “መናፍቃ.ን”
ናቸው እያሉ በሐሰት ይከስሳሉ። ከዚህም በላይ ጁንታ[የዳንኤል ክብረት ስያሜ የተባለለት] ናቸው፤ ኹሉም ትግራይ እንጂ በመካከላቸው
አማራ የለም ይሉናል።” ይላሉ የቤተ ጣዕማ መነኮሳት፣ የቤተ ሚናስ መነኮሳትን ሲወቅሱ። ይህን ያህል ዘረኝነት በስውራን መካከል
እንዴት ገነነ?!
4.
“የቤተ ሚናስ መነኮሳት ገዳማችንን
በእሳት አቃጠሉብን፤ የምናመልክበትን ሕንጻ ቤተክርስቲያን አቃጠሉብን፣ መነኮሳቱ የቤተክርስቲያንን ብራናና ንብረታችንን ዘረፉ፣ በቤንዚን
አርከፍክፈው ቤተክርስቲያናችንን አቃጠሉት፣ በክላሽና በዱላ አሳደዱን።” ይላሉ የቤተ ጣዕማ መነኮሳት። ይህ እጅግ አሳፋሪ ተግባር
አይደለም ወይ?! ዋልድባ መካከል እንዲህ ያሉ መነኮሳት ካሉ፣ “ዓለማዊነት” በከፋ ኹኔታ በገዳም የገነነ አይደለም ወይ?
እነ እንጦንስ ቤተክርስቲያን ከመንግሥት ጋር ስትጣበቅ፣ ከቤተክርስቲያን ወደ
ገዳም ሸሹ፤ የቤተ ክርስቲያንንና የመንግሥትን ጋብቻ በዓይናቸው ላለማየትና እነርሱም አብረው እንዳይረክሱ በመጠንቀቅ። በዋልድባ
ገዳም ያሉ መነኮሳት ግን የሚሸሹ[ሊርቁአቸው የሚገባ] እንጂ የሚሸሽባቸው አይደሉም። ምክንያቱም የቤተ ጣዕማ መነኮሳት እንደሚናገሩት
በዘረኝነት ሌላውን ያጠቃሉ፣ በሐሰት ክስ የሌላውን ስም ያጠለሻሉ ብሎም በፍቅረ ነዋይ ዓይናቸው የታወረ ነው። እንዲህ ያለ ርኩሰት
“መልካም ስብዕና ባላቸው ዓለማውያን ወይም አሕዛብ” መካከል እንኳ ጨርሶ የማይሰማ ነው።
ሰው በገዳም ተቀምጦ እንጥፍጣፊ ርኅራኄ፤ ዘለላ ቸርነት ከሌለው፣ በገዳም ከሚኖረው
ይልቅ “ወንጌል ገና ያልሰማውና ጌታን ጨርሶ የማያውቀው የተሻለ ተስፋና የመዳን አለኝታ” አለው። ከከፋ “አማኝ”፤ የከፋ ኢአማኒ
የተሻለ የንስሐ ዕድል አለውና። ለዚህም ነው በተደጋጋሚ፣ በገዳማት በከንቱ መመካት አይገባም ስንል የነበረው። በገዳም ጽድቅ ብቻ
እንዳለ የሚነገረውም “ተቃርኖ እንዳለበት” ዋልድባ ድንቅ ምሳሌ ነው። የክርስቶስን ጽድቅ ሽሮ፣ የራስን ጽድቅ ለማቆም መጣር ፍጻሜው
እንዲህ ያለ አስቀያሚ ርኩሰት ነው!
ይህ ብቻ ያይደለ፣ ከሰሞኑ “መነኮሳት ወደ ገዳም ይግቡ” የሚለውም ክርክርና
ቅስቀሳ፣ በሚገባ ቢጤን የተሻለ ነው፤ “በገዳም ምን አለ?” ብሎ መጠየቅ ተገቢ ጥያቄ ይመስለኛል። ሰው ለመግደል፤ በዘረኝነት ለማበር፤
ከዓለማዊነት ባልተሻለ ማንነት ለመመላለስ፣ የክርስቶስን ጽድቅ ነቅፎ የራስን ጽድቅ ለማቆም ከኾነ፣ ገዳማዊነት ቢቀርና አግብተው
እንበለ በዓት በጽድቅ የሚመላለሱ ባለትዳሮች እጅግ የተሻሉ መኾናቸውን ልንመሰክርላቸው ይገባናል! ክርስቶስ የሌለበት ገዳም ከአውሬነት
ይልቅ ይከፋል፤ ክርስቶስ ያለበት ትዳር ደግሞ ከገዳማዊነት ጋር ጨርሶ ሊወዳደር አይገባውም፤ ይበልጣልና!
አቤቱ ወደ እኛ ተመለስ፤ ትውልዱ ወዳንተ ይመለስ ዘንድ፤ አሜን።
.jpg)

አቤቱ ጌታ ሆይ አንተ በእውነት ታያለህ አባ ከማስመሰል ሕይወት አውጣኝ እኔ አቅቶኛል❤❤❤
ReplyDeleteየምናገረውን ለመኖር የምፍጨረጨር ትግል የበዛብኝ ነኝና ጌታ ሆይ እርዳኝ።
ReplyDelete