Sunday, 31 August 2025

“ተሐድሶ ነን” ባይ የተሐድሶ ተግዳሮቶች!

Please read in PDF

ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከክርስቶስ ትምህርት፣ ሕይወትና ሥራ አንጻር ተሐድሶ እንደሚያሻት ለጥያቄ የማይቀርብ ሐቅ ነው። በተደጋጋሚ ቤተ ክርስቲያኒቱ ራስዋ፣ “ተሐድሶ እንደሚያሻት” ስትናገር ሰምተናታል። ከዚኹ ጋር በተያያዘ፣ “ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማደስ” ከሚንቀሳቀሱ አካላት ሦስት ዓይነት ተግዳሮቶች በግልጥ ይታያሉ፤

Wednesday, 27 August 2025

“ሄደህ …ስበክ”! (ዮና. 1፥1)

 Please read in PDF

እግዚአብሔር አምላክ የተልእኮ አምላክ ነው። አስቀድሞ ሰው በኀጢአቱ በወደቀ ጊዜ ለማንሳት ወደ ወደቀበት ስፍራ፣ “ወዴት ነህ?” (ዘፍ. 3፥10) እያለ ፍለጋ የመጣው ያህዌ ኤሎሂም ነው። እግዚአብሔር ፍጥረት በወደቀ ጊዜ በመፈለጉና ፈልጎም በማግኘቱ፣ የተልእኮ አምላክ ነው። ርሱ ፍጥረት በመውደቁ ደስ አይሰኝም፤ “የምዋቹን ሞት አልፈቅድምና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ስለዚህ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ።” (ሕዝ. 18፥32) እንዲል።

Thursday, 14 August 2025

የ“እውነት ቃል አገልግሎት” እና ሕግ!

 Please read in PDF

የ“ሥፍረ ዘመን አማንያን” ትምህርቶቻቸው ከተመሠረቱባቸው  መሠረታዊ ትምህርቶች አንዱ፣ የሕግና የጸጋ አስተምኅሮአቸው ነው። ጸጋን እጅግ ከመለጠጣቸውም የተነሳ፣ ስለ ሕግ አንዳችም ነገር እንዲነገር አይፈልጉም፤ ከዚህ ስሑት አስተምኅሮአቸው ነጻ የወጣው ሚስተር ማውሮ ሲናገር እንዲህ ይላል፣ “ … በእግዚአብሔር ቅዱስ ሕግ ላይ የሚጥሉት ምኞቶች በጠቅላላው ሙሉ እና ከባድ ደግሞም የተሳሳተ መግለጫ ነው።”

Sunday, 3 August 2025

የትዝታው ሳሙኤል ኮንሰርት ምን ገለጠልኝ?

 Please read in PDF

ይህን ጽሑፍ ለመጻፍ ብዙ አመንትቻለኹ፤ ለተሐድሶ አገልግሎት ከማይመቹ አካሄዶች መካከል የነትዝታውን የሚመስል አስከፊ መንገድ የለም፤ እነ ትዝታው ከ“አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል” ውስጥ ራሳቸውን አዳብለዋል፤ ይኹንና ካውንስሉ በውስጡ፣ የክርስቶስን ርቱዕ ትምህርት፣ ሕይወትና ሥራ የማይቀበሉ ያሉትን ያህል፣ እነ ትዝታውም እውነተኛ የወንጌላውያን አማኞች እንዳልኾኑ የሚያሳዩ አያሌ ምልክቶች አሉ።




Sunday, 27 July 2025

ከኦርቶዶክስ የወጡና ወደ ኦርቶዶክስ የሚመለሱ!

Please read in PDF

 በዚህ ባለንበት "የክርስትና ዐውድ" ሰዎች "ወንጌል ተረዳን" ሲሉ፣ ከአንድ ኅብረት ወደ ሌላ ኅብረት "ቀለል ባለ መንገድ ሲሸጋገሩ" ማየት የተለመደ ኾኖአል። ርግብ ቤቷ ጨርሶ እስካልፈረሰና ጫጩቶቿን እስካልገደሉባት ድረስ ስላባረሯት፣ ስለመቷት ... ብቻ ከጎጆዋ አትወጣም ተብሎ በሚነገረው የኦርቶዶክስ ማኅበረ ሰብ ውስጥ የኖረውም ኾነ፣ ከኅብረት መውጣት "የዓሳ ከባሕር የመውጣት ያህል" ከባድ ነው በሚለው የወንጌላውያን ማኅበረ ሰብ ሰዎች ይወጣሉ፤ ይፈልሳሉም።



Monday, 21 July 2025

ስሙን መልሱልን

Please read in PDF

በሰሎሞን አበበ ገ/መድኅን

ከበርካታ ወራት በፊት በተንቀሳቃሽ ስልኬ በተላከልኝ አጭር የጽሑፍ መልዕክት (SMS) ላይ አንድ “ፍተላ” ብጤ አነበብኩ፡፡ “ፍተላው” የሚያስፈግግ ነገር ነበረው፡፡ ኾኖም ግን ድንጋጤው በቅጡ ነዝሮኛል፡፡ ነገርዬው እንደሚለው፣ አንድ የሃይማኖት አባት “አንድ ወርኀዊ በዓል በነባሮቹ ላይ አከሉ፡፡ ይኸውም፤ በ1 ልደታ፣… በ3 በኣታ፣… በ5 አቦዬ፣ በ6 ኢየሱስ፣ በ7 ሥላሴ፣ በ8 ቢዮንሴ” ይላል፡፡ ይህ ሥላቅ ያላስፈገገኝ በሁለት ምክንያቶች ነው፡፡ ሁለተኛው፣ የሕዝብህን አለቃ አታንጓጥጥ (ዘዳ. 22÷28፤ የሐዋ. 23÷5) የሚለውን ቅዱስ መርሕ ስለጣሰ ነው፡፡ አንደኛውንና ዋነኛውን ምክንያት ደግሞ በዚህ ጽሑፍ መጨረሻ ላይ አመላክታለሁ፡፡

Friday, 18 July 2025

ጋብቻና ሕመሙ

 Please read in PDF

እግዚአብሔር አምላክ በፍጥረት መጀመሪያ ያስቀመጠው እውነት፣ “እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ፤ እነሆም፣ እጅግ መልካም ነበረ።” (ዘፍ. 1፥31) የሚል ነው። ስለዚህም የእግዚአብሔር ፈቃድ በመልካም ነገር ደስተኞች ኾነን እንድንኖር ነው። ነገር ግን በብዙ ጥንዶች መካከል፣ ይህ መልካም ደስታ ጨንግፎና መክኖ ይስተዋላል። በተለይም ደግሞ በዚህ ዘመን ፍቺና “ከፍቺ በኋላ ያለ የብቻ እናትነት” እንደ በጐ ነገር ሲቈጠር ይስተዋላል። የሠርጉ ቀን “ኪዳን” እንደ ዋዛ ተሰብሮ ወይም ኾን ተብሎ ተሰብሮ ወይም ከልክ ባለፈና በተደጋገመ ቸለተኝነት ተሰባብሮ፤ ሠርጉ ብቻ ደስታ፤ ትዳሩ ግን “የልቅሶ አውድማ” የኾነባቸው ቊጥራቸው ቀላል አይደለም።

Sunday, 6 July 2025

አታስመስሉ፤ አትገበዙም!

 Please read in PDF

ከአገልግሎት በፊት ርስ በርስ መዋደድ ይቀድማል። ኢየሱስን ከመስበክ በፊት ሕይወቱንና ትምህርቱን በሚገባ ማሰላሰል ብርቱ ማስተዋል ነው። ኢየሱስን እየሰበኩ ትህትናቸው የታይታ፣ ክርስቶስን በድንቅ ንግግር እየናኙ ኅብረት የሚጠየፉ፣ መዝሙረኛው፣ “አፉ ከቅቤ ይልቅ የለዘበ ነው፤ በልቡ ግን ጦርነት አለ፤ ቃሉ ከዘይት ይልቅ የለሰለሰ ነው፤ ይሁን እንጂ የተመዘዘ ሰይፍ ነው።” (መዝ. 55፥21) እንደሚለው፣ ልባቸውና አፋቸው የተጣላባት ግብዝ አገልጋዮችና አማኞችን እንደ ማየት ቅስም እንክት የሚያደርግ ነገር ያለ አይመስለኝም።

Sunday, 22 June 2025

“በእግዚአብሔር እስራኤልም ላይ ሰላምና ምሕረት ይሁን” (ገላ. 6፥16)

 Please read in PDF

መሲሐዊው የክርስቶስ መንግሥት ወንጌል ሰውና እግዚአብሔርን ብቻ ሳይኾን ሰውና ሰውን ወይም ጎረቤቱንም የማስታረቅ ዓላማ አለው። ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅቶ በመጥራት (ራእ. 5፥10) በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ በሰላም እንዲኖሩ ማስቻል የእግዚአብሔር መንግሥት ወንጌል ቀዳሚ ዓላማ ነው።

Saturday, 21 June 2025

ለኅብረት እንጠንቀቅ!

 Please read in PDF

ለመንፈሳዊ ኅብረት በምሳሌነት እንዲያገለግሉ ከተጠቀሱት ምሳሌዎች መካከል፣ የሰውነት ክፍሎችን ወይም ብልቶች ናቸው። እነርሱም የተለያየ ችሎታና ተግባር ተሰጥቶአቸዋል። ልክ እንዲኹ፣ በክርስቶስ አንድ አካል የኾኑ አማኞች፣ የተለያዩ ጸጋ፣ ስጦታና ተግባር ተሰጥቶአቸዋል፤ “ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፥ እርስ በርሳችንም እያንዳንዳችን የሌላው ብልቶች ነን።” (ሮሜ 12፥5) እንዲል።

Saturday, 31 May 2025

በወንድሞች መካከል ጠብን የሚዘራ (ምሳ. 6፥19)

 Please read in PDF

እግዚአብሔር፣ ኀጢአትን እንደሚጠየፍ በግልጥ ከተናገረባቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች መካከል አንዱ ክፍል ይህ ነው። ጠቢቡ የገለጣቸው ስድስት ኀጢአቶች በፍጻሜያቸው፣ መለያየትና ግጭት ብሎም ወንድሞች እንዳይቀባበሉ የሚያደርግ ኀጢአት እንደ ኾነ መረዳት እንችላለን። በወንድሞች መካከል ጠብን ለማነሣሣት ወይም ለመዝራት አስቀድሞ ሐሰተኛ ምላስ ትዋሻለች፤ መዋሸቷ ብቻ ሳይኾን ጠብን ለመጫር ሌሎችንም ማታለሏ አደገኛ ያደርታል።

Tuesday, 27 May 2025

“ድንግል ማርያምን ሳትቀበል ጌታን መቀበል አትችልም!” [እውነት!?]

 Please read in PDF

ይህን ከላይ በርዕስነት የጠቀስኹትን ቃል የተናገረው ስሙር አላምረው ይባላል፤ ባልሳሳት “ሊቀ ሊቃውንት” የሚል ማዕረግ ያለው ይመስለኛል፡፡ ኦርቶዶክሳውያን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በድንግል ማርያም ዙሪያ የሚሰጡት “ትምህርትና ስብከት” ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነት እያፈነገጠና መስመር እየሳተ ከመኾኑም ባለፈ፣ ድንግል ማርያምን ታክከው የክርስቶስን መካከለኝነት በትክክል መንቀፍ ደግሞ የአደባባይ እውነት ኾኖአል፡፡

Monday, 26 May 2025

ይሁዳና የሌሊት መንገዱ!

 Please read in PDF

ይሁዳ ወዲያው ወጣ፤ ሌሊትም ነበረ።” (ዮሐ. 13፥30)

ጌታችን ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ መካከል በአንዱ፣ ተላልፎ እንደሚሰጥ፣ “እንጀራዬን የሚበላ በእኔ ላይ ተረከዙን አነሣብኝ ያለው ይፈጸም ዘንድ” (ዮሐ. 13፥18-21) በማለት ከትንቢት ጠቅሶ ተናግሮአል። ጌታችን ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ መካከል ወደ ደረቱ ተጠግቶ ለጠየቀው ሐዋርያ፣ “እኔ ቍራሽ አጥቅሼ የምሰጠው እርሱ ነው ብሎ” መልሶአል፤ (ቊ. 26)። ይሁዳ እጅግ በሚያሳዝን መልኩ፣ ጌታችን ኢየሱስ ነገረ ሥራውን ኹሉ እንዳወቀ ባረጋገጠለት ጊዜ፣ “… ወደ ካህናት አለቆች ሄዶ፦ ምን ልትሰጡኝ ትወዳላችሁ እኔም አሳልፌ እሰጣችኋለሁ?” (ማቴ. 26፥14-15) ባለበት ቅጽበት፣ በሰይጣን ቊጥጥር ሥር ዋለ፤ “ቍራሽም ከተቀበለ በኋላ ያን ጊዜ ሰይጣን ገባበት” (ዮሐ. 13፥27) እንዲል።

Wednesday, 21 May 2025

ማርያም “የጌታ ባሪያ” መባልዋ ያዋርዳታልን?

 Please read in PDF

በመጽሐፍ ቅዱስ ከቀረቡ ተወዳጅ መዝሙራት መካከል፣ የማርያም መዝሙር አንዱ ነው፤ የቅድስት ማርያም ዝማሬ የሚጀምረው እግዚአብሔርን በማመስገን ነው (ሉቃስ 1፥46)። እግዚአብሔርን ስታመሰግንም፣ የአዳኝነት ሚናውን በግልፅና በትህትና በማሳየት ነው (ሉቃስ 1፥47)። መዝሙሮቿም ከቅዱሳት መጻሕፍት ማለትም ከብሉይ ኪዳን ምንባባት የተቀዱና የተወሰዱ ናቸው።

Tuesday, 20 May 2025

የተዘነጋው የመዳናችን ክፍል!

 Please read in PDF

“እነዚህ ነገሮች የሌሉት ዕውር ነውና፥ በቅርብም ያለውን ብቻ ያያል፥ የቀደመውንም ኃጢአቱን መንጻት ረስቶአል።” (2ጴጥ. 1፥9 - 1954)

እነዚህ ባሕርያት የሌሉት ግን የሩቁን የማያይ ወይም ዕውር ነው፤ ከቀድሞው ኀጢአቱ መንጻቱንም ረስቷል።” (ዐመት)

መጽሐፍ ቅዱስ “በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም” (ሮሜ 8፥1)፣ “ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤” (2ቆሮ. 5፥17) ብሎ መናገሩ የታመነና የተረጋገጠ ሕያው እውነት ነው። ስለ መዳናችን በኀላፊ ንግግር ስንናገር እኒህ ኹለቱን መናገር እንችላለን፣ (1) ድነናል (ኤፌ. 2፥8፤ ቲቶ 3፥6-7፤ ሮሜ 3፥24፤ 8፥24፤ 9፥30)፣ (2) ተቀድሰናል (ሮሜ 6፥24-25፤ 1ቆሮ. 1፥12፤ 6፥11፤ ዕብ. 10፥10፡ 14፤ 1ጴጥ. 2፥24)።