"Yommuu bakka Qaraaniyoo jedhamu ga'anitti achitti isa fannisan;" (Luqa. 23:33)
Friday, 30 April 2021
Wednesday, 28 April 2021
Saturday, 24 April 2021
Saturday, 17 April 2021
ኒቆዲሞስና ነገረ ዳግም መወለድ
ኒቆዲሞስ፣ ኢየሱስን እጅግ በብዙ ከሚንቁት ፈሪሳውያን ወገንና ከአይሁድ አለቆች መካከል አንዱ የነበረ ሰው ነው። በዚያ ዘመን ፈሪሳዊ መኾን ሕጉን እንጠብቃለን፤ ሕጉን በመጠበቅም እንጸድቃለን ለሚሉ ሃይማኖተኞች ብርቱ ትምክህት ነው። ፈሪሳውያን ለሕጉ እጅግ ቀናተኞች ከመኾናቸው የተነሣም፣ ከመካከላቸው ቀራጮችንና ኀጢአተኞችን ፍጹም በማግለል ራሳቸውን እንደ ፍጹም ጻድቃን ይቈጥሩ ነበር።
Thursday, 15 April 2021
መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፯)
ካለፈው የቀጠለ …
ጽድቅ፦ “ጽድቅ” የሚለው ቃል የአማርኛ ተካካይ ትርጉሙ፣ “ሕግን መፈጸም፣ እንደ ሕግ መኖርና መመራት፣ ትክክለኛነት፣ እውነት፣ ቀጥተኛ፣ ፍትሓዊ፣ በጎ ምግባር” ማለት ነው። አለቃ ኪዳነ ወልድም በመዝገበ ቃላቸው ሲተረጕሙ “እውነት፣ ርግጥ፣ ቅንነት”።[1] ይላሉ። ይህም በቀጥታ ከእግዚአብሔር ባሕርይ ወይም ከፍጹም ትክክለኛነቱ ጋር የሚገናኝ ነው። ሰው ኀጢአተኛ ስለ ኾነ የእግዚአብሔርን ጽድቅ መፈጸም አይችልም። በተለይ ደግሞ ከመዳን ትምህርት ጋር አያይዘን ስናነሳው እንዲህ ማለት እንችላለን፤ ሰው መጽደቅ የሚችለው ከእግዚአብሔር ልጅ ከክርስቶስ የቤዝወት ሥራ የተነሣ ብቻ ነው።
Tuesday, 13 April 2021
አባባይ “shows”
የስህተት መምህራን “የክርስቶስን ሐዋርያት እንዲመስሉ ራሳቸውን እየለወጡ ምን ያህል የጽድቅ አገልጋዮች እንደሚመስሉ” (2ቆሮ. 11፥13-14)፣ ምን ያህል ውስጠ ተኵላነታቸውን ደብቀው የበግ ለምድ እንደሚለብሱ (ማቴ. 7፥15) … ጃፒ ከኬፋ ሚደቅሳ ጋር ያደረገው ቃለ መጠይቅ ጥሩ ማሳያ ነው[በእርግጥ እንዲህ ዓይነት አባባይ ቃለ መጠይቆች፣ ከዚህ በፊት ብዙ ተደርገዋል]።
Saturday, 10 April 2021
Wednesday, 7 April 2021
ዳንኤል ክብረት፣ እውን ባንተ ግብር ተከሰሱ?
“… ኢየሱስ ክርስቶስም ተቃዋሚ ነበረበት፤ ሙሴም
ተቃዋሚ ነበረበት፤ … ሌሎች ትልልቅ ሰዎችም ተቃዋሚ ነበረባቸው”
ይህን
ቃል የተናገረው ዳንኤል ክብረት(“ቀሲስ”) ነው፤ የተናገረበትም ምክንያት፣ ከፋና ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ፣ “ካንተ ጋር የሚነሡ ክሶችን
በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በተዘጋጁ ሰልፎች ላይ ኹሉ፣ ያንተን ፎቶ ኤክስ ምልክት እያደረጉበት ወይም አንተን
እያወገዙ የተቃውሞ ድምጾችን እየሰማን ነው … ምንድነው ምላሽህ?” ለሚለው የሰጠው መልስ ነው። በርግጥ ዳንኤል ይህን መልስ አስተውሎ
ስለ መመለሱ እርግጠኛ ነኝ።
Saturday, 3 April 2021
Maaraanaataa! (1Qoro. 16:22)
Jechi “maaraanaataa”
jedhu afaan Araamaayik irraa argame; hiikni isaas “yaa Gooftaa! Koottu!” jechuu
dha. Kana kan jedhe ergamaa qulqullu kan ta’e Paawloos dha. Kanas kan jedhe kadhannaa
isaa keessatti. Ergaa tokkooffaa gara warra Qorontoosiitti barreesse gaafa
goolabu ykn xumuru yoo ka’u; dhufaati Kiristoos hawwudhaan ykn bayyee dheeboochuudhaan
kan kadhatee dha.
Thursday, 1 April 2021
የኮቪድ 19 ክትባትና ውርጃ
“ስለ ምንስ መልካም
እንዲመጣ ክፉ አናደርግም? እንዲሁ ይሰድቡናልና አንዳንዱም እንዲሁ እንድንል ይናገራሉና።” (ሮሜ 3፥8)
ክርስትናና ሳይንሳዊ ግኝቶች
ክርስትናና ሳይንስ እርስ
በርሳቸው ጥዩፋን አይደሉም፤ ሳይንስ በብዙ መንገዱ ከእግዚአብሔር ባገኘው ጥበብ፣ መልሶ እግዚአብሔርን ተቃዋሚና ተጠያፊ ቢኾንም፣
ክርስትና ግን ለሳይንስ ፍጹም ጀርባውን የሰጠ አይደለም። ክርስትና ለሳይንስ ጀርባውን የማይሰጠውና በእግዚአብሔር መግቦታዊና ሉዓላዊ
ጌትነት ሥር ኾኖ የሚቀበለው ግን፣ ሳይንስ ለእግዚአብሔር ፍጥረት አክብሮት ሲሰጥና ራሱ እግዚአብሔርን የሚቃወም እስካልኾነ ድረስ
ብቻ ነው። የእግዚአብሔርን ፍጥረት የሚቃወምና ፍጥረት የሚገዛበትን ሥርዓት የሚቃወም እርሱ እግዚአብሔርን ይቃወማልና።
Tuesday, 30 March 2021
በጌታ ቸርነት ኹለተኛ መጽሐፌ ታተመ!
“ያለ እውነት፥ የእውነት ቃል አገልግሎት!?” በሚል ርዕስ፣ ስለ “እውነት
ቃል አገልግሎት” ማኅበር ከታሪካዊ ዳራቸው ጀምሮ፣ ትምህርቶቻቸውን የሚያስቃኘው መጽሐፌ ታትሞ ከቀን 22/7/2013 ጀምሮ ለንባብ
ይበቃል! እንድታነቡት በፍቅር እየጋበዝኩ፣ አስተያየት እንድትሰጡበት፣ አንብባችሁ የማይረባና የማይጠቅም መስሎ ከታያችሁ “ጊዜያችንን
አቃጥለህብናል፤ የማይገባ ድካም ደክመሃል” ብላችሁ ልትወቅሱኝ፣ ፍሬና ቁም ነገር ካገኛችሁበት ደግሞ “ታንጸንበታል፤ በርታ!” ልትሉኝ
ትችላላችሁ።
Wednesday, 24 March 2021
Friday, 19 March 2021
አቢግያ - ኹለት ቤት ያዳነች ሴት
(የታማኝ ትዳር ውብ ምሳሌ)
መጽሐፍ ቅዱስ፣ እጅግ
አስደናቂ ስለ ኾኑ ሴቶች ካስቀመጠልን ሕያው ምስክር አንዷ አቢግያ ናት፤ እንዲህም የተመሰከረላት፣ “የሴቲቱም
አእምሮ ታላቅ፥ መልክዋም የተዋበ ነበረ፤” (1ሳሙ. 25፥3)። በተቃራኒው አቢግያ የስሙ ትርጓሜ “ጅል” ተብሎ ለሚጠራው
ለናባል ሚስቱ ነበረች፤ እርሱ በምግባሩ “ባለጌ፥ ግብሩም ክፉ ነበረ፤ ከካሌብም ወገን የኾነና
… ምናምንቴና ባለጠጋም ነበረ” (ቊ. 3፡ 25)። ሰውየው ባለጌ፣ ግብረ ክፉ፣ ካሌብ የስሙ ትርጉም “ውሻ” እንደ ኾነ፣ የውሻ
ጠባይ ያለው ሰው ነበረ፤ ከሚስቱ ፍጹም ተቃራኒ ሰው!
Thursday, 11 March 2021
መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፮)
ካለፈው የቀጠለ …
ባለፉት ጊዜያት የ“መድሎተ
ጽድቅ” መጽሐፍን በቀጥታ በመጽሐፍ ቅዱስ ከመመዘናችን በፊት፣ በመጽሐፉ ውስጥ ከቅዱሳት መጻሕፍት ዐሳብ ውጭ በኾነ መንገድ እንደ
ገና ተተርጕመው የቀረቡትን ቃላት መመልከት መጀመራችን ይታወሳል። ቃላቱን በተመለከተ ዛሬም ቀጣዩን ክፍል የምናቀርብ ይኾናል። መልካም
ንባብ።
· መዳን፦ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥና በአጭር ቃል ስለ መዳን ሲናገር እንዲህ ይላል፣ “በእርሱ[በክርስቶስ] የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።” (ዮሐ. 3፥16)። በመጽሐፍ ቅዱስ መዳን የሚለው ዐሳብ፣ ልክ በዚህ ክፍል እንደ ተጠቀሰው የዘላለም ሕይወት፣ አዲስ ልደት (ቲቶ 3፥5)፣ አዲሱን ሰው መልበስ (ቈላ. 3፥10)፣ አለመጥፋት (ዮሐ. 3፥16፤ 2ጢሞ. 2፥11)፣ ልጅነት (ሮሜ 8፥13)፣ ዳግመኛ መወለድ (ዮሐ. 1፥12-13፤ 3፥3-8) በሚሉ ተካካይ ዐሳቦች ገልጦት እንመለከታለን።
Monday, 8 March 2021
ኢየሱስ እስኪመጣ - ዘጠኝ የአገልግሎት ዓመታቴ
በእግዚአብሔር ቸርነትና የተትረፈረፈ
ምሕረት፣ ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት በብሎግ ወይም በጡመራ መድረክ አገልግሎት አገልግያለሁ፤ በእነዚህ ዓመታት ከእግዚአብሔር የሰማኋቸውን፣
የተቀበልኳቸውን፣ ቅዱስ ቃሉን ሳነብብና ሳጠና መንፈስ ቅዱስ የገለጠልኝን፣ በኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች የደረሱትን እጅግ አሳዛኝ
ሰቆቃዎችንና ከፍ ያሉ በደሎችን በአካል በስፍራው ተገኝቼ በመመልከት እግዚአብሔር ምን ይሰማው ይኾን? ብዬ ሙሾ አውርጄአለሁ።







