ካለፈው የቀጠለ …
ቅድስና፦ ከመጽሐፍ ቅዱስ፣ ቊልፍ ቃላት መካከል አንዱ ቅድስና የሚለው ነው። በተቃራኒው
ደግሞ፣ “የመድሎተ ጽድቅ ጸሐፊ”፣ ከመጽሐፍ
ቅዱስ ውጭ ትርጕም ከሰጣቸው ቃላት አንዱ ቅድስና ነው። ቅድስና የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ነው፣ “እንደ
እግዚአብሔር ቅዱስ የለምና፥ እንደ አምላካችንም ጻድቅ የለምና፤ ከአንተ በቀር ቅዱስ የለም።” (1ሳሙ. 2፥2)፤ “እኔ እግዚአብሔር
አምላካችሁ ነኝና፤ ሰውነታችሁን ቀድሱ፥ ቅዱሳንም ሁኑ፥ እኔ ቅዱስ ነኝና፤” (ዘሌ. 11፥44)፤“ ጌታ ሆይ፥ የማይፈራህና
ስምህን የማያከብር ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህና፥” (ራእ. 15፥3) ተብሎ እንደ ተጻፈ፣ እግዚአብሔር አምላክ ብቻ ቅዱስ ነው። በዕብራይስጥ (godesh), በግሪክ
(hagiosune) ተብሎ የተጠራው ቅድስና ትርጉሙ፣ መለየት ወይም እግዚአብሔርን መምሰል የሚል ነው። ቃሉ በተለይ በዘሌዋውያን
መጽሐፍ ላይ እጅግ ተደጋግሞ የተጠቀሰ ነው።



