ከንቱ ትምክህት!
ማኅበረ ቅዱሳንና አንዳንድ የኦርቶዶክስ ሰባክያን፣ ስለ ክርስትና ሲያወሩ፣
ክርስትናን ራሳቸው ጠፍጥፈው የሠሩትና ለዓለም የናኙት ይመስላሉ። እነርሱ በግብዝነት የሚመኩትን ያህል ክርስትና የሰበኩት፣ የመንግሥቱን
ወንጌል ለዓለሙ የናኙት የመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት እንኳ እንደ እነርሱ ፈጽሞ አይመኩም፤ አይገበዙምም። እጅግ በጣም የሚያስደንቀው
ነገር፣ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ አባ ሰላማ፣ ኢትዮጵያዊ እንዳልኾነ የሚያውቁ እጅግ ጥቂቶች ናቸው። እንዲያውም ከታወቁት የቤተ ክርስቲያን
ታሪክ ጸሐፍት አንዱ፣ ቅዱስ ማቴዎስ የተገደለው በኢትዮጵያ ምድር እንደ ኾነ ይነግረናል። ክርስትና አገር በቀል ቢኾን፣ ክርስቲያን
በኢትዮጵያ ምድር ባልተገደለ!



