Wednesday, 27 November 2019
Wednesday, 20 November 2019
ንቀት (ክፍል ፫)
Please read in PDF
ጌታ ኢየሱስ ማንንም አልናቀም!
“… በተስፋ የተጠበቀው መሲሕ ሌላ ዐይነት ክብር፣ ማለትም የትሕትናን
ክብር ለብሶ ነበር በመካከላቸው የተገኘው። አባ ኔቪል ፈጊስ የተባሉ ካህን እንደ ተናገሩት፣ ‘እግዚአብሔር ታላቅ ነው የሚለው
የሙስሊሞች እወጃ እውነትነቱ ጉልህ በመሆኑ ያለልዕለ ተፈጥሮአዊ ህልው እገዛ ሰው ሊረዳው ይችላል። እግዚአብሔር ትንሽ ነው
የሚለውን ግን ኢየሱስ ለሰው ልጆች ያስተማራቸው እውነት ነው።’ …”[1]
ጌታ ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣበት መንገድ እጅግ አስደናቂና ልብን
በመደነቅ የሚመላ ነው። የመጣበት መንገዱና ዓላማው ለብዙዎች የሚጥምና የሚጣፍጥ አይደለም፤ በአዲስ ኪዳንም አገላለጥ ጠባብ
መንገድ፣ የግመል መርፌ ቀዳዳ ታህል፣ እስከ መስቀል ሞት መታዘዝ፣ የራስ ክብርንና መብትን መተው፣ ባልንጀራን እንደ ራስ መውደድ … በሚል ውብ ሕይወትና ዝንባሌዎች
የተመላ ነው።
Wednesday, 13 November 2019
ንቀት (ክፍል ፪)
Please read in PDF
እግዚአብሔር አይንቅም!
እግዚአብሔር
አምላክ በክብር የተከበበና በፍቅር የተትረፈረፈ አምላክ ነው፤ እግዚአብሔር ፍጥረትንም ሲፈጥረው በድንቅና በግሩም ክብር ነው፤ “ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ፤ ሥራህ ድንቅ ነው፥ ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች።” (መዝ. 139፥14) እንዲል፣ ሰው በግሩም፤ በድንቅ አድናቆት ተመልቶ የተፈጠረ ነው። መዝሙረኛው እንዲህ
ሲል የፈጠርከውን ሰው የምታውቀው አንተ ነህ፤ እኔንም የፈጠርኸኝ አንተ ነህና በሚገባ ታውቀኛለህ፤ ምክንያቱም በእናቴ ማኅፀን ያበጃጀኸኝና
በእናቴ ማኅፀን ሳለሁ ንቁ ኾነህ የተንከባከብኸኝ አንተ ነህ እያለ ነው፣ ያህዌ ኤሎሂምን!
Friday, 8 November 2019
አቤንኤዘር
Please read in PDF
አቤንኤዘር አቤንኤዘር መዝሙራችን
ድል አይተናል ተዋግቶልን ረዳታችን
ቅኔ አምጡ ተንጓደዱ በምስጋና
ከሳሽ ወድቋል ጌታ ቀኙን ልኳልና
Monday, 4 November 2019
ንቀት (ክፍል ፩)
Please read in PDF
መግቢያ
ቅዱስ ጳውሎስ ዘርዝሮ ካልጨረሳቸው(ገላ.
5፥19-21) እና ተዘርዝረው ከማያልቁት የሥጋ ሥራዎች አንዱ ንቀት ወይም ሰዎችን መናቅ ነው፤ የሥጋ ሥራዎችን እንዘርዝራቸው
ብንል ዳርቻው ኹሉ እንደማይበቃቸው እናውቃለን፤ ነገር ግን ክርስቶስ ኢየሱስ በመስቀሉ ኃይል እኒህንና ሌሎችንም ኃይላት ደካማ
በሚመስል መንገድ ሰብሮና በመስቀሉ ጠርቆ አስወግዶአቸዋል። አለቅነት፣ ሥልጣን፣ ኃይል፣ ጌትነት ኹሉ በክርስቶስ ጌትነትና ኃይል
ተሽሮአል፤ (ኤፌ. 1፥20-21፤ 3፥10፤ ፊልጵ. 2፥9)። ክርስቶስ በመስቀል ሞቱ የተወደደና ቅዱስ ሕይወት እንኖር ዘንድ
በደሙ ፉጨት ጠርቶናል።
Wednesday, 30 October 2019
“ሂዱና … ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው።” (ማቴ. 28÷19)
Please read in PDF
የቤተ
ክርስቲያን የመጀመርያና የመጨረሻው ዋነኛ ራዕይና ተልዕኮ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል ለፍጥረት ሁሉ ማድረስና ደቀ
መዛሙርት አድርጎ ወደመንግስቱ መሰብሰብ ነው። ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር የመንግሥት ወንጌል ከማገልገል በቀር ሌላ ምንም
ተልዕኮ፤ የምትዋደቅለትም ዓላማ የላትም። በስደት ዘመን ሰማዕታት፤በሰላም ዘመን መምህራንና መጋቢዎችን፣ ድንቅ አማኞችን ቤተ
ክርስቲያን ያፈራችው በእውነተኛው ዘር በክርስቶስ ህያውና ቅዱስ ዘር በሆነው ቃሉ ነው።
Thursday, 24 October 2019
ገና አልተመለከታችሁምን? (ማር. 8፥17)
Please read in PDF
ይህ ጽሑፍ በ2008 ዓ.ም አጋማሽ
ላይ በአንድ ሌላ የጡመራ መድረክ ላይ በብዙዎች የተነበበ ነው! መልእክቱ ዛሬም ደማቅ ስለ ኾነ በድጋሚ እንዲቀርብ ኾኖአል!
ቃሉን የተናገረው በወርቀ ደሙ የዋጀንና ያዳነን መድኅን አለም ኢየሱስ
ክርስቶስ ነው። ደቀ መዛሙርቱ በፈሪሳውያንና በሄሮድስ እርሾ ክፉ ኃጢአት በመዋጥ እንዳይጠፉ ባስጠነቀቃቸው ጊዜ፣ እነርሱ ግን ከማስተዋል
ዘግይተው እንጀራ ባለመያዛቸው እንደ ተናገረ አስበው ተነጋገሩ። ጌታ ያየላቸው ዘላለማዊውን ዐሳብ ነው። እነርሱ ግን ገና በሥጋ
አዕምሮ ነበሩና ስለ ቍሳዊውና ተበልቶ እዳሪ ስለሆነው እንጀራ አሰቡ። እርሱ ስለመንፈሳዊው ነገር ይነግራቸዋል እነርሱ ግን የሚናገራቸውን
እንኳ በወግ አያስተውሉም።
Saturday, 19 October 2019
በልብ መጠበቅ
Please read in PDF
ነገርን በልብ ስለ
መጠበቅ በመጽሐፍ ቅዱስ በአንድ ምዕራፍ ኹለት ጊዜ የተነገረላት እናት የኢየሱስ እናት ቅድስት ማርያም ናት። ቅድስት ድንግል ማርያምን
በተመለከተ ከኹለት ልዩ ልዩ አካላት የሚሰነዘሩትን ነገሮች በጥሙና ለሰማ ሰው ዲያብሎስ ሐሳቡ የተሳካለት ይመስላል። (አንዱ ቤት
ከአምላክ እንድትስተካከል አድርጎ፣ ሌላው ቤት ደግሞ ፈጽሞ እንድትጠላ በማድረግ)። ኹለቱም ወገኖች ከመጽሐፍ ቅዱስ አድራሻ ለመራቃቸው
እማኙና የመጀመርያው ማስረጃ ያው ታላቁ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። (ስለነዚህ ወገኖች ሌላ የብዕር ቀጠሮ ልያዝና በቀጥታ ወደ ዛሬው ዐሳቤ
ላቅና)።
Thursday, 17 October 2019
Sunday, 13 October 2019
Sunday, 6 October 2019
ሾላኮቹ (የመጨረሻ ክፍል)
Please read in PDF
ምን እንድርግ?
በባለፉት ጊዜያት እጅግ መልካም ነገሮችን በማንሣት በዚህ ርእስ ሥር ስናጠና
ቆይተናል፤ ሾላኮችን ጠባያቸውንና ኹለንተናዊ ባሕርያቸውን አንስተንም ተመልክተናል፤ ከዚህ በመቀጠል ደግሞ እኛ ምን ማድረግ እንደሚገባን
በማንሣት የእግዚአብሔርን ቃል እንጫወታለን።
1.
ወደ ቃሉ
እንመለስ፦ የሾላኮቹ ያላሳለሰ ተግባራቸው እኛን ከቃሉ መነጣጠል ነው፤ ወደ ቃሉ ልንመለስና ዘወር የምንልባቸውን ማናቸውንም
ምክንያቶችና መንገዶችን ጨርሰው ነው የሚዘጉት። ብንመለስ እንኳ ለገዛ ራሳቸው እንዲመች አድርገው ቃሉን ያጣምማሉ እንጂ በትክክል
እንድንመለስ አያደርጉም፤ አይፈልጉምም።
Friday, 4 October 2019
እሬቻን የማላከብርበት ክርስቲያናዊ ምክንያቴ
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ “የፖለቲካው ጡዘት አገራዊ መልኩን በመልቀቁ፣ ብሔርና ሃይማኖት ተደጋፊ” ከመኾን ጋር ተያይዞ፣
የበአላትን ፉክክር ሃይማኖታዊ መልክ ሲያለብሱ እየተመለከትን ነው። ይህ ደግሞ ውል አልባ የኾነ መጠዛጠዝንና መገፋፋትን፣ “እኔ
እበልጥ እኔ እበልጥ!” የሚል ሥጋዊ መቀናናትን ሲያስከትልና ትውልድ የሚመርዙ ተግባራት “ሃይ ባይ” ማጣታቸውንም እንድንመለከት
አድርጎናል። ልክ እንደ ዘመነ መሣፍንት፣ “በዚያም ዘመን በእስራኤል ዘንድ ንጉሥ አልነበረም፤ ሰውም ሁሉ በፊቱ መልካም መስሎ
የታየውን ያደርግ ነበር።” (መሣ. 16፥7) ተብሎ እንደ ተነገረው፣ የትኛውም ሰውና ብሔር መልካም መስሎ የታየውን ከማድረግ
ከልካይ የሌለበትና እግዚአብሔር የተገፋበት የተናቀበት ዘመን ላይ ነን።
Friday, 27 September 2019
Lallaba gowwummaa (1Qoro. 1:21)
Please read in PDf
Waaqayyoon ilma namaa
cubbuudhaan bade jiru gara qulqullumaa fi qajeelumaatti deebisuuf; ilma isaa
tokkicha Goofta Yasuus Kiristoos gara biyya lafaatti ergee jira. Ilmi isaa
tokkichaan haalli inni gara biyya lafaatti ittiin dhufe bayyee kan nama
haawachisuufi gammachiisu miti. Tasumaa karaan itiin dhufe kabajaa fi
jaalatamummaa biyya lafaa barbaadu hundaaf faallaa ta’eti.
Wednesday, 25 September 2019
Monday, 23 September 2019
ሾላኮቹ (ክፍል ፬)
Please read in PDF
ባለፈው በተመለከትነው ክፍል ሾላኮቹ ማንን ያስታሉ? ብለን በቀዳሚነት
ከቅዱሳት መጻሕፍት ጠቅሰን “እውነትን ማወቅ የማይወዱ
ሞኞች ሴቶችን” እንደሚያስቱ ተመልክተናል፤ ዛሬ ደግሞ የዚኹን ቀጣይ ክፍል እንዲህ እንድታነቡት ጋብዛችኋለሁ፤ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ፤
አሜን።
2.
አዳዲስ አማኞችን፦ አዳዲስ
አማኞች ለቃለ እግዚአብሔር ጥማት የተጋለጡ ናቸው፤ ከቃለ እግዚአብሔር ጋር የተያያዘ ማናቸውንም ትምህርቶች ለመስማት ይቸኩላሉ።
በተለይም ሾላካ መናፍቃን የሚጠቅሷቸውንና እውነተኛ መምህራን የሚጠቅሷቸውን እውነተኛ ትምህርት ከመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ጋር በማነጻጸር
የትኛው እውነተኛና የትኛው ደግሞ ሾልኮ እንደ ገባ የመለየትና የማስተዋል እንከን አለባቸው።
Subscribe to:
Posts (Atom)


