Wednesday, 18 September 2019

ሾላኮቹ (ክፍል ፫)

Please read in PDF

   በባለፉት ኹለት ክፍሎች የመናፍቃንን የሾላካነት ጠባይ መመልከታችን አይዘነጋም፤ ከዚያ በመቀጠል ዛሬም እንመለከታለን፤ የጌታ ጸጋና ሰላም ከኹላችሁ ጋር ይኹን፣ አሜን፡፡
4.      ዩነትን ወይም እንግዳ ዘርን ለመዝራት፦ ጌታችን ኢየሱስ እንክርዳድ ዘሪው ክፉ፣ ማንም ሳያየው በሌሊት ወይም ጨለማን ለብሶ በመሹለክ ተግባር እንዳደረገው ነግሮናል፤ ጠላት እንክርዳድ የዘራው በዚያው መልካሙ ዘር በተዘራበት እርሻ ላይ ነው፤ አበቃቀሉም ኹለቱም በአንድነት በቀሉ፤ የስንዴውም የእንክርዳዱም አበቃቀላቸው ተመሳሳይና አንዱን ከሌላው ለመለየት እጅግ አዳጋች እንደ ኾነ፣ “እንክርዳዱን ስትለቅሙ ስንዴውን ከእርሱ ጋር እንዳትነቅሉት አይሆንም” (ማቴ. 13፥29) ከሚለው ከጌታችን ኢየሱስ ንግግር እናስተውላለን።

Wednesday, 11 September 2019

መጨመሩን ሳይኾን

Please read in PDF

አዲስ ዐመት መጣ ዘመን ተጨመረ
ፊተኛው አረጀ አዲስ ተሞሸረ                                                               
ይህ ለእኔ አይደለም ላመንኩት በልጁ  ... 

Monday, 2 September 2019

ሐዋ. 2 ላይ የብሔርተኞቹ ሸቃጭነት!



በቃሉ ውስጥ ባዕድ ዐሳብ ቀላቅሎ ማቅረብና መሸቀጥ ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነት የማይታዘዙ ሰዎች ኹነኛ መገለጫ ነው (2ቆሮ. 2፥17፤ 4፥2)፤ ከሰሞኑ የተነሡት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም፣ ዝቅ ብለውና ወርደው “በክልል ደረጃ፣ በአንድ ብሔር ስም” ክርስትናን “እንመስርት” ባዮቹ አካላት፣ እጅግ ድፍረት በተሞላበት ንግግር መጽሐፍ ቅዱስን ጠቅሰው፣ ይህን እኩይና እቡይ ድርጊታቸውን እንደሚደግፋቸው ሲጠቅሱ ሰምተናቸዋል፤ በቋንቋና በብሔር ክርስትናን ለመደራጀት እንደሚፈቅድላቸው ከጠቀሱት ጥቅስ አንዱ ደግሞ  የሐዋርያት ሥራ ኹለትን ነው።

Friday, 30 August 2019

የቄሳር ተላላኪ “ቀሳውስት” - ሠርግና ምላሽ



ቤተ ክርስቲያን ከመንግሥት ጋር “ተቃራኒ” በነበረችባቸው ዘመናት፣ ማለትም ነገሥታት ጸረ ክርስትና አቋም ይዘው ተነሥተው በነበሩባቸው ዘመናት፣ ቤተ ክርስቲያን ከሩቅ የሚታይ አብረቅራቂ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋን ተጐናጽፋ ነበር፤ ከአንድ መቶ ሃምሳ ዓመታት በላይ ከኔሮን ቄሣር እስከ ዲዮቅልጥያኖስ የዘለቀው ጽኑ የመከራ ዘመን ቤተ ክርስቲያን እንደ ቦኸር በዐለት ላይ ተከላት እንጂ፣ ፈጽሞ ካመነችው እውነትና ከመንፈስ አንድነቷ አላነወጣትም፤ አልከፋፈላትም፡፡ መከራ ማጥሪያዋ ብቻ ሳይኾን መጽናኛዋም ጭምር ነበር፡፡

Tuesday, 27 August 2019

ሾላኮቹ (ክፍል ፪)

Please read in PDF
2.   መስረቅ፦ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ወደ በጐች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው፤” በማለት ሲናገር ሾላኮቹ ራሳቸውን በማመሳሰልና በመደበቅ የተካኑ መኾናቸውን እየነገረንም ጭምር ነው፤ (ዮሐ. 10፥1)። ሌባ በባሕርይው ተደብቆ ወይም ሾልኮ እንጂ በግልጽ መግባትን አያውቅም። ይህንም የሚያደርገው ተቀዳሚ ዐላማው የእርሱ ያልኾነውን ነገር፣ ለራሱ ጥቅምና ፍላጎት ለመስረቅና ለመውሰድ ነው።

Monday, 19 August 2019

ከኢየሱስ በቀር!

Please read in PDF
ሙሴ ቢናገርም ኤልያስ ቢያወራም፣
ጴጥሮስ ሦስት ዳስን ለመሥራት ቢነቃም፣
ከክብሩ ነጸብራቅ ከመንግሥቱ በቀር

Monday, 12 August 2019

ሾላኮቹ (ክፍል ፩)

Please read in PDF
   መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ ቃል ሐራጥቃ[1] የኾኑ መናፍቃንን ጠባያቸውን ሊገልጥ በሚችል መንገድ፣ ሾላኮች ወይም ወደ ቤቶች ሾልከው የሚገቡ በማለት ይጠራቸዋል፤ (ገላ. 2፥4፤ 2ጢሞ. 3፥6፤ ይሁ. 4)። ቅዱስ ጳውሎስ ወደ እግዚአብሔር አደባባይና ወደ አማኞች የሚገቡት እንደ ሰላይ ነው ይለናል፤ ጌታችን ኢየሱስ ደግሞ ከአማኞች ጋር ልዩነት የሌላቸው እስኪመስሉ ድረስ “እንደ ተኩላ” (ማቴ. 7፥15) ነው ይለናል፤ ሰላይ መመሳሰልን ገንዘብ ያደርጋል፤ ተኩላም ኹለ ነገሩ ከበግ ጋር አንድ ዓይነት መኾንን ይመርጣል፤ ይህን ተፈጥሮአዊ ተመሳስሎታቸውን የሚጠቀሙት ግን የሚፈልጉትን ለማግኘት ወይም በጭካኔያቸው ለመንጠቅና በግን በሕይወቱ ቦጫጭቀው ለመብላት ነው።

Saturday, 3 August 2019

የእምነት እንቅስቃሴ አማኞች መጽሐፍ ቅዱስን በዐውድ አያውቁትም!

Please read in PDF
ዐውድ አንድን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ለመረዳት ወሳኝ ነው፤ ዐውድን አለመረዳት ጠቅላላ የመጽሐፉን ዐሳብ አለመረዳት ነው፤ መንፈስ ቅዱስ ቀድሞ የተናገረውን ያብራራልናል ይገልጥልናል እንጂ፣ አዲስ መገለጥም ኾነ ኢየሱስ ከተናገረው የተለየ የሚነግረን ምንም ነገር የለውም፤ ይህም በዐውድ ውስጥ ልንረዳው እንችላለን ማለት ነው፡፡ ከመንፈስ ቅዱስ ቀጥሎ፣ ዐውድ የቀደመው መልእክት ለዝንተ ዓለም ዘመን ዘለቅ ኾኖ እንዲሻገር ኹነኛ አጥር ነው ማለት እንችላለን፡፡

Monday, 29 July 2019

ወርሰህ ክበርበት

Please read in PDF
እኔ …
ኹል ጊዜ ስሑት ፍጹም የማልረባ
ዘወትር በደጄ ኃጢአት የሚያደባ

Monday, 22 July 2019

ከክርስቶስ ይልቅ “ቄሣርን” አወዳሽ “ነቢያት”! (የመጨረሻ ክፍል)

Please read in PDF
“ወንጌላውያን” ነቢያትና ቤተ መንግሥታዊ ማስታወቂያነታቸው
  “ወንጌላውያን” ነቢያትና ጥቂት የማይባሉ ኦርቶዶክሳውያን አገልጋዮችም ጭምር ቤተ መንግሥቱ በሕዝብ ዘንድ ዕውቅና ያገኝ ዘንድ ተግተው “እያገለገሉ” ይመስላል፤ ለዚህም ለምሳሌ፦ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ መወቀስ አይገባቸውም እስከሚለው ጥግ የሄዱ አገልጋዮችን አይተናል፤ እንዲያውም ቤተ ክርስቲያን ከቤተ መንግሥት ባነሰ ማንነት መኖሯን ራሳቸውን ጭምር በመስደብ ያቀረቡትን ሰምተናቸዋል። ለዚህም ለከት አልባ በኾነ መንገድ ግልጥ ፖለቲካዊ ቃላትን በመጠቀም ሲወርዱ ተመልክተናቸዋል።
ለምሳሌ፦
-       “አርበኝነት በደሙ የተዋሐደው” ኢትዮጲያዊነት፣
-       ሃያ ሰባት ዓመታት መብታችን ተጥሶ … ፣
-       የኢትዮጵያ … የጠላቶቿ ድንጋይ አቀባዮች (የማርሲሉ ዮናታን አክሊሉ)፣
-       ኢትዮጵያን እግዚአብሔር በቃል ኪዳን ጠብቆአታል፣
-       የጠቅላዩ ዙፋን የተቀባና በእግዚአብሔር ፈቃድ የተከናወነ ነው፤(ኢዩ ጩፋ) የሚሉትንና ሌሎችንም መጥቀስ ይቻላል።

Tuesday, 16 July 2019

ከክርስቶስ ይልቅ “ቄሣርን” አወዳሽ “ነቢያት”! (ክፍል - 2)

Please read in PDF
ጸያፍ ድፍረት
   ራሱን ከወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት እንደ አንዱ እንደ ኾነ የሚቈጥረው፣ የ“Christ Army” ቴሌቪዥን ባለቤት ኢዩ ጩፋ፣ ስሙንና ክብሩን በሚናኝበት በገዛ ቲቪው ላይ “ለጠቅላይ ሚኒስቴሩ ጻፍኩት” ባለውና በገዛ ቲቪው ላይ “ሲደሰኩር”፣ ለኢየሱስ የሚነገሩትን ምሳሌዎች በመላ ወስዶ ለጠቅላዩ ሲናገር እንሰማዋለን፤ እንዲህ ይላል …
“ … ዕውቀትህ አስገራሚ ነው፣ ንግግርህም ይፈውሳል፤ እንደ ነቢይ ትተነብያለህ፣ እንደ መምህር አስተማሪ፣ እንደ አባት መካሪ ነህና ዕድሜ ይጨምርልህ፤ አባት ነህና እንደ አብርሃም፣ ንጉሥ ነህና እንደ ዳዊት፣ ነቢይ ነህና እንደ ሙሴ፣ ካህን ነህ እንደ ኢያሱ፣ ጠቢብ ነህ እንደ ሰሎሞን፣ ደፋር ነህ እንደ ጳውሎስ፣ ታጋሽ ነህ እንደ ኢዮብ፣ ቆራጥ ነህ እንደ ሩት፣ ባለ ራእይ ነህ እንደ ዮሴፍ … እነዚህን ኹሉ ነህና …”
  ከሰማኹት በኋላ ጆሮዬ ጭው ብሎአል፤ ደንግጬ ከመናገርም ከመስማትም ተቆጥቤ፣ ነገሩን ነፍሴ ተጸይፋውም በተደጋጋሚ “በኢየሱስ ስም እንዲህ ያለ ክፉ ነገር ከእኔ ይራቅ!” ብዬአለሁ። የመሸታ ቤት አዝማሪ እንኳ ይህን ያህል ገንዘብ ለከፈለው ወርዶ አያወድስም!!!


Saturday, 13 July 2019

ከክርስቶስ ይልቅ “ቄሣርን” አወዳሽ “ነቢያት”! (ክፍል - 1)

Please read in PDF
መግቢያ
   በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መካከለኛ ዘመን ታሪክ፣ የቤተ መንግሥትን አስነዋሪ ድርጊት ፊት ለፊት ከተጋፈጡት መካከል በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን የተነሡት ደቂቀ እስጢፋኖሳውያን፣ በአጼ ፋሲል ዘመን የተነሡት መነኮሳት፣ አባ ፊልጶስና አኖሬዎስ ዘጸጋጅን ተጠቃሽ ናቸው፤ እኒህ አባቶች የነገሥታቱን አመንዝራነት፣ ፍትህ አልባነት፣ ድኃ ገፊነት፣ እጆቻቸውን በደም መታጠብ ፊት ለፊት የተጋፈጡና በሕይወታቸው ተወራርደው ዋጋ የከፈሉ ናቸው።
   እስጢፋኖሳውያን ዘርዐ ያዕቆብ እጁን ከቤተ ክህነትና ከቤተ ክርስቲያን እንዲያነሣ ደጋግመው ሞግተዋል፤ ቤተ መንግሥትና ቤተ ክህነት ጋብቻ ሊፈጽሙ አይገባም በማለት ይናገሩ የነበሩት የመጀመሪያዪቱ ቤተ ክርስቲያን አማኞችና አባቶች ሳይሳሱ ፊት ለፊት ተጋፋጭና ተሟጋችም ነበሩ፤ በቤተ ክርስቲያን በትር ዙፋናቸውን ያጸኑ አያሌ ነገሥታት ኢትዮጵያ የነበራትን ያህል፣ ነገሥታት በቤተ ክርስቲያን በትር ዙፋናቸውን ማጽናታቸውን እንዲያቆሙ የተጋደሉ አያሌ አባቶችንም[መጨረሻቸው መሥዋዕትነት ቢኾንም] ነበሩ።



Friday, 12 July 2019

የዓምዳዊ ስምዖን ጸሎት

በመስቀል ላይ ሳለህ ራስህን ዘንበል(ዘለስ) ያደረግህ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ወደ አንተ ምስጋና አሳርግ ዘንድ ለሞተውና ላዳነኝ ምስጋና ይሁን እያለች ነፍሴ በአምላካዊ በገና ታመሰግን ዘንድ የነፍሴን ራስ ከፍ ከፍ አድርግ፡፡
ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በመስቀል ላይ የሞትክ፥ በሞትህም ሞት ድል የሆነ አንተ እንደ አባትህ ሕያው ስትሆን በሥጋ ሞትን የምትቀበል ሁነሃልና፡፡ ሞትንም የምታጠፋ አንተ ነህና፤ አንተስ መቼም መች አንተ ነህ፤ አንተም የሕይወት አካል ነህ፡፡

Thursday, 27 June 2019

ሰዶማዊነት - መዘንጋት የሌለበት ጉዳይ! (የመጨረሻው ክፍል)


የሰዶማውያን ስውር ደባ
    በግልጥ ማንነታቸው ቢመጡ የሚቀበላቸው እንደሌለ ያውቁታል፤ ስለዚህም ስውርና ሰዎች ቀስ በቀስ ወይም በድንገት እንዲላመዱ የሚያደርጉባቸው መንገዶች አሏቸው፤ ለምሳሌ፦ የታወቁ የፊልም አክተሮችን በዋና ተዋናይነት ማጫወት፣ በሕጻናት ፊልሞች ውስጥ ሰዶማዊነትን መሰንቀር [ስንቶቻችን ለሕጻናቶቻችን ፊልሞችን አስቀድመን አይተን መርጠን እናቀርብላቸዋለን?]፣ በአኹን ሰዓት ከክርስቲያን ፊልሞች በቀር በማናቸውም ፊልሞች ላይ እጅግ በአብላጫው የሰዶማውያንን ሃሳብ እናያለን፣ ቀስ በቀስ ያላምዱናል፣ በቀዝቃዛ ውኃ ጥደውን ቀስ አድርገው እሳቱን እያነደዱ መቀቀልና መፍረስን ያላምዱናል፤ ምልክቶቻቸውን በተቃውሞ መልክ እንድናሠራጭ ይቈሰቁሳሉ፤ በዚህ ረገድ የአገራችን የቅርቡ ኹኔታ በሚገባ ተሳክቶላቸዋል፡፡