ኹሉም ነገሮቻችን በእኛ አቅም የተያዙ አይደሉም፣ መያዝም አይችሉም፤ በጌታ
እግዚአብሔር ኹሉን ቻይነትና አለኝታነት ተደግፈው ያሉ እንጂ። የሕይወት እስትንፋሳችን እንኳ ተቀጥላ ያለችው፣ በእስትንፋስና በሕይወት
ባለቤት በእግዚአብሔር መግቦት ብቻ ነው። ምሕረቱ ባይበዛልን፣ ቸርነቱ ባይገንልን፣ ፍቅሩ ባይትረፈረፍልን፣ ተግሳጹ ነፍሳችንን ባይመልሳት፣
ምክሩ ድካማችንን ባያበረታው፣ ማጽናናቱ ልባችንን ባይደግፈው … ገና ያኔ ገና በተዋጥን፣ የአዳኙ ወጥመድ ይዞን በጠፋን ነበር።
Friday, 8 March 2019
Tuesday, 5 March 2019
ከሰማይ በመውረዱ ራሱን ባዶ ያደረገ ኢየሱስ[ዘወረደ]
Please read in PDF
ጌታ ኢየሱስ የሰውን ሥጋ በመልበሱ፣ ከሰማየ ሰማያት ገሊላዊት ወደ ኾነችው የናዝሬት መንደር በመውረዱ፣ ከአንዲት በናዝሬት አገር ከምትኖር ድኃ ድንግል ሴት በመወለዱ፣ ኃጢአት በሚገዛው ዓለም በመመላለሱ … እጅግ ተዋርዷል። ይህን በማድረጉም በገዛ ፈቃዱ ራሱን ከራሱ ባዶ በማድረግ ለአባቱ ፈቃድ ፍጹም ታዟል።
ጌታ ኢየሱስ ከሰማይ ወደ ምድር ወረደ ስንል፣ በአምላካዊ ማንነቱ ወይም በመንፈሱ ወዳልነበረበት ዓለም መጣ እያልን አይደለም፤ እርሱ ኹሉን የሚያውቅ (ዮሐ. 2፥24-25)፣ ኹሉን የፈጠረና የደገፈ ደግሞም፣ “ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል”፤ (ዮሐ. 1፥3፤ ቈላ. 1፥16፤ ዕብ. 1፥2-3) እንዲል፣ ኹሉ በኹሉ የኾነ፣ ጌታና የፍጥረት ኹሉ ባለቤት ነው። ምድርና መላዋ የእርሱና እርሱም ያለባት ናት፤ (መዝ. 24፥1)።
Sunday, 3 March 2019
“እኔ የመረጥሁት ጾም ይህ ነውን?” (ኢሳ. 58፥3)
እስራኤል በግልጥ ነውር
ተይዛለች፤ በነውር የተያዘችው እስራኤል በሠራችው ኀጢአት ንስሐ መግባትና ራስዋን በጾም ክዳ ወደ አምላኳ ያህዌ ኤሎሂም መምጣት
ሲገባት፣ እርሷ ግን ሃሰተኛ አምልኮ በማቅረብ፣ አምላኳን በሃሰተኛ አምልኮ ለመደለል፤ ለማታለል ፈለገች። በሰው አተያይ አምላክ
የሚያይ መስሏት ኢየሩሳሌም ተታለለች፤ በታይታዊ የግብዝነት ሕይወት ትጾማለች ግን ጾሟ በእግዚአብሔር ፊት የተወደደ አልነበረም፤
ሰውነቷን ታዋርዳለች ግን ውርደቷን በክብር የሚለውጥላት አንዳች የለም፤ ምክንያቱም ፈቃድዋን እንጂ የያህዌን ፈቃድ
አትፈጽምምና።
Wednesday, 27 February 2019
Tuesday, 19 February 2019
“ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ” (ማቴ. 12፥41)
Please read in PDF
የአይሁድ መሪዎችና ሕዝቡም የክርስቶስን መሲሕነት ለማረጋገጥ ምልክትን [ተአምራትን] በተደጋጋሚ ጠይቀውታል። የጠየቁት መሲሕነቱን ለማመንና እርሱን ለመከተል አይደለም፣ ይልቁን መሲሕነቱን ለማወቅ የመጡበት መንገድ ጠማማና ያለማመን መንገድ ነው። በዚህ በማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 12 ላይ ብቻ እንኳ ሊፈታተኑ በተደጋጋሚ ጥያቄ አቅርበዋል፤ (ቁ. 2፤ 14፤ 24፤ 38)፤ ፍጹምና ጻድቅ የኾነውን መሲሕ ሊፈትኑት እርሱ የሚያሳየውን ምልክት በተደጋጋሚ ጠይቀዋል። የፈለጉት ተአምራት በጉልህ የሚታይና አሁን በሰማያት ላይ የሚደረገውን ነበር፤ (ሉቃ. 11፥16)።
የአይሁድ መሪዎችና ሕዝቡም የክርስቶስን መሲሕነት ለማረጋገጥ ምልክትን [ተአምራትን] በተደጋጋሚ ጠይቀውታል። የጠየቁት መሲሕነቱን ለማመንና እርሱን ለመከተል አይደለም፣ ይልቁን መሲሕነቱን ለማወቅ የመጡበት መንገድ ጠማማና ያለማመን መንገድ ነው። በዚህ በማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 12 ላይ ብቻ እንኳ ሊፈታተኑ በተደጋጋሚ ጥያቄ አቅርበዋል፤ (ቁ. 2፤ 14፤ 24፤ 38)፤ ፍጹምና ጻድቅ የኾነውን መሲሕ ሊፈትኑት እርሱ የሚያሳየውን ምልክት በተደጋጋሚ ጠይቀዋል። የፈለጉት ተአምራት በጉልህ የሚታይና አሁን በሰማያት ላይ የሚደረገውን ነበር፤ (ሉቃ. 11፥16)።
ምልክቱን የፈለጉት ራሳቸው እንደሚሹት ነው እንጂ ሊታነጹበትና እግዚአብሔርን
የተአምራት ድንቅ አምላክ ብለው ለማመስገንና ለማምለክ አይደለም፤ ይልቁን ሊነቅፉት፣ ሊፈትኑት፣ በእርሱም ላይ ሊሳለቁ ነበር። በቀጥታ
ንግግራቸውም ኢየሱስ ተአምራትን ያደርግ የነበረው በሰይጣን ኃይል እንደ ኾነ በግልጥ በመናገር ንቀታቸውን አሳይተዋል። በዚህ ንግግራቸው
ይህን ብቻ የሚያደርጉ አይደሉም። እግዚአብሔር የዘለላም አምላክ መኾኑን የሚቃወሙ ናቸው። ምክንያቱም እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን
የሠራቸው ሥራዎቹ፣ ተአምራቶቹ፣ ምልክቶቹ የሚያረጁና የሚያልፉ አይደሉምና። ይህን ባለማስተዋል በፍጹም ስተዋል።
ኢትዮጲያ በግልጥ ኢየሱስን ለመከተል ከአስቸጋሪ አገራት መካከል ስትመደብ!
Please read in PDF
ምድራችን ኢትዮጵያ ኢየሱስን በግልጥ ለመከተል አስቸጋሪ ከኾኑት ከዓለማችን
አገራት 29ኛ ደረጃ ላይ መገኘቷን ያውቃሉ? አዎን ምድራችን ብዙ ሃይማኖተኛ ሕዝብ ቢኖራትም ነገር ግን ለክርስቶስ ኢየሱስና ለኢየሱስ
አማኞች ምቹ ምድር አይደለችም፡፡ ምድራችን ኢየሱሳውያንን፣ በኢየሱስ የሚያምኑትንና ስሙን ወደው የሚጠሩትን ታሳድዳለች፣ ታንገላታለች፣
የመንቀሳቀስ ነጻነታቸውን ትነፍጋለች፣ ትደበድባለች፣ ንብረት የማፍራት መብታቸውን ትነፍጋለች፣ ኢየሱሳውያን[የኢየሱስ ትውልዶች]
መከራቸው ዛሬም አለ፡፡
Sunday, 17 February 2019
አርባ ምንጭና ተሰሎንቄአዊ ልቧ
በኹለተኛው ሐዋርያዊ ጉዞው፣ ቅዱስ ጳውሎስና ሲላስ ወንጌል በመመስከር ካለፉባቸው ከተሞች አንዷ ተሰሎንቄ ናት፤ “በአንፊጶልና በአጶሎንያም ካለፉ በኋላ ወደ ተሰሎንቄ መጡ፥ በዚያም የአይሁድ ምኵራብ ነበረ።” (ሐዋ. 17፥1) እንዲል፣ ወደ ተሰሎንቄ እንደ ገቡ ያደረጉት እንደ ልማዳቸው ከቅዱሳት መጻሕፍት እየጠቀሱ ወንጌልን ማስተማር ነበር። የቅዱስ ጳውሎስና ሲላስም የምስክርነታቸው ማዕከል “ይህ እኔ የምሰብክላችሁ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው” የሚል ነው፤ ምክንያቱም “ክርስቶስ መከራ እንዲቀበልና ከሙታን እንዲነሣ ይገባው ነበርና”።
Monday, 11 February 2019
ቤተ ክርስቲያን ተጐታችና ዘመነኛ ችግሮቿን አስተውላ ይኾንን!? (የመጨረሻ ክፍል)
1.10.
የዘፋኞችንና የአለማውያንን ዝናና ዕውቅና “መቀላወጥ”
ቤተ ክርስቲያን ከአስተማሪዋ መንፈስ ቅዱስ የተማረችው አንድ ትልቅ
እውነት “ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞትን በመካድ … ራስዋን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን መኖርን”
ነው (ቲቶ 2፥12-14)። “እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው
መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ እንጂ፥ በእኛ መልካም ሥነ ምግባር አለመዳናችንንም አውቀን” (ቲቶ 3፥5) መዳናችንን በመልካም
ሥራ መገለጽ እንዳለበት ጸጋን አደላዳዩ መንፈስ ቅዱስ ያስተምረናል። ምክንያቱም ትክክለኛ የኾነ ሥነ ምግባር ምንጩ ትክክለኛ ትምህርት
ነውና።
Tuesday, 5 February 2019
ዘመነኛ “አገልጋዮችን” ሳስብ ትዝ የሚለኝ እንዲህ ነው!
ጌታ አትረፍርፎ ባርኮኛል፣ ዲታና ቱጃር አድርጐ¡ እንዴ ጌታ
ቢባርከኝ አይደል እንዴ የ10 ሚሊየን ብር መኪና ለራሴ፣ የ12 ሚሊየን ብር መኪና ለባለቤቴ መግዛቴ?¡ ጌታማ ልዩነት
ያደርጋል፣ እንኳን በማያምኑትና በእኔ፣ በሚያምኑትና በእኔ መካከል ራሱ ልዩነት ያደርጋል፣ አዎን ያደርጋል፣ ስለሚያደርግም ነው፣
የ200 ሚሊየን ብር መኖሪያ ቤት የሰጠኝ፤ ደግሞ ባርኮቱ እጅግ በጣም ስለተትረፈረፈልኝ፣ ከሰሞኑ ደግሞ የ600 ሚሊዮን ብር
ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ላሠራ ነው፤ ገና ደግሞ በእስቴዲየም ደረጃ የወንጌል ማገልገያ አዳራሽ እናሠራለን፤ ለወንጌልማ ሰማይ
ጠቀስ ሕንጻ ሊገነባለት ይገባል¡¡¡ ለምን ብለን በየመንደሩ፣
ለምን ብለን በየቀዬው፣ ለምን በየገበያው፣ ለምን በየወንዛ ወንዙ እየሄድን እንደ ኢየሱስና ጳውሎስ እንደ ቀደሙት ደቀ መዛሙርት
ለምን “ሳይመቸን እየተንዘላዘልን” እንሰብካለን?¡ ኢየሱስ ራሱ፣ “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና
በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ …” ማለቱ ትክክል
አይደለም፤ እርሱ ዞሮ ያልሰበሰበውን ሕዝብ እኮ እኛ ይኸው ተቀምጠን በቀላሉ ሰብስበን አይደለም ወይ? የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ባይኾኑም
የእኛ ምርጥ ደቀ መዛሙርት ናቸውና ደስ ይለናል?
Tuesday, 29 January 2019
ቤተ ክርስቲያን ተጐታችና ዘመነኛ ችግሮቿን አስተውላ ይኾንን!? (ክፍል 9)
1.8.
ግብረ ሰዶማዊነት
“ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ፤ እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን
ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ …” (ሮሜ 1፥26-27)
“… ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ … የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።” (1ቆሮ. 6፥9-10)
ኀጢአትን አዘውትረው ለሚሠሩ ሰዎች ሁሉ
(ክርስቲያኖችን ጭምር) መንፈሳዊ ሞት የሚያገኛቸው መኾኑን ታላቁ መጽሐፍ ደጋግሞ ተናግሯል (ሮሜ 6፥16፤ 8፥13፤ ገላ. 5፥21፤
ኤፌ. 5፥5-6፤ 1ዮሐ.2፥4፤ 3፥9፤ ያዕ. 1፥15)። ኀጢአትን በተመለከተ ምንም መታለል አይገባም፤ ብዙ ሰዎች በክርስቶስ ሞት
ያገኙትን ነጻነት ለራሳቸው የኃጢአት ሥራ በነጻነት ለመፈጸም እንዲያመቻቸው ሲጠቀሙበት እናያለን። ይህንንም በተመለከተ ታላቁ መጽሐፍ፦
“ወንድሞች ሆይ፥ እናንተ ለአርነት ተጠርታችኋልና፤ ብቻ አርነታችሁ ለሥጋ ምክንያትን አይስጥ፥ … ” (ገላ. 5፥13) እንዲሁም
“አርነት ወጥታችሁ እንደ እግዚአብሔር ባሪያዎች ሁኑ እንጂ ያ አርነት ለክፋት መሸፈኛ እንዲሆን አታድርጉ” (1ጴጥ. 2፥16) በማለት
በግልጥ ያለምንም ማወላወል አርነታችንን ኀጢአትን ለመፈጸም እንደ መሸፈኛ ማቅረብ እንደማንችል ያስቀምጣል።
Tuesday, 22 January 2019
“ከ“መጋቢ”ው የተሻለ መናፍቅ፣ በዚህ ዘመን ይገኝ ይኾንን?”
Please read in PDF
“ … መጽሐፍ ቅዱስ ማኑዋል አይኾንም ወይ? መጽሐፍ ቅዱስ እኮ፣ የኃጢአታችን
ውጤት እንጂ የጽድቃችን ውጤት አይደለም፣ አርፈን ገነት ብንቀመጥ አንድ ሺህ ገጽ መጽሐፍ አይጫንብንም ነበር፣ አዳምና ሔዋን ተንቀዥቅዠው
ከገነት ከወጡ በኋላ ነው፣ አንድ ሺህ ገጽ ጉዳችንን የሚዘረዝር ኀጢአት ተዘርዝሮ፤ እርሱማ የጉዳችን ማኑዋል ነው፣ ጠባያችንን አይገልጥም፤
ለዚህ ነው እኔ የኀጢአት ውጤት ነው፣ በነገራችን ላይ ብሉይ ኪዳንም ኾነ አዲስ ኪዳን፣ ቁርአንም ኾኑ ሌሎቹም መጻሕፍት በጠቅላላ
ከገነት ከተባረርን በኋላ ለስደተኛ የተጻፉ መጻሕፍት ናቸው፤ ስደተኛውን ለማረጋጋት የተጻፉ መጻሕፍት ናቸው እንጂ፣ ማኑዋልማ ሊኾን
አይችልም፤ በግል ልታወራኝ ትችላለህ፣ እኔ የገባኝ ይህ ነው፤”(ጫጫታና ሳቅ፣ ጭብጨባ ከሕዝቡ)
“መጋቢ” [አ]ዲስ ይህን ንግግር የተናገሩት፣ ዶክተር
ምሕረት ደበበ በሚያዘጋጀው፣ “mindset” እየተባለ በሚጠራ መደበኛ ፕርግራም ላይ፣ “ህሊናና ስብዕና” በሚል ርእስ ተዘጋጅቶ
በነበረው የውይይት መድረክ ነው። በውይይቱ ላይ ማናቸውም ሰው መሳተፍ
እንደሚችልና “አእምሮን ለመገንባት” በሚል “ዒላማም”፣ የተለያዩ ዝግጅቶች ጭምር እንደሚቀርቡበት ይታመናል። ለዚህም ይመስላል የተለያየ
ግንዛቤና ዝንባሌ ያላቸው ሰዎች በፕሮግራሙ ላይ በመጋበዝ ሃሳብ ይሰነዝራሉ፣ የውይይት መነሻ ሃሳቦችን ያቀርባሉ፣ ጥናቶችን ያስደምጣሉ፣
ውይይቶች ይደረጋሉ። ከሚቀርቡት ሰዎች መካከል ደግሞ መጋቢ” አዲስ አንዱ ናቸው።
Tuesday, 15 January 2019
ቤተ ክርስቲያን ተጐታችና ዘመነኛ ችግሮቿን አስተውላ ይኾንን!? (ክፍል 8)
Please read in PDF
1.7.
እንደ ወንጌሉ ታላቅ መርሖ አለመኖር
1.7.1.
መርሖ አንድ፦ “ሂዱ”
ከወንጌል ትውፊትና ዋና መርሖ አንዱ ሂዱ የሚለው
ነው። የቤተ ክርስቲያን የዕድሜ ልክ ታላቁ ተልዕኮዋም “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥
ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ …” (ማቴ. 28፥19) የሚለው ነው። ቤተ ክርስቲያን
ተዘልላ ተቀምጣ የሚመጡትን ብቻ መጠበቅ የለባትም። ውኃ በአንድ ቦታ ሲቀመጥ ይሸታል፤ አማኞችም አንድ ቦታ ሰፍረው እንዲቀመጡ አልተባለላቸውም።
እንደ ዘር እንዲበተኑና እየዞሩ ወንጌሉን እንዲሰብኩ እንጂ (ሉቃ.
10፥1፤ ሐዋ. 8፥4 ፤ 13፥1-4)።
Wednesday, 9 January 2019
ቤተ ክርስቲያን ተጐታችና ዘመነኛ ችግሮቿን አስተውላ ይኾንን!? (ክፍል 7)
1.5.
በፍርድ ቤት መክሰስና
መካሰስ
በታሪክ እስከ አኹን ያልተሰማ እንግዳ ሆኖ እየሰማን ካለው ነገር አንዱ፣
የቤተ ክርስቲያን የገዛ ልጆቿን ዓለማዊ ፍርድ ቤት አቁማ፤ ጠበቃ ቀጥራ የመክሰሷ ጉዳይ ነው። እንዲህ ያለ ነገር በቆሮንቶስ ቤተ
ክርስቲያን ተከስቶ እንደ ነበር “… ወንድም ወንድሙን ይከሳል፥ ይህም በማያምኑ ፊት ይደረጋልን? እንግዲህ ፈጽሞ የእርስ በርስ
ሙግት እንዳለባችሁ በእናንተ ጉድለት ነው” (1ቆሮ. 6፥6-7) በማለት ሐዋርያው አስቀምጧል።
Saturday, 5 January 2019
ሕጻኑና እናቱ
Please read in PDF
የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ከቅድስት ድንግል
የመወለዱን ነገር ከጻፉልን ወንጌላውያን አንዱ ቅዱስ ማቴዎስ ነው፤ መሲሑ ተናፋቂው ማስያስ፣ በነቢያት ትንቢትና በአበው ምሳሌ የተነገረለትና
የዘመናት ናፍቆት የነበረው ሕጻንና ጌታ፣ አባትና ልዑል ምጡቅ ከኾነው ከአባቱ ከሰማይ ወጥቶ ወደ ሰው ልጆች ኹሉ[ወደ እኛ] በመምጣቱ
ተገለጠ፤ ቅዱስ ማቴዎስ ይህን እውነታ የመሲሑን ነገረ ልደት ከአይሁድና ከአሕዛብ የትውልድ ሐረግ ቈጥሮ በመምዘዝ፣ በመዘርዘርም
መሲሑን ዘላለማዊ ነገር ግን በሥጋ ዕድሜ የተወሰነ ጊዜ ሊቈጠርለት እንዳለው (1ጢሞ. 2፥6) በመንፈስ ቅዱስ ተነድቶ ጻፈልን።
ወንጌላዊው ቅዱስ ማቴዎስ ስለሕጻኑና እናቱ ሲናገር፣
ሕጻኑን ቀዳሚና አቻ የሌለው በማድረግ ኹል ጊዜ ያቀርበዋል። በምዕራፍ ኹለት ላይ ብቻ ይህን እውነታ በጕልህ መመልከት እንችላለን፤
“ሕፃኑን ከእናቱ
ከማርያም ጋር አዩት”፣ “ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ”፣ “እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን በሌሊት ያዘና …”፣
“ሕፃኑንና እናቱን ያዘና ወደ እስራኤል አገር ገባ”፣ (ማቴ. 2፥11፣ 13፣ 14፣ 21) በማለት በማናቸውም ስፍራ ላይ ከእናቱ
በፊት ሕጻኑን በማስቀደም፣ ፊተኛ በማድረግ፣ በማግነን፣ በማላቅ ያስቀምጠዋል[በእርግጥስ ሕጻኑ ያልላቀ ማን ሊልቅ፣ መሲሑ ያልገነነ ማን ሊገንን፣ ኢየሱስ ፊተኛ ያልኾነ ማን ሊቀድም
…?]።
Friday, 4 January 2019
ቤተክርስቲያን ተጐታችና ዘመነኛ ችግሮቿን አስተውላ ይኾንን!? (ክፍል 6)
·
ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል።
·
ሹም ሲቆጣ ማር ይዞ እደጁ፥
ደስ ሲለው ማር ይዞ እደጁ።
በምሳሌነት ይህን
ተረት አነሳን እንጂ ከዚህ ተመሳሳይነት ያላቸው ተረቶችና ምሳሌያዊ ንግግሮች በተወሰነ መልኩ በባህላችን ውስጥ ተሰንቅረው ለጉበኝነትና
ለመታያ ስጦታ የሚሰጡት ኢ ሥነ ምግባራዊና ሞራላዊ ድጋፍ አለ።
የእግዚአብሔር ቃል
በግልጥ፦ “ፍርድን አታጣምም ፊት አይተህም አታድላ ጉቦ የጥበበኞችን ዓይን ያሳውራልና፥ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና
ጉቦ አትቀበል” (ዘዳግ. 16፥19) በማለት ይናገራል። አንድ ሹም ጉቦ ወይም መማለጃን የሚቀበለው እውነቱን ሐሰት፤ ሐሰቱን እውነት
ለማለት ወይም ለማድረግ ነው። እውነቱን ሐሰት ስንል ጻድቁን ወይም እውነተኛውን እንበድላለን፤ ሐሰቱን ደግሞ እውነት ነው ስልን
ኅጢአተኛውን በጻድቁ ላይ እናሰለጥናለን።
Subscribe to:
Posts (Atom)
