በጋሻው የሰውን ሰውነት አያምንም፡፡ ሰው
ሥጋና ነፍስ ወይም ሥጋና መንፈስ ነው፤ የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት በጋሻው፣ “ሰው መንፈስ ነው፤ ነፍስ አለው፤ በሥጋ ውስጥ
ያድራል፡፡” በሚለው ፍጹም ክህደት ደምድሞታል፡፡ የዚህ ኑፋቄ ትምህርቱንም ሲያብራራ እንዲህ ይላል፦
“ ... በእግዚአብሔር የተፈጠረው
መንፈስ የሆነው ሰው ከምድር አፈር አዘጋጀው፡፡ ... ያበጀውን፣ የፈጠረውን ያበጀው ውስጥ ጨመረው፤ መንፈስ ሥጋ ውስጥ ገባ
ማለት ነው፡፡ ... ነፍስ ማለት ሦስተኛ አካል ምናምን አይደለችም … ነፍስ የተባለው ነገር ዕውቀት ስሜት ፈቃድ ናት፡፡ ለምሳሌ፦
አንድ ዕውቀት ወይም ትምህርት ... ለምሳሌ፦ ባዮሎጂ አካል አለው እንዴ? ... እርሷ[ነፍስ] በመንፈስና በሥጋ መካከል ሆና
ላሸነፈው ላሳመነው ... እርሷን ራሱ በዕውቀት ነው የምታሳምነው፡፡ ... በተጨባጭ ነገር ካመነች ስሜት ይፈጠራል ማለት ነው፡፡
...
... ስለዚህ ሰው የራሱ ፈቃድ፣ የራሱ እውቀት፣ የራሱ
ስሜት ያለው ማንም ጣልቃ የማይገባበት ለወደደው ነገር ራሱን የሚያስገዛ ማንነት ባለቤት ሆኖ ተፈጠረ፡፡ ስለዚህ ሰው ማን ነው?
ከተባለ መንፈስ ነው ነፍስ አለው በሥጋ ውስጥ ያድራል ነው መልሱ፡፡ ሰው ሥጋ ነው፤ ነፍስ ነው አትልም፤ ሰው ማን ነው? ከተባለ
ሰው መንፈስ ነው፤ …”
|



