Sunday, 18 January 2026

ተጠመቀ ጌታ!

 Please read in PDF

ርደተ ገሃነም ርደተ መቃብር

በመርገመ ሥጋም የነፍስ ሲጨመር

ጽሕፈተ ዕዳችንም ደልቦ ወርዝቶ

በእኛነታችን ላይ እንደ ለምጽ ነጥቶ

መቅረብ እንዳንችል ሰማዩ ተዘግቶ …

ሳለን ኀጢአተኛ ፍጹም ጠላቶቹ

ሊታረቀን መጣ የሱስ የናዝሬቱ፡፡

ከኀጢአት በቀር ሊኾን ከኛ እንዳንዱ

መጣ ክብሩን ትቶ ወዶ በፈቃዱ፤

በዕደ ዮሐንስ ልክ እንደ ኀጥዕ ሰው

ተጠመቀ ጌታ ዕዳችንን ሊሽር፤ ሰማዩን ሊከፍተው!

No comments:

Post a Comment