ለቤተ
ክርስቲያን ከተሰጡ ሐዋርያዊ ተልእኮዎች ውስጥ፣ ቀዳሚውና የዘወትር ተግባር “አማኞችን ደቀ መዛሙርት ማድረግ” ነው። እንደ
ጌታችን ትምህርት፣ አማኞች ደቀ መዛሙርት የሚኾኑት፣ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሲጠመቁ፣ ጌታ ያዘዘውን ኹሉ እንዲጠብቁ
ሲማሩ፣ እንዲሁም በመታመን እርሱን ለመከተል ደቀ መዛሙርት በሕይወት ሲኾኑ ነው።
Friday, 19 January 2024
“እያጠመቃችኋቸው፥ … እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤” (ማቴ. 28፥20)
Thursday, 18 January 2024
“ከእኛ ጋር ለምን አስተካከልሃቸው?” (ማቴ. 20፥11)
ጌታችን ኢየሱስ መንግሥተ ሰማያት ምን እንደምትመስል በሰጠው ውብ ምሳሌ፣ እግዚአብሔርን የወይኑ እርሻ ባለቤት አድርጎ ያቀርበዋል። የእርሻው ባለቤት በአትክልቱ ስፍራ ሰውን ለመቅጠር ፈልጎ ጥሪ አቀረበ። በጥሪው መሠረት ሠራተኞቹ፣ አንድ ዲናር ሊከፈላቸው ተስማምተው ወደ እርሻው ቦታ መጡ። የሥራው ሰዓትም ከማለዳ 12 ሰዓት እስከ ምሽት 12 ሰዓት ነበር።
Wednesday, 17 January 2024
ነገረ ሥላሴን የምናጠናበት ምክንያት (ክፍል ፯)
ካለፈው ቀጠለ …
5. የቅድስት ሥላሴ ትምህርት ምስጢር ነው!
ትምህርተ ሥላሴ ምስጢር ነው ስንል፣ ምን ማለታችን ነው? ብንል፣ ለሰው ያልተገለጠ ብዙ ትምህርት ወይም ብዙ ነገር አለ ማለታችን ነው። ኾኖም ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ሦስቱን አካላት ለማጥናት ብዙ ትምህርት እንዳለ ልንዘነጋ አይገባም። በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ትምህርቶች ምስጢር ተብለዋል፤ ለምሳሌ፦ ጌታችን ኢየሱስ፣ ለደቀ መዛሙርቱ፣ “ለእናንተ የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፥ ለእነርሱ ግን አልተሰጣቸውም።” ሲል (ማቴ. 13፥11)፣ ምሳሌዎቹ የተነገሩት በሕዝቡ ኹሉ ፊት ቢኾንም፣ ትርጕማቸው ወይም ምስጢሩ ግን የተነገረው ለደቀ መዛሙርት ብቻ ነው።
Thursday, 11 January 2024
Sagantaa Addaa Ayyaana Yaadannoo Dhaloota Kiristoos!
Saturday, 6 January 2024
ከባሪያዪቱ የተወለደ ንጉሥ!
የክርስትና ትምህርት ከደመቀበትና ከተንቈጠቈጠበት ቀዳሚው እውነት አንዱ፣ የእግዚአብሔር
ልጅ በእርሱ የሚያምኑትን ኹሉ በጸጋ የእግዚአብሔር ልጆች ያደርግ ዘንድ የሰው ልጅ መኾኑ ነው። እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ ኾኖ፣
ዓለማትን የፈጠረና ደግፎም
የያዘ ወይም ዓለሙ ተያይዞ የቆመው (ዮሐ. 1፥3፤ ቈላ. 1፥17፤ ዕብ. 1፥3) በእርሱ በታላቁ አምላክ ቢኾንም፣ በተለየ አካሉ ከባሪያዪቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም (ማቴ. 1፥21፤ ዮሐ. 1፥14)
ሥጋን ነሥቶ ተወለደ።
Monday, 1 January 2024
መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፳፯)
ካለፈው የቀጠለ …
ባለፈው “የመድሎተ
ጽድቅ” ጸሐፊ፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ (Exegesis) ሳይኾን ወደ መጽሐፍ ቅዱስ (Eisegesis) እንደሚተረጕም አንድ ምሳሌ አንስተን
ነበር። ዛሬ በድጋሚ ኹለተኛ ምሳሌ በማንሳት በዚህ ርዕስ ሥር ያለውን ዐሳብ እንቋጫለን።
Thursday, 28 December 2023
ገብርኤል መልአክ - የመሲሑ ምስክር
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በስማቸው የተጠሩና በስም የታወቁ መላእክት ኹለት ብቻ ናቸው፤ እነርሱም ሚካኤል (ዳን. 10፥13፤ ይሁ. 9፤ ራእ. 12፥7) እና ገብርኤል (ዳን. 8፥16፤ 9፥21)። ከእነዚህ መላእክት ውጭ በስም ተጠቅሰው የሚታወቁ ሌሎች መላእክት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሉም። እኒህ መላእክት በቀደመው ኪዳን ሕዝብ ውስጥ እጅግ የታወቁና ስሞቻቸው በተደጋጋሚ የተጠቀሱ መላእክት ናቸው።
Wednesday, 27 December 2023
መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፳፮)
1.5.
ወደ መጽሐፍ ቅዱስ መተርጎም፦ ለዚህ እጅግ አያሌ ማስረጃዎችን ማቅረብ
ይቻላል። በኑዛዜና ቀኖና ውስጥ ከጠቀስናቸው ባሻገር፣ ሌሎች ጥቂት የመጽሐፍ ቅዱስን ክፍሎችን እንዴት ወደ መጽሐፍ ቅዱስ እንደ
ተረጐመ እንጥቀስ።
1.5.1.
“ … ከክርስቶስ መወለድ በኋላ ያለው የሰው ኹኔታ፣ በምልዓተ ኀጢአት ከደረሰበት ርኩሰት
ነጽቷል፤ ተቀድሷል፤ ከድካሙ በርትቷል፤ ከውድቀቱ ተነሥቷል።” [1]
Sunday, 17 December 2023
Friday, 17 November 2023
ነገረ ሥላሴን የምናጠናበት ምክንያት (ክፍል ፮)
ካለፈው
ቀጠለ …
4.2.
አካል፦
“አካል ማለት የሚታየውና የሚጨበጠው ቁስ አካል አይደለም።
አካል ‘ፍጹም ምሉዕና ቀዋሚ እኔ ባይ ማለት ነው’”[1]
ብዙ ሰዎች አካል የሚለውን ፅንሰ ዐሳብ የሚረዱት፣ ከሚዳሰስ ቍሳዊ ነገር ጋር በማያያዝ ብቻ ነው። በርግጥ የሰው ኹለንተና አካል ተብሎ መጠራቱ እውን ቢኾን፣ የሰው አካላዊነት ከዚህ የዘለለ ነው፤ ማለትም አካላዊነት ማንነትንና እኔነትን የሚያካትት ነውና። ስለዚህ አካል ስንል፣ የሰውን ወይም የአንድን ነገር የሚታየውን ቍሳዊ ነገር ብቻ እንዳልኾነ ልናስተውል ይገባል።
Friday, 10 November 2023
ትምህርቱን ያር'ቅ ዘንድ!
ትምህርተ ሥላሴ የክርስትና ዋነኛ ትምህርት ነው። ጠንቅቀን ካልተረዳን ደግሞ ስተን የምናስትበት ትምህርት ነው። ቅድስት ሥላሴ የእምነት መሠረት እንደ መኾኑ፣ ይህን ትምህርት አለማመን ወይም ከትምህርቱ አንዱን አለመቀበል፣ ከኑፋቄ ያስመድባል። ለዚህ ምሳሌ፦ አርዮስንና መቅዶንዮስን በትምህርተ ሥላሴ ላይ ባመጡት ኑፋቄ መወገዛቸውን የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያስታውሷል።
Saturday, 4 November 2023
Wednesday, 1 November 2023
ነገረ ሥላሴን የምናጠናበት ምክንያት (ክፍል ፭)
ካለፈው ቀጠለ …
4. ስለ ምሥጢረ ሥላሴ ስናጠና ልናስተውላቸው የሚገቡ ቃላት
ቃላትን
በትክክል መረዳት ወይም ትክክለኛ ትርጕማቸውን ማወቅ ወደ እውነተኛ ዕውቀት ያደርሳል። በተለይ ደግሞ ትምህርተ ሥላሴን ስናጠና፣
በጥንቃቄ ልናጠናቸው የሚገቡ ቃላት አሉ። እኒህም፦
4.1.
ሥላሴ፦ በአጭር ቃል፣ “ሥላሴ” የሚለው ቃል በአዲስ
ኪዳን መጻሕፍት ምንባባት ውስጥ የለም። ነገር ግን ለቃሉ ሳይኾን ለትምህርቱ ፍጹም ዕውቅናን እንሰጣለን። ምክንያቱም በቅዱሳት
መጻሕፍት ውስጥ የሥላሴ ትምህርትና መገለጥ በስፋት አለና።
“በግእዝ ቋንቋ ቃሉ “ሦስትነት” ማለት ነውና በትምህርተ
መለኮት ጥቅም ላይ ሲውል በአንዱ በእግዚአብሔር ሦስት አካላት እንዳሉ ያሳስባል። በ2ኛው መቶ ዓመት የአንጾኪያ ጳጳስ የነበረው
ቴዎፍሎስ[1]
በግሪክ ቋንቋ “ትሪአስ” እና ተርቱሊያን[2]
በላቲን ቋንቋ “ትርንታስ” (በእንግሊዘኛ TRINITY) ስለ እግዚአብሔር ሲያስተምሩ፥ አካላት ሦስትነትን ለማመልከት
ተጠቀሙባቸው። ከዚያን ጊዜ ጀምረው የቤተ ክርስቲያን አባቶች በእነዚህ ቃላት እየተጠቀሙ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ለማብራራትና
ለመወሰን ሰፊ ጥረት አደረጉ።”[3]
Tuesday, 24 October 2023
ነገረ ሥላሴን የምናጠናበት ምክንያት (ክፍል ፬)
ካለፈው
ቀጠለ …
3.4. ከሰውም ኾነ ከሌላው ፍጥረት ጋር ያለንን
ግንኙነት የተሻለ ያደርገዋል፤
ሰው ከእግዚአብሔር ጋር በኤደን ገነት በቅድስና ይመላለስ ሳለ፣ ግንኙነቱ ፍጹምና እንከን አልባ ነበር፤ (ዘፍ. 2፥8፡ 15፡ 25)። ነገር ግን ሰው በኀጢአት በወደቀ ጊዜ፣ ኀጢአት የሰውንና የእግዚአብሔርን ግንኙነት አበላሸ። ከዚህም የተነሣ ሰው፣ ወደ ወደቀውና ወደ ተሰበረው ዓለም መጣ፤ እግዚአብሔር ግን ለዘላለም ጸንቶ በሚኖረውና በማይለወጠው የቅድስናና የፍቅር ባሕርይው ጸንቶ አለ፤ (ዘጸ. 3፥14፤ ሚል. 3፥6፤ ኢሳ. 48፥12)።
Friday, 6 October 2023
በአጭሩ፣ ኢሬቻ የዋቄፈታ አማኞች አምልኮአዊ በአል ነው!
በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ የሮማ ቄሳራውያን ያህል፣ ለባህላዊ ሃይማኖት መስፋፋት ታላቅ
አስተዋጽዖ ያደረገ አካልን መጥቀስ አይቻልም። በተለይም እኒህ ነገሥታት ክርስቲያኖችን ለማጥፋት ከተጠቀሙበት መንገድ አንዱ፣
ራሳቸውን እንዲመለኩ በማቅረብና ጣዖታትን እንዲመለኩ አዋጆችን በማውጣት ነው፤ የሚቃወሙአቸውን ኹሉ ደግሞ ያለ አንዳች ርኅራኄ
በመፍጀት ተካካይ የላቸውም።[1]
የኢየሱስን ጌትነት አውጀው፣ የቄሳራውያንን አል ጌትነት መቃወምና ጣዖታትን ፍጹም መጠየፋቸው ለክርስቲያን ወገኖች ብርቱ
የስደትና የሰማዕትነት ዋና ምክንያት ነበር።[2]
በተለይም በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ የቤተ ክርስቲያን የስደት ዘመን ወይም ዘመነ ሰማዕታት በመባል የተጠራበት አንዱ
ምክንያት፣ የክርስቲያኖች ቄሳራዊ አምልኮን፣ ሮማዊና ሌሎችንም ባህላዊ ሃይማኖቶችን መጠየፋቸውና አለመቀበላቸው ነበር።[3]







