Monday, 19 June 2023

“ጠላቶቻችሁን ውደዱ” (ማቴ. 5፥43-48)

 Please read in PDF

ጌታችን ኢየሱስ የሚመሠርታት መንግሥት፣ እንደ ሰው ሥርዓትና ትምህርት አይደለችም፤ መንግሥቱ ለፍጹማንና እርሱን ለሚከተሉ ብቻ የምትገባና የምትሰጥ ናት። ጌታችን ኢየሱስ ስለ መንግሥቱና በመንግሥቱ ውስጥ ተከታዮቹ እንዴትና በምን መልኩ መመላለስ እንዳለባቸው ሊያስተምራቸው ወደደ፤ ትምህርቱ ባዶ ቃላት አይደሉም፤ ውብና የሕይወት ተስፋዎችን ጭምር የያዙና በምትመጣውም መንግሥቱ እንዴት መመላለስ እንዳለባቸው በንጉሣዊ ወርቃማ ቃሉ አስተምሮአል።

Sunday, 4 June 2023

የምንጠማው መንፈስ!

 Please read in PDF

ከበዓሉም በታላቁ በኋለኛው ቀን ኢየሱስ ቆሞ፦ ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ። … ይህን ግን በእርሱ የሚያምኑ ሊቀበሉት ስላላቸው ስለ መንፈስ ተናገረ፤ …” (ዮሐ. 7፥37፡ 39)

በአይሁድ ባህል መምህራን የሚያስተምሩት ተቀምጠው ነው፤ ጌታችን ኢየሱስ ግን ከአይሁድ ባህልና ሥርዓት ወጣ ባለ መንገድ፣ ስለ መንፈስ ቅዱስ ሲናገር፣ ኹሉም ሰው እንዲሰማውና ትኵረት እንዲሰጠው ለማድረግ ፈልጐ ቆሞ ደግሞም “ጮኾ” (ቍ. 38) ተናገረ። ቆሞና ጮኾ በመናገሩ፣ ከበዓሉ በመጨረሻው ቀን የነበሩት ሕዝቦች ኹሉ እርሱን ለመስማት ችለዋል።

Thursday, 25 May 2023

“ከእነርሱ ተለይቶ ወደ ሰማይ ዐረገ” (ሉቃ. 24፥51)

Please read in PDF 

የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ዕርገት ከዘገቡልን ወንጌላት መካከል ሉቃስ ቀዳሚውና ብቸኛው ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን መካከል ከተነሣ በኋላ፣ ለአርባ ቀናት ያህል ለደቀ መዛሙርቱ እየተገለጠ ታያቸው፤ በመካከላቸውም ተመላለሰ፤ በመጨረሻም ከሚወዳቸው ደቀ መዛሙርት ጋር በመኾን ወደሚወዳት ከተማ ቢታንያ ሄደ።

Tuesday, 9 May 2023

ግንቦት ልደታና ቦረንቲቻ አይዛመድ ይኾን?

 Please read in PDF

ቦረንቲቻ፣ በዋቄፈና አስተምህሮ መሠረት፣ በዓመት ኹለት ጊዜ ዋቃን ለማመስገንና ምልጃ ለመጠየቅ (መስከረምና ግንቦት አከባቢ) በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ የሚከናወን ባህላዊና አምልኮታዊ ሥርዓት[1] ወይም የሚከበር በዓል ነው። በአርሲ ኦሮሞዎች ዘንድም በቤተሰብ፣ በከብቶቻቸው ላይ የሚመጣቸውን ማናቸውንም ክፉ ነገር ለማስወገድ ከሚከበሩ በአላት አንዱ ቦረንቲቻ ነው።[2] ቦረንቲቻ ክብረ ብኵርና ነው፤ የኦሮሞ ኹለቱ የትውልድ ሥርወ ግንዶች ቦረናና በሬንቱ ናቸው። ቦረና ታላቅ እንደ መኾኑ፣ በኦሮሞ ዘንድ ብኵርና ታላቅ ክብር ስላለው፣ ለቦረና ልዩ ክብር “ቦረንቲቻ” የሚባል በአል ይከበርለታል።[3]

Friday, 21 April 2023

ኀጢአትን ይቅር የማለት ጉዳይ! (ዮሐ. 20፥23)

 

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ፣ ለደቀ መዛሙርቱ ከሰጣቸው ሥልጣን መካከል አንዱ፣ “ኃጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ሁሉ ይቀርላቸዋል፤ የያዛችሁባቸው ተይዞባቸዋል” (ዮሐ. 20፥23) የሚል ነው፤ ብዙዎች የዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ ዓውዳዊ ትርጕም ለሌላ ነገር ሲጠቀሙበት ብንመለከትም፣ በቀጥታ ሲተረጐም የሚሰጠን ትርጕም ግን፣ “እናንተ ኀጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ኀጢአታቸው ይቅር ተብሎአል፤ ያላላችኋቸው ግን ይቅር አልተባለም” የሚል ነው።

Saturday, 15 April 2023

የጴጥሮስ ጌታ ዛሬም ይራራል! (ማር. 14፥66-72)

 Please read in PDF

ቅዱስ ማርቆስ፣ ወንጌሉን ሲጽፍ በቅዱስ ጴጥሮስ ላይ ያተኵራል፤ ነገር ግን ከኢየሱስ በላይ አያልቀውም ወይም ከፍ ከፍ አያደርገውም። ኢየሱስ በተያዘበት ሌሊት ስለ ነበረው ኹኔታ ሲናገር፣ “ጴጥሮስንም፦ ስምዖን ሆይ፥ ተኝተሃልን? አንዲት ሰዓት ስንኳ ልትተጋ አልቻልህምን?” (ማር. 14፥37) ሲል፣ ሌሎቹ ወንጌላት ግን ኢየሱስ ይህን ጥያቄ ያቀረበው ለኹሉም ደቀ መዛሙርት እንደ ነበር ይናገራሉ (ማቴ. 26፥40፤ ሉቃ. 22፥46)።

Friday, 14 April 2023

እናንተ ባሮች ሆይ...!

 Please read in PDF

ንጉሥ በባዶነት ዝቅ አለ ወረደ

አሮጌውን አዳም በአዲስ አስወገደ

Sunday, 9 April 2023

አትተወኝ!

 Please read in PDF

የሰቆቃ አድማስ ተንዶ ሲፈጨኝ
ዋይታና እሪታ ምግብ መጠጥ ሲኾነኝ
እንደ ዘጠኝ ወር ምጥ
በየቀኑ ሳምጥ
ሰቀቀን ወዳጄ ሐዘን ባልንጀራ

Saturday, 1 April 2023

“የሴት ትሸፈን” ትእዛዝ፣ ለአገልጋዮች ምን መልእክት አለው?

 Please read in PDF

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ከሰጣቸው “ሥርዓታዊ ትእዛዞች” አንዱ፣ “ሴትም ራስዋን ባትሸፍን ጠጉርዋን ደግሞ ትቆረጥ፤ ለሴት ግን ጠጉርዋን መቆረጥ ወይም መላጨት የሚያሳፍር ከሆነ ራስዋን ትሸፍን።” (1ቆሮ. 11፥6) የሚል ነው። “ሥርዓታዊ ትእዛዙ”፣ በአምልኮ ሰዓት ሴቶችም “ኾኑ ወንዶች” ተገቢውን ልብስ ለብሰውና የባሕርይ ሥርዓትን መከተል እንዳለባቸው የሚያሳስብ ነው።

Thursday, 30 March 2023

“እርሱ ሊልቅ እኔ ላንስ ይገባል” (ዮሐ. 3፥30)

 Please read in PDF

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኪደተ እግሩ ተመላልሶ ባስተማረበት ወቅት፣ ስለ ራሱ የሰጠውን ምስክርነት የተቀበሉ ጥቂቶች ናቸው። ምስክርነቱን ያልተቀበሉት እርሱ እውነተኛ ስላልኾነ ሳይኾን፣ ብዙዎች ከኢየሱስ ሕይወትና ትምህርት ይልቅ የጨለማ ሥራን በመምረጣቸው ነው፤ (ዮሐ. 1፥6-11)። መጽሐፍ እንደሚል፣ ኢየሱስን የደኅንነታቸው ምንጭ አድርገው የተቀበሉ ሰዎች፥ እግዚአብሔር ለዘላለም ለልጆቹ የሚሰጠውን ልዩ ሕይወት ያገኛሉ። ይህን የማይቀበሉ ግን ለዘላለም ፍርድና ቍጣ የሚጠብቃቸው ናቸው።

Saturday, 18 March 2023

ኢየሱስ ጌታ እንደ ኾነ ትመሰክራለህን?

 Please read in PDF

“ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤” (ሮሜ 10፥9)

ይህን ቃል የተናገረው ታላቁ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ነው፤ የተናገረውም ለሮሜ ቤተ ክርስቲያን አማኞች ነው። ሐዋርያው ይህን ምስክርነት የሚመሰክረው የመዳንን ታላቅና ብቸኛ መንገድ እያመለከተ ባለበት ክፍል ነው። በሮም ምድር የቄሳር ጌትነት ገንኖ ይነገር ነበር፣ አማኞች ግን የኢየሱስን ጌትነት በመመስከር ሰማዕታት ኾኑ፤ ምክንያቱም የኢየሱስ ጌትነትን መቀበልና አለመቀበል፣ ከዘላለም ጉዳያችን ጋር የተያያዘ ነውና።

Friday, 10 March 2023

የ“ምኵራብ” አገልግሎት ቢቀጥልስ?

 Please read in PDF

የምኵራብ አገልግሎት፣ ባቢሎናዊው ንጉሥ ናቡከደነጾር፣ የአይሁድን መቅደስ አፍርሶ፣ ሕዝቡን ማርኰና አፍልሶ ወደ ባቢሎን ሲወስድ፣ ሕዝበ እስራኤል ከአምልኮ ማዕከል ከኢየሩሳሌምና ከመቅደሱ ፍጹም በመራቃቸው፣ ለጸሎትና ለማኅበርተኛነት ልዩ ቤት(ምኵራብ) መሥራትንና በዚያ ጸሎትና ቅዱሳት መጻሕፍትን በማንበብ ለማምለክ ምኵራቦችን አስቀድሞ በባቢሎን ኋላም ደግሞ በኢየሩሳሌም መሥራት እንደ ጀመሩ ይታመናል፤ (ሕዝ. 11፥16)።[1]

Sunday, 19 February 2023

ኑ እንቀደስ!

Please read in PDF

ለቅበላ ሥጋ ማጣጣም ወግ ኾነ
ሰውን ያህል ክቡር  እየመነመነ፤

Saturday, 18 February 2023

የብሔር ተስፋው ምንድር ነው?

Please read in PDf

 እግዚአብሔር አምላክን የምንከተለው ዛሬ የሚታመንና ነገ የሚፈጸም ተስፋ አለው ብለን ስለምናምን ነው። እግዚአብሔርን ብንታመነው የሰጠንን ተስፋ ፈጽሞ ያሳርፈናል፤ “ባናምነው ደግሞ እርሱ የታመነ ሆኖ ይኖራል፤ ራሱን ሊክድ አይችልምና።” (2ጢሞ. 2፥13)፤ እኛ ብንሰናከልና እግዚአብሔርን ብንክድ፣ እግዚአብሔር ጻድቅ ነውና ታማኝ ኾኖ ይኖራል።

Friday, 10 February 2023

“ሰላም ለኹላችሁ ይኹን”

Please read in PDF

ይህን ቃል የተናገረው ናዛዜ ኅዙናን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ይህንም ቃል የተናገረው ለተወደዱ ደቀ መዛሙርቱ ነው፤ ጊዜውም ደግሞ እርሱ በሥጋ ሞቱ በአይሁድ እጅ ከተገደለ በኋላና በመቃብር ተቀብሮ፣ ደቀ መዛሙርት ኹላቸውም በፍርሃት ቆፈን ውስጥ፣ “በመሸ ጊዜ፥ ደቀ መዛሙርቱ ተሰብስበው በነበሩበት፥ አይሁድን ስለ ፈሩ ደጆቹ ተዘግተው ሳሉ፥ ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቆሞ፦ ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው።” (ዮሐ. 20፥19)።