የጌታችን ኢየሱስ
ክርስቶስን ዕርገት ከዘገቡልን ወንጌላት መካከል ሉቃስ ቀዳሚውና ብቸኛው ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን መካከል ከተነሣ
በኋላ፣ ለአርባ ቀናት ያህል ለደቀ መዛሙርቱ እየተገለጠ ታያቸው፤ በመካከላቸውም ተመላለሰ፤ በመጨረሻም ከሚወዳቸው ደቀ መዛሙርት
ጋር በመኾን ወደሚወዳት ከተማ ቢታንያ ሄደ።
Thursday, 25 May 2023
“ከእነርሱ ተለይቶ ወደ ሰማይ ዐረገ” (ሉቃ. 24፥51)
Tuesday, 9 May 2023
ግንቦት ልደታና ቦረንቲቻ አይዛመድ ይኾን?
ቦረንቲቻ፣ በዋቄፈና አስተምህሮ መሠረት፣ በዓመት ኹለት ጊዜ ዋቃን ለማመስገንና ምልጃ ለመጠየቅ (መስከረምና ግንቦት
አከባቢ) በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ የሚከናወን ባህላዊና አምልኮታዊ ሥርዓት[1]
ወይም የሚከበር በዓል ነው። በአርሲ ኦሮሞዎች ዘንድም በቤተሰብ፣ በከብቶቻቸው ላይ የሚመጣቸውን ማናቸውንም ክፉ ነገር
ለማስወገድ ከሚከበሩ በአላት አንዱ ቦረንቲቻ ነው።[2]
ቦረንቲቻ ክብረ ብኵርና ነው፤ የኦሮሞ ኹለቱ የትውልድ ሥርወ ግንዶች ቦረናና በሬንቱ ናቸው። ቦረና ታላቅ እንደ መኾኑ፣ በኦሮሞ
ዘንድ ብኵርና ታላቅ ክብር ስላለው፣ ለቦረና ልዩ ክብር “ቦረንቲቻ” የሚባል በአል ይከበርለታል።[3]
Friday, 21 April 2023
ኀጢአትን ይቅር የማለት ጉዳይ! (ዮሐ. 20፥23)
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ፣ ለደቀ መዛሙርቱ ከሰጣቸው ሥልጣን መካከል አንዱ፣ “ኃጢአታቸውን
ይቅር ያላችኋቸው ሁሉ ይቀርላቸዋል፤ የያዛችሁባቸው ተይዞባቸዋል” (ዮሐ. 20፥23) የሚል ነው፤ ብዙዎች የዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ ዓውዳዊ ትርጕም ለሌላ ነገር ሲጠቀሙበት
ብንመለከትም፣ በቀጥታ ሲተረጐም የሚሰጠን ትርጕም ግን፣ “እናንተ ኀጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ኀጢአታቸው ይቅር ተብሎአል፤
ያላላችኋቸው ግን ይቅር አልተባለም” የሚል ነው።
Saturday, 15 April 2023
የጴጥሮስ ጌታ ዛሬም ይራራል! (ማር. 14፥66-72)
ቅዱስ ማርቆስ፣ ወንጌሉን ሲጽፍ በቅዱስ ጴጥሮስ ላይ ያተኵራል፤ ነገር ግን ከኢየሱስ በላይ አያልቀውም ወይም ከፍ
ከፍ አያደርገውም። ኢየሱስ በተያዘበት ሌሊት ስለ ነበረው ኹኔታ ሲናገር፣ “ጴጥሮስንም፦ ስምዖን ሆይ፥ ተኝተሃልን?
አንዲት ሰዓት ስንኳ ልትተጋ አልቻልህምን?” (ማር.
14፥37) ሲል፣ ሌሎቹ ወንጌላት ግን ኢየሱስ ይህን ጥያቄ ያቀረበው ለኹሉም ደቀ መዛሙርት እንደ ነበር ይናገራሉ (ማቴ.
26፥40፤ ሉቃ. 22፥46)።
Friday, 14 April 2023
Sunday, 9 April 2023
Saturday, 1 April 2023
“የሴት ትሸፈን” ትእዛዝ፣ ለአገልጋዮች ምን መልእክት አለው?
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ከሰጣቸው “ሥርዓታዊ ትእዛዞች” አንዱ፣ “ሴትም ራስዋን
ባትሸፍን ጠጉርዋን ደግሞ ትቆረጥ፤ ለሴት ግን ጠጉርዋን መቆረጥ ወይም መላጨት የሚያሳፍር ከሆነ ራስዋን ትሸፍን።” (1ቆሮ. 11፥6) የሚል ነው። “ሥርዓታዊ ትእዛዙ”፣ በአምልኮ
ሰዓት ሴቶችም “ኾኑ ወንዶች” ተገቢውን ልብስ ለብሰውና የባሕርይ ሥርዓትን መከተል እንዳለባቸው የሚያሳስብ ነው።
Thursday, 30 March 2023
“እርሱ ሊልቅ እኔ ላንስ ይገባል” (ዮሐ. 3፥30)
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኪደተ እግሩ ተመላልሶ ባስተማረበት ወቅት፣ ስለ ራሱ የሰጠውን ምስክርነት የተቀበሉ
ጥቂቶች ናቸው። ምስክርነቱን ያልተቀበሉት እርሱ እውነተኛ ስላልኾነ ሳይኾን፣ ብዙዎች ከኢየሱስ ሕይወትና ትምህርት ይልቅ የጨለማ
ሥራን በመምረጣቸው ነው፤ (ዮሐ. 1፥6-11)። መጽሐፍ እንደሚል፣ ኢየሱስን የደኅንነታቸው ምንጭ አድርገው የተቀበሉ ሰዎች፥
እግዚአብሔር ለዘላለም ለልጆቹ የሚሰጠውን ልዩ ሕይወት ያገኛሉ። ይህን የማይቀበሉ ግን ለዘላለም ፍርድና ቍጣ የሚጠብቃቸው ናቸው።
Saturday, 18 March 2023
ኢየሱስ ጌታ እንደ ኾነ ትመሰክራለህን?
“ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን
እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤” (ሮሜ 10፥9)
ይህን ቃል የተናገረው ታላቁ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ነው፤ የተናገረውም ለሮሜ ቤተ ክርስቲያን
አማኞች ነው። ሐዋርያው ይህን ምስክርነት የሚመሰክረው የመዳንን ታላቅና ብቸኛ መንገድ እያመለከተ ባለበት ክፍል ነው። በሮም ምድር
የቄሳር ጌትነት ገንኖ ይነገር ነበር፣ አማኞች ግን የኢየሱስን ጌትነት በመመስከር ሰማዕታት ኾኑ፤ ምክንያቱም የኢየሱስ ጌትነትን
መቀበልና አለመቀበል፣ ከዘላለም ጉዳያችን ጋር የተያያዘ ነውና።
Friday, 10 March 2023
የ“ምኵራብ” አገልግሎት ቢቀጥልስ?
የምኵራብ አገልግሎት፣ ባቢሎናዊው ንጉሥ ናቡከደነጾር፣ የአይሁድን መቅደስ አፍርሶ፣ ሕዝቡን ማርኰና አፍልሶ ወደ
ባቢሎን ሲወስድ፣ ሕዝበ እስራኤል ከአምልኮ ማዕከል ከኢየሩሳሌምና ከመቅደሱ ፍጹም በመራቃቸው፣ ለጸሎትና ለማኅበርተኛነት ልዩ
ቤት(ምኵራብ) መሥራትንና በዚያ ጸሎትና ቅዱሳት መጻሕፍትን በማንበብ ለማምለክ ምኵራቦችን አስቀድሞ በባቢሎን ኋላም ደግሞ
በኢየሩሳሌም መሥራት እንደ ጀመሩ ይታመናል፤ (ሕዝ. 11፥16)።[1]
Sunday, 19 February 2023
Saturday, 18 February 2023
የብሔር ተስፋው ምንድር ነው?
እግዚአብሔር አምላክን የምንከተለው ዛሬ የሚታመንና ነገ የሚፈጸም ተስፋ አለው ብለን ስለምናምን ነው። እግዚአብሔርን ብንታመነው የሰጠንን ተስፋ ፈጽሞ ያሳርፈናል፤ “ባናምነው ደግሞ እርሱ የታመነ ሆኖ ይኖራል፤ ራሱን ሊክድ አይችልምና።” (2ጢሞ. 2፥13)፤ እኛ ብንሰናከልና እግዚአብሔርን ብንክድ፣ እግዚአብሔር ጻድቅ ነውና ታማኝ ኾኖ ይኖራል።
Friday, 10 February 2023
“ሰላም ለኹላችሁ ይኹን”
ይህን ቃል
የተናገረው ናዛዜ ኅዙናን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ይህንም ቃል የተናገረው ለተወደዱ ደቀ መዛሙርቱ ነው፤
ጊዜውም ደግሞ እርሱ በሥጋ ሞቱ በአይሁድ እጅ ከተገደለ በኋላና በመቃብር ተቀብሮ፣ ደቀ መዛሙርት ኹላቸውም በፍርሃት ቆፈን
ውስጥ፣ “በመሸ
ጊዜ፥ ደቀ መዛሙርቱ ተሰብስበው በነበሩበት፥ አይሁድን ስለ ፈሩ ደጆቹ ተዘግተው ሳሉ፥ ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቆሞ፦ ሰላም
ለእናንተ ይሁን አላቸው።” (ዮሐ. 20፥19)።
Sunday, 5 February 2023
ለዮናስ ነነዌ፤ ለዮናታን አክሊሉ ኦርቶዶክስ፣ ግድ አይደሉም!
እግዚአብሔር፣ ታላቅ ኀጢአት ሠርታ ስለ ነበረችው ነነዌ ሲናገር እንዲህ ይላል፣ “እኔስ ቀኛቸውንና ግራቸውን የማይለዩ ከመቶ ሀያ ሺህ የሚበልጡ ሰዎችና ብዙ እንስሶች ላሉባት ለታላቂቱ ከተማ ለነነዌ አላዝንምን?” (ዮና. 4፥11)። ዮናስ ምንም እንኳ የእግዚአብሔር ነቢይ የነበረ ቢኾንም፣ ለነነዌ ግን እንጥፍጣፊ ርኀራኄና ሃዘኔታ አለማሳየቱ እጅግ አስደናቂ ነገር ነው። ነቢይነት ሰዎች ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱ በግልጥ የእግዚአብሔርን ዐሳብና ፈቃድ የመናገርን ያህል፣ ስለ ኀጢአት ደግሞ ሲገስጹና ሲቈጡ የእግዚአብሔርን የርኅራኄ ልብ ሳይጥሉና ፍጹም እየሳሱ መኾን ነበረበት።
Friday, 27 January 2023
የአዳዲሶቹ ጳጳሳት ሹመት ስጋት፣ ተስፋዬና ትዝብቴ
ጌታ እግዚአብሔር
በሉዓላዊ አምላክነቱ፣ ክፉውን ነገር ኹሉ ለክብሩ ሊጠቀምበት፣ ወደ በጎ እንደሚያመጣው እናምናለን፤ ኀጢአት እንኳ ከእግዚአብሔር
የሉዓላዊነት ወሰን አልፎ አያውቅም፤ እናም በምድራችን ላይ የምንሰማውን መለያየትና ጥቅመኝነትን ጌታ እግዚአብሔር አጥፍቶ፣
ለሕዝባችን መታነጽና ለክብሩ ታላቅነት እንዲሠራ ከኹሉ በፊት አስቀድመን እንማልዳለን።
አዎን! እግዚአብሔር የፈርዖንን ልበ ደንዳናነት፣ ለሕዝቡ ጥበቃና ትድግና እንደ ተጠቀመበት መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። እግዚአብሔር ሉዓላዊ ነው ስንል፣ በመላለሙ ላይ መጋቢና ሠራዒ፤ አስተዳዳሪና ጌታ ነው እያልን ነው፤ ስለዚህ የምድራችን ነገር የሚገደውና የሚያስብልን ተንከባካቢና ጻድቅ ጌታ አለን ማለታችንም ነው!










