ዘጠነኛ ክፍል እንግሊዘኛ ያስተምሩን አስተማሪያችን ይኅደጐ ይባላሉ፣ ማስተማር
ከመጀመራቸው በፊት ጥቊር ሰሌዳውን በሚገባ ደጋግመው ያጸዱት ነበር፤ አንድ ቀን አንዱ ተማሪ፣ “ቲቸር ለምን እንዲህ ውልውል አድርገው
በሚገባ ያጸዱታል?” ብሎ ጠየቃቸው፤ እነርሱም፣ “በሚገባ ባልታጠበ ትሪ ምግብ ትበላለህ?” ብለው ጥያቄውን በጥያቄ መለሱለት። እኔም
ዛሬ ሳስተምር፣ እንደ ቀደመው አስተማሪዬ በሚገባ መወልወልን ልማዴ አድርጌ አስቀርቼዋለሁ። ወደ ክርስትና ስመጣ የእኒህ አስተማሪ
“መርህ” በዋዛ የሚታለፍ አይደለም።
Saturday, 27 February 2021
ኢየሱስ ጣዖት አይደለም!
Monday, 22 February 2021
“በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ።” (ዮና. 3፥8)
ጥንተ ታሪክ
ሊመጣ ካለው ቊጣና ፍርድ ታመልጥ ዘንድ፣ የንስሐ ዕድልን ሊሰጥ እግዚአብሔር
የአማቴ ልጅ ዮናስን ወደ ነነዌ ላከ። ነገር ግን ነቢዩ ዮናስ እግዚአብሔር ላዘዘው ምላሹ አለመታዘዝና ወደ ራሱ ፈቃድ አዘንብሎ
ከእግዚአብሔር ፈቃድ ሸሸ። እግዚአብሔር ግን ሉዓላዊና ኹሉን ሲያደርግ የሚሳነው የሌለ ነውና ዮናስን ወደ ነነዌ በራሱ ማጓጓዣ [በተአምራዊ
መንገድ] በዓሳ አንበሪ ሆድ ጭኖ ነነዌ አደረሰው።
Tuesday, 16 February 2021
ራቪ ከሞት ወዲያ፤ እኛ ከወዲህ ኾነን!
ራቪ ዘካርያስ፣ “የገዛ ሚኒስትሪያቸው” ያረጋገጠባቸው አስቀያሚው የዝሙት ገመና ብዙ ነገሮችን እንዳብሰለስል አድርጎኛል። በርግጥ ከደካማው ሥጋ ለባሽ ይልቅ፣ ቅዱስ ቃሉ የማይለወጥና ብርቱ አስተማሪያችን፣ የሚረባንንና የሚጠቅመንን የሚነግረን ኹነኛ መምህራችን ነበረ፤ እንዳለመታደል በትክክል ከመስማትና ከመታዘዝ ቸል አልን እንጂ። አዎን መጽሐፍ ቅዱስ “የብርቱዎችን” ድካም ያራቆተው፣ እንማርበትና እንታነጽበት ዘንድ እንጂ እንገበዝበት ዘንድ አይደለም።
Monday, 8 February 2021
Tuesday, 2 February 2021
መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፭)
ካለፈው የቀጠለ …
·
እግዚአብሔርን መምሰል፦
“በርካታ የምዕራብ
ክርስቲያኖች የኦርቶዶክስን የቲኦሲስ ወይም እግዚአብሔርን የመምሰል ሥነ ሐሳብ በትክክል ሊረዱት አልቻሉም። በተለይም ‘ሰው አምላክ
ይኾን ዘንድ አምላክ ሰው ኾነ’ የተሰኘውን የቅዱስ አትናቴዎስን ጥቅስ ሲያነቡ፣ ይህ የምሥራቃዊ ሂንዱይዝም ወይም የፓንቴይዝም ተጽዕኖ
ነው በማለት ያስባሉ።”[1]
“በቅድስና እግዚአብሔርን
በመምሰል የማደግ ሂደትም ከእግዚአብሔር ቅድስና የመሳተፍ ሱታፌያዊ ሂደት ነው። … ሐዋርያው፣ ‘ … ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች በተስፋ ቃል እንድትሆኑ፥
በእነዚያ ክብርና በጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን ሰጠን።’ ያለው የባሕርዩ መገለጫና መታወቂያ የኾኑትን ነገሮች
- ኃይላተ እግዚአብሔር ቅድስና፣ ቸርነት፣ ደግነት፣ ጥበብ፣ እውነተኛነት፣ ገዢነት … የመሳሰሉትን ገንዘብ እናደርግ ዘንድ የተሰጠን
በመኾኑ ነው። ይህም ከፓንቴይዝም እርሾ የጸዳ መጽሐፍ ቅዱሳዊና ሐዋርያዊ ትምህርት ነው።”[2]
Sunday, 24 January 2021
የማርያም ምስልና የሚካኤል ክንፍ!
መግቢያ
በብዙዎች ዘንድ ከምንከሰስበት ነገር አንዱ፣ “ስለ ማርያም አትሰብኩም፤ ስለ ቅዱሳንም አትመሰክሩም” የሚል ክስ ነው። ይህን የሚሉ አካላት እያወቁም ይኹን በጽንፈኝነት ከመጽሐፍ ቅዱስ ተቃራኒ በመኾን ዘመናቸውን ስለ ማርያምና ስለ ቅዱሳን “በመስበክ” ይከስራሉ። ከዚህም የተነሣ አያሌዎች ማርያምን በመስበክ የታወቁ ናቸው። ከሰሞኑ እንኳ ካየነው የዘበነ ለማን ዓይን ያወጣ ግብዝነት ማንሳት እንችላለን። ይህን ሳሰላስል የመጣልኝ አንድ አስቂ ታሪክ አለ። መልአኩ ሚካኤል አንድ ክንፉ ያዘቀዘቀበት ምክንያትና የማርያም ከፍጥረተ ዓለሙ በፊት መታየት።
Monday, 18 January 2021
የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት
መግቢያ
በመጽሐፍ ቅዱስ ዋና
ዋና ከሚባሉት ትምህርቶችና አማኞች ሊጠመቁት ከሚገባው ጥምቀት አንዱ፣ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ነው። የብዙዎች ትኵረትና መሻት ያለው
የውኃ ጥምቀትና በየዓመቱ ከጥምቀት በዓል ጋር ተያይዞ የሚከበረውን የከተራ በዓልን እንጂ ስለ መንፈስ ቅዱስ ጥምቀት እምብዛም ግንዛቤው
ያላቸው አይመስልም። ነገር ግን አስገዳጅ ከኾኑ መንፈሳዊ እውነቶች አንዱ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ነው፤ በመንፈስ ቅዱስ ያልተጠመቀ
እርሱ እውነተኛ አማኝ ወይም መንፈሳዊ አይደለም።
Thursday, 14 January 2021
መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፬)
ካለፈው የቀጠለ …
·
የእግዚአብሔር ቊጣ፦
መጽሐፍ ቅዱስ፣ ኀጢአት የእግዚአብሔርን ቊጣ እንደሚያነሣሣ በግልጥ ይናገራል፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ባሕርይውና ፈቃዱ ቅዱስና ጻድቅ ነውና፣ በኀጢአት ፈጽሞ አይደሰትም። በሌላ ንግግር ኀጢአትን ፈጽሞ ይጠየፋል፣ ይጠላልም፤ በኀጢአት ከቶም ደስ አይሰኝም ማለታችን ነው። አደራረጉ ፍጹም ቅዱስና ንጹሕ ነው። ስለዚህም “በቍጣውና በመዓቱ ኀጢአተኞችን ይገለባብጣቸዋል፤ ኪዳኑን የሚተዉትንም ይነቅላቸዋል፤ ” (ዘዳ. 29፥23-28)። ቅዱሱ እግዚአብሔር፣ ያለ ተጨባጭ ምክንያት እንደ ሰው በንዴትና በብስጭት የሚቈጣ አይደለም፤ ቊጣው ወዲያው የሚነሣ ደግሞም ቶሎ የሚበርድም አይደለም። በተለይ ኀጢአተኞችን ለኀጢአታቸው በመተው ቊጣው ይገለጣል፤ (ሮሜ 1፥24)።
Monday, 11 January 2021
ብሔራዊ ውርደታችን!
ዛሬ ላይ በምንም ዓይነት ሚዛን፣ አጼ ኃይለ ሥላሴን እንዲያ መዋረዳቸውን፣ 60ዎቹ ሚኒስትሮቻቸው ደግሞ በአንድ ጉድጓድ ውስጥ በጅምላ ተገድለው መቀበራቸውን የሚደግፍ ሰብዓዊና ጤነኛ ሰው ይኖራል ብዬ አልገምትም። ይህን የማይደግፈው አጼው አልበደሉም፤ ሚኒስትሮቻቸውም ንዑዳን፤ ቅዱሳን ናቸው ብሎ እንዳይደለ፤ ነገር ግን አገር ለመሩ፣ ጥቂት ውለታ ለዋሉ ምንም ያህል ክፉ ቢሠሩ ብድራታቸው ግድያ፤ በጅምላ መረሸን፣ መዋረድና መንገላታት እንዳልኾነ ዕዝነ ልቡናው ያስባል፤ ያሰላስላል ብዬ እንጂ።
Friday, 8 January 2021
Monday, 4 January 2021
Wednesday, 30 December 2020
መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፫)
ካለፈው የቀጠለ …
·
ኀጢአት
በመጽሐፍ ቅዱስ ኀጢአት
ወይም ኀጢአትን ማድረግ አንድና ወጥ ትርጉም ያለው ብቻ አይደለም፤ በተለይ በአዲስ ኪዳን ውስጥ በአምስት በተለያዩ መንገዶች ተገልጦ
እንመለከተዋለን፤
1.
ሃማርቲያ[ሺያ]፦ (ዒላማን መሳት)፦ ይህ ቃል በአዲስ
ቃል ውስጥ ኀጢአት ወይም ኀጢአተኛ ተብሎ ከ250 ጊዜ በላይ ተጠቅሶአል፤ ትርጕሙም እግዚአብሔር ወዳቀደላቸው ዓላማና ግብ ኀጢአትን
በማድረግ፣ በገዛ ፈቃዳቸው ወይም ምርጫቸው ባለመድረሳቸው አዳምና ሔዋን[የሰው ልጆች] ዒላማ መሳታቸውን የሚያመለክት ነው፤ እግዚአብሔር
ወዳሰበላቸውና ወዳቀደላቸው ዐሳብና ክብር አልደረሱምና ከእግዚአብሔር ክብር ጎደሉ (ማቴ. 9፥2፤ ዮሐ. 1፥29፤ ሮሜ 3፥23)።
Saturday, 26 December 2020
ውርርዱ በገብርኤል አልነበረም!
መግቢያ
በመጽሐፎቻቸው ምዕራፍ ብዛት ዓበይት ነቢያት ተብለው ከሚጠሩት አንዱ፣ የነቢየ እግዚአብሔር
የዳንኤል ትንቢት መጽሐፍ ነው። የመጽሐፉ ጸሐፊ ራሱ ለመኾኑ በራሱ በትንቢት መጽሐፉ ውስጥና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ምስክርነት አለ (9፥2፤ 10፥2፤ ማቴ. 24፥15ን ከዳን. 9፥27 እና 11፥31 ጋር ያስተያዩ)። የዳንኤል መጽሐፍ ዋና
ሃሳብ ወይም ሊነግረን የወደደው እግዚአብሔራዊ መልእክት፣ የእግዚአብሔርን ሉዓላዊ ጌትነትና ድል ነሺነቱን ለማሳየት ነው።
እግዚአብሔር ሉዓላዊ ጌታ ስለ ኾነ፣ “ልዑል አምላክም በሰዎች መንግሥት ላይ የወደደውን ያሰለጥናል” (5፥21)።
Wednesday, 23 December 2020
መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፪)
መግቢያ ፪
የ“መድሎተ ጽድቅ” ጸሐፊ ሰጊጎት
የሠራባቸው ቃላት
ካለፈው የቀጠለ …
ቀጥታ ወደ መጽሐፉ ምዘና
ከመሄዳችን በፊት፣ በመጽሐፉ ውስጥ ከመጽሐፍ ቅዱስና ከአማናዊት ኦርቶዶክሳዊት[1] እምነት ወይም
እይታ ውጪ፣ ትርጉም ስለ ተሰጣቸው ቃላት መመልከቱ እጅግ ጠቃሚ መስሎ ታይቶናል። በተለይም በመግቢያ ላይ ካለው፣ ከመዳን ትምህርት
ጋር ተያይዘው የተነገሩትን ቃላት መመልከት፣ ብዙ ሳንደክም የ“መድሎተ ጽድቅን”፣ መድሎተ ስሑትነት በሚገባ እንድናስተውል ይረዳናል።
ጸሐፊው ቃላትን በማጣመም ለራሱ ትምህርት ተጠቅሞባቸዋል። እንዲያውም በአንዳንድ የነገረ መለኮት ቃላት ላይ አንዳች ግንዛቤ የለውም
ወይም ኾን ብሎ ያምታታል።
Monday, 21 December 2020
“ዲያቆን” ሄኖክ ሃይሌና አዲሱ ኑፋቄው!
“እመቤታችን ማማለድ አይደለም አፍርሳን
መሥራት ትችላለች” [እውነት?!]
“ማንም የእግዚአብሔርን
ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ።” (1ቆሮ.
3፥17)
ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ውስጥ፣ ቅዱስ ቃሉ የሚናገረውን ብቻ መናገር ኑፋቄነት፣ ቅዱስ ቃሉ የማይለውን መናገር ደግሞ አማኝነት ወይም “የቤት ልጅ”
የሚያስብለው ተግባር ከኖረ ሰነባበተ። ለቅዱሳን መላእክትም ኾኑ ሰዎች፣ “ቃሉ ከተናገረው በላይ መናገር ትክክል አይደለም፣
የተነገረው ብቻ ሊነገርላቸው ይገባል” ስንል፣ “ጸረ ቅዱሳን፣ ጸረ ማርያም፣ ጸረ መላእክት …” የሚል ስድብ ያስቀጥላል። ነገር
ግን ለቅዱሳን፣ ቅዱስ ቃሉ የሚናገረውን ብቻ አለመናገር የቅዱሳኑ ጠላቶች መኾናቸውን በቅዱስ ቃሉ ላይ ጨምረው ተናጋሪዎቹ
ያስተዋሉ አይመስሉም።










