ቤተ ክርስቲያን ከመንግሥት ጋር “ተቃራኒ” በነበረችባቸው ዘመናት፣ ማለትም
ነገሥታት ጸረ ክርስትና አቋም ይዘው ተነሥተው በነበሩባቸው ዘመናት፣ ቤተ ክርስቲያን ከሩቅ የሚታይ አብረቅራቂ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋን
ተጐናጽፋ ነበር፤ ከአንድ መቶ ሃምሳ ዓመታት በላይ ከኔሮን ቄሣር እስከ ዲዮቅልጥያኖስ የዘለቀው ጽኑ የመከራ ዘመን ቤተ ክርስቲያን
እንደ ቦኸር በዐለት ላይ ተከላት እንጂ፣ ፈጽሞ ካመነችው እውነትና ከመንፈስ አንድነቷ አላነወጣትም፤ አልከፋፈላትም፡፡ መከራ ማጥሪያዋ
ብቻ ሳይኾን መጽናኛዋም ጭምር ነበር፡፡
Friday, 30 August 2019
Tuesday, 27 August 2019
ሾላኮቹ (ክፍል ፪)
Please read in PDF
2.
ለመስረቅ፦ ጌታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ወደ በጐች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው፤” በማለት ሲናገር ሾላኮቹ ራሳቸውን በማመሳሰልና በመደበቅ የተካኑ መኾናቸውን
እየነገረንም ጭምር ነው፤ (ዮሐ. 10፥1)። ሌባ በባሕርይው ተደብቆ ወይም ሾልኮ እንጂ በግልጽ መግባትን አያውቅም። ይህንም የሚያደርገው
ተቀዳሚ ዐላማው የእርሱ ያልኾነውን ነገር፣ ለራሱ ጥቅምና ፍላጎት ለመስረቅና ለመውሰድ ነው።
Monday, 19 August 2019
Monday, 12 August 2019
ሾላኮቹ (ክፍል ፩)
Please read in PDF
መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ
ቃል ሐራጥቃ[1] የኾኑ መናፍቃንን
ጠባያቸውን ሊገልጥ በሚችል መንገድ፣ ሾላኮች ወይም ወደ ቤቶች ሾልከው የሚገቡ በማለት ይጠራቸዋል፤ (ገላ. 2፥4፤ 2ጢሞ. 3፥6፤
ይሁ. 4)። ቅዱስ ጳውሎስ ወደ እግዚአብሔር አደባባይና ወደ አማኞች የሚገቡት እንደ ሰላይ ነው ይለናል፤ ጌታችን ኢየሱስ ደግሞ
ከአማኞች ጋር ልዩነት የሌላቸው እስኪመስሉ ድረስ “እንደ ተኩላ” (ማቴ. 7፥15) ነው ይለናል፤ ሰላይ መመሳሰልን ገንዘብ ያደርጋል፤
ተኩላም ኹለ ነገሩ ከበግ ጋር አንድ ዓይነት መኾንን ይመርጣል፤ ይህን ተፈጥሮአዊ ተመሳስሎታቸውን የሚጠቀሙት ግን የሚፈልጉትን ለማግኘት
ወይም በጭካኔያቸው ለመንጠቅና በግን በሕይወቱ ቦጫጭቀው ለመብላት ነው።
Saturday, 3 August 2019
የእምነት እንቅስቃሴ አማኞች መጽሐፍ ቅዱስን በዐውድ አያውቁትም!
Please read in PDF
ዐውድ አንድን
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ለመረዳት ወሳኝ ነው፤ ዐውድን አለመረዳት ጠቅላላ የመጽሐፉን ዐሳብ አለመረዳት ነው፤ መንፈስ ቅዱስ ቀድሞ
የተናገረውን ያብራራልናል ይገልጥልናል እንጂ፣ አዲስ መገለጥም ኾነ ኢየሱስ ከተናገረው የተለየ የሚነግረን ምንም ነገር የለውም፤
ይህም በዐውድ ውስጥ ልንረዳው እንችላለን ማለት ነው፡፡ ከመንፈስ ቅዱስ ቀጥሎ፣ ዐውድ የቀደመው መልእክት ለዝንተ ዓለም ዘመን ዘለቅ
ኾኖ እንዲሻገር ኹነኛ አጥር ነው ማለት እንችላለን፡፡
Monday, 29 July 2019
Monday, 22 July 2019
ከክርስቶስ ይልቅ “ቄሣርን” አወዳሽ “ነቢያት”! (የመጨረሻ ክፍል)
Please read in PDF
“ወንጌላውያን” ነቢያትና ቤተ
መንግሥታዊ ማስታወቂያነታቸው
“ወንጌላውያን” ነቢያትና ጥቂት የማይባሉ ኦርቶዶክሳውያን አገልጋዮችም
ጭምር ቤተ መንግሥቱ በሕዝብ ዘንድ ዕውቅና ያገኝ ዘንድ ተግተው “እያገለገሉ” ይመስላል፤ ለዚህም ለምሳሌ፦ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ
መወቀስ አይገባቸውም እስከሚለው ጥግ የሄዱ አገልጋዮችን አይተናል፤ እንዲያውም ቤተ ክርስቲያን ከቤተ መንግሥት ባነሰ ማንነት
መኖሯን ራሳቸውን ጭምር በመስደብ ያቀረቡትን ሰምተናቸዋል። ለዚህም ለከት አልባ በኾነ መንገድ ግልጥ ፖለቲካዊ ቃላትን በመጠቀም
ሲወርዱ ተመልክተናቸዋል።
ለምሳሌ፦
- “አርበኝነት
በደሙ የተዋሐደው” ኢትዮጲያዊነት፣
- ሃያ
ሰባት ዓመታት መብታችን ተጥሶ … ፣
- የኢትዮጵያ
… የጠላቶቿ ድንጋይ አቀባዮች (የማርሲሉ ዮናታን አክሊሉ)፣
- ኢትዮጵያን
እግዚአብሔር በቃል ኪዳን ጠብቆአታል፣
Tuesday, 16 July 2019
ከክርስቶስ ይልቅ “ቄሣርን” አወዳሽ “ነቢያት”! (ክፍል - 2)
ራሱን ከወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት እንደ አንዱ እንደ ኾነ
የሚቈጥረው፣ የ“Christ Army” ቴሌቪዥን ባለቤት ኢዩ ጩፋ፣ ስሙንና ክብሩን በሚናኝበት በገዛ ቲቪው ላይ “ለጠቅላይ
ሚኒስቴሩ ጻፍኩት” ባለውና በገዛ ቲቪው ላይ “ሲደሰኩር”፣ ለኢየሱስ የሚነገሩትን ምሳሌዎች በመላ ወስዶ ለጠቅላዩ ሲናገር
እንሰማዋለን፤ እንዲህ ይላል …
“ … ዕውቀትህ አስገራሚ ነው፣ ንግግርህም ይፈውሳል፤ እንደ ነቢይ
ትተነብያለህ፣ እንደ መምህር አስተማሪ፣ እንደ አባት መካሪ ነህና ዕድሜ ይጨምርልህ፤ አባት ነህና እንደ አብርሃም፣ ንጉሥ ነህና
እንደ ዳዊት፣ ነቢይ ነህና እንደ ሙሴ፣ ካህን ነህ እንደ ኢያሱ፣ ጠቢብ ነህ እንደ ሰሎሞን፣ ደፋር ነህ እንደ ጳውሎስ፣ ታጋሽ
ነህ እንደ ኢዮብ፣ ቆራጥ ነህ እንደ ሩት፣ ባለ ራእይ ነህ እንደ ዮሴፍ … እነዚህን ኹሉ ነህና …”
Saturday, 13 July 2019
ከክርስቶስ ይልቅ “ቄሣርን” አወዳሽ “ነቢያት”! (ክፍል - 1)
Please read in PDF
መግቢያ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መካከለኛ ዘመን ታሪክ፣ የቤተ መንግሥትን አስነዋሪ ድርጊት ፊት ለፊት
ከተጋፈጡት መካከል በዘርዓ ያዕቆብ ዘመን የተነሡት ደቂቀ እስጢፋኖሳውያን፣ በአጼ ፋሲል ዘመን የተነሡት መነኮሳት፣ አባ
ፊልጶስና አኖሬዎስ ዘጸጋጅን ተጠቃሽ ናቸው፤ እኒህ አባቶች የነገሥታቱን አመንዝራነት፣ ፍትህ አልባነት፣ ድኃ ገፊነት፣
እጆቻቸውን በደም መታጠብ ፊት ለፊት የተጋፈጡና በሕይወታቸው ተወራርደው ዋጋ የከፈሉ ናቸው።
እስጢፋኖሳውያን
ዘርዐ ያዕቆብ እጁን ከቤተ ክህነትና ከቤተ ክርስቲያን እንዲያነሣ ደጋግመው ሞግተዋል፤ ቤተ መንግሥትና ቤተ ክህነት ጋብቻ
ሊፈጽሙ አይገባም በማለት ይናገሩ የነበሩት የመጀመሪያዪቱ ቤተ ክርስቲያን አማኞችና አባቶች ሳይሳሱ ፊት ለፊት ተጋፋጭና ተሟጋችም
ነበሩ፤ በቤተ ክርስቲያን በትር ዙፋናቸውን ያጸኑ አያሌ ነገሥታት ኢትዮጵያ የነበራትን ያህል፣ ነገሥታት በቤተ ክርስቲያን በትር
ዙፋናቸውን ማጽናታቸውን እንዲያቆሙ የተጋደሉ አያሌ አባቶችንም[መጨረሻቸው መሥዋዕትነት ቢኾንም] ነበሩ።
Friday, 12 July 2019
የዓምዳዊ ስምዖን ጸሎት
በመስቀል ላይ ሳለህ ራስህን
ዘንበል(ዘለስ) ያደረግህ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ወደ አንተ ምስጋና አሳርግ ዘንድ ለሞተውና ላዳነኝ ምስጋና ይሁን እያለች
ነፍሴ በአምላካዊ በገና ታመሰግን ዘንድ የነፍሴን ራስ ከፍ ከፍ አድርግ፡፡
Monday, 8 July 2019
Thursday, 27 June 2019
ሰዶማዊነት - መዘንጋት የሌለበት ጉዳይ! (የመጨረሻው ክፍል)
የሰዶማውያን ስውር ደባ
በግልጥ ማንነታቸው ቢመጡ የሚቀበላቸው እንደሌለ ያውቁታል፤ ስለዚህም ስውርና
ሰዎች ቀስ በቀስ ወይም በድንገት እንዲላመዱ የሚያደርጉባቸው መንገዶች አሏቸው፤ ለምሳሌ፦ የታወቁ የፊልም አክተሮችን በዋና ተዋናይነት
ማጫወት፣ በሕጻናት ፊልሞች ውስጥ ሰዶማዊነትን መሰንቀር [ስንቶቻችን ለሕጻናቶቻችን ፊልሞችን አስቀድመን አይተን መርጠን እናቀርብላቸዋለን?]፣
በአኹን ሰዓት ከክርስቲያን ፊልሞች በቀር በማናቸውም ፊልሞች ላይ እጅግ በአብላጫው የሰዶማውያንን ሃሳብ እናያለን፣ ቀስ በቀስ ያላምዱናል፣
በቀዝቃዛ ውኃ ጥደውን ቀስ አድርገው እሳቱን እያነደዱ መቀቀልና መፍረስን ያላምዱናል፤ ምልክቶቻቸውን በተቃውሞ መልክ እንድናሠራጭ
ይቈሰቁሳሉ፤ በዚህ ረገድ የአገራችን የቅርቡ ኹኔታ በሚገባ ተሳክቶላቸዋል፡፡
Friday, 21 June 2019
ሰዶማዊነት - መዘንጋት የሌለበት ጉዳይ! (ክፍል አንድ)
እግዚአብሔር
አምላክ የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ምድር ከባርነት ቤት ከወጡ በኋላ፣ ወደ ተስፋይቱ ምድር በተቃረቡ ጊዜ በተደጋጋሚ የተናገራቸው
ቃል ቢኖር እንዲህ የሚል ነው፤ “… ዛሬ እኔ አንተን የማዝዘውን ትእዛዙንና ፍርዱን ሥርዓቱንም ባለመጠበቅ አምላክህን እግዚአብሔርን
እንዳትረሳ ተጠንቀቅ፤” (ዘዳግ. 8፥11፤ 4፥9፤ 6፥25)። የታዘዘውን ትእዛዙንና ፍርዱን ሥርዓቱንም ሊረሳ የሚችልባቸውን ምክንያቶችንም
ሲያስቀምጥ እንዲህ ይዘረዝራቸዋል፤
“ከበላህና ከጠገብህ
በኋላ፥ መልካምም ቤት ሠርተህ ከተቀመጥህበት በኋላ፥ የላምና የበግ መንጋ ከበዛልህ በኋላ፥ ብርህና ወርቅህም ያለህም ሁሉ ከበዛልህ
በኋላ፥ ልብህ እንዳይጓደድ፤ ከግብፅም ምድር ከባርነት ቤት ያወጣህን፥ እባብና ጊንጥ ጥማትም ባለባት፥ ውኃም በሌለባት፥ በታላቂቱና
በምታስፈራው ምድረ በዳ የመራህን፥ ከጭንጫ ድንጋይም ውኃን ያወጣልህን፥ በመጨረሻም ዘመን መልካም ያደርግልህ ዘንድ ሊፈትንህ ሊያዋርድህም
አባቶችህ ያላወቁትን መና በምድረ በዳ ያበላህን አምላክህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳ፤ በልብህም፦ ጉልበቴ የእጄም ብርታት ይህን
ሀብት አመጣልኝ እንዳትል። ነገር ግን ዛሬ እንደሆነ ለአባቶችህ የማለውን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ፥ ሀብት ለማከማቸት እርሱ ጉልበት
ሰጥቶሃልና አምላክህን እግዚአብሔርን አስብ።” (ዘዳግ. 8፥12-18)
Sunday, 16 June 2019
አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ
Please read in PDF
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን መካከል ከተነሣ በሃምሳኛው ቀን፣ ወደ
ሰማያት ባረገ ደግሞ በአሥረኛው ቀን መንፈስ ቅዱስን ለደቀ መዛሙርቱ እንደ ገባላቸው ተስፋ ቃል ከአባቱ ዘንድ በመላክ የቤተ ክርስቲያን
ልደት አብስሮአል።
ከግሪኩ “ፓራክሊቶስ” ወይም ከዕብራይስጡ “ፕራቅሊጥ” ከሚለው ግስ የተገኘው፣
“ጰራቅሊጦስ” የሚለው ቃል ትርጉሙ፦ “አማላጅ፣ አስታራቂ፣ አፍ፣ ጠበቃ፣ ትርጁማን፣ አምጃር፣ እያጣፈጠ የሚናገር፣ ስብቅል ካፉ
ማር ጠብ የሚል።…፤ ናዛዚ፣ መጽንዒ፣ መስተፈስሒ፤ መንፈስ ቅዱስ” በማለት አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ተርጉመውታል። [1]
Monday, 10 June 2019
ይድረስ ለውድ እህቴ ዘርፌ ከበደ … !
ይህ ጽሑፍ ዘማሪት ዘርፌ ወደ ስሑት መምህራን ጐራ ባለችበት ወቅት
የተጻፈ ነበር፤ ነገር ግን ጽሑፉን ከተመለከቱ ወንድሞች መካከል ጥቂቶች አስተያየቶችን ስለ ሰጡኝ ለጊዜው ከማውጣት አዘግይቼዋለሁ፤
ዘርፌ ግን አኹንም ከፊተኛ ስህተትዋ የሚብስ፣ እንኳን ለመንፈሳዊነት ለአመክንዮ የማይመጥን “ከኦርቶዶክስ የለቀቅሁበት ምክንያቴ”
የሚል ርእስ ሊሰጠው የሚችል ምስለ ወድምጽ(Video) ሠርታ ለቅቃለች።
አንዳንድ አገልጋዮች የራሳቸውን አገልግሎት ትክክል ለማድረግ ሲሉ
ብቻ፣ አእላፋት በኹለንተናቸው ዋጋ ከፍለው የሚያገለግሉትን ደገኛ አገልግሎት፣ ጥላሸት ለመቀባት ሲዳዱ ማየት እየተለመደ መጥቷል፤
አለመታደል! እንዲህ ከማድረግ ልከኛ የአገልጋይ ጠባይ ይዘን ብናገለግል እጅግ መልካም ነበር፤ ከአገልግሎት በፊት አገልጋይ መኾን
ይቀድማልና፤ ሽብርቅና ድምቅ ያሉ አገልግሎቶች ኹሉ አገልግሎት እንዳይደሉ፣ ሰው እንጂ ክርስቶስ እንዳይከብርበት በአጭር ዕድሜዬ
አይቻለሁ።
Subscribe to:
Posts (Atom)






