Wednesday, 24 May 2017
Tuesday, 23 May 2017
ከኢየሱስ ተኮር - ወደ “አገልጋይ[ስጦታ]” ተኮር ሩጫ (ክፍል ዘጠኝ)
Please read in PDF
3. መከራን ተቀባይ ነው፦ “እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ በጎ ወታደር ሆነህ፥ አብረኸኝ መከራ ተቀበል” (2ጢሞ.2፥3)፡፡ የእውነተኛ አማኝም ሆነ አገልጋይ ዋና መገለጫው፣ ከጠላት ዘንድ የሚመጣበት ብርቱ ሰልፍና ዋና ተቃውሞ ነው፡፡ ክርስቲያንን ከዓለም ጋር የሚያስማማው ምንም የሕይወት ዘይቤ ወይም ሥርዓት የለውም፡፡ ጌታ ራሱም፣ “በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ” (ዮሐ.16፥32) በማለት መከራው የማይቀርና ነገር ግን አሸናፊው ቀድሞ መከራውን ስላሸነፈው ፍርሃት እንደማይገባ አስረግጦ ነግሮናል፡፡ ዓለም ስለእኛ የምትመሰክረው “በጎ ነገር” ካላት፣ ክርስትናችንን ቆም ብለን መፈተሽ ይገባናል፡፡

ቅዱስ ጢሞቴዎስ በኋለኛው ዘመኑ በመከራው ጽናትና እየሆነ ባለው ነገር
ፈጽሞ በፍርሃት ተውጦ ነበር፡፡ ስለዚህም ከመከራው ጽናት የተነሣ መንፈሳዊ ድፍረትን አጥቶ ነበር፤ (2ጢሞ.1፥7)፡፡ በመፍራትም ወደኋላ እንዳይል አበክሮ ቅዱስ ጳውሎስ ያበረታታዋል፡፡ እምነታችንም፤
አገልግሎታችንም በክርስቶስ ጸጋ ላይ የተመሠረተ ነው፤ ደግሞም ይህን ብርቱ ሥራ መከራ በመቀበል ልናምነውና ልናገለግለው ይገባናል፡፡
ውጊያችንም ሁሉ ታላቅ ወታደራዊ ጽናትን በሚጠይቅ ማንነት ውስጥ ማለፍ ይገባናል፡፡
Friday, 19 May 2017
ዘፈን - የወደቀው መልአክ እንጉርጉሮ (ክፍል 3)
ዘፈን የሚለውን ሃሳብ
አስቀድመን ስንተረጉም፣
1.
“በጥንት ግሪክ ለወይን አምላክ በሚደረግ
ታላቅ ግብር ላይ ተሰልፎ መዞር፣ መፈንደቅ፣ መጨፈር፣ መጯጯኽ፣ መፈንጠዝ፣ ኢ ሥነ ምግባራዊና ገደብ የለሽ በኾነ የአልኮል መጠጥና
ገደብ የለሽ በኾነ የአልኮል መጠጥና በምግባረ ብልሹነት እርካታ ለማግኘት የሚደረግ ወሲባዊ ጭፈራ( ... Drinking
parties involving unrestrained indulgence in alcoholic beverages and
accompanying immoral behaviour, - ‘orgy, revelling, carousing.)
2.
በአማልክት (በጣዖታት) ፊት በቡድንና በግል የሚደረግ ፈንጠዝያ፣ ዝሙትና መጠጥ ባካተተ መልኩ የሚደረግ ጭፈራ፣
3.
በቡድን በተደራጀ መልኩ በተለያየ ሁኔታ የሚደረግን አደባባያዊ ትርኢት
መልክ ያለው የመንደር ክብር በዓል፣ ጭፈራ፣ ዘፈን፣ ግጥም፣ ዜማ፣ መሽከርከርን ... የሚያመለክት ትርጉም ያለው ነው፡፡”
ብለን በክፍል አንድ ላይ ማቅረባችንን መርሳት የለብንም፡፡
እናም፣ ዘፈንን ኃጢአት ነው የምንለው “ዘፈን” የተባለውን “አንድ ቃል” አንጠልጥለን፤ እርሱኑ ደግሞ ለጥጠን
አይደለም፡፡ ቀድሞ እንደተናገርነው የምንተረጉመውን
ሁሉ የምንተረጉመው ለእግዚአብሔር ክብርና ለእኛ ጥቅም ነው፡፡ ከላይ በተለያየ ይዘት በትርጉም ከተጠቀሱት ውስጥ፣ ዝርዝር
ሃሳብ እናውጣ ብንል፤ ዘፈን ማለት፦
1.
ከመንፈሳዊ አምልኮ ጋር መዛመድ የማይችል ርኩስ ጠባይን
አመልካች ነው፡፡ በተለይም በጣዖታት ፊት የሚደረግ ማናቸውም የደስታ መግለጫ ሥርዓትን ማከናወን፣ “ከእኔ
በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ” (ዘጸ.20፥3) የሚለውን ሕግ ለማስቃረን አሳላጭ መንገድ ስለሆነ፣ ዘፈን አደገኛነቱ ምንም አያጠያይቅም፡፡
Monday, 15 May 2017
ዘፈን - የወደቀው መልአክ እንጉርጉሮ (ክፍል 2)
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ በተለይም በአማርኛው በተመሳሳይ
ቃል ወይም ሐረግ ተጠቅሶ የተለያየ ፍቺ ያለው ቃል ብዙ ቦታ ይገኛል፡፡[1] ስለዚህ
ቅዱሳት መጻሕፍትን ስናጠና የቃሉን መመሳሰል ሳይሆን ቃሉ ያለበትን ወይም የተነገረበትን ዓውድ በትክክል ማጥናትና መስተዋል ይገባናል፡፡
“ዘፈን”ም ለተለያየ ሃሳብ፤ በተለያየ ዓውድ ተነግሯል፡፡ እናም እንደየተነገረበት ዓውዱ የተለያየ ትርጉሞችና ሰፊ ሃሳቦችን ይዟል
ማለት ነው፡፡ ጥቂቱን ብንመለከት እንኳ፦
1.
“ዘፈን” በቅዱስ አምልኮ ውስጥ ሲጠቀስ፤
በብሉይ ኪዳን የእስራኤል
ልጆች በዘፈን ለእግዚአብሔር መንፈሳዊ አምልኮን ያቀርቡ ነበር፡፡ የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ምድር፤ ከባርነት ቤት ሲወጡ፣ ፈርዖንንና
ሠረገላውን ሁሉ በባሕር አስጥሞ፣ ለእነርሱ ግን ሞገስንና ግርማን ሰጥቶ፣ የኤርትራን ባሕር በድል ሲሻገሩ በዝማሬ አመሰገኑ፤
(ዘጸ.15፥1)፡፡ በሌላ ሥፍራ፣ “ዳዊትም በሙሉ ኃይሉ በእግዚአብሔር ፊት ይዘፍን ነበር፤ ዳዊትም የበፍታ ኤፉድ ለብሶ ነበር፤ …
የእግዚአብሔርም ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ በገባ ጊዜ የሳኦል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ሆና ተመለከተች፥ ንጉሡም ዳዊት በእግዚአብሔር
ፊት ሲዘልልና ሲዘፍን አየች፤ በልብዋም ናቀችው፡፡ … በእግዚአብሔር ፊት ዘፍኛለሁ፤ በእግዚአብሔር ሕዝብ በእስራኤል ላይ አለቃ
እሆን ዘንድ ከአባትሽና ከቤቱ ሁሉ ይልቅ የመረጠኝ እግዚአብሔር የተባረከ ይሁን ስለዚህም በእግዚአብሔር ፊት እጫወታለሁ፤”
(2ሳሙ.6፥14-16 ፤ 21) በማለት ራሱም ገልጦታል፡፡
Wednesday, 3 May 2017
ዘፈን - የወደቀው መልአክ እንጉርጉሮ (ክፍል 1)
መግቢያ
በአንድ ሰሞን “ኦርቶክሳዊ ተብሎ ባለመጠራቱና የሌላ ቤተ እምነት ተከታይ
ሆኗል ተብሎ መጠርጠሩ ያናደደውን ዘፋኝ” ተመልክቼ፣ “ዘፋኝ ለኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ምኗ ነው?” ብዬ ሃሳቤን ማፍሰሴ የሚዘነጋችሁ
አይደለም፤ በዚያን ሰሞንና ከዚያም በኋላ ዘፋኙን “በመገሰጼ” የበዙ ተቃውሞዎች ገጥመውኝ ነበር፤ ተቃውሞዎቹ ሁለት መልክ አላቸው፤
አንዳንዶች የሌላውን[የዘፋኝን] ኃጢአት የምታወራው አንተ ማን ነህ? የሚሉ ሲሆኑ፣ ሌሎች ደግሞ ዘፈን ያልተከለከለ መሆኑን፣ ሥራ(ሙያ)
መሆኑን፣ “እግዚአብሔር የሚባርከው” መሆኑን፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ራሱ የተጠቀሰ መሆኑንና ዳዊት መዝፈኑን፣ “እግዚአብሔርን በዘፈን
አመስግኑት” መባሉን፣ ብሎም መኃልይ መኃልይ ዘሰሎሞን ስለ“ተቃራኒ ጾታ” ግንኙነት ካወራ፣ እኛስ ምናለ እንዲያ ብናደርግ የሚል
“ሙግት” መልክ ሊያቀርቡልኝ ብዙ ጥረዋል፡፡ በአብዛኛው ግን ስድብ መልክ ስለነበረው አያንጽም፣ ሰውንም አያስተምርም ያልኩትን ሁሉ
ለራሴ ከማንበብ፣ ሰዎችም እንዳይመለከቱት በማድረግ ወደቅርጫት እንዲጣል አድርጌዋለሁ፡፡ በዚህም ምክንያት ስለዘፈን አስፍቼ ለመጻፍ
ከብዙ ጊዜ በፊት አስብ፤ አሰላስል ነበር፡፡
ለዚህ ጽሁፍ ሌላው መነሻ ምክንያት የሆነኝ፣ በጄ ቲቪ የቴሌቪዥን ጣቢያ
ሰኞ በ16/8/09 እና 23/8/09[2]
ምሽት አራት ሰዓት ገደማ በሚተላለፈው የ“ብራና” ፕሮግራም ላይ፣ ሰርጸ ፍሬ ስብሐት የተባለ ሰው ሙዚቃን(ዘፈንን) በተመለከተ አንድ
“ጥናታዊ ጽሁፍ”፣ በአንድ ሌላ ቦታ ላይ አቅርቦ የነበረውን ሲያስተላልፍ ያሳያል፤ ለሰርጸ “ጥናታዊ ጽሁፍ” መነሾ ምክንያቱ ደግሞ፣
ዮናስ ጎርፌ የተባለ ሌላ ሰው “ቤት ያጣው ቤተኛ-
ሙዚቃ፣ ሙዚቀኛነትና ኢትዮጵያዊቷ ቤተ ክርስቲያን” በሚል ዘፈንን[ሙዚቃን] ባስመለከተ በጻፈው መጽሐፍ ላይ የቀረበ ነው፡፡ ዮናስ ጎርፌ ለተባለው ሰው
በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ዓቃቤ እምነት ላይ የሚሠሩ ብዙዎች መልስን ስለሰጡት እርሱን ማንሳት አልፈልግም፡፡ ሰርጸ ግን፣
“ቤት ያጣ ቤተኛ” መጽሐፍን፣ “ከዚያኛው ቤት ሲሰደድ”[በእርግጥ ተሰዷል ብዬ ለማመን ብቸገርም] አዲስ ጎጆ ሊሠራለት ዳድቶ፣ ወደሚድያ
እንዲመጣ የመፈለጉ አንድምታ፣ አደገኛነቱ የቱም መንፈሳዊና ለእግዚአብሔርና ለሕዝቡ ቅድስና የሚቀና አገልጋይ ይጠፋዋል ብዬ አላስብም፡፡
Saturday, 29 April 2017
ከኢየሱስ ተኮር - ወደ “አገልጋይ[ስጦታ]” ተኮር ሩጫ (ክፍል ስምንት)
3. ወታደር፦ ከሰይጣንና ከክፋት ኃይላት ጋር የምናደርገው ትግል ወታደር በጦርነት ሥፍራ
ከሚያደርገው መጋደል ጋር ተመሳስሏል፡፡ እንዲያውም የተነገረን፣ “በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ” (ኤፌ.6፥10)
በሚል ትእዛዛዊ ቃል ነው፡፡ መጋደላችንም ደምን እስከማፍሰስ ድረስ መቃወም ሊኖርበት ይችላል፤ (ዕብ.12፥4)፤ እንደበጎ ወታደርም
የክርስቶስ ኢየሱስን መከራ መካፈል እንደሚገባም ጭምር፤ (2ጢሞ.2፥3)፡፡
የብዙዎቻችን የክርስትና ሕይወት ሲታይ በክርስቶስ
ለክርስቶስ መኖርን አያመልክትም፡፡ በሌላ ንግግር ትኩረታችን ጌታ ኢየሱስ ብቻ አይደለም፡፡ ከእርሱ[ከጌታ ኢየሱስ] የሚያንሱ ነገሮችንም
ከእርሱ ጋር አስተካክለን ይዘን መጓዝ እንፈልጋለን፡፡ እንደሯጭ የሩጫውን ሥርዐት ወይም መማችንን[መስመራችንን] ብቻ፤ እንደባርያ ደግሞ ለገዛን
ጌታ ፈቃድ ብቻ መኖርን አልተለማመድንም፤ አላሳደግነውምም፡፡ መንገዳችንን ለማቅናትና ትኩረታችንን ሁሉ በጸጋውና በ“ጸጋው ተቀባዮች”
ላይ ከማድረግ ይልቅ፣ በእርሱ ላይ ብቻ እንድናደርግ፤ የወታደርን ጠባያት ከመጽሐፍ ቅዱስ አውጣጥተን እንማማርበታለን፤ ጌታ እግዚአብሔር
መንፈስ ቅዱስ ይርዳን፤ አሜን፡፡
ወታደር፦
Sunday, 23 April 2017
ቶማስ - ከደቀ መዛሙርቱ የመጨረሻ አማኝ
Please read in PDF
አይሁድ በይሁዳ ምድር በቢታንያ መንደር ለግድያና ለወገራ ጌታ ኢየሱስን ይፈልጉ በነበረበት ወቅት፣ አልዓዛር በጠና መታመሙን ሰማ፡፡ ወዳጁ አልዓዛርን ስለእግዚአብሔር ክብር ሊያስነሣው ደቀ መዛሙርቱን “ወደይሁዳ ደግሞ እንሂድ” አላቸው፤ (ዮሐ.11፥8) ይህንን ሲል ሁሉም ፈርተው ነበር፤ ቶማስ ግን “ለባልንጀሮቹ ለደቀ መዛሙርት፦ ከእርሱ ጋር እንሞት ዘንድ እኛ ደግሞ እንሂድ” በማለት ደፋርና የማይፈራ ሰው መሆኑን አስመሰከረ፡፡

በቤተ ክርስቲያን ቀኖና የዛሬው እሁድ ዳግማይ ትንሣኤ ወይም ዳግም ትንሣኤ
ተብሎ ይጠራል፡፡ ከስምንት ቀን በፊት ለደቀ መዛሙርቱ በዝግ ቤት ውስጥ ሳሉ ተገለጠላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ልክ ጌታ ኢየሱስ
ከሙታን መካከል እንደተነሣ አንድ ክስ በአይሁድ ሽማግሌዎች ቀርቦባቸዋል፡፡ “… ደቀ መዛሙርቱ በሌሊት መጥተው ሰረቁት” (ማቴ.28፥11)
የሚል፡፡ ስለዚህ ከዚህ ክስ የተነሣ በጥብቅ ይፈለጉ እንደነበር መገመት አያዳግትም፡፡ እናም ይህን ክስና “አይሁድን ስለ ፈሩ ደጆቹን
ዘግተው” (ዮሐ.20፥19) ተቀምጠው ነበር፡፡
Tuesday, 18 April 2017
Friday, 14 April 2017
ዳኞቹ
Please read in PDF
እግዚአብሔር እውነተኛ ዳኛ ነው፤ (መዝ.7፥11)፡፡ በፍርዱም ጻድቅና የማይሳሳት፤ በቅንም ፈራጅ(ኤር.11፥20) ነው፡፡ ልብንና ኵላሊትን የሚመረምር አምላክ ነው፤ የሰውን ውስጣዊ ማንነት የሚፈትንና በፊቱም አንዳች የተሰወረ ነገር የሌለ አምላክ ነው፡፡ ደግሞም “ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱ፥ እንደ ሥራው ፍሬ የሚሰጥ” አምላክ ነው፤ (ኤር.17፥10 ፤ ራእ.2፥23)፡፡ እግዚአብሔር የልብንና የውስጣችንን ነገር ሁሉ ስለሚያውቅና ስለሚመረምር በፊቱ የተሰወረ አንዳች ነገር የለም፡፡ ስለዚህም ጻድቅ በእግዚአብሔር ጽድቅ በእምነት ይመካል፤ እንጂ አልበደልኩም እያለ አይሞግትም፡፡

ዳኝነት እውነትን በማጽደቅ፤ ሐሰትን በመጸየፍ የተከበበ ሥራ ነው፡፡ ስለዚህም
ፈራጅ ከምንም በላይ በመልካምነቱ በተመሰከረለት “ትልቅ” ሥነ ምግባር የታነጸ ሊሆን ይገዋል፡፡ ጌታ እግዚአብሔር ለዚህ ነው፣ የእስራኤል
ዳኞችን የሥነ ምግባር መመዘኛን ለቅዱስ ነቢይ ሙሴ፣ “አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ በአገርህ ደጅ ሁሉ በየነገዶችህ ፈራጆችንና
አለቆችን ሹም፤ ለሕዝቡም ቅን ፍርድ ይፍረዱ፡፡ ፍርድን አታጣምም፤ ፊት አይተህም አታድላ፤ ጉቦ የጥበበኞችን ዓይን ያሳውራልና፥
የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና ጉቦ አትቀበል፡፡ በሕይወት ትኖር ዘንድ፥ አምላክህ እግዚአብሔርም የሚሰጥህን ምድር ትወርስ ዘንድ እውነተኛውን
ፍርድ ተከተል፤” (ዘዳግ.16፥18-20) በማለት የተናገረው፡፡
Wednesday, 12 April 2017
ሰሙነ ሕማማት - “ … ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁና” (1ቆሮ.11፥26)
የጌታ ጾም መታሰቢያ የመጨረሻው ሳምንት ስያሜ ሰሙነ ሕማማት ይባላል፡፡
በዚህ ሳምንት ከምን ጊዜውም በላይ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአይሁድ “ወገኖቹ” የደረሰበት ጸዋተወ መከራ ከወንጌላት፣
ከግብረ ሕማማትና ከሌሎችም መጻሕፍት እየተውጣጡ ይነበባሉ፤ ሕማማቱንም ማዕከል ያደረጉ ሥርዓተ አምልኮዎች በጸሎት፣ በዝማሬ፣ በንባብና
በቅዳሴ ይቀርባሉ፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ የጌታን ሕማም የጌታ እራት በቀረበበት ጊዜ መናገርና መመስከር
እንዳለብን “ይህን እንጀራ በበላችሁ ጊዜ ሁሉ፥ ይህንም ጽዋ በጠጣችሁ ጊዜ ሁሉ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁና፤”
(1ቆሮ.11፥26) በማለት ይናገራል፡፡ ጌታ ኢየሱስም ከሙታን መካከል ከተነሣ በኋላ ደቀ መዛሙርቱን፣ “እርሱም፦ ከእናንተ ጋር
ሳለሁ በሙሴ ሕግና በነቢያት በመዝሙራትም ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ይገባል ብዬ የነገርኋችሁ ቃሌ ይህ ነው አላቸው፡፡
በዚያን ጊዜም መጻሕፍትን ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው፤ እንዲህም አላቸው፦ ክርስቶስ መከራ ይቀበላል በሦስተኛውም ቀን
ከሙታን ይነሣል፥” (ሉቃ.24፥46) አላቸው፡፡
Saturday, 8 April 2017
“Wanti kun ija kee duraa dhokatee jira” (Luqa.19:12)
Please read in pdf
Torbeen kun Moggaafama “Hosaa’inaa” jedhu qaba. Moggaasa kana Qulqulluun Yaareed torbeewwan sooma Kristoos hunda moggaaseen kan moggaafamee dha. Yaareed torbeewwan sooma guddaa kana keessa jiran hunda baruumsa Kristoos wajiin walsimsiidhaan moggaasa kenneefi jira. Kanaanis Kristoos bu’ura waan hundaa ta’u isaa agarsiisee jira.

Hosaa’inaan seenaa mataa isaa danda’e qaba. Nuti garuu seenaa balla’a keessa
kutaa seensaa qofa ilaala. Goftaan Yasuus “gaara Ejersaa” irraa bu’e gara
magaalaa Yerusaalemitti gale. Gaara ejersaa irra taa’e magaala Yeruusaaleem
gutumaan guututti arguu ni danda’a ture. Haata’uti gaara irraa bu’e gara
magaalatitti seene. Lubootni, barsiisootni fi hoggantootni Ayihuud gara hammenyaan
akka isa morman osoo beeku(Maar.15:12); dabalataaniis yeroo dhiyoo keessatti
magaalatti fi ummata irratti naasuu fi badiin guddaan akka irratti qaqqabuu
beekuu gara magaalaatti seene.
Sunday, 2 April 2017
ኒቆዲሞስ - ለሕጉ እውነት የሚሟገት ጻድቅ! (ዮሐ.7፥51)
ነቢያት ለሕጉ ቀናተኞችና ሕጉ እንዲተገበር የሚተጉ ከእግዚአብሔር ለሕዝቡ
የተላኩ ናቸው፡፡ ከእግዚአብሔር የተነገራቸውንና በተለያየ መንገድ የተቀበሉትን (ዕብ.1፥1)፤ በማናቸውም ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ሆነው
የሚታዘዙትን (ኤር.1፥7) የትንቢት ቃል ሸክም ከእግዚአብሔር በተላኩ ጊዜ (ኤር.1፥4 ፤ ሉቃ.3፥2) ሳይሸራርፉ፤ ሳይቀንሱና
ሳይጨምሩ እንዲናገሩ ይገደዳሉ፡፡ በዋናነት ነቢያት ራሳውና ሕዝቡ እንደሕጉ እንዲኖሩ ትልቅ ሥራን ይሠራሉ፡፡ ደጋግመውም የሕጉን
መጽሐፍ ያውጃሉ፡፡ ከዚህ የበለጠ ትልቅና ዋና ሥራም የላቸውም፡፡
ከዚህም ባሻገር፣ ጌታ እግዚአብሔርም ሕግ ሲላላ ሕዝብ ወደተላላነት እንደሚያደላ
አስቀድሞ ስለሚያውቅ መሪዎችና አስተዳዳሪዎችን እንደወደደው ይሾማል፡፡ የአይሁድ መምህራንም የተጠሩበት ዋና ዓላማም ይህ ነበር፤
የሕዝቡ መሪና የሕግ መምህራን እንደመሆናቸው መጠን ሕጉን በመጠበቅ ለሕዝቡ ትልቅ ምሳሌ በመሆን፣ ሕዝቡን ያስተምራሉ፤ እንዲጠብቁም
ያደርጋሉ፡፡ ዳሩ፣ በአንድ ወቅት በሕዝቡ መሪዎችና በሕጉ መምህራን መካከል ጌታ ኢየሱስን በተመለከተ ትልቅ ክርክር ሆነ፡፡ ለሕዝቡ
ጥቂቱን እንጀራና ዓሳ ለብዙ ሺሆች በመመገቡ ምክንያት፣ ከመከበርና ከመደነቅ ይልቅ ለመገደል በቂ ምክንያት ሆነ፡፡
Tuesday, 28 March 2017
ከኢየሱስ ተኮር - ወደ “አገልጋይ[ስጦታ]” ተኮር ሩጫ (ክፍል ሰባት)
Please read in PDF
7. አገልጋይ ለጌታው በፍጹም ፈቃዱና በፍጹም ሃሳቡ መታዘዝ ይገባዋል፦ ከሕጉ ትዕዛዛት አንዱ “ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ” (ዘጸ.20፥3) የሚል ነው፤ ይህ ቃል የምሥራቅ ዓለሙን ሁሉ አምላኪነት የሚቃወም ብቻ ሳይሆን፣ እስራኤል እግዚአብሔርን በመፍራትና በማክበር ልታመልከው እንደሚገባ ፍጹም አመልካች ሕግ ነው፡፡ ይህ ቃል በአዲስ ኪዳን ሌሎችንም ሃሳቦች በውስጡ ይዟል፡፡ ይኸውም (1) አማኞች ቅዱስ ለሆነው እግዚአብሔር ከአማልክትና ከርኩሳን አጋንንት ራሳቸውን በመለየት መቀደስ አለባቸው፡፡ ከከንቱ አማልክትም መራቅ ይገባቸዋል፡፡ ይህ የቆሙትንና የሚሰገድላቸውን አማልክት ብቻ ይይደለ፣ ከእግዚአብሔር ያስበለጥነውን ወይም ያስተካከልነውን ማናቸውንም ነገራችንን ይመለከታል፡፡ (2) አማኞች እግዚአብሔር በጎውን ነገር ብቻ እንደሚሰጣቸው በማመን በፍጹም ኃይላቸውና ፈቃዳቸው፤ ሃሳባቸውም ሊያምኑትና ሊታዘዙለት ይገባል፤ (ዘዳግ.6፥5 ፤ ፊልጵ.3፥8)፡፡

Sunday, 19 March 2017
“እነሆ፥ አስቀድሜ ነገርኋችሁ” (ማቴ.24፥25)
Please read in PDF
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምድር ሳለ ከተናገራቸው የመጨረሻ ቃሎች መካከል፣ በደብረ ዘይት ለደቀ መዛሙርቱ ስለዳግመኛ መምጣቱ ምልክቶች የተናገረው አንዱና ሠፊውን ክፍል የያዘ ነው፡፡ በውስጡ ብዙ ነገር መናገሩን ወንጌላዊው ጽፎልናል፡፡ በመካከሉም ቅዱስ ማቴዎስ፣ ጌታችን “እነሆ፥ አስቀድሜ ነገርኋችሁ” ብሎ መናገሩን ከጻፈልን የወንጌል ቃል ውስጥ ሁለት መሠረታዊ ጭብጦችን ማውጣት እንችላለን፤ ይኸውም፦

ጌታችን ሁሉንም
ነገር የነገረን በግልጥ ነው፦ ጌታ ለእኛ
ከሚያስፈልገን ቀድሞ ያልተናገረን ምንም ነገር የለም፡፡ በሰማይም
ሆነ በምድር ሊሆንና ሊመጣ ያለው ነገር ሁሉ ተነግሮናል፡፡ በዚህ ምድር ሕይወት ስላለው ብርቱ ሰልፍነት፣ ጌታ ኢየሱስንም አምነን በመከተላችንም ሆነ ሳናምን በመከተላችን ስለሚገጥመን
ሕይወትና ሞት፣ ስሙን አምነን በመከተላችንና በመመስከራችን ስለሚያገኘን ነቀፋ፣ ስድብ፣ ግርፋት፣ ስደት፣ ስም ማጥፋት፣ ርስትና
ጉልት ማጣት፣ በቤተሰብ ሁሉ ዘንድ ከበሬታና ቦታ መነፈግ፣ መጠላትና መገለል፣ መገደል፣ ... እኒህ ሁሉ አስቀድመው የተነገሩ ናቸው፤ (ማቴ.10፥16 ፤ 24፥9
፤ ዮሐ.15፥19)፡፡
Monday, 13 March 2017
Subscribe to:
Posts (Atom)