|
“አባቶቻችሁም እንደ ነበሩ አንገተ ደንዳና አትሁኑ ፤ እጃችሁንም ለእግዚአብሔር ስጡ፥ ለዘላለም
ወደ ተቀደሰው ወደ መቅደሱም ግቡ፥ ጽኑ ቍጣውም ከእናንተ እንዲመለስ አምላካችሁን እግዚአብሔርን አምልኩ። አምላካችሁም እግዚአብሔር
ቸርና መሐሪ ነውና፥ ወደ እርሱም ብትመለሱ ፊቱን ከእናንተ አያዞርምና ወደ እግዚአብሔር ብትመለሱ ወንድሞቻችሁና ልጆቻችሁ በማረኩአቸው
ፊት ምሕረትን ያገኛሉ፥ ደግሞም ወደዚህች ምድር ይመለሳሉ።” (2ዜና.30፥8-9)
|
ከወደጋምቤላ እናት እስካዘለችው ልጇ ድረስ ተቀልታ በጠቅላላ ከ148 ሰዎች
መታረዳቸውን ሰምተን ጆሮዋችን ሳያባራ፥ ከወደሜድትራኒያን ባሕር ዳርቻ ደግሞ ትውልደ ኢትዮጲያውንና ኤርትራውያን ይበዙበታል በተባለ
የስደተኞች የባሕር ጉዞ ጀልባ ተገልብጦ ከ400 በላይ ሰዎች መሞታቸውን ተረዳን፡፡ የዛሬ ዓመት ገደማ ኢትዮጲያውያን በዚሁ በሜድትራኒያን
ባሕር ዳርቻ በሰው በላው አይ ኤስ አይ ኤስ ዜጎቻችን እንደዋዛ እንደበግ ታርደው ደማቸው በከንቱ ከባሕር ጋር ተቀላቀለ፡፡
