Monday, 29 December 2014

እኛ ኢትዮጲያውያን በአጼ ቴዎድሮስ እይታ …

      
                                  
                             Please read in PDF                       

       “እኛ ኢትዮጲያውያን” የሚለው ሃሳብ “ደምና አጥንታችንን ገብረንላታል” ለሚሉ አርበኞች ልብ የሚመላ ነገር አለው፤ በጥንት በሕገ ልቡና፣ ቀጥሎም በሕገ ኦሪት ከዚያም በክርስትና መኖሯን ለሚያምኑ ደፍረው የሚሉት ነገር አላቸው ፤ በአክሱምና በዛጉዌ የታነጹትን ሐውልትና ህንጻ አብያተ ክርስቲያናትን ለሚያደንቁ አርክቴክቸሮችና ሌሎች፥ እጃቸውን በአፋቸው ጭነው ብዙ የሚተነትኑት ነገር አላቸው፤ ሁሉም በየሙያውና በያለበት ደረጃ ስለኢትዮጲያችን ቢጠየቅ የሚለው ብዙ ብዙ አለው፡፡
     ሃሳቤ ግን ወዲህ ነው፤ አጼ ቴዎድሮስ በጥር 22 በ1858 ዓ.ም ለእንግሊዛዊቷ ንግሥት ለቪክቶሪያ በኢትዮጲያ ምድር ከታሠሩት የእንግሊዝ እስረኞች ጋር በተያያዘ፤ እንዲሁም ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ሲያስቀምጡ፦  “የኢትዮጲያን ሰዎች ድንቁርነታችነን ዕውርነታችነን ሣይሰሙት አይቀሩም ያማረ መስሎኝ ደፍሬ የላክሁብዎን ከፍቶብኝ (አጥፍቼ እንደሆነ) ቢገኝ ይምከሩኝ እንጂ አይክፉብኝ፡፡ እግዚአብሔር የመረጠዎ ንግሥት ዓይንዎ የበራ ነውና፡፡”(ጳውሎስ ኞኞ ፤ ዐጤ ቴዎድሮስ ፤ ግንቦት 1985 ፤ ቦሌ ማተሚያ ድርጅት ፤ አዲስ አበባ ፤ ገጽ.214)
    አሁንም በድጋሚ በሚያዝያ 10 ቀን 1858 ዓ.ም ለዚህችው ንግሥት ድጋሚ በጻፉት ድብዳቤ እኛን ኢትዮጲያውያንን እንዲህ ገልጠዋል፦ “ የኢትዮጲያ ሰዎች እውር ነንና ዓይናችነን ያብሩልነ፡፡ እግዚአብሔር በሰማይ ያብራልዎ፡፡” በማለትም በግልጥ አስቀምጠዋል፡፡ (ጳውሎስ ኞኞ ፤ ዐጤ ቴዎድሮስ ፤ ግንቦት 1985 ፤ ቦሌ ማተሚያ ድርጅት ፤ አዲስ አበባ፤ ገጽ 233)

Tuesday, 23 December 2014

የትኩረት ጩኸት ትኩረትን ሲያደበዝዝ


                                  Please read in PDF              

     በአገራችን ትኩረትን የሚስበው ድርጊት እንጂ ዝግጅት አይደለም፤ አንድ ከባድና ዘግናኝ ድርጊት ሲፈጸም ብዙ ጊዜ ስሜቶቻችን ተጋግሎ መንጫጫት፤ ድርጊቱ እንዳይፈጸም ቀድመን ከመሥራት ይልቅ ከድርጊቱ በኋላ በጣም መጯጯህ ፣ ሰላማዊ ሰልፎች ፣ ብዙ ስብሰባዎች ፣ የአቋም መግለጫዎችና የስሜት ዕርምጃዎችም ይወሰዳሉ፡፡  ማሳያዎችን በምሳሌ ብናነሳ፦ በባለፈው ወር የአዋሽ ፓርክን በሚያቋርጠው ትልቁ የምሥራቅ ኢትዮጲያ መንገድ በጉዞ ላይ ሳለ በአንድ ቅጥቅጥ አይሱዙ ላይ በደረሰው አደጋ ከሐያ ሰባት ሰዎች በላይ የሞት አደጋ መድረሱን ሰምተን ሳናባራ፤ ወዲያውኑ በተወሰደው እርምጃ መንገዶች ላይ በተደረገው (በዋናው አስፓልት ላይ መኪናዎች በጉዟቸው እንዲያቀዘቅዙ ለማድረግ በተደረገው ሌላ የአስፓልት ጉማጅ ሥራ) በተወሰደው የስሜት ዕርምጃ ሌሎች የመኪና አደጋዎች መከሰታቸውን ከቦታው ሄዶ ማስተዋል ይቻላል፡፡
    አሁንም ሌላ ማሳያ ብናነሳ ፦ በባለፈው ወር ከተከሰተው ጆሮን ጭው ከሚያደርጉ ነገሮች አንዱ የእህት ሐና ላላንጎ ጉዳይ  ነው፡፡ ድርጊቱ ከዳር እስከዳር ብዙ በጣም ብዙ አነጋግሯል፡፡ ከወረዳ እስከ ሚኒስቴር ቢሮ ፤ ከሆስፒታል እስከ የፖሊስ መምሪያና ጣቢያዎች ፤ ከመንገድ ዳር “ታዛቢ” እስከመኪና አሽከርካሪዎች በዚህ ሂደት ውስጥ ያሉበትን ልልነትና ግድ የለሽነት በሚገባ አጢነናል፡፡ ጥቂት ስህተት ምን ያህል ዋጋ እንደሚያስከፍል አይተናል፡፡ የፖሊስ ዳተኝት ፣ የሆስፒታሎቻችን ከልክ ያለፈ ቸለተኝነት ድርጊቱን ከፈጸሙት የማይተናነስ መሆኑን ሌላ ምስክር ሳያሻ የአደባባይ ገመና ሆኗል፡፡

Thursday, 18 December 2014

በመሠወሬ ነው!


                     Please read in PDF

ሺህ ሰልፍ ከፊቴ ፥ ትዕልፊት ከኋላ፤
እንደጉንዳን ፈልቶ ፥ እንዳʻንበሳ ቢያጓራ፤

Monday, 15 December 2014

የብርሃን መልአክ የሚመስሉ አገልጋዮች(የመጨረሻ ክፍል)



4. አገልግሎቱን ለእግዚአብሔር ለቃሉ አደራ መስጠትን ያውቃል (ቁ.32)

                  “ብዙ ሰዎች የመሰከሩለትን ከእኔም የሰማኸውን ሌሎችን ደግሞ
                  ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች አደራ ስጥ።” (2ጢሞ.2፥1)

   አገልጋዮች የእግዚአብሔርን መንጋ የምንጠብቅ ሲመስለን እንስታለን፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ የኤፌሶንን ሽማግሌዎች (ጳጳሳት) “እናንተን ራሳችሁን … ለጸጋው ቃል አደራ ሰጥቻችኋችሁ” ሲላቸው እናያለን፡፡ የእግዚአብሔር መንጋ የሚጠፋው ወይም የሚጎዳው ከእግዚአብሔር በኃጢአቱ ሲለይ ወይም እግዚአብሔር ንስሐ ባለመግባቱ በኃጢአቱ ምክንያት ሲለየው  ነው፡፡ ያ እንዳይሆን መሪዎቹ ሕዝቡን ትክክለኛው የጸጋውን ቃል ወንጌል በማስተማር ሊመሩት ይገባል፡፡ በትክክል ሳይነግሩትና ሳያስተምሩት ሲቀር ግን ይጎዱታል ማለትም የመንግሥተ ሰማያት በር ይዘጉበታል፡፡
      ቅዱስ ጳውሎስ እርሱ ቀድሞ ወንጌልን ለመስበክ አደራ ከክርስቶስ ኢየሱስ እንደተቀበለ እንዲሁ፤ (ሐዋ.9፥1-16 ፤ 26፥16 ፤ 1ቆሮ.9፥17) አሁን ደግሞ እርሱ ለታመኑት ሲሰጥና የታመኑትም ለሌሎች ለታመኑ አደራ እንዲሠጡ ሲተጋ እናየዋለን፡፡ ወንጌል መስበክ አደራ ከሆነ አደራው ኃላፊነት ያለበት አደራ ነው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ወንጌልን ኃላፊነት ተሰምቷቸው ከፍቅር በተነሳ ውዴታ እንጂ በምርጫ እንዲያገለግሉ አልተጠሩም፡፡

Tuesday, 9 December 2014

የብርሃን መልአክ የሚመስሉ አገልጋዮች(ክፍል - አራት)




2. ለመንጋው ሁሉና ለራሱ ሊጠነቀቅ ይገባል፡፡(ቁ.28)

    ቅዱስ ጳውሎስ ቅዱስ ጢሞቴዎስን “ለራስህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፥ በእነዚህም ጽና፤ ይህን ብታደርግ፥ ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህና።” በማለት ይመክረዋል፡፡ በእርግጥ የሚያድን እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ አማኞች ወደጌታ በመምጣት ሕይወታቸው  ዕለት ዕለት በማደግ እግዚአብሔርን ወደመምሰል እንዲደርሱ አገልጋዮች ትልቁን ድርሻ አላቸውና፥ ለራሳቸውም፤ ለትምህርታቸውም ሊጠነቀቁ ይገባቸዋል፡፡ ጤናማውን ጉዞ እስከፍጻሜው ልንጓዝ የምንችለው ለትምህርታችንና ለምናስተምረው የእግዚአብሔር መንጋ መጠንቀቅ ስንችል ነው፡፡
    ጥቂት እርሾ ብዙውን ሊጥ እንደሚያቦካ (1ቆሮ.5፥16)፤ ጥቂት የተባለም ኃጢአት ወይም ክፉ ትምህርት ብዙውን መንጋ ከመበከል አይመለስም፡፡ እንደዋዛ የሚደረጉና የሚነገሩ ነገሮች በመንጋው ላይ ሊያሳርፉ የሚችሉት ተጽዕኖ ቀላል አይደለም፡፡ ትላንት እንደዋዛ ሲነገሩ የነበሩ ተረታ ተረቶች፥ ዛሬ ወደቤተ ክርስቲያን ሾልከው ገብተው ለብዙ ምዕመናን የሕይወት መመሪያ እስከመሆን ደርሰዋል፡፡ በዚህ ሳያበቃ አሁንም ለመንጋው ባለመራራት የሚጻፉትና የሚሰበኩት ስብከቶች በቃሉ ሚዛንነት ልንፈትሻቸው፤ ቀለው ከተገኙ ልናስወግዳቸው ይገባናል፡፡

Tuesday, 2 December 2014

የብርሃን መልአክ የሚመስሉ አገልጋዮች(ክፍል - ሦስት)



5. የሚነሱት ከመካከላችን ነው፡፡
     እውነተኛውና ለእግዚአብሔር የጨከነ አገልጋይ ሲጠፋ ክፉው አገልጋይ ከውጪ ወደውስጥ ወይም በብዛት ከመንጋው መካከል ይነሳል፡፡ ከመካከል የሚነሱ የሐሰት መምህራን በዋናነት የመሳታቸውና የማሳታቸው ምክንያት ከመሠረተ እምነት ትምህርት ጉድለት ነው፡፡ ገበሬ እርሻውን አለስልሶ ከዘራ በኋላ በየጊዜው መከታተል ይገባዋል፡፡ የሚከታተለው አለስልሶ የዘራው እርሻ የማይበቃ ሆኖ ሳይሆን አረምና እንክርዳድ ዋናውን ዘር እንዳይውጠው ነው፡፡ አረምና እንክርዳድ ገበሬው የዘራው አይደልም፤ እርሱ ያልዘራው ከመካከል የበቀለው አረም ግን የዘራውና ዋና ዘር ሊያጠፋው ይችላል፡፡ ስለዚህ በየጊዜው  ሊያርም ፤ ሊኰተኩተው ይገባዋል፡፡ በመንፈሳዊ አለም ደግሞ መልካሙ ገበሬ እግዚአብሔር ዘርን ከዘራ በኋላ መጥቶ ክፉን ዘር የሚዘራው ጠላት ዲያብሎስ ነው፡፡ (ማቴ.13፥28) ስለዚህ ልንተጋ ቃሉን በማጥናት ልንበረታ ይገባናል፡፡

Saturday, 22 November 2014

ግብረ ሰዶማዊነትና የእኛ ዘመን አገልጋዮች


                          Please read in PDF                  

        ይህ ጽሁፍ በዚህ ብሎግ በመጀመርያ ሲወጣ ተቃዋሚዎች ገጥመውታል፤ በተቃውሞው ምክንያትም ለጊዜው ከዚህ ብሎግ ላይ ለማንሳትና ያለውን ነገር ለማጤን ጥረት አድርጌያለሁ፡፡ ነገር ግን ቁጣውና ተቃውሞው ለእግዚአብሔር ስላላደላና ኃጢአትን ስላልተቃወመ ምንም ሳልቀንሰው ሙሉ ጽሁፉን እንዳለ መልሼ አውጥቼዋለሁ፡፡ ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው ፊት አናደላም፤ የሚያስጨንቀን የቤተ ክርስቲያን ቅድስናና ሸክም እንጂ በእግዚአብሔር ምህረት ላይ ለሚዘብቱና ለክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን መነቀፍ ግድ ለማይላቸው አይደለም!!!
     ስለግብረ ሰዶም ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሔር ጉልበት ቤተ ክርስቲያንን ስለሚያሳድፍ ስለየትኛውም ነውር ለክርስቶስ አድልተን ከመገሰጽ ዝም አንልም፡፡ ግብረ ሰዶም አገር እያካለለ ለመሆኑ የቅርብ ሌላ ማሳያ ብናመጣ፤ ሬድዮ ፋና “የአመቱ የፍቅር አሸናፊ ግጥም” ብሎ በግዮን ሆቴል በሸለመው ሽልማትና በራሱ ሬድዮ በትላንትናው ዕለት የለፈፈው ከሴት ለሴት የተጻፈ “የፍቅር ግጥምን” ነው፡፡ መቼም በአገራችን የፍቅር ግጥም ብሎ ከሴት ለሴት የሚጻፍ ይኖራል ብሎ ማሰብ ወይ የአገርን ባህል መናቅ፤ ወይ ግብረ ሰዶምን መደገፍ እንጂ ሌላ ትርጉም አይሰጠውም፡፡  ይህንና ሌላም እየሰማን ዝም ለማለት የተቀበልነው አደራ አይፈቅድልንም፡፡ መልካም ንባብ፡፡ 
 ስለግብረ ሰዶማዊነት በሁለት የተለያዩ ክፍሎች መጻፌና በሁለቱ ክፍሎችም ለጊዜው የነበረኝን ሃሳብ ማጠቃለሌን አልዘነጋውም፡፡ ነገር ግን አሁንም ግብረ ሰዶማዊነት የቤተ ክርስቲያንን ቅድስና ከማርከስ፤ ምድራችንን ለከፋ ጉስቁልናና ርኩሰት አሳልፎ ከመስጠት ያላቆመ ፍጹም ወደመስፋፋት የሄደ ክፉ ርኩሰት ነውና ዳግም ይህንን ርዕስ ማንሳት አስፈልጎኛል፡፡ ለዚህ እውነታ ብዙ የቅርብ ጊዜ ማሳያ ብቻ ማንሳቱ በቂ ይመስለኛል፡፡
    ድርጊቱ የተፈጸመው በምስራቁ የሃገራችን ክፍል ነው፡፡ የሠላሳ ሁለት አመት አጐት የአራት አመት የወንድም ልጁን በእረኝነት ሥፍራ በመሄድ ጫት እንዲቅም ያግባባዋል፡፡ ህጻኑ እንቢ ቢልም ያስገድደዋል፡፡ ጫት እንዲቅም ካስገደደው በኋላ ልጁ ራሱን መቆጣጠር ሲያቅተው ልጁን የግብረ ሰዶም ጥቃት ይፈጽምበታል፡፡ የልጁ የሰገራ ማውጫ ሙሉ ለሙሉ ይቀዳዳል፡፡ ከሆዱ የወጣው የውስጠኛው የሰገራው ክፍል ሙሉ ለሙሉ የልጁን ጠረን ይለውጠዋል፡፡ ልጁ ፍጹም ራሱን ስቶ ሲወድቅ ከወደቀበት ቦታ ተሸክሞት ከወላጆቹ ጓሮ አምጥቶ ጥሎት ይሰወራል፡፡ ከዚያ በኋላ ብዙም ሳይቆይ የልጁ ህይወት ያልፋል፡፡

Friday, 14 November 2014

በድል ነሺው ስምህ …


                             Please read in PDF

በጐነት ለዛ አጣ፤
ወዳጅ ከወዳጅም ፥ ፍቅሩ ሆነ ለበጣ፤
መልክ ብቻ ሆኖ፤
እምነት ከኃይል ጦሞ …
ኪሳራ ገነነ፤

Tuesday, 11 November 2014

የብርሃን መልአክ የሚመስሉ አገልጋዮች (ክፍል - ሁለት)



3. ደቀ መዛሙርትን ወደኋላ ይስባሉ(ቁ.30)

   ጌታ ኢየሱስ በወንጌል “መስቀሉንም የማይዝ በኋላዬም የማይከተለኝ ለእኔ ሊሆን አይገባውም።” ብሏል፡፡  (ማቴ.10፥38) እኛ ሁል ጊዜ ከክርስቶስ በኋላ ነን፡፡ ተፎካካሪ ስላልሆንን ከጐኑ ፤ ወይም የተሻልን ሆነን ከኋላችን የምናስከትለው አይደለንም፡፡ እርሱ ሰባሪ ነውና ሁል ጊዜ ከፊት የሚወጣ ነው፡፡ (ሚክ.2፥13) ተመርቆ የተከፈተው አዲስ፤ ህያው መንገድና (ዕብ.10፥19) ቀድሞም በመንገዱ የሄደበት እርሱ ስለሆነ እኛ የእርሱን ፋናና ፍለጋውን የምንከተል ነን፡፡ (1ጴጥ.2፥21) ይህ ጉዞ የዕለት ተዕለትና ያለምንም ማቋረጥ ልናደርገው የሚገባን ነው፡፡(ሉቃ.9፥23)

Friday, 7 November 2014

የብርሃን መልአክ የሚመስሉ አገልጋዮች(ክፍል - አንድ)


                                          Please read in PDF
    
     የመከራው አይነቱና መጠኑ ይለያይ እንጂ ክርስትና ያለመከራ የኖረበት ዘመን የለም፡፡ የትላንት ቄሳሮች ክርስቲያኖችን በማረድ ፤ የኋላ መናፍቃን የእውነትን ወንጌል በማጣመም፤ ፖለቲከኞችም ድርሳኖቻቸውን አግዝፈው መጽሐፍ ቅዱስን “ሊያንኳስሱ” ፤ ህሊናቸውን የሳቱ ፈላስፎች በወንጌሉ ቃል ሊሳለቁ ፤ ሳይንሳዊ ምርምር (ሁሉም አይደለም) ሐለወተ እግዚአብሔርን ሊቃረን … መልከ ብዙ ስህተቶችንና መከራዎችን በክርስትና ውስጥና ላይ ተስተናግዷል፡፡ ይህ ግን ክርስቶስንና ቤተ ክርስቲያንን የተቃወሙትን አደከመ እንጂ፤ ቤተ ክርስቲያንን እንደትክል ድንጋይ በሙሽራዋ ጽናት ዛሬም ህያው ምስክር ሆና አለች፡፡
    ከዚህ የሚከፋው ነገር ግን፥ ከውጪ ሆኖ በግልጥ የሚዋጋው የጠላት አሠራር ሳይሆን በስውር “ሌላ ወንጌል ሳይይዙ”(ገላ.1፥7) እንደብርሃን መልአክ (2ቆሮ.11፥14) ተገልጠው ሊያናውጡ የሚወዱቱ ናቸው፡፡ በዘመናት የሰይጣን ውጊያ ልዩ ልዩ ነው፡፡ ትላንት ጣዖት አቁሞ ያሰግድ የነበረው፤ ዛሬ ያንን ስልት ትቶ ጣዖትን የብርሃን መልአክ አልብሶ በእያንዳንዱ ልብ አቁሟል፡፡ ሰው ዛሬ ከእግዚአብሔር ጋር ላለመገናኘት የራሱ “የብርሃን ምክንያት” አለው፡፡ ያንን “ብርሃናዊ ምክንያት” በጸሎትና በመንፈስ ቅዱስ ሃሳብ ብንመረምረው ግን ጣዖት እንጂ ሌላ ትርጉም የለውም፡፡ ምንም ነገር ቢሆን ለእግዚአብሔር የሆነውን ነገር እንዲሰርቅብን አልተፈቀደለትምና፡፡(ማቴ.10፥37)

Friday, 31 October 2014

ተጠርተናል ጥሪ


                               Please read in PDF
                                     
እግዚአብሔር አዳምን በመልኩ ሲፈጥረው፤
አዳም በራሱ መልክ ቃየልን ወለደው፤

Sunday, 26 October 2014

ዘመን የሚያረጀው …


                                          Please read in PDF

ዘመንማ ጠብቷል፣ ፈክቷል በማለዳ፤
ቀንበር አለዝቦ፣ አንከባ’ሎ ፍዳ፤
ንጋቱ ፈንጥቋል፣ ጨለማውን ገፏል፤

Thursday, 16 October 2014

የአብያተ ክርስቲያናት ሐሳብ ያስጨንቀናል?



     የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብ ለተነገረለት ሳይሆን ላልተነገረለት ነገር በግድ በማስጨነቅ ከሚተረጐሙት ክፍሎች አንዱ ነው፡፡ የመጻህፍትና የእግዚአብሔርን ኃይል ስለማናስተውል ብዙ ጊዜ በስህተት ወጥመድ እንያዛለን፡፡(ማቴ.22፥29) ቤተ ክርስቲያን በመመስረት ከሌሎች ሐዋርያት ግንባር ቀደሙ ሐዋርያ፥ ቅዱስ ጳውሎስ ነው፡፡ ለዚህም አገልግሎቱ ሦስት በመጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀሱ አንድ ደግሞ በታሪክ የተረዳ በድምሩ አራት ታላላቅ ሐዋርያዊ ጉዞዎችን አድርጓል፡፡ በእነዚህ ጉዞዎቹ እጅግ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት መሥርቷል፡፡  (አንደኛው ሐዋርያዊ ጉዞ ሐዋ.13፥4-18፥28 ፤ ሁለተኛው ሐዋርያዊ ጉዞ 15፥39-18፥22 ፤ ሦስተኛው ሐዋርያዊ ጉዞ 18፥23-21፥17 ያለው ነው፡፡)

Monday, 13 October 2014

ደመወዛችሁ ይብቃችሁ! (ሉቃ.3፥14)

       
                                                  Please read in PDF

 ለዚህች አጭር ጽሁፍ መነሻ የሆነኝ የምወደው፤ በአክብሮትም የሚያስተምረኝ ወንድሜ ከነገረኝ ነገር በመነሳት ነው፡፡ “አየር መንገድ ላይ ነው፡፡ ወንድሜ ሰው ለመጠበቅ እዚያ ከተቀመጠበት ከጐኑ ‘የተፈራና የተከበረ’ አገልጋይ ተቀምጦ በኪሱ ስልክ ያወራል፡፡ የሚደውልለት ለአገልግሎት ከኢትዮጲያ ውጪ እየጋበዘው ነው፡፡ ግና ሲጀምር ለአገልግሎት ከአንድ አገር ተጠርቶ በእርሱ በኩል ሌላ አገልጋይ የጠየቀው ጥያቄ ‘በአሪፍ ይሸኛሉ ወይ?’ ብሎ ነው፡፡ … ቀጠለ በአሪፍ የማይሸኙ ከሆነ ላይመጣ እንደሚችል በሚያቅማማ ድምጸት መለሰ፡፡ ወይ በአሪፍ መሸኘት!

Thursday, 9 October 2014

“ታይታኒክን ራሱ እግዚአብሔር እንኳ አያሰጥማትም!!!”

   

                                               



 በሰው እጅ ተንቀሳቃሽ ሆነው ከተሠሩ ነገሮች ተወዳዳሪ ያልተገኘላትን ኤም. ኤስ ታይታኒክ መርከብን በባለቤትነት የያዛት ጆን ፒርፖንት በ1912 ዓ.ም ስለታይታኒክ መርከብ የተናገረውን ቃል ነው በርዕስነት የወሰድኩት፡፡ ስለመርከቢቱ ብዙ የተባለ ስለሆነ እኔ ስለዚያ የምለው ነገር የለኝም፤ ይሁንና የመርከቢቱ ባለቤት የተናገረው ቃል እጅግ ድፍረትና “መዓት አውርድ” መሆኑን መርከቢቱ ያሰጠመቻቸውን 1522 ሰዎችን በሞት፤ በንብረትም ላይ ካደረሰችው ጥፋት መረዳት ይቻላል፡፡