Friday, 31 October 2014
Sunday, 26 October 2014
Thursday, 16 October 2014
የአብያተ ክርስቲያናት ሐሳብ ያስጨንቀናል?
የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብ ለተነገረለት ሳይሆን ላልተነገረለት
ነገር በግድ በማስጨነቅ ከሚተረጐሙት ክፍሎች አንዱ ነው፡፡ የመጻህፍትና የእግዚአብሔርን ኃይል ስለማናስተውል ብዙ ጊዜ በስህተት
ወጥመድ እንያዛለን፡፡(ማቴ.22፥29) ቤተ ክርስቲያን በመመስረት ከሌሎች ሐዋርያት ግንባር ቀደሙ ሐዋርያ፥ ቅዱስ ጳውሎስ ነው፡፡
ለዚህም አገልግሎቱ ሦስት በመጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀሱ አንድ ደግሞ በታሪክ የተረዳ በድምሩ አራት ታላላቅ ሐዋርያዊ ጉዞዎችን አድርጓል፡፡
በእነዚህ ጉዞዎቹ እጅግ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት መሥርቷል፡፡ (አንደኛው
ሐዋርያዊ ጉዞ ሐዋ.13፥4-18፥28 ፤ ሁለተኛው ሐዋርያዊ ጉዞ 15፥39-18፥22 ፤ ሦስተኛው ሐዋርያዊ ጉዞ 18፥23-21፥17
ያለው ነው፡፡)
Monday, 13 October 2014
ደመወዛችሁ ይብቃችሁ! (ሉቃ.3፥14)
ለዚህች አጭር ጽሁፍ መነሻ የሆነኝ የምወደው፤ በአክብሮትም የሚያስተምረኝ ወንድሜ ከነገረኝ ነገር በመነሳት ነው፡፡
“አየር መንገድ ላይ ነው፡፡ ወንድሜ ሰው ለመጠበቅ እዚያ ከተቀመጠበት ከጐኑ ‘የተፈራና የተከበረ’ አገልጋይ ተቀምጦ በኪሱ ስልክ
ያወራል፡፡ የሚደውልለት ለአገልግሎት ከኢትዮጲያ ውጪ እየጋበዘው ነው፡፡ ግና ሲጀምር ለአገልግሎት ከአንድ አገር ተጠርቶ በእርሱ
በኩል ሌላ አገልጋይ የጠየቀው ጥያቄ ‘በአሪፍ ይሸኛሉ ወይ?’ ብሎ ነው፡፡ … ቀጠለ በአሪፍ የማይሸኙ ከሆነ ላይመጣ እንደሚችል
በሚያቅማማ ድምጸት መለሰ፡፡ ወይ በአሪፍ መሸኘት!
Thursday, 9 October 2014
“ታይታኒክን ራሱ እግዚአብሔር እንኳ አያሰጥማትም!!!”
በሰው እጅ ተንቀሳቃሽ ሆነው ከተሠሩ ነገሮች ተወዳዳሪ ያልተገኘላትን ኤም.
ኤስ ታይታኒክ መርከብን በባለቤትነት የያዛት ጆን ፒርፖንት በ1912 ዓ.ም ስለታይታኒክ መርከብ የተናገረውን ቃል ነው በርዕስነት
የወሰድኩት፡፡ ስለመርከቢቱ ብዙ የተባለ ስለሆነ እኔ ስለዚያ የምለው ነገር የለኝም፤ ይሁንና የመርከቢቱ ባለቤት የተናገረው ቃል
እጅግ ድፍረትና “መዓት አውርድ” መሆኑን መርከቢቱ ያሰጠመቻቸውን 1522 ሰዎችን በሞት፤ በንብረትም ላይ ካደረሰችው ጥፋት መረዳት
ይቻላል፡፡
Saturday, 4 October 2014
Tuesday, 30 September 2014
Thursday, 25 September 2014
የመስቀሉ ቃል
የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉ አህዝብ ሞኝነት፤
ለአይሁድም ማሰናከያ ነው፡፡ ምክንያቱም አይሁድ የመስቀሉን ቃል በእንጨት
ላይ መዋልና መሰቀልን እንደተረገመ ስለሚቆጥሩት ነው፡፡(ዘዳግ.21፥23 ፤ ገላ.3፥13) ነገር ግን ክርስቶስ ኢየሱስ በመስቀል
ላይ በመሰቀሉ “እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ … ” እንደኃጢአተኛ
የተቆጠረ ሆነ፡፡(2ቆሮ.5፥21) ለግሪክ ሰዎች ደግሞ በእንጨት ላይ መሰቀል የአማልክትን ክብርና ልዕልና ዝቅ የሚያደርግና እንደድኩም
የሚያስቆጥር ስለሆነ ፈጽሞ አይቀበሉትም፡፡
ቀድሞ የጥንት ፋርሶች በኋላም ሮማውያን አንድን ወንጀለኛ በመስቀል
ላይ በመስቀል የሚቀጡት “ኦርዝሙድ” የተባለ የመሬት አምላካቸው እንዳይረክስባቸው በመጠንቀቅና ለአማልክታቸው ክብርን ለመስጠት በማሰብ
ነበር፡፡(አባ ጐርጐርዮስ(ሊቀ ጳጳስ)፤ የኢትዮጲያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ 3ኛ ዕትም፤ 1991፤ አዲስ አበባ፤ ትንሳኤ ዘጉባኤ ማተሚያ
ድርጅት፤ ገጽ.104)
Monday, 22 September 2014
ሦስቱ ባህታውያን(የመጨረሻ ክፍል)
ነገር ግን ሁለተኛው ባህታዊ ቃላቶቹን
አቀላቅለው አሳስተው ተናገሩ፡፡ ራቁታቸውን ያሉት ረዥሙ ባህታዊም አጣርተው አልደገሙትም፡፡ ጢማቸው አፋቸውን ሸፍኖት ስለነበር የተጣራ
ድምፅ ሊያወጡ አልቻሉም፡፡ ጥንታዊው ደግሞ ጥርሶቻቸው ስለረገፉ በግልጽ የማይሰማ ነገር ነው ያጉተመተሙት፡፡
አቡኑ እንደገና ደገሙላቸው፡፡ ባህታውያኑም እንደገና ደገሙት፡፡ አቡኑ በትንሽ
ድንጋይ ላይ ተቀምጠው ባህታውያኑም በአጠገባቸው ቆመው አፍ አፋቸውን አፍጠው እየተመለከቱ የሚሏቸውን ይደግሙላቸው ነበር፡፡ ቀኑን
ሙሉ እስከአመሻሽ ድረስ ሊያስተምሯቸው ደከሙ፡፡ አንዲቷን ቃል አስር፣ ሃያ፣ መቶ ጊዜ እየመላለሱ አስጠኗቸው፡፡ ቃላት እየተቀለቀሉባቸው
ሲቸገሩ ያርሟቸውና እንደገና ከመነሻው ያስጀምሯቸዋል፡፡
የጌታን ጸሎት ሙሉ ለሙሉ እስከሚያስተምሯቸው ድረስ አቡኑ ከባህታውያኑ
ዘንድ ቆዩ፡፡ በመጨረሻም ያለ አቡኑ ድጋፍ እያንዳንዳቸው በራሳቸው ሙሉ ጸሎቱን ወረዱት፡፡
አቡኑ ወደ መርከቡ ሊመለሱ ሲነሱ ጨለማው እየከበደ ከባህሩም ጨረቃ እየወጣች
ነበር፡፡ ባህታውያኑን ሲሰናበቱ ሁሉም እስከመሬት አጐንብሰው ሸኟቸው፡፡ እሳቸውም እያንዳንዳቸውን ካጐነበሱበት ቀና እያደረጉና እያቀፏቸው
ባስተማሯቸው መሠረት እንዲጸልዩ ካዘዟቸው በኋላ ወደ ጀልባዋ ገቡ፡፡
Friday, 19 September 2014
ሦስቱ ባህታውያን (ክፍል - ሁለት)
አቡኑ ከመርከቢቷ የፊት ጫፍ ላይ ወንበር ቀርቦላቸው ሲቀመጡ ሌሎቹም
ሁሉ መጥተው ወደ ትንሿ ደሴት መመልከታቸውን ቀጠሉ፡፡ ጥሩ የማየት ችሎታ ያላቸው ሰዎች በደሴቷ ላይ የሚገኙትን አለቶችና የጭቃ
ጎጆዋንም ማየት ችለው ነበር፡፡ ከመሃላቸው አንዱ ሦስቱን ባህታውያን ጭምር መለየት ችሎ ነበር፡፡ ካፒቴኑ አጉሊ መነጽር አምጥቶ
ከተመለከተ በኋላ ለአቡኑ እየሰጣቸው፦
“ትክክል ነው፡፡ ከባህሩ ጠረፍ ላይ ከትልቁ አለት እንዲህ ወደ ቀኝ ሲሉ
ሦስቱ ባህታውያን ቆመው ይታያሉ፡፡” አለ፡፡
አቡኑ በመነጽር ተመለከቱ፡፡ ወደትክክለኛው አቅጣጫም አዞሩት፡፡ የተባለው
እውነት ነው፡፡ ሦስቱም እዚያው ቆመዋል፡፡ አንደኛው ረዥም ሌላኛው ትንሽ አጠር የሚሉና ሦስተኛው ደቃቃ ትንሽ፡፡ ሦስቱም ከባህሩ
ጠረፍ ላይ እጅ ለእጅ ተያይዘው ቆመው ነበር፡፡
Monday, 15 September 2014
ሦስቱ ባህታውያን (ክፍል አንድ)
አጭር ልብወለድ
(ምንጭ ብሪቱ መጽሔት ጥር - የካቲት
1991)
(ደራሲ፦ ሊዎ ቶልስቶይ)
(ተርጓሚ፦ ሁነኛው ጥላሁን)
“አሕዛብም በመናገራቸው ብዛት እንዲሰሙ
ይመስላቸዋልና ስትጸልዩ እንደ እነርሱ በከንቱ አትድገሙ።ስለዚህ አትምሰሉአቸው፤ ሳትለምኑት አባታችሁ የሚያስፈልጋችሁን ያውቃልና።”
(ማቴ.6፥7-8)
አቡኑ ከአርካንጌልስክ ከተማ ወደ ሶሎቬትስኪ ደሴት በመርከብ እየተጓዙ
ነበር፡፡ ቅዱሱን ሥፍራ ለመሳለም የሚሄዱ ምዕመናንም አብረዋቸው ነበሩ፡፡ የነፋሱ አቅጣጫ አመቺ፣ አየሩም ማለፊያ ነበረ፡፡ ባህሩም
ጸጥ ብሏል፡፡ ምእመናኑ ገሚሱ ጋደም ብለው ከፊሉም ከያዙት ስንቅ እየቀማመሱ የተቀሩትም በቡድን በቡድን ተቀምጠው እርስ በእርስ
ያወራሉ፡፡ አቡኑ ከነበሩበት ተነስተው ወደ መርከቡ መተላለፊያ መራመድ
ጀመሩና ወደጫፉ ሲቃረቡ ሰብሰብ ያሉትን ሰዎች አዩዋቸው፡፡ አንድ ባላገር ወደባህሩ እያመለከተ አንድ ነገር እያሳያቸው
ሲናገር ሰዎቹ ያዳምጡት ነበር፡፡ አቡኑ ቆም ብለው ባላገሩ ወደሚያመለክትበት በኩል ተመለከቱ፡፡ በፀሐይ ከሚያብረቀርቀው ባህር በስተቀር
ምንም የሚታይ ነገር አልነበረም፡፡ ወደሰዎቹም ጠጋ ብለው ባላገሩ የሚለውን ማዳመጥ ጀመሩ፡፡ ባላገሩ አቡኑን እንዳየ ባርኔጣውን
በማውለቅ ንግግሩን አቋርጦ ፀጥ አለ፡፡ የሚያዳምጡትም ሰዎች ባርኔጣዎቻቸውን በማንሳት በአክብሮት ተቀበሏቸው፡፡
“በመምጣቴ አትጨነቁ ወዳጆቼ” አሉ አቡኑ፡፡ ወደባላገሩም ፊታቸውን አዙረው
“የመጣሁት አንተ የምትነግራቸውን ለመስማት ብዬ ነው” አሉት፡፡
Tuesday, 9 September 2014
የተወደደችው የጌታ አመት (ሉቃ.4፥19)
እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ በሰላም በፍቅር አሸጋገራችሁ!!!
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ያለማቋረጥ ከብዙ ህዝብ ጋር ለአምልኰ በመገኘት
ለተከታዮቹ ደቀ መዛሙርት የሚደነቅ ምሳሌ የሚሆን ልምድ አለው፡፡(ማቴ.13፥54፤ ማር.1፥21፤ ሉቃ.4፥16፤ ዮሐ.7፥14) ጌታ
ለጸሎትና ቃሉን ለማስተማር ዘወትር “መሰብሰብን ባለመተው” ለደቀ መዛሙርቱ አብነት ሆኗል፡፡(ዕብ.10፥24) ዘወትር በእግዚአብሔር
ፊት ለጸሎት፤ ቃሉን ለመመርመርና ለማስተማር መሆንን ጌታ በእውነት እኛንም አስተምሮናል፡፡ ናዝሬት ጌታን ለመቀበል ፈቃደኛ ባትሆንም
እርሱ ግን ወዳደገባትና ወደሚያውቃት ከተማ ምኩራብ መጥቶ አስተማረ፡፡ ዕድገታችንን፣ ማንነታችንን፣ ገመናችንን፣ ልጅነታችንንና፣
ውድቀታችንን … ምናልባትም “ልካችንን” በሚያውቁን ሰዎች ፊት ማገልገል ከባድ ህመም ይኖርበት ይሆናል፤ ጌታ ግን አድርጎታልና ልጆቹ
በህይወቱ ልንታዘዝ፤ ህይወቱም ሊያስተምረን ይገባል፡፡
ጌታ ወደምኩራብ
በገባ ጊዜ የኢሳይያስን ትንቢት ጥቅልል አንስተው ሰጡት፡፡ እርሱም ተነስቶ መጽሐፉን በመተርተር ማንበብ ጀመረ፡፡ አይሁድ ምንም
እንኳ ወደ ተስፋው ፍጻሜ ባይደርሱም፤ የእግዚአብሔርን ቃል የማንበብ ብቻ ሳይሆን መጻህፍትን በመቅደሱና በየምኩራቦቻቸው በአግባቡ
የማስቀመጥ ልማድ ነበራቸው፡፡ በምኩራባቸው የእግዚአብሔር ቃል ጥቅልል ትልቁንና የመጨረሻውን ሥፍራ በክብር ይይዛል፡፡ ትልቅና የመጨረሻው
አምልኰ ለእግዚአብሔር ቃልና ላስተማረን ትምህርቱ ልዩ ክብርን በመስጠት መታዘዝ ነው፡፡ የብዙዎቻችን ቤት “መጻህፍት መደርደርያ”
የተመሉት በልቦለድና በፍልስፍና “ጥቅልል ጽሁፎች” ነው፡፡ ለእግዚአብሔር ቃል ቸል በማለት ለሌሎች “ፍጡራን ጥቅልሎች” ትልቅ ክብርና
ሥፍራ የሰጠ ትውልድ ይህ የእኛ ዘመን ትውልድ ነው ብል ያልተጋነነ እውነት ነው፡፡
Tuesday, 2 September 2014
ማስተስረያውን ክዶ
ሳይጐድል ደምግባቱ፣ አምሮ እንደደመቀ፤
ትኩስ ሥጋነቱ፣ ግሎ እንደሞቀ፤
ሸጋ ቆንጆነቱ፣ ጉድ አጀብ አስብሎ፤
ከደሙ ቤዛነት፣ ከ‘ርሱ ተነጥሎ፤
Thursday, 28 August 2014
የመቶ አለቆቹ (የመጨረሻ ክፍል)
4. የመቶ አለቃው ዩልዮስ (ሐዋ.27፥43)
“የመቶ አለቃው ግን ጳውሎስን ያድነው
ዘንድ አስቦ ምክራቸውን ከለከለ … ”
ቅዱስ ጳውሎስ ለቁጥር በሚታክቱና ምላሳቸው በሳለ ከሳሾች መካከል “እየተብጠለጠለ” ቅንጣት ታህል አለመፍራቱን ሳስብ
የጌታ ኢየሱስ “ … አሳልፈውም ሲሰጡአችሁ፥ የምትናገሩት በዚያች ሰዓት ይሰጣችኋልና እንዴት ወይስ ምን እንድትናገሩ አትጨነቁ፤
በእናንተ የሚናገር የአባታችሁ መንፈስ ነው እንጂ፥ የምትናገሩ እናንተ አይደላችሁምና፡፡” የሚለው የትንቢት ቃል መፈጸሙን ትዝ ይለኝና
ልቤ ይረካል፡፡(ማቴ.10፥19-21) የእስያ አይሁድ፣ የኢየሩሳሌም አይሁድ፣ ጠርጠሉስ፣ ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ … ስለእርሱ በጎነት
የላቸውም፡፡ ፊስጦስም እንደቀደሙት ባዕለ ሥልጣናት ክፉ ልማድ አይሁድን ደስ ለማሰኘት ጳውሎስ በኢየሩሳሌም ተመልሶ እንዲዳኝ ይጐተጉተዋል፡፡(ሐዋ.25፥9፤21)
ቅዱስ ጳውሎስ ነገሩ እንዳላማረ፤ ፊስጦስ ራሱ ወደአይሁድ እንዳደላ ያወቀ ይመስላል፡፡ አሁን በቆመበት የሮማ የፍርድ
ችሎት ፊት መዳኘት እንደሚፈልግ በጽናት ተናገረ፡፡ ምክንያቱም በአይሁድ ሸንጎ ፊት ቢዳኝ የልባቸውን ክፋት ያውቀዋል፡፡ ይገድሉታልና፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ለሌለው ሞት ራሱን አሳልፎ አልሰጠም፡፡(ዮሐ.8፥59) ጳውሎስ “ሰማዕትነት አያምልጠኝ” ብሎ ለስንፍና ሞት
ሳይሸነፍ ወደቄሳር ይግባኝ በማለት በሮማዊ ዜግነቱ የተሰጠው መብቱን ተጠቀመበት፡፡(ሐዋ.25፥11)
Monday, 25 August 2014
የመቶ አለቆቹ (ክፍል አራት)
የሮማ
መቶ አለቆች
3.2.
በሰፈሩ ውስጥ(ሐዋ.23፥10)
ቅዱስ ጳውሎስ ከመገረፍና ጭካኔ ከተመላበት ድብደባ በኢየሱስ መንፈስና
ብርታት፤ በየመቶ አለቃውም ቅንነት ተርፏል፡፡ በማግስቱ ሻለቃው አይሁድ እርሱን የከሰሱበትን እርግጡን ምክንያት ምን እንደሆነ ለማወቅ
አስቦ ከፈታው በኋላ፤ ሸንጎውንና የካህናት አለቆችን እንዲሰበስቡ አዞ፤ ጳውሎስን በፊታቸው አቆመው፡፡ የአይሁድ ሸንጎ እንዲሰበሰቡ
የተፈለገበት ምክንያት ሻለቃው የጳውሎስን ጥፋት ማወቅ ስለተሳነው የእርሱ ወገኖች እንዲያጣሩ ነበር፡፡ ግን ዳኝነቱ ቀድሞ በአድሎአዊነት
አጋድሏል፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ በሸንጎው ፊት በቆመ ጊዜ ሁለት የማይስማሙ ወገኖች ጳውሎስን
ለመክሰስ ግን ተስማምተው ቆሙ፡፡ ሁል ጊዜ ይደንቀኛል፡፡ የጌታ የሆኑ ክርስቲያኖችን ለመግደል፤ ለማሳደድ፤ ለመክሰስ ሁለት ፈጽሞ
የማይስማሙ አካላት ይፋቀራሉ፡፡ የዚህ ጽሁፍ ጸሐፊ በሁለት ፍጹም ተቃራኒ የእምነት አካላት የተከሰሱ አማኞችን የአለማዊ ፍርድ ቤት
ችሎት እየደነቀው የማየት ዕድል አጋጥሞታል፡፡ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን አብረው ለመኖር አይስማሙም፣ ይበላላሉ፤ ክርስቶስ ኢየሱስንና
እንደጳውሎስ ያሉ አማኞችን ግን ለመክሰስ ከባልና ሚስት ይልቅ ይዋሃዳሉ፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)



