Thursday, 14 November 2013

በከንፈሩ የሚያከብር ህዝብ(ኢሳ.29÷13)


         ሰሞኑን ከወደምድረ ዓረብ ስለሰማሁትና ስላየሁት ነገር እንዲህ አልኩ…!!!
         በመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ዘንድ "ደረቅ አዲስ ኪዳን" እየተባለ የሚጠራው መጽሐፉ፣ኢሳይያስ የስሙ ትርጓሜ "እግዚአብሔር ያድናል" ማለት ነው፡፡በነቢዩ ዘመን ይሁዳና ህዝቦቿ "የእስራኤልን ቅዱስ" ተወዳጁን ጌታ ንቀውና አቃለው ነበር፡፡ከህዝቡም ኃጢአትና ነውር የተነሳ የእርሻው ቡቃያ ተዘርቶ ሊሰጥ ከሚገባው እጅግ አነስተኛውን የሰጠበት ዘመን ነበር፡፡(ኢሳ.5÷9-10)የእግዚአብሔር ቃል በዘመኑ ለባለራዕዮችና ለነቢያት እንኳ ሳይቀር የተዘጋና የተሰወረ ሆኖም ነበር፡፡(ኢሳ.29÷10)
       መስዋዕቱ፣ቁርባኑ፣የመቅረዙ መብራት፣ዝማሬው ፣ቃሉን መስማት ፣መስገዱ ፣መጾሙ፣መጸለዩ፣…. ያልተጓደለበት ነገር ግን ይህ ሁሉ ሆኖ ህዝብና መሪ በአንድ ያበደበት፣ነቢዩ ከጠንቋይ የተስማማበት፣ አዝማሪ ከዘማሪ የተቋመሩበት፣መሪው በጉቦ አይኑ የታወረበት ፣ሰባኪ ከዘማሪ በዝሙት የረከሰበት፣ህዝቡ "በአስረሽ ምቺው" ኃጢአት የተካነበት፣ካህኑና ዲያቆኑ ተማክረው ሙዳየ ምጽዋት ሰብረው የሚሰርቁበት፣ ህዝቡ ላየው ሁሉ ልቡን የሚከፍትለትን ይህን የእኛን ዘመን ይመስላል የነቢዩ ዘመን፡፡
      ይሁዳ ዕለት ዕለት እግዚአብሔርን የምትፈልግ ፣መንገዱን ለማወቅ የምትጓጓ፣ትዕዛዙን እንዳልተወች፣    እግዚአብሔር ወደእርሷ እንዲቀርብ የምትወድ ፣የምትጾም፣ራስዋን ያዋረደች … ብትመስልም ነገር ግን ሠራተኞችን የምትበዘብዝ፣ጾሟ ከጥልና ከክርክር ያልጸዳ፣ በግፍና በጡጫ የምትደበድብ … ነበረች፡፡(ኢሳ.58÷1-4)፡፡

Monday, 11 November 2013

የሕጻኑን ነፍስ የሚፈልጉት (ማቴ.2÷20)

     በሥጋ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደው ኢየሱስ፥ ዓለምን ብቻውን ሊያድን ብቃት ያለው አዳኝ፣ መሲህ ክርስቶስ ሆኖ የሰውን ልጅ ሊያድን ተገልጧል፡፡ ነቢዩ "ሕጻን ተወልዶልናልና …"(ኢሳ.9÷6) ያለውን ያንን ሕጻን፥ ማቴዎስም ሕጻን ብሎ ይጠራዋል፡፡ ይህ ሕጻን ገና ሳያድግና አንደበቱን ከፍቶ ሳይናገር የንጉሥ ፍርሐት፤ የዲያብሎስ ጭንቀት ሆነ፡፡ ኢየሱስ ገና የሁለት ዓመት ሕጻን ቢሆንም፥ ጎልማሳው ሄሮድስ ግን የመግደል ሴራን በስውር ጠነሰሰ፡፡ ጠላት ዓላማ ቢስ ከሆነ ሽማግሌና ጎልማሳ ይልቅ ዓላማ ያለውን ሕጻን በአላማ አጽንቶ ይዋጋል፡፡ ጉዳዩ አላማ እንጂ ዕድሜ አይደለምና፡፡
      የሁለት አመት ሕጻን በሰው ፊት ትርጉም ላይሰጥ ይችላል፡፡ እግዚአብሔር ግን እጅ በአፍ እስክንጭን  በድንቅ ቃል ምስጢር ያወራዋል፡፡ በነቢዩ ሳሙኤልም የሆነው እንዲህ ነው፡፡ እግዚአብሔር ታላላቅ ነን ከሚሉት ጋር ሳይሆን ስለእስራኤል ጉዳይ ከሁለት አመቱ ብላቴና ጋር ያወራ ነበር፡፡ ዓለማውያንና የመቅደሱ አገልጋዮች በእግዚአብሔር ላይ በኃጢአት ሲያምጹ እግዚአብሔር ሳሙኤልን በትሑት ቃል ተናገረው፡፡

Thursday, 7 November 2013

የቆምኩኝ ሲመስለኝ



ማዘያው ከጠፋ የህፃን አንቀልባ
መልካሙ ተጣሞ ካጨድን ገለባ
አፅናኙ ተክዞ መፅናናትን ካጣ
የቆመ የሚመስለው ጎብጦብን ከመጣ
ረሀብ አጠውልጎት  ህፃን ካለቀሰ
ጻድቅ መላ ጠፍቶት ሰይጣን ከቀየሰ

Monday, 4 November 2013

ለተበተኑ



       Please read in PDF 
  ነገሩ ለምድር ያልተሰማና እንግዳ ነው፡፡ኢየሩሳሌም አዲስ ነገር አስተናግዳለች፡፡እነዚያ የተናቁና ፊደል ያልቆጠሩ የገሊላ ሠዎች(ሐዋ.2÷7)በቅዱስ ጴጥሮስ መሪነት የሰበኩት ስብከት ፍሬው በግልጥ ታይቶ ብዙ አማኞችን ወደመንግስቱ አፍልሷል፡፡ሐዋርያት ከዚህ ቀን የበለጠ ሌላ ደስታ ይኖራቸዋል ብዬ አልገምትም፡፡በእርግጥም ሰው ሲድን እንደማየት ያለታላቅ ደስታ ከወዴት ይገኛል?! በዚህ ሳይበቃ "ጌታም የሚድኑትን ዕለት ዕለት በእነርሱ ላይ ይጨምር ነበር።"(ሐዋ.2÷47)፡፡በክርስቶስ ደም የተመሰረች ቤተ ክርስቲያን በዚህ ቃል መሰረት ራሷን ልታይ ይገባታል፡፡ክርስቶስ ያለባት ህያው ቤተ ክርስቲያን  የሚድኑ ነብሳት ሊበዙና ሊጨመሩባት እንጂ አንድ እያስገባች አስር በሌላ በር መሸኘት የለባትም፡፡ሥርና ልምላሜ ያለው ነገር ያድጋል፡፡እንኪያስ የሚያጸና ቃሉንና የሚያለመልም ደሙን የጨበጠች ቤተ ክርስቲያን በምንም አይነት መልኩ ልትጠወልግና ልትታወክ አይገባትም፡፡ጠውልጋ ከታወከች ግን ራሷን ህይወት ባለው ንስሐ ዳግም ማደስ ይገባታል፡፡
         እኒህ ያመኑና የበዙ ነፍሳት በኢየሩሳሌም በአንድነት ተቀምጠው ሳለ መነቃቀፍና ማንጎራጎር ስለጀመሩ(ሐዋ.6÷2) ሐዋርያት እስጢፋኖስንና ሌሎች ስድስት መጋቢዎችን ሾሙላቸው፡፡ወንጌሉን ከሚቀብሩ ተግዳሮቶች መካከል አንዱ ተሟሙቆ መቀመጥ ነው፡፡በዚህ ሁኔታ መቀመጥ ደግሞ ሌላ ችግሩ ሐሜትና መነቃቀፍ ይበዛዋል፡፡ብዙ ጊዜ በጾም ወራት ለጸሎትና ቃሉን ለማጥናት የመሰብሰብ ልማድ ነበረን፡፡በዚህ ጊዜ ግን የሚበዛው ሰዓት ከዝግጅቱ በኋላ ላለው አገልግሎት ሳይሆን በፌዝና በቧልት ነበር የሚያልፈው፡፡የኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን ይህ ችግር ተከስቶባት ነበር፡፡

Wednesday, 30 October 2013

ይሟገትልኛል



መታጠቂያውን ታጥቆ
በስጦታ ብዛት አፉን ስሎ
ሊራገም ሊያራኩት
እዚያው ቀልጦ ሊያስቀር በምድረ በዳው ውስጥ
በምዋርት በአስማቱ
ጉዟቸውን ሊያደርግ ራዕይ አልባ ገልቱ
በለአም በባላቅ ተመክሮ ተዘክሮ
ማለዳ ተነስቷል ሊያስቀር አቅልጦ
እንደቅጠል ሊያረግፍ በእንጭጩ አምክኖ፡፡

Friday, 25 October 2013

ጸሎት - "አቤቱ! ዋጋዬን ለባርያህ ግለጥልኝ "

                           ሺህ ……   1,000?
እልፍ ……   10,000?
አዕላፍ ……   100,000?
አዕላፋት ….    1,000,000?
ትዕልፊት ……    10,000,000?
ምዕልፊት  ….     100,000,000?
አዕላፈ አዕላፋት .…     100,000,000,000?
አዕላፈ ትዕልፊት ……      1,000,000,000,000?
ትዕልፊት አዕላፋት ……     10,000,000,000,000?
ምዕልፊት አዕላፋት ……      100,000,000,000,000?
.?
.?
.?

.?




Monday, 21 October 2013

ለምን ከደካማው ጋር?



   የሰማዩን አለም ቅዱስና ፍጹም ያደረገው በዚያ ያሉ ሁሉም ለስሙና ለፈቃዱ ብቻ ስለሚገዙ ነው፡፡ በቀንና በሌሊት ሳያርፉ የሰማዩን ዓለም በምስጋና ችቦ የሚያፈኩት በፊታቸው የተገለጠች በጎ ፈቃዱን መቀደስ ምግባቸው ፣ማመስገን እረፍት ሆኖላቸው ነው፡፡በእርግጥም የእግዚአብሔር ፈቃዱ በሰማይ የተገለጠች ናት፡፡"ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነችእንዲል ታላቁ የህይወት መዝገብ፡፡(ማቴ.6÷10)
          ምድር ግን መልካምነትና በጎነት የበዛበት ይህን ፈቃዱን ፣ከማለዳ እስከማለዳ የተዘረጋ ቅዱስ ምሪቱን በኃጢአትዋ ከመካከልዋ አሰደደችው፡፡ስለዚህም በክፉዎችና በአስጨናቂዎች ተያዘች፡፡ህይወት የደገሰላትን ትልቁን ጌታ ትታ ሞት የሠረገላትን ተራ ባርያ ዲያብሎስን ሰምታ እንዲያስጨንቃት በላይዋ ሾመችው፡፡ስለዚህም ሲቻለው በግልጥ አልያ ደግሞ የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም ለክፉ ሐሳቡና ምኞቱ ያጠምደናል፡፡
       እኛ ክርስቲያኖች የጌታ ፈቃድ ብቻ የነገሰባትን ያቺን የጽዮን ተራራ ለመውረስ የምንጓዝ የዘወትር መንገደኞች ነን፡፡በተሰፈረ እድሜ የማይሰፈርና መጠኑና ይዘቱ ሊለካ የማይቻለውን በረከትና ህይወት ለመውረስ በቀንና ማታ የምንቃትት ነን፡፡ክፉ ገዢ ካለባት ከዚህች ምድር ወደሚያሰማራን ጌታ ለመጓዝ  የምንፋጠን ፣በተስፋ የምንናፍቅ ደጅም የምንጠና ነን፡፡
     ከሁሉ ይልቅ ደግሞ አንድ ትልቅ እውነት ተረድተናል፡፡ጠላታችን መናፍስት መሆናቸውንና ተግዳሮታቸውም ውስብስብ መሆኑን፡፡ደግሞ አለሙ ሁሉ በክፋት እንደተያዘም በሚገባ እናውቃለን፡፡ (1ዮሐ.5÷19) ስለዚህም ሰልፋችንና ውጊያችን ከአጋንንትና ከጨለማው አለም ገዢዎችና አለቆች ጋር ነው፡፡ ከሥጋና ከደም ጋር ሳይሆን ከነዚህ በዓይን ከማይታዩ አዕላፍና ልምድ ካላቸው መናፍስት ጋር ነው፡፡(ኤፌ.6÷12)

Thursday, 17 October 2013

እጅጉን ቀላል ናት

ከባድማ አይደለም የማይቻል ነገር
በፍቅር የታዘዝነው የጌታችን ወንጌል
በጣት 'ማይነካ አስቸጋሪና ጭንቅ
አይደለችም ወንጌል የአምላካችን መንገድ፡፡

         ከባዱ ሌላ ነው እጅግ አስጨናቂው

Monday, 14 October 2013

የቱ ይበልጥብናል?


                  Please read in PDF
    
     ስለመብለጥ ሚዛናችንን ከቅዱስ ቃሉ አንጻር ካላየንና ብልጫነትን ከሌላ ነገር ተነስተን የምንመዝን ከሆነ በቅጽበት እድሜ ቃሉ ያልፈቀደውንና ፈጽሞ የማይወደውን ሚዛን እናበጃለን፡፡በዓለም ላይ ከሚገመተው ቁጥር በላይ የሆነው ሰው የሚዋደቅለትና አብዝቶ የሚመኘው ነገር ቢኖር ብልጫነትን ወይም መብለጥን ነው፡፡መቼም ለመልካምና እግዚአብሔር በሚወደው ነገር በቅዱስ ቅንአት ማደግና መጎልመስን ከዚህ እንደማናያይዘው ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ምክንያቱም በክርስትና ትምህርት ባደግን፣በቤቱ በኖርን ቁጥር መብለጣችንን ሳይሆን በተወደደ ትህትና አለልክ ዝቅ ብለን ሁሉን ማገልገል እንዲገባን እንቆጥራለን እንጂ በአንዳች እንኳ የምንበልጥበት እንዳለን በልባችን ሐሳብ አይገባንም፡፡
      በእርግጥ ዛሬ ለምጽፋት "ትንስዬ" ጭብጤ ይህን ብዬ ተንደረደርኩ እንጂ ዋና ሐሳቤ ሌላ ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ የመስዋዕትን ህግ ለሙሴ ሲሰጠው የተናገረውን ብዙ ጊዜ እንዲህ ሲገለጥ እወደዋለሁ "ለእንሰሳ ቀንዱ ካልከረከረ፣ጠጉሩ ካላረረ፣ጥፍሩ ካልዘረዘረ ከንጹህና ከተወደደው መካከል መርጦ" ፣ለእህል ቁርባኑ ደግሞ "ነቀዝ ካልበላው ፣ወፍ ካልጠረጠረው፣ እንክርዳድ ከሌለው ከሰባውና "ከመልካም ዱቄቱ" መባሉን አብዝቼ እወደዋለሁ፡፡በእርግጥ ቃሉም ይህን በሚገባ ይገልጠዋል፡፡
      እግዚአብሔር የብሉይ ኪዳኑን የሞትና የኩነኔ አገልግሎቱን እንኳ እንዴት ባለ ክብር እንደወደደ እዩ!! እንኪያስ በደሙ የከበረውና የመንፈስና የጽድቅ አገልግሎት የሆነው የምህረቱ ዘመን አገልግሎት እንዴት ባለክብር ይበልጥ ይሆን?እንደከበረው ምርጡና ውድ መስዋዕት ሆኖ የቀረበውን ትልቁና ዋናውን ነገር ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ብሎ ይገልጥልናል