Monday, 5 May 2025

አባ በርናባስና የ“ክርስቶስ ያማልዳል” አቋማቸው!

Please read in PDF

“… በየትኛውም ቋንቋ የተጻፈ መጽሐፍ ቅዱስ አከራካሪ ነገር ከተነሳበት፣ አስታራቂው በግሪክ የተጻፈው መጽሐፍ ቅዱስ ነው። አዲስ ኪዳን በመጀመሪያ የተጻፈው በግሪክ ስለ ኾነ። ግሪኩ “በአብ ቀኝ ያለው ስለ እኛ የሚማልደው” ካለ፣ “የሚማልደው” ማለት ምን ማለት ነው? የሚለውን ማብራራት፤ መተርጐም ነው እንጂ ቃሉን ቀይሮ “ይፈርዳል” ማለት ምን ማለት ነው? … ለምን ተቀየረ? ብሎ መጠየቅ ደግሞ መብቴ ነው … ቃል ቀይሮ መሸሹስ የት ያደርሳል? … ይህ ቢቀየር እኮ ዕብራውያን፣ ቅዳሴ፣ ሃይማኖተ አበው ስንት ቦታ አለ? … ከመሸሽ መተርጐም ይሻላል … ስንቱንስ ቀይረህ ትችለዋለህ? … ”

Friday, 2 May 2025

ኢየሱስን የቀመሰው ብቻ ይሰብከዋል!

 Please read in PDF

መጽሐፍ ቅዱስ ቃል በቃል ስለ ስብከት ሲናገር፣ “እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤” (1ቆሮ. 1፥23) ይላል። ይህ ክርስቶስን የቀመሱትና አምነው በነፍስ ተወራርደው የሚከተሉት ኹሉ፣ በቃልም በሕይወታቸውም የሚመሰክሩት ነው። ለዚህም ነው፣ “ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን” የሚለው ቃል የመዳን መሠረት ኾኖ የተቀመጠው፤ (ሮሜ 10፥9)።

ማርያምን ከጌታ የሚያስበልጡማ በኦርቶዶክስ ቤት አይነኩም!

Please rad in PDF 

ማስረጃው ይኸው!

በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ፣ ስለ ማርያም የሚሰሙ “ስብከቶች” ማርያም ያለ እግዚአብሔር ሳይኾን፣ እግዚአብሔር ያለ ማርያም ሕይወት አልባ የሚያስብል ብካይና የተመረዘ ትምህርት አለ። ነገረ ማርያም በነገርነቱ ሳይኾን፣ “እንደ ተሰቀለው ክርስቶስ” በደረጀ ስብከቱና እምነቱ አለ!

ሊቀ ጳጳስ ገብርኤል “ማርያም ቤዛ አይለችም” ብለው ሲናገሩ፣ ከኢየሱስ የመስቀል ሥራ ጋር አነጻጽረው መናገራቸው በአደባባይ እየታወቀ፣ የኦርቶዶክስ ካራ ጀማ በአንድነት ተሰባስቦ፣ “ቤዛ ዐውድ አለው፣ እንኳን ማርያም ወ/ሮ ቤዛና ነቢይ ሙሴም ቤዛ ተብለዋል” ... የሚል ኢየሱስንና የመስቀሉን ሥራ በግልጥ የሚነቅፍ ምላሽ ሲሰጡ አየን። ከዚህ የሚከፋው ደግሞ፣ ማርያምን ያከበሩ ለማስመሰልና እውነተኞች ለመምሰል፣ ከእግዚአብሔር በላይ አድርገዋት ሲያቀርቡ ነው።

Thursday, 1 May 2025

ካራው “አቡነ” እንድርያስና “ዝክረ ኒቂያ” ስለ ወንጌላዊው አቡነ ገብርኤልና …!

 Please read in PDF

“የዝክረ ኒቂያ” ጉባኤ ትላንት ማምሻውን ማጠቃለያ ዐሳብና “የአቋም መግለጫ” በማውጣት ተጠናቅቆአል፤ “የመዝጊያ ንግግር” የሚመስል የካራ ትምህርት የተንሠራፋበትን ንግግር ያቀረቡት አቡነ እንድርያስ ናቸው፡፡ አቡኑ ገና ከጅማሬያቸው፣ “"ማርያም ቤዛዊተ ዓለም አትባልም የሚለው ስብከት ሕገ ወጥ ነው!" ማለታቸው እምብዛም አላስደነገጠኝም፤ ከዚህ የተሻለ ከነርሱ አልጠብቅምና፡፡ ነገር ግን በዚያ ኹሉ ንግግራቸው ማርያም ለኦርቶዶክስ አስፈላጊነቷን ደጋግመው ያጐሉትን ያህል፣ ክርስቶስ ኢየሱስን ደጋግመው ለማንሳት ይቅርና አንድም ጊዜ “እርሱ በርግጥ ቤዛና መድኃኒታችን ነው” አለማለታቸው እጅግ አስደንቆኛል፡፡

Sunday, 27 April 2025

ሚካኤል ስለ ሙሴ ሥጋ ከዲያብሎስ ጋር ለምን ተከራከረ?!

 Please read in PDF

ይሁዳ በመልእክቱ ውስጥ በሙሴ ሥጋ ምክንያት የሊቀ መላእክት ሚካኤልና የዲያብሎስ ክርክር መቅረቡን ይነግረናል። ስለ ሙሴ ሥጋ ጥቂት ብናነሣ፣ በዘዳ.  34፥5-6 እንደ ተጠቀሰው በሞዐብ ምድር እንደ ሞተና ከቤት ፌጎር አንጻር ባለው ሸለቆ ውስጥ እንደ ተቀበረ ይነግረንና የመቃብሩን ስፍራ ግን እስከ ዛሬ ድረስ የሚያውቅ እንደሌለም ይነግረናል።

Saturday, 26 April 2025

Furiin dhugaa Yasuus malee hinjiru!

 Please read in PDF

Jechoota gurguddoo dubbii Waaqummaa keessaa inni tokko Furii dha. Kakuu duraa keessatti qabeenyi lubbuudhaaf furii ta'e caqasameera (Fkn. 13:8); warri Israa'el lafa ykn mana isaani erga gurguratan booda furii gochuudhaan deebisifachuu danda'u ture (Leewo. 25:24-34). Raajiin Muuseen ummata Israa'el gabrummaa Gibxi jalaa sababa bilisa baaseef furii ykn bilisa baasaa ta'eera ykn jedhamee yaamameera. (Ho. Erg. 7:35).

የትክክለኛ ቤዛ መስፈርቱ ይኸው!

Please read in PDF

በአጭር ቃል ስብከት፣ “... እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤” (1ቆሮ. 1፥23) እና “ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤" 1ጢሞ. 1፥15) የሚለው ብቻ ነው። ቅዱሳን ሐዋርያትም፣ የስብከታቸው ማዕከል፣ "መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።” (ሐ.ሥ. 4፥12) የሚል ነበር።

Thursday, 24 April 2025

ሄኖክ ኃይሌ፣ “ሰባኪ” ከኾነ ከመጽሐፍ ለምን አይጠቅስም?

 Please read in PDF

ሄኖክ ሃይሌ፣ ለጳጳሱ አባ ገብርኤል በመለሰው መልስ ውስጥ እንዲህ የሚል ንግግር አለው፣

ያስተማሩት የታሰበበት ክህደት ነውና … ሙሴ ቤዛ በተባለበት መጽሐፍ ቅዱስ እያመኑ ድንግል ማርያም ቤዛ አትባልም ላሉት ጳጳስ ቅዱስ ሲኖዶስ ቤዛ ሲሆናቸው ማየት አንፈልግም። ጠንከር ያለ ቀኖናዊ እርምጃ እንጠብቃለን።”

ነገሩን ግልጽ ለማድረግ፣ ሙሴ “ቤዛ” የተባለበትን ዐሳብ፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ ማየቱ እጅግ መልካም ነው። በታላቁ መጽሐፍ ውስጥ በእስጢፋኖስ አንደበት፣

“ … ሙሴን በቍጥቋጦው በታየው በመልአኩ እጅ እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው።” (ሐ.ሥ. 7፥35)

ተብሎ ተጠቅሶአል። ስለ ሙሴ ጥቂት እንናገር፣ ሙሴ በግብፃዊቷ ልዕልት ቤት ያደገ ዕብራዊ ሰው ነበር (ዘጸአት 2፥1-10)። ለእኛ ባልተገለጠና የመጀመሪያው ዘገባ በማይገልጠው መንገድ፣ ሙሴ ሕዝቡን ከባርነት ነፃ ለማውጣት እግዚአብሔር እንደ ላከው ያውቅ ነበር (ሐ.ሥ. 7፥25)። በመጀመሪያ ሙከራው ሙሴ ዕብራዊውን እየደበደበ ያለውን ግብፃዊ ሰው ገደለ። በማግስቱ፣ እስራኤላውያን ረድኤቱንና ሥልጣኑን አለመቀበል ብቻ ሳይሆን ግድያውን እንደሚያውቁ ተገነዘበ። ፈርዖን ሳይገድለው ሙሴ ወደ ምድያም ምድር ሸሸ (ዘጸ. 2፥11–15)።

Wednesday, 23 April 2025

"ሊቃውንቱና መምህራኑ" እንዴት ከመጽሐፉ ተራራቁ?!

 

ደግሜ ቤዛ ለሚለው ቃል የተሰጠ ፍቺ ልጥቀስ፣ " ... ቤዛ ማለት፦ “... ካሣ፣ የደም ቤዛ፣ አንዱ ሰው የሰውን ደም ስለሚያፈስሰው ለውጥ ወይም ዋጋን፣ ገንዘብን፣ ካሣን መስጠት ወይም መዋጀት ማለት ነው።” ይላል የከሣቴ ብርሐን መዝገበ ቃላት። (ከሣቴ ብርሃን መዝገበ ቃላት፤  1951 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ ገፅ 532)። ጌታችን ኢየሱስ ስለ ቤዝወት በተናገረ ጊዜ እንዲህ አለ፣ "የሰው ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።" (ማቴ. 20፥28፤ ማር. 10፥45) ብሎአል።


Tuesday, 22 April 2025

“ነይ ነይ እምዬ ማርያም… ቤዛዊት ዓለም … ስህ-ተ-ት ነው” (አባ ገብርኤል)

Please read in PDF

ከሰሞኑ በጣም ያከራከረ አንድ ርዕሰ ጉዳይ አለ፤ ነገረ ቤዝወት። “ቤዝወት” ታላቅ ነገረ መለኮታዊ ዕሳቤን በውስጡ የያዘ አስደናቂ ቃል ነው። በብዙዎች አንደበት የሚጠቀስ ቃል ቢኾንም፣ ቃሉ በትክክል ስፍራውንና ትርጕሙን አጊኝቷል ብዬ ግን አላምንም። ጥቂት ስለ ቃሉ እናውጋ እስኪ!

ቤዛነት ምንድር ነው?

“ቤዛ” የሚለው ቃል፣ ከግዕዝ ቋንቋ የተወሰደ ሲኾን፣ ሰውን ከባርነት ነጻ ለማውጣት የሚከፈል ዋጋ ወይም አንድን  የተያዘን ወይም የተወሰደን ነገር ለማስመለስ የሚከፈል ዋጋን፣ ካሳን አመልካች ነው። ቤዛን የመክፈል ሥራ ደግሞ፣ ቤዛነት ተብሎ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጠቅሶአል። ቤዛነት፣ በበደለኛው ሰው የተወሰነውን ትክክለኛ ፍርድ ተመጣጣኙን ዋጋ ከፍሎ ነፃ ማውጣት ነው። ስለዚህም ቤዛ ማለት፣ “በቁሙ ዋጋ፣ ካሳ፣ ለውጥ፣ ምትክ፣ ዋቢ፣ ዋስ፣ መድን፣ ተያዥ … የመሰለው ኹሉ። [በደቂቅ አገባብ] ደግሞ፣ ስለ፣ ፈንታ፣ ምክንያት”[1] በማለት አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ያብራሩታል። ከዚህ በመነሣት፦

Sunday, 23 March 2025

በአጕል ትህትና ሥጋን አትጨቁኑ!

 Please read in PDF

መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ ቃል፣

“… ለዚህ ዓለም መርሕ ከክርስቶስ ጋራ ከሞታችሁ፣ ታዲያ በዚህ ዓለም እንደሚኖር ለምን ትገዙላቸዋላችሁ? “አትያዝ! አትቅመስ! አትንካ!” እንደሚሉት ዐይነት፣ እነዚህ ሁሉ በሰው ትእዛዝና ትምህርት ላይ የተመሠረቱ ስለ ሆኑ በተግባር ላይ ሲውሉ ጠፊ ናቸው። እነዚህ ነገሮች በገዛ ራስ ላይ ከሚፈጥሩት የአምልኮ ስሜት፣ ከዐጕል ትሕትናና ሰውነትን ከመጨቈን አንጻር በርግጥ ጥበብ ያለባቸው ይመስላሉ፤ ነገር ግን የሥጋን ልቅነት ለመቈጣጠር አንዳች ፋይዳ የላቸውም።” (ቈላ. 2፥21-23)

ይላል።

Saturday, 8 March 2025

12 ዓመታት በጡመራ መድረክ!

 

መልካሚቱም የአምላኩ እጅ በእርሱ ላይ ነበረችና” እንዲል፣ ጌታ እግዚአብሔር በመልካምነቱ ባለፉት አሥራ ኹለት ዓመታት በረድኤቱ በጽሑፍ እንዳገለግል ረድቶኛል። በነዚህ ጊዜያቶች ከእግዚአብሔር ልጅ ከክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ለመስበክ አልተመኘኹም፤ ሰብኬውም ገና አልጠገብኩትም፤ ኢየሱስ ጽዋዬና ርስቴ ነውና ከርሱ በቀር ሌላ ምንም አያጓጓኝም፤ እግዚአብሔር አለኝ፤ በቂዬ ነው!

Saturday, 1 March 2025

“ … ውስጣችሁ ግን ቅሚያና ክፋት ሞልቶበታል።” (ሉቃ. 11፥39)

 Please read in PDF

ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን ሲጽፍልን፣ ትኵረት ካደረገባቸው ታላላቅ መንፈሳዊ ነገሮች አንዱ፣ ድኾችን በተመለከተ ነው። በወንጌሉ ውስጥ ኢየሱስ ቤት አልባ ድኻ ነው (9፥58)፣ አገልግሎቱ አምነው በተከተሉት ሴቶች ይደገፍ ነበር (8፥3)፣ አገልግሎቱ ለድኾች ወንጌልን በመስበክ እንደ ኾነ ተናገረ (4፥18)፣ ቅድስት ድንግል ማርያም ድኻ እናት መኾንዋን በመሥዋዕት አቀራረቧ አሳየ (2፥24)፣ “የተራቡትን በበጎ ነገር አጥግቦአል፤” (1፥53) እንዲል፣ ድኾችን በብዙ እንደሚጐበኝና እንደ አልዓዛር ያሉ ድኾችን በሰማያት በብዙ ደስታ እንደሚያከበር ማስተማሩን ጽፎልናል (16፥19)፤ ይህ ብቻ ሳይኾን ሉቃስ፣ በኤልያስ ዘመን የነበረችውንም የሰራፕታዋንም ድኻይቱን መበለት አንስቶአል (4፥26)።