አይሁድ በምርኮ ዘመን መሥዋዕት የሚያቀርቡበት መቅደስ ስለ ፈረሰባቸውና፣ ወደ አገራቸውም ተመልሰው መሥራት ስላልተቻላቸው፣ በየጊዜው የሚገናኙበትንና ቃሉን በማንበብ፣ በመተርጐም የሚተጉበትን ምኵራብን መሥራት ጀመሩ። በምኩራብ ራቢ ወይም መንፈሳዊ መሪ ያለ ሲኾን፣ ሌሎች ደጋፊ ሰዎች ወይም ሠራተኞችን በተካተቱበት የሚመራ አነስተኛ ጉባኤ ነው።
Sunday, 24 March 2024
Sunday, 17 March 2024
የ“ነቢይ” ጥላሁን ነገረ ማርያም!
የ“ነቢይ” ጥላሁንን
የተወሰኑ ስብከቶችን የማድመጥ ዕድል አጊኝቼ አውቃለሁ፣ በኋላ ግን እርሱም “በግሉ” ወደ “ቸርች ከፈታ” ሲያዘነብል ተደንቄ
ራቅኹት። ከሰሞኑ ደግሞ ስለ ማርያም የተናገረውን አይቼ፣ የነዶክተር ወዳጄነህንና የነፓስተር ቸሬን መንገድ ለመከተል ምን
አደከመው? ብዬአለሁ። በስብከቱ መካከል ማርያምን (የጌታ ኢየሱስን እናት) “እየሰበከ” በመካከል እንዲህ ይላል፣
" ... የወንጌላውያን ጸሐፊዎች [አራቱ ወንጌላትን ማለቱ ነው]
የማርያምን ኹኔታ ስላላወቁና እርሷም ምናልባት አብራርታ ስላልነገረቻቸው እንጂ ... መለኮት ልትወልጂ ነው ሲላት …" ይላል፡፡
Tuesday, 12 March 2024
Friday, 8 March 2024
ኢየሱስ እስኪመጣ - ላለፉት አሥራ አንድ ዓመታት!
የማይዋሸውና (ቲቶ 1፥2)
በምሕረቱ ባለጠጋ የኾነ እግዚአብሔር (ኤፌ. 2፥4)፣ ነፍሴም ሕያው ወደ አደረጋት
ሕያው አምላክዋ ሳትመለስ (መክ.12፥7) ኢየሱስ እስኪመጣ ድረስ ዕንኾ፣ አሥራ አንድ ዓመታት በብሎግ(በጡመራ መድረክ) አገልግሎት
በጌታ ፊት አለኹ! በዚህ አጭር ዘመኔ ከእርሱ በቀር የረዳኝ፣ ያጸናኝ፣ ከፍ ከፍ ያደረገኝ፣ ሞገስ የሰጠኝ፣ ብርሃኑን ያበራልኝ፣
ስጠወልግ ያለመለመኝ፣ ስደክም መንገድ አቋርጦና አሳብሮ መጥቶ ያበረታኝ፣ እጆቼን ይዞ “አይዞህ!” ያለኝ ከጌታ በቀር ማንም የለም፤
ክብር ይኹንለት!
Thursday, 7 March 2024
መንፈሳዊውን ጾም እንጹም!
ጾም፣ በብሉይም ኾነ በአዲስ ኪዳን አማኞች ዘንድ፣ በጐላ መልኩ ሲተገበር የነበረ ደግሞም ያለ መንፈሳዊ
ልምምድ ነው። ጾም በአማኞች ሕይወት እንደ መለኮታዊ ተግሳጽ የሚፈጸም መንፈሳዊ አምልኮም ነው። በብሉይ ኪዳን ንስሐ ሲገቡ
(1ሳሙ. 7፥6)፣ ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ፣ ከእግዚአብሔር ዕርዳታ ለመፈለግ (ዘጸ. 34፥28፤ ዕዝ. 8፥21-23)፣ ራስን
በመንፈሳዊ ተግሳጽ ለመገሰጽና የኀጢአት ኑዛዜ በእግዚአብሔር ለማቅረብ መንፈሳውያን ሰዎች በግል (2ሳሙ. 12፥22) ወይም
በማኅበር (መሳ. 20፥26፤ ኢዩ. 1፥4) በእግዚአብሔር ፊት ይጾሙ ነበር!
Tuesday, 5 March 2024
ነገረ ሥላሴን የምናጠናበት ምክንያት (ክፍል ፱)
ካለፈው የቀጠለ …
- መንፈስ ቅዱስ፦ መንፈስ የኾነ (ዮሐ. 4፥24)፣ ፍጥረትን በመፍጠርና በውበት
በማጌጥ (ዘፍ. 1፥2)፣ ከርሱ በመወለድና አዲስ ልደትን ለአማኞች የሚሰጥ (ቲቶ 3፥5)፣ ኃይልን በማልበስና የጸጋ
ስጦታን ለቤተ ክርስቲያን በመስጠት ወይም በማከፋፈል (ዘካ. 4፥6፤ የሐ.ሥ. 1፥8፤ 1ቆሮ. 12፥7-11) በጽደቅ
ፍሬዎች በመሙላትና በመቀደስ በአማኞች ሕይወት ውስጥ የሚኖር (ዮሐ. 14፥17፤ 1ቆሮ. 3፥16፤ 6፥19፤ ገላ.
5፥22-23፤ ኤፌ. 2፥22)፣ አብሮን በጸሎት የሚቃትት (ሮሜ 8፥26)፣ ቅድስት ድንግል ወልድን በተለየ አካሉ በሥጋ
እንድትፀንስ በፈቃዱ ወድዶ የመጣ (ማቴ. 2፥11) የዘላለም እግዚአብሔር ነው፤ (ዕብ. 9፥14)።
Friday, 1 March 2024
ድንግል ማርያም የአሚናዳብ ሠረገላ?
“የዛሬን አያድርገውና” ዲያቆን ትዝታው ሳሙኤል፣ ለድንግል ማርያም “ከዘመራቸው ዝማሬዎች” መካከል “የአሚናዳብ
ሠረገላ” የሚል ይገኝበታል። ብዙ አገልጋዮች ከኦርቶዶክስ አገልጋይነታቸው ራሳቸውን አግልለው ወደ ወንጌል እውነት ሲመለሱ፣ አስቀድሞ
“ለፍጡራን በግልጥ የዘመሩትን ዝማሬ” በትክክል ስህተት መኾኑን አምነው፣ ንስሐ ሲገቡ አላየኹም፤ ምናልባት የገቡ ካሉና መግባታቸውም
እንደ ዝማሬያቸው አደባባያዊ ከኾነ እንዴት መልካም ነበር!
Monday, 26 February 2024
እግዚአብሔር ለአሕዛብም ግድ ይለዋል!
እግዚአብሔር የሰማይና የምድር ፈጣሪ ነው፤ “እነሆ፥ ሰማይ
ሰማየ ሰማያትም፥ ምድርም በእርስዋም ያለው ሁሉ የአምላክህ የእግዚአብሔር ነው።” (ዘዳግ. 10፥14) እንዲል፣ ከእግዚአብሔርና ለእግዚአብሔር ያልኾነ ፍጥረት ፈጽሞ የለም። በአዲስ ኪዳንም፣
“እርሱ[እግዚአብሔር]
በክፎዎችና በበጐዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።” (ማቴ. 5፥44-45) በሚለው ንግግሩ እግዚአብሔር ለመላለሙ ግድ ይለዋል።
Tuesday, 13 February 2024
ነገረ ሥላሴን የምናጠናበት ምክንያት (ክፍል ፰)
ካለፈው የቀጠለ …
5.2. ሥላሴ
ምግባራዊ ሦስትነት (Economic Trinity) አላቸው፦
በሌላ ንግግር አብ ከወልድ ወይም ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያለውን ዐይነት ግንኙነት፣ ከፍጥረት
ጋርም እንዲያ ያለ ግንኙነት የለውም። በሥላሴ መካከል ያለውን ኅብረትና አንድነት የሚያመለክተው ግንኙነት፣ ምግባራዊ ሦስትነት
(Economic Trinity) ተብሎ ይጠራል። በዚህ ረገድ የሥላሴ እያንዳንዱ አካል በመለኮታዊ ማንነቱ ፍጥረትን በመፍጠር፣
በመመገብ፣ በልዕልና በመምራት፣ በሥልጣን፣ በአገዛዝ፣ በማዳን በሚሠሩት መለኮታዊ ሥራዎች ያላቸውን ፍጹም አንድነት የሚያመለክት
ነው።
Friday, 19 January 2024
“እያጠመቃችኋቸው፥ … እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤” (ማቴ. 28፥20)
ለቤተ
ክርስቲያን ከተሰጡ ሐዋርያዊ ተልእኮዎች ውስጥ፣ ቀዳሚውና የዘወትር ተግባር “አማኞችን ደቀ መዛሙርት ማድረግ” ነው። እንደ
ጌታችን ትምህርት፣ አማኞች ደቀ መዛሙርት የሚኾኑት፣ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሲጠመቁ፣ ጌታ ያዘዘውን ኹሉ እንዲጠብቁ
ሲማሩ፣ እንዲሁም በመታመን እርሱን ለመከተል ደቀ መዛሙርት በሕይወት ሲኾኑ ነው።
Thursday, 18 January 2024
“ከእኛ ጋር ለምን አስተካከልሃቸው?” (ማቴ. 20፥11)
ጌታችን ኢየሱስ መንግሥተ ሰማያት ምን እንደምትመስል በሰጠው ውብ ምሳሌ፣ እግዚአብሔርን የወይኑ እርሻ ባለቤት አድርጎ ያቀርበዋል። የእርሻው ባለቤት በአትክልቱ ስፍራ ሰውን ለመቅጠር ፈልጎ ጥሪ አቀረበ። በጥሪው መሠረት ሠራተኞቹ፣ አንድ ዲናር ሊከፈላቸው ተስማምተው ወደ እርሻው ቦታ መጡ። የሥራው ሰዓትም ከማለዳ 12 ሰዓት እስከ ምሽት 12 ሰዓት ነበር።
Wednesday, 17 January 2024
ነገረ ሥላሴን የምናጠናበት ምክንያት (ክፍል ፯)
ካለፈው ቀጠለ …
5. የቅድስት ሥላሴ ትምህርት ምስጢር ነው!
ትምህርተ ሥላሴ ምስጢር ነው ስንል፣ ምን ማለታችን ነው? ብንል፣ ለሰው ያልተገለጠ ብዙ ትምህርት ወይም ብዙ ነገር አለ ማለታችን ነው። ኾኖም ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ሦስቱን አካላት ለማጥናት ብዙ ትምህርት እንዳለ ልንዘነጋ አይገባም። በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ትምህርቶች ምስጢር ተብለዋል፤ ለምሳሌ፦ ጌታችን ኢየሱስ፣ ለደቀ መዛሙርቱ፣ “ለእናንተ የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፥ ለእነርሱ ግን አልተሰጣቸውም።” ሲል (ማቴ. 13፥11)፣ ምሳሌዎቹ የተነገሩት በሕዝቡ ኹሉ ፊት ቢኾንም፣ ትርጕማቸው ወይም ምስጢሩ ግን የተነገረው ለደቀ መዛሙርት ብቻ ነው።
Thursday, 11 January 2024
Sagantaa Addaa Ayyaana Yaadannoo Dhaloota Kiristoos!
Saturday, 6 January 2024
ከባሪያዪቱ የተወለደ ንጉሥ!
የክርስትና ትምህርት ከደመቀበትና ከተንቈጠቈጠበት ቀዳሚው እውነት አንዱ፣ የእግዚአብሔር
ልጅ በእርሱ የሚያምኑትን ኹሉ በጸጋ የእግዚአብሔር ልጆች ያደርግ ዘንድ የሰው ልጅ መኾኑ ነው። እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ ኾኖ፣
ዓለማትን የፈጠረና ደግፎም
የያዘ ወይም ዓለሙ ተያይዞ የቆመው (ዮሐ. 1፥3፤ ቈላ. 1፥17፤ ዕብ. 1፥3) በእርሱ በታላቁ አምላክ ቢኾንም፣ በተለየ አካሉ ከባሪያዪቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም (ማቴ. 1፥21፤ ዮሐ. 1፥14)
ሥጋን ነሥቶ ተወለደ።
Monday, 1 January 2024
መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፳፯)
ካለፈው የቀጠለ …
ባለፈው “የመድሎተ
ጽድቅ” ጸሐፊ፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ (Exegesis) ሳይኾን ወደ መጽሐፍ ቅዱስ (Eisegesis) እንደሚተረጕም አንድ ምሳሌ አንስተን
ነበር። ዛሬ በድጋሚ ኹለተኛ ምሳሌ በማንሳት በዚህ ርዕስ ሥር ያለውን ዐሳብ እንቋጫለን።











