መጥምቁ ዮሐንስንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን
ከሚያመሳስላቸው የስብከት ርዕሶች ቀዳሚው፣ “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ” የሚለው መንግሥተ ሰማያዊ አዋጅ ነው።
ቅዱስ ማቴዎስ ስለ መጥምቁ ዮሐንስ ሲናገር፣ “በዚያም ወራት … በይሁዳ ምድረ በዳ እየሰበከ መጣ። የስብከቱም ማዕከል
የእግዚአብሔር መንግሥትና ንስሐ ነበር። “ንስሐ” ድርጊታዊ ትርጒሙን ስንመለከት፣ “መመለስ” ማለት ነው። ይህም ከክፉ ድርጊቶች
ኹሉ መመለስ፣ ክፉ ድርጊትን ኹሉ መተው፣ ከክፉ መንገድ ኹሉ ዘወር ማለትና ወደ ክርስቶስ መመለስ የሚል ትርጒምን የያዘ ነው።











