በእግዚአብሔር ቃልና በእግዚአብሔር መንፈስ ተፈጥሮ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንደ ሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ ያለውን ተሐድሶን ለማጥፋት እንዴት ይቻላል? የሚለው ጥያቄ፣ የብዙ ዓመታት ጥያቄ ነው፤ ከታሪክም ኾነ በዚህ ዘመን እየኾነ ካለው እውነታ እንደምንረዳው አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናትና ግለሰቦች ተሐድሶ እንዲጠፋ ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን እንዴት ሊያጠፉት እንደሚችሉ አያውቁም። ለምሳሌ፦ በአገራችን ታሪክ በአባ እስጢፋኖስና በተከታዮቹ ደቂቀ እስጢፋኖስ ላይ በኢትዮጵያውያን ነገሥታትና ጳጳሳት በተለይም በዐጼ ዘርዓ ያዕቆብ የተፈጸመውን ግፍ፣ ከአውሮፓ ታሪክም በአሥራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን በተነሣው የተሐድሶ እንቅስቃሴ ላይ ከካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የተደረገውን ተቃውሞ ማንሳት ይቻላል።
Sunday, 20 November 2022
Saturday, 5 November 2022
መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፳፪)
ምጽዋት የናቡከደነጾርን በደል
ደመሰሰን?
1.1.3. “… ልዑሉም በሰዎች መንግሥት ላይ እንዲሠለጥን፥ ለሚወድደውም እንዲሰጠው
እስክታውቅ ድረስ ከሰዎች ተለይተህ ትሰደዳለህ፥ መኖሪያህም ከምድር አራዊት ጋር ይሆናል፥ እንደ በሬም ሣር ትበላ ዘንድ
ትገደዳለህ፥ በሰማይም ጠል ትረሰርሳለህ፥ ሰባት ዘመናትም ያልፉብሃል። የዛፉንም ጉቶ ይተዉት ዘንድ ማዘዙ፥ ሥልጣን ከሰማያት
እንደ ሆነ ካወቅህ በኋላ መንግሥትህ ይቆይልሃል። ንጉሥ ሆይ፥ ስለዚህ ምናልባት የደኅንነትህ ዘመን ይረዝም እንደ ሆነ ምክሬ
ደስ ያሰኝህ፤ ኃጢአትህንም በጽድቅ፥ በደልህንም ለድሆች በመመጽወት አስቀር። ይህ ሁሉ በንጉሡ በናቡከደነፆር ላይ
ደረሰ።” (ዳን. 4፥25-28)።
Saturday, 29 October 2022
መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፳፩)
የመድሎተ “ጽድቅ” ጸሐፊ፣ የመጽሐፍ ቅዱስን ሥልጣን በግልጥ በመቃወም፣ ሌሎችን
መጻሕፍት ከቅዱሳት መጻሕፍት ጋር ለማስተካከል የሄደበትን ሩቅ መንገድና እንዲሁም ቅዱሳት መጻሕፍትን አጥምሞ ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ
ቃላትን እንደ ገና በመተርጐም በመጽሐፉ ውስጥ እንዴት እንዳስገባ በጥቂቱ በማሳየት፣ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣን ያለንን ዐሳብ እንቋጫለን፤
የ“መድሎተ ጽድቅ” ጸሐፊ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣንን ከተቃወመባቸው ወይም ከሻረባቸው መንገዶች ጥቂቶቹን እናንሳ፦
1. ያላለውን እንዳለ አድርጎ በማቅረብ፦ የመጽሐፍ ቅዱስን ሥልጣን የሚቃወሙ አካላት ከሚፈጽሟቸው ግልጽ ስህተቶች አንዱ፣ የመጽሐፉን ዐውድ በመጣስ ያልተናገረውን
እንደ ተናገረ አድርጐ ማቅረብ ነው። የ“መድሎተ ጽድቅ” ጸሐፊ በዚህ ረገድ ለምሳሌ፦
Thursday, 20 October 2022
ተሐድሶ፣ በማኅበረ ቅዱሳን አደባባይ!
ስለ “አጥማቂ” ግርማ ወንድሙ፣ በተደጋጋሚ ጠንቋ ይነቱን፣ በመቍጠሪያ ላይ
ባስደገመው ድግምት እንደሚሠራና ሰዎችን ማሳበድ እስከሚያደርስ በሽታ ላይ እንደሚጥል በተደጋጋሚ ጽፈናል፤ አስጠንቅቀናል። ነገር
ግን የዚያኔ አሰምተን ጮኸን ስንናገር እኛን እንደ መና ፍቅና ሐሰተኛ እንጂ ማንም “አሜን” ብሎ ሊቀበለን የወደደ አልነበረም።
Tuesday, 11 October 2022
“ባዕዱ ወንጌል 2”ና ግለ ምልከታዬ!
ባዕድ 2 - ሌላ ኢየሱስ (የሐሰተኛ አስተማሪዎች ኢየሱስ - በቅዱስ ቃሉ
ሲፈተሽ) ወይም “Baed Documentary Film” የሚለውን ዘጋቢ ፊልም ተመልክቼዋለሁ። የብልጽግና ወንጌል ለእውነተኛዪይቱ
ቤተ ክርስቲያን ፈተናና ከባድ ተግዳሮት ሊኾን እንደሚችል ጥያቄ የሚያስነሳ ጉዳይ አይደለም። በዚህ ረገድ እኔም የድርሻዬን
ለመወጣት በ2010 ዓ.ም “የእምነት እንቅስቃሴ - የዛሬዪቱ ቤተ ክርስቲያን ፈተና” በሚል ርዕስ፣ የእንቅስቃሴውን አደገኛነትና
በተለይም በተሐድሶአውያን መካከል በነበጋሻው ደሳለኝ አማካይነት ማቆጥቆጡን ተመልክቼ ተቃውሜ ጽፌአለሁ።
Friday, 7 October 2022
መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፳)
ከያዝነው ርዕስ ጋር በሚስማማ መልኩ፣ የ“መድሎተ ጽድቅ” ጸሐፊ፣ ሮሜ 8፥34ን ለመተርጐም በተጠቀመበት መግቢያ ላይ እንዲህ ይላል፤
“በአዲስ ኪዳን የተጻፉ መጸሕፍት ኹለት ነገሮችን ታሳቢ ማድረግ አለባቸው። መጽሐፍ ቅዱስን የምትተረጕመው ቤተ ክርስቲያን
ናት። መጽሐፉ ይህ ነው ብላም ለይታ፤ ሰፍራ፤ ቈጥራ የሰጠችውም ቤተ ክርስቲያን ናት። ቤተ ክርስቲያን ናት መጽሐፍ ቅዱስን የሠራችው
እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያንን አልሠራም።”[1]
እንግዲህ አስቀድመን እንደ ተናገርን፣ ይህ የ“መድሎተ ጽድቅ” አቋም ወይም አስተምኅሮ
የካቶሊክ እንጂ የኦርቶዶክሳውያን አቋም አይደለም። ጸሐፊው ግን የካቶሊክን አስተምኅሮና እምነት በግልጥ እንደ ኦርቶዶክስ አስተምኅሮ
ሲያቀርብ እንመለከተዋለን። ይህን ግልጥ መስመር መለየት ባልቻለበት ኹኔታ፣ ማለትም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥልጣንን ከቤተ ክርስቲያን አሳንሶ
ማቅረብ፣ መድሎተ ስሑትነቱን በግልጥ ያሳያል።
Sunday, 2 October 2022
አእመረ አሸብርና ብልጠታዊ ቋንቋው!
አእመረ አሸብር፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቲቪ ላይ
ያደረገውን የክፍል አንዱን ቃለ መጠይቁን አድምጬዋለሁ። እጅግ ሊደንቀኝ በሚችል መልኩ፣ ቃለ መጠይቁን ያደረገው ሰው ደጋግሞ
ላነሳቸው ግልጽ ጥያቄ አእመረ አለመመለሱ ሳይኾን፣ ጠያቂው ጨርሶ ለማመን አለመቻሉ፣ ከአእመረ ይልቅ ጠያቂውን እንዳምነው ግድ
ብሎኛል።
Friday, 30 September 2022
Dubbi Ateetee warra Waaqefannaa Gabaabinaan!
“ Waaqtaanummaa – Waaqefannaa fi
Kiristaanummaan maal waliif ta’u? mata duree jedhuun kitaaba dhiyootti
maxxansiisu irraa kan fudhatame.
“… Ateeteen mallattoo ykn mallattoo aadaa qofaati
yaada jedhu irraa ni darba. Hawaasa Oromoo keessatti dhugummaa hawaasichaatiin
alatti mallattoo waaqefachuus ni qaba.[1] Ateeteen mallattoo firii,
hortee, kabaja haadhummaa ti. Ateetee dubartiin takka kabaja olaantummaa
hafuuraa keessatti kenna fudhatamummaa hortee kan kennituu dha. Humna nageenya waaqummaa dubarti,[2]
ykn ayyaana dubartootaa fi[3]
waggootti yeroo tokko kan kabajamtu yoo ta’u; sababni kabajaas gadaamessaa fi eebba
firii gadaameessaa (goddess of fertility) waaq eebbistu jedhamee ti.[4] Dubartootnis ateeteedhan
waa’e fayyaa fi hortee ni kadhatu.
የዋቄፈና ነገረ አቴቴ በአጭሩ!
“ዋቄስትና - ዋቄፈናና ክርስትና ምንና ምን ናቸው?” ከሚለውና በቅርብ
ከሚታተመው መጽሐፌ የተወሰደ!
“… አቴቴ ለምልክትነት ወይም የባህሉ ምልክት ብቻ ከመኾን ያልፋል፤ በኦሮሞ
ማኅበረ ሰብ ዘንድ ከማኅበራዊ እውነታነቱ ባሻገር አምልኮአዊ ምልከታዎች አሉት።[1] አቴቴ የፍሬያማነት፣ የወላድነት፣
የእናትነት ክብር መገለጫ ናት። አቴቴ ሴት ልጅ በመንፈሳዊ ልዕልናና ክብር ውስጥ የመውለድን ሞገስ እንድታገኝ ጸጋ የምትሰጥ
ናት። ሰላማዊ የሴት መለኮት ኃይል[2]
ወይም የሴቶች መንፈስና[3]
በዓመት አንድ ጊዜ የምትከበር ሲኾን፣ የመከበርዋም ምክንያት የማኅፀንና የፅንስ ባርኮትን (goddess of fertility)
ባራኪ አማልክት ናት ተብሎ ነው።[4] ሴቶችም አቴቴን ስለ ጤናና ስለ መውለድ
ይለማመናሉ።
Monday, 26 September 2022
ከዕጸ መስቀሉ ወደ ተሰቀለው ፊታችሁን አቅኑ!
በዚህ ሳምንት ከሚከበሩት በአላት አንዱ፣ ጌታችን ኢየሱስ ተሰቅሎበታል የተባለው፣ የዕጸ መስቀሉ በአል ነው። የሚከበርበት ምክንያት በአጭሩ ሲገለጽም፣ አይሁድ በጥላቻ ኢየሱስ የተሰቀለበትን መስቀል ከቆሻሻ መጣያ ቦታ ወስደውት ስለ ቀበሩት፤ ይህን የተቀበለውን መስቀል ከዓመታት በኋላ በአንድ ሰው መሪነት የቆስጠንጢኖስ እናት የኾነችው ከዓመታት ፍለጋ በኋላ፣ የተቀበረውን የእንጨት መስቀል እንዳወጣችና በአሉም ከዚህ ጊዜ ጀምሮ መከበር እንደ ጀመረ ይተረካል።
Saturday, 24 September 2022
ጳጳሳት ባሉበት ጉባኤ የሴት አገልግሎት!
በአንድ ወቅት አቡነ መርሐ ክርስቶስ ባሉበት ጉባኤ፣ አንዲት “ዘማሪ” ስለ ተክለ ሃይማኖት፣ “ባለ ስድስት ክንፉ” ብላ ስትዘምር፣ “ሰውየውን ወፍ አደረገችው” ብለው አሳፍረው አስቀምጠዋታል ይባላል። በርግጥ የአደባባይ ስህተት አደባባይ ላይ መታረም አለበት፤ አግባብም ነው! በዚህ ረገድ አቡነ መርሐ ክርስቶስ ብዙ መልካም ምሳሌነት አላቸው።
Sunday, 18 September 2022
“ጳጳስ፣ የማይነቀፍና የአንዲት ሚስት ባል ሊኾን ይገባዋል!”
አባቶቻችን ሐዋርያት በነበሩበት
ዘመን ሳይፈቱት የቀረ ችግር፣ ረስተው የተዉት ነገር የለም። በመልእክታቸው ተጽፎ የምናገኘው እምነታቸውን ደግሞም የእምነታችውን
ሥርዓት ነው። በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ ውሳኔ ሰጥተዋል። ከእነዚህ ውሳኔዎች አንዱ የጵጵስና ጉዳይ ነው። ጳጳስ መኾን ያለበት ምን
ዓይነት ሰው ነው? እኛ የሐዋርያትን ውሳኔ ላለመቀበል ቃላትን በመሰንጠቅ ትርጉምን ማጣመም ውስጥ ካልገባን በስተቀር፣ እውነቱን
በቀጥታ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እናገኘዋለን።
“ማንም ኤጲስ ቆጶስነትን ቢፈልግ መልካምን ሥራ ይመኛል የሚለው ቃል የታመነ ነው። እንግዲህ ኤጲስ ቆጶስ እንዲህ ሊኾን ይገባዋል፤ የማይነቀፍ፥ የአንዲት ሚስት ባል፥ ልከኛ፥ ራሱን የሚገዛ፥ እንደሚገባው የሚሠራ፥ እንግዳ ተቀባይ፥ ለማስተማር የሚበቃ፥ የማይሰክር፥ የማይጨቃጨቅ ነገር ግን ገር የኾነ፥ የማይከራከር፥ ገንዘብን የማይወድ፥ ልጆቹን በጭምትነት ሁሉ እየገዛ የራሱን ቤት በመልካም የሚያስተዳድር፤ ሰው ግን የራሱን ቤት እንዲያስተዳድር ባያውቅ፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን እንዴት ይጠብቃታል?” (1ጢሞ. 3፥1-5)።
Saturday, 10 September 2022
በዘመናት የሸመገለው “የሰው ልጅ”!
ከሰማይ በታች ያለው መላለም(መላው ዓለም) አንድ ቀን ወይም በጌታ ቀን፣ በታላቅ ድምጽ፣ በትኵሳትና በመቅለጥ ሊያልፍ ቀን ተቀጥሮለታል፤ መጽሐፍ፣ “በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፥ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይቀልጣል፥ ምድርም በእርስዋም ላይ የተደረገው ሁሉ ይቃጠላል።” እንዲል (2ጴጥ. 3፥10)። ሰማይና ምድር የሚያልፍበት ኹኔታ፣ የሰው ልጆች ኹሉ ሥራ በእግዚአብሔር ፊት የሚመረመርበት ወይም የሚታይበት መንገድ እጅግ አዳጋችና ኹኔታውን ለመግለጥ የሚያስቸግር እንደ ኾነ ይታመናል፤ ለጌታ ግን ኹሉ ይቻላል!
Thursday, 1 September 2022
መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፲፱)
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣን የእግዚአብሔር
የራሱ ሥልጣን ነው ስንል፦
1.
ቃሉ የእግዚአብሔር ነው፦ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ስለ
ኾነ፣ ለቤተ ክርስቲያና መሠረትና ዓምድዋ ነው። ቃሎቹ የእግዚአብሔር ባሕርይ ገንዘብ አድርገዋልና፣ መጽሐፍ ቅዱስ አይለወጥም (ማቴ.
5፥17)፤ ልብን ኹሉ ይመረምራል (ዕብ. 4፥12)፣ ይቀድሳል (ዮሐ. 17፥17)፤ ይፈውሳል (መዝ. 107፥20)።
Sunday, 21 August 2022
ስለ ኹለቱ መጻሕፍቴና አዲሱ መጽሐፌ ጥቂት ነገር!
ከአኹን ቀደም ኹለት መጻሕፍት በዕቅበተ እምነት ዙሪያ አሳትሜአለሁ፤ በአጭሩ፣ የመጀመሪያውን መጽሐፍ በአብዛኛው ያሰራጨኹት በማኅበራዊ ሚድያ ለምተዋወቃቸው ወንድምና እህቶች ነበር፤ ነገር ግን ከ2000 ኮፒ ውስጥ መጽሐፉን ለማሳተም ተበድሬ ለመክፈል፣ በዕዳ ካስያዝኩት 800 መጻሕፍት ውጭ፣ ካከፋፈልኩት ከ406 በላይ የሚጠጉት መጻሕፍት ቢሸጡም፣ የተሸጡበት ብር ግን ለእኔ አልደረሰኝም። ኹለተኛው መጽሐፌ ደግሞ ገና በስርጭት ላይ ነው። በጽሑፍ ዓለም አሳትሞ፣ መልሶ ማሰራጨት እጅግ ከባድና ፈታኝ ሥራ ነው።













