Friday, 8 January 2021
Monday, 4 January 2021
Wednesday, 30 December 2020
መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፫)
ካለፈው የቀጠለ …
·
ኀጢአት
በመጽሐፍ ቅዱስ ኀጢአት
ወይም ኀጢአትን ማድረግ አንድና ወጥ ትርጉም ያለው ብቻ አይደለም፤ በተለይ በአዲስ ኪዳን ውስጥ በአምስት በተለያዩ መንገዶች ተገልጦ
እንመለከተዋለን፤
1.
ሃማርቲያ[ሺያ]፦ (ዒላማን መሳት)፦ ይህ ቃል በአዲስ
ቃል ውስጥ ኀጢአት ወይም ኀጢአተኛ ተብሎ ከ250 ጊዜ በላይ ተጠቅሶአል፤ ትርጕሙም እግዚአብሔር ወዳቀደላቸው ዓላማና ግብ ኀጢአትን
በማድረግ፣ በገዛ ፈቃዳቸው ወይም ምርጫቸው ባለመድረሳቸው አዳምና ሔዋን[የሰው ልጆች] ዒላማ መሳታቸውን የሚያመለክት ነው፤ እግዚአብሔር
ወዳሰበላቸውና ወዳቀደላቸው ዐሳብና ክብር አልደረሱምና ከእግዚአብሔር ክብር ጎደሉ (ማቴ. 9፥2፤ ዮሐ. 1፥29፤ ሮሜ 3፥23)።
Saturday, 26 December 2020
ውርርዱ በገብርኤል አልነበረም!
መግቢያ
በመጽሐፎቻቸው ምዕራፍ ብዛት ዓበይት ነቢያት ተብለው ከሚጠሩት አንዱ፣ የነቢየ እግዚአብሔር
የዳንኤል ትንቢት መጽሐፍ ነው። የመጽሐፉ ጸሐፊ ራሱ ለመኾኑ በራሱ በትንቢት መጽሐፉ ውስጥና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ምስክርነት አለ (9፥2፤ 10፥2፤ ማቴ. 24፥15ን ከዳን. 9፥27 እና 11፥31 ጋር ያስተያዩ)። የዳንኤል መጽሐፍ ዋና
ሃሳብ ወይም ሊነግረን የወደደው እግዚአብሔራዊ መልእክት፣ የእግዚአብሔርን ሉዓላዊ ጌትነትና ድል ነሺነቱን ለማሳየት ነው።
እግዚአብሔር ሉዓላዊ ጌታ ስለ ኾነ፣ “ልዑል አምላክም በሰዎች መንግሥት ላይ የወደደውን ያሰለጥናል” (5፥21)።
Wednesday, 23 December 2020
መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፪)
መግቢያ ፪
የ“መድሎተ ጽድቅ” ጸሐፊ ሰጊጎት
የሠራባቸው ቃላት
ካለፈው የቀጠለ …
ቀጥታ ወደ መጽሐፉ ምዘና
ከመሄዳችን በፊት፣ በመጽሐፉ ውስጥ ከመጽሐፍ ቅዱስና ከአማናዊት ኦርቶዶክሳዊት[1] እምነት ወይም
እይታ ውጪ፣ ትርጉም ስለ ተሰጣቸው ቃላት መመልከቱ እጅግ ጠቃሚ መስሎ ታይቶናል። በተለይም በመግቢያ ላይ ካለው፣ ከመዳን ትምህርት
ጋር ተያይዘው የተነገሩትን ቃላት መመልከት፣ ብዙ ሳንደክም የ“መድሎተ ጽድቅን”፣ መድሎተ ስሑትነት በሚገባ እንድናስተውል ይረዳናል።
ጸሐፊው ቃላትን በማጣመም ለራሱ ትምህርት ተጠቅሞባቸዋል። እንዲያውም በአንዳንድ የነገረ መለኮት ቃላት ላይ አንዳች ግንዛቤ የለውም
ወይም ኾን ብሎ ያምታታል።
Monday, 21 December 2020
“ዲያቆን” ሄኖክ ሃይሌና አዲሱ ኑፋቄው!
“እመቤታችን ማማለድ አይደለም አፍርሳን
መሥራት ትችላለች” [እውነት?!]
“ማንም የእግዚአብሔርን
ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ።” (1ቆሮ.
3፥17)
ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ውስጥ፣ ቅዱስ ቃሉ የሚናገረውን ብቻ መናገር ኑፋቄነት፣ ቅዱስ ቃሉ የማይለውን መናገር ደግሞ አማኝነት ወይም “የቤት ልጅ”
የሚያስብለው ተግባር ከኖረ ሰነባበተ። ለቅዱሳን መላእክትም ኾኑ ሰዎች፣ “ቃሉ ከተናገረው በላይ መናገር ትክክል አይደለም፣
የተነገረው ብቻ ሊነገርላቸው ይገባል” ስንል፣ “ጸረ ቅዱሳን፣ ጸረ ማርያም፣ ጸረ መላእክት …” የሚል ስድብ ያስቀጥላል። ነገር
ግን ለቅዱሳን፣ ቅዱስ ቃሉ የሚናገረውን ብቻ አለመናገር የቅዱሳኑ ጠላቶች መኾናቸውን በቅዱስ ቃሉ ላይ ጨምረው ተናጋሪዎቹ
ያስተዋሉ አይመስሉም።
Wednesday, 16 December 2020
መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፩)
መግቢያ
እውነተኛ መድሎተ
ጽድቅ ወይም የእውነት ሚዛን መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው። “መሠረቱ የጌታችንና እርሱ አድሮባቸው ቀድመው ትንቢት የተናገሩ የነቢያት
በኋላም ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው የተረጐሙና ያስተማሩ የሐዋርያት ትምህርት ነው። ከዚህ ውጭ አልተንቀሳቀሱም።”[1] ራሱ የ“መድሎተ ጽድቅ” ጸሐፊ፣ “ቅድስት
ቤተ ክርስቲያን ከማንኛውም መጽሐፍ በላይ ምንም ሊነጻጸርና ሊወዳደር በማይችል መልኩ አክብራና አልቃ የምታምነው መጽሐፍ ቅዱስን
ነው” በማለት ቢመሰክርም፣ ለዚህ ታላቅ እውነት ግን ጸሐፊውም ኾነ ቤተ ክርስቲያኒቱ ተግባራዊ ምላሽ ሲሰጡ አይስተዋልም።[2]
Monday, 14 December 2020
“ዘማሪት” ትርሃስና “ወደ ኋላ አልልም ከእንግዲህ” የሚለው መዝሙሯ!
“አልወጣሁም እያልሽኝ ነው፤ … እያልሽ ያለው ነገር ግን እየተዋጠልኝ አይደለም፤ እየተቀበልኹትም አይደለም … ” ይህን
የተናገረው ቃለ መጠይቅ ያደረገላት ልጅ ነው፤ ጌታ ኢየሱስን የሚያፍሩበት ኹሉ እንዲህ ሊዋረዱና ሊያፍሩ ይገባቸዋል! በልጁ የሚያፍር፣
በምድር ማንም ባያምነውና “ንግግርህ አይዋጥልኝም” ቢለው ትክክል ነው፤ ትርሃስ እንዲህ ስትባይ ምን ተሰምቶሽ ይኾን? በኢየሱስ
አፍረሽ ማን እንዲመሰክርልሽ ወደሽ ነበር?!
Wednesday, 9 December 2020
Monday, 30 November 2020
ጽዮን፣ ታቦትን አይወክልም!
መግቢያ
በኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር አሳታሚነት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዕሥራ ምዕት(አዲሱ ሚሊኒየም) ላይ “የራስዋን” አዲስ መጽሐፍ ቅዱስ አሳትማለች። መጽሐፉ በተለምዶ “ሰማንያ
አሐዱ” ተብሎ የሚጠራ ቢኾንም፣ ነገር ግን አያሌ ግልጽ ስህተቶችን በውስጡ እንደ ያዘ ወይም እንዲይዝ ታስቦበት የታተመ መጽሐፍ
ቅዱስ ነው። በተለይም በግልጽ የተቀመጡና የታወቁ ሐረጋትን በመቀየር ድፍረት ያለበትን ስህተት ሠርቶአል። ከሠራቸው ስህተቶች
አንዱም የእግዚአብሔርን ታቦት ለግል ዓላማቸው ከእግዚአብሔር ይልቅ ለማርያም[ለታቦተ ጽዮን] ለመስጠት በሚመች መንገድ ወደ ሴት
ጾታ መለወጣቸው ነው።
Wednesday, 25 November 2020
በኢየሱስ የሚያፍሩ የማርያም ባርያዎች!
መግቢያ
ተአምረ ማርያምን የስህተት መጽሐፍ ከሚያሰኘው እልፍ ነገሮች አንዱ፣ “ፍጥረት ሁሉ እመቤታችንን
ለማመስገን ተፈጠረ፣ የእመቤታችን ክብሯ ምስጋናዋ ሁሉ ተጽፎ ቢኾን ምን ብራና በቻለው ነበር፣ የቤተ ክርስቲያን ልጆች እርስዋን
አክብሯት ለእናንተ ለኀጥአን መድኀኒታችሁ ናትና …” የሚሉ ሐረጋትን በመጠቀም፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ከምናውቃት ከኢየሱስ እናት
ማርያም በተቃራኒ፣ እንግዳና ልዩ የኾነችውን፣ አምልኮ ወዳድዋን ማርያምን ለመሳል በብርቱ በመጣሩ ነው። ይህ ላይደንቅ ይችላል፤
ነገር ግን ወንጌል ተረዳን፣ መጽሐፍ ቅዱስ አነበብን፣ እንዘምራለን፣ እንሰብካለን፣ ዐሰረ ክህነት አለን … የሚሉቱ ከተአምረ
ማርያም ያነሰ እውቀት መያዛቸው፣ ጌታችን ኢየሱስ በናዝሬት ሰዎች የተደነቀውን ያህል እኛም እጅግ እንደነቅባቸዋለን።
አለማመናቸው በእውነት ያስደንቃል!
Tuesday, 24 November 2020
Monday, 16 November 2020
“ንስሐ ባትገቡ ሁላችሁ እንደዚሁ ትጠፋላችሁ” (ሉቃ. 13፥5)
ሉቃስ
ወንጌላዊው በቅዱስ ወንጌሉ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ለመላለሙ የመጣ መድኀኒት” እንደ ኾነ በስፋት ይጽፍልናል (2፥14፤
3፥3፤ 9፥52፤ 10፥33)። “ሥጋም የለበሰ ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን ያይ” ዘንድ ሰው ኹሉ ንስሐ ይገባ
ዘንድ ጌታችን ኢየሱስ በየመንደርና ከተሞች እየተዘዋወረ ማስተማሩን ደጋግሞ ይነግረናል። “መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም
የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥” እንዲል፤ (ሐዋ. 10፥38)።
ሉቃስ በወንጌሉ ትኵረት ከሰጣቸው ትምህርቶች አንዱ ደግሞ ንስሐና የክርስቶስን ፍጹም ርኅራኄ ነው፤ በተለይም ደግሞ ማኅበረ ሰቡ ፍጹም ስላገለላቸው ኀጢአተኞች፣ ቀራጮች፣ ሳምራውያን (7፥36፤ 9፥52፤ 10፥33፤ 15፥1፤ 19፥5)፣ ከራሱ ጋር ለተሰቀለው ወንበዴ (23፥39) ክርስቶስ ልዩ ፍቅርና እንክብካቤ እንዳሳየ ሉቃስ አምልቶ ይነግረናል። ሉቃስ፣ ኢየሱስ ለኀጢአተኞች ያሳየውን ርኅራኄ በሚያስደንቅ ዕይታ፣ አንጀት ስፍስፍ በሚያደርግ መልኩ ገልጦልናል። ዛሬም ድረስ ይህ እውነት ፈክቶና ደምቆ መታየቱ እንዴት ይደንቃል!?
Friday, 6 November 2020
ሰዱቃዊ ጠባይ ከመያዝ ተጠበቁ!
የሰዱቃውያንን ጠባይ ያጠኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች፦
1-
የመሲሑ ክርስቶስን
መምጣት የማይቀበሉና የማያምኑ፣
2-
የሙሴን
ሕግ ብቻ እንጂ የመዝሙራትንና የትንቢትን መጻሕፍት የማይቀበሉ፣
3-
ትንሣኤ
ሙታንን፣ መላእክትንና መንፈስ ቅዱስን የማይቀበሉና መኖሩንም የማያምኑ(ማቴ. 22÷23-33)፣
4- ባለጠጐችና በጊዜው በጣም የተሻለውን ቅንጡ ኑሮ የሚኖሩ፣ የካህናት ቡድን የኾኑ፣







