“እመቤታችን ማማለድ አይደለም አፍርሳን
መሥራት ትችላለች” [እውነት?!]
“ማንም የእግዚአብሔርን
ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ።” (1ቆሮ.
3፥17)
ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ውስጥ፣ ቅዱስ ቃሉ የሚናገረውን ብቻ መናገር ኑፋቄነት፣ ቅዱስ ቃሉ የማይለውን መናገር ደግሞ አማኝነት ወይም “የቤት ልጅ”
የሚያስብለው ተግባር ከኖረ ሰነባበተ። ለቅዱሳን መላእክትም ኾኑ ሰዎች፣ “ቃሉ ከተናገረው በላይ መናገር ትክክል አይደለም፣
የተነገረው ብቻ ሊነገርላቸው ይገባል” ስንል፣ “ጸረ ቅዱሳን፣ ጸረ ማርያም፣ ጸረ መላእክት …” የሚል ስድብ ያስቀጥላል። ነገር
ግን ለቅዱሳን፣ ቅዱስ ቃሉ የሚናገረውን ብቻ አለመናገር የቅዱሳኑ ጠላቶች መኾናቸውን በቅዱስ ቃሉ ላይ ጨምረው ተናጋሪዎቹ
ያስተዋሉ አይመስሉም።





