ካለፈው የቀጠለ…
ይህን ማወቅ ለምን አስፈለገ?
እግዚአብሔር ሃይማኖታዊ ዝንባሌና መልኩ ብቻ እንዲኖረን አይወድም። “ሙሉ ሰው ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ” ለማደግ፥ “ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት መምጣት (ኤፌ. 4፥13)፤ ስለ እውነት ስለ እግዚአብሔር ልጅ ዕውቀት ሊኖረን ይገባል።
ካለፈው የቀጠለ…
ይህን ማወቅ ለምን አስፈለገ?
እግዚአብሔር ሃይማኖታዊ ዝንባሌና መልኩ ብቻ እንዲኖረን አይወድም። “ሙሉ ሰው ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ” ለማደግ፥ “ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት መምጣት (ኤፌ. 4፥13)፤ ስለ እውነት ስለ እግዚአብሔር ልጅ ዕውቀት ሊኖረን ይገባል።
እንዲህ ነበርን!
ካለፈው የቀጠለ...
5. በአሳባችን ጠላቶች ነበርን፦ ኹላችን በእግዚአብሔር ፊት፣ “… ክፉ ሥራንም በማድረግ በአሳባችን ጠላቶች ነበርን” (ቈላ.1፥21-22)፡፡ እጅግ ክፉዎች ከመኾናችን የተነሣ በእእምሮአችንና በልባችን ለራሳችን የምናዳላ ራስ ወዳዶች ነበርን፡፡ በምድር ላይ አንድም መልካም ሰው መገኘት እስከማይችል ድረስ ኹላችንም ለእግዚአብሔር ጠላቶች ነበርን፡፡
መግቢያ
ስለ እሬቻ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከምንሰማቸው ልዝብ አሳቦች አንዱ፣ “የኦሮሞ ባህልን የምናንጸባርቀበት ብቻ እንጂ አንዳችም አምልኮአዊ መልክ የለውም” የሚለው ግንባር ቀደሙን ስፍራ ይይዛል። ይህን ለማለት ያስደፈረው እውነታ ደግሞ በክርስትና ጥላ የተጠለሉ አያሌ ኦርቶዶክሳውያንና የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት “አማኞች” እና ስለ እሬቻ ዘብ የቆሙ ሰዎች የሚያቀርቡት የተለሳለሰ ዐሳብ ነው። እሬቻን የሚያከብሩት ኦርቶዶክሳውያንና የወንጌላውን አብያተ ክርስቲያናት አማኞች፣ አምልኮአዊ መልክ እንዳለው ስለ ገባቸው ወይም ስለ ተጠራጠሩ፤ በሌላ መልኩ ደግሞ “ባህላችንን እንወዳለን” የሚል አባባይ ምክንያት በመጥቀስ ለማስረዳት ሲንገታገቱ አስተውያለሁ።
መግቢያ
በአገራችን በኢትዮጲያ ከሚከበሩት ሃይማኖታዊ በዓላት መካከል አንዱ ከደመራ ጋር ተያይዞ የሚከበረው በዓል ነው፤ በዓሉ፣ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት እንጨቱ መስቀል፣ ለዓመታት ከተቀበረበት ቦታ መውጣቱን በማሰብ የሚከበር በዓል ነው። በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይኾን፣ ይህ የመስቀል በዓል በአያሌ የአገራችን ሕዝብ ባህሎች ውስጥ የተለያየ መልክና ቅርጽ ይዞ ሲከበር እንመለከታለን። ሃይማኖታዊው ትውፊት መስቀሉ ከተቀበረበት መውጣቱን በማሰብ ሲያከብር፣ አያሌ ባህሎች ደግሞ ከዘመን መለወጫ ጋር በማያያዝ በዓሉን ያከብሩታል።
መግቢያ
አሸናፊ ገብረ ማርያም(ቀሲስ) ጥቂት የማይባሉ መዝሙሮችን “ሠርቶ”፣ ከሰንበት
ትምህርት ቤት ጀምሮ ተጠቅመንባቸዋል፤ ታንጸንባቸዋል፤ አምልከንባቸዋል። ለጌታ የሚሠራቸው መዝሙሮች እጅግ መሳጭና ትኵረትን ቀንብበው
የሚይዙና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያላቸው ናቸው። በዚህ ረገድ ከማከብራቸውና ከምወዳቸው ዘማሪዎች መካከል አንዱ ነው።
እንዲህ ነበርን!
አዳም “የመታዘዝን ፍሬ” ባለመብላት እንዲታዘዝ ቢነገረውም፣ እርሱ ግን የሰይጣንን ድምጽ ተከትሎ በመሄድና የተከለከለውን ወስዶ ከበላበት ቀን ጀምሮ ክርስቶስ እስኪመጣ ድረስ እርሱና ልጆቹ ሁሉ፣ እግዚአብሔር የተወን እየመሰለን አብዝተን ኃጢአትን ሠራን፤ ጨመርንም። ከዚህም የተነሣ፦
ጳጉሜ 3 ብዙዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚላተሙበትን ድርጊት የሚፈጽሙበት ቀን ነው፤ በሌላ ቋንቋ፣ “የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ ያንንም የተቀደሰበትን የኪዳኑን ደም እንደ ርኵስ ነገር የቆጠረ የጸጋውንም መንፈስ ያክፋፋ፥ እንዴት ይልቅ የሚብስ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል?” (ዕብ. 10፥29) የሚለውን ቃል በግልጥ የሚቃወሙበት ቀን ነው፤ “በመልአኩ ሩፋኤል” ስም መጠበል ወይም መጠመቅ ከኀጢአት ያነጻል የሚል ከንቱ ልፍለፋ።
“ሁላችን በሃይማኖትና የእግዚአብሔርን ልጅ በማወቅ አንድ እስክንሆን
ድረስ በክርስቶስ ፍጻሜ ልክ የአካል መጠን እንዲደርስ ፍጹም ሰው እንሁን” (ኤፌ.4፥13)
መግቢያ
በዘመናችን ሰዎች ክርስቶስን በትክክል መኾን እንደሚቻላቸው አያሌ የስህተት ትምህርቶችን መስማት ከጀመርን ሰነባብተናል። አንዳንዴ ክርስቶስን የፍጥረቱ አካል በማድረግ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ እኛ ራሱ ክርስቶስን ልንኾን እንደምንችል በአደባባይ ታውጆአል፤ በተለያየ መንገድ ይህን ትምህርት ፊት ለፊት በመቃወም፣ የትምህርቱን ስሑትነትና ከመጽሐፍ ቅዱስ ያልተቀዳ መኾኑን ተናግረናል፤ አስተምረናል። ዛሬም ክርስቶስ የፍጥረት አካል እንዳይደለ፤ ቅዱሳት መጻሕፍት ያስተማሩንን፣ ፍጹም አምላክነቱና ፍጹም ሰውነቱን ደፍረን እንናገራለን።
በግርማ መለኮት የተፈራውና ማንም ሊቀርበው የማይችለው ጌታ፣ በክበበ ትስብእት በናዝሬት ከምትኖር ከአንዲት ድኻ ሴት ከማርያም ተወልዶ፣ በተዋረደው ዓለም በውርደት ተመላለሰ። ከመሰቀሉ በፊት ሰውን ሥጋ በመልበሱ ብቻ ተዋረደ። በበረት ከመወለዱ በፊት፣ በናዝሬት መንደር ከአንዲት ሴት ማኅፀን በማደሩ እጅግ፤ እጅግ ዝቅ አለ። ከኀጢአተኞች ጋር በመቈጠሩና ከእነርሱም ጋር በመዋሉ ደግሞ ኢየሱስ፣ ስድባችንን ኹሉ በመሸከም መስቀሉን በመላ ዘመኑ ታገሠ።
መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን ብቻ መናገር አስተዋይነት፤ ያልተናገረውን ደግሞ አለመጨመር ፍጹም ታማኝነት ነው። እኛ ሰውን ደስ ለማሰኘት የተናገርነው “እውነት”፣ መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ ያልተናገረው ሐሰት ሊኾን የሚችልበት አንዳች ሚዛን የለም፤ የእውነት እውነተኛው ሚዛን መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ከኾነ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ያልተናገረውና ያላለው ኹሉ ሐሰት፣ እርሱ የተናገረውና በእርሱ ያለው ብቻ እውነት ነው። ሚዛንን ስቶ ሚዛናዊ መኾን ፈጽሞ አይቻልምና።
ጌታችን ኢየሱስ ስለ ማልቀሱ የተነገረው እጅግ በጣም ውሱን ቦታ ብቻ ነው፤ ካለቀሰባቸው ምክንያቶች አንዱ ደግሞ ስለ ኢየሩሳሌም ያለቀሰው ልቅሶ ነበር። ያለቀሰው በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ፣ ከተማይቱን ፊት ለፊት በመመልከት ነበር። ሚስቱን አብዝቶ የሚወድድ ጐልማሳ፣ ሚስቱ በተወችው ጊዜ በስብራት እንደሚያለቅስ እንዲሁ፣ ኢየሱስም የከተማዋ ኹለንተና ከሚታይበት ከደብረ ዘይት ተራራ ፊት ለፊት ተቀምጦ ለኢየሩሳሌም አለቀሰላት።
ለምንኖረው ሕይወትና ለማናቸውም የክርስትናችን የኑሮ ዘይቤ፣ ማዕከሉ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ያልተኖረ የሕይወት አብነት የለንም፤ የተኖረና በድል የተጠናቀቀ የሕይወት አብነት ግን አለን፤ እርሱም የክርስቶስ። ክርስቶስ ያልኖረውን ሕይወት ኑሩ አላለንም፤ “ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤” (ማቴ. 11፥28) ያለን ጌታ፣ “ፍለጋውን እንድንከተል ምሳሌ ትቶልናል” (1ጴጥ. 2፥21) ስለዚህ የማይጨበጥ፣ በንግግር ብቻ የሚተረክ፣ በተመስጦአዊ ስብከቶች የሚሰበክ ብቻ ያይደለ፤ የሚኖር፣ የሚሻተት፣ የሚቀመስ፣ የሚጣጣም ቅዱስ ሕይወትን ሰጥቶናል።