ጌታችን ኢየሱስ ስለ ማልቀሱ የተነገረው እጅግ በጣም ውሱን ቦታ ብቻ ነው፤ ካለቀሰባቸው ምክንያቶች አንዱ ደግሞ ስለ ኢየሩሳሌም ያለቀሰው ልቅሶ ነበር። ያለቀሰው በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ፣ ከተማይቱን ፊት ለፊት በመመልከት ነበር። ሚስቱን አብዝቶ የሚወድድ ጐልማሳ፣ ሚስቱ በተወችው ጊዜ በስብራት እንደሚያለቅስ እንዲሁ፣ ኢየሱስም የከተማዋ ኹለንተና ከሚታይበት ከደብረ ዘይት ተራራ ፊት ለፊት ተቀምጦ ለኢየሩሳሌም አለቀሰላት።
Thursday, 13 August 2020
Tuesday, 4 August 2020
ክርስቲያኖች ወደ ቄሳር ሲጠጉ እፈራለሁ!
ለምንኖረው ሕይወትና ለማናቸውም የክርስትናችን የኑሮ ዘይቤ፣ ማዕከሉ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ያልተኖረ የሕይወት አብነት የለንም፤ የተኖረና በድል የተጠናቀቀ የሕይወት አብነት ግን አለን፤ እርሱም የክርስቶስ። ክርስቶስ ያልኖረውን ሕይወት ኑሩ አላለንም፤ “ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤” (ማቴ. 11፥28) ያለን ጌታ፣ “ፍለጋውን እንድንከተል ምሳሌ ትቶልናል” (1ጴጥ. 2፥21) ስለዚህ የማይጨበጥ፣ በንግግር ብቻ የሚተረክ፣ በተመስጦአዊ ስብከቶች የሚሰበክ ብቻ ያይደለ፤ የሚኖር፣ የሚሻተት፣ የሚቀመስ፣ የሚጣጣም ቅዱስ ሕይወትን ሰጥቶናል።
Saturday, 1 August 2020
Sunday, 26 July 2020
የልቤ ሙሾ! (ስለ ወገኖቼ፣ ስለ ፍትሕ፣ ስለ ክፋት ማገንገን)
Please read in PDF
በባሌ አጋርፋ(አምቤንቱ)፣ በሻሸመኔ፣ እንዲሁም “በትውልድ መንደሬ” በአርሲ
ነጌሌ የተፈጸመውን ጆሮ ጭው የሚያደርግ ዘግናኝ ተግባር ሰምቼ፣ አይቼ በሰውነቴ ተሸማቅቄአለሁ፤ ለረጅም ሰዓት አልቅሼአለሁ፤ በባሌ
አጋርፋ(አምቤንቱ) በአካል ተገኝቼ የኾነውን ኹሉ አይቻለሁ፤ አቤቱ! ይህን ለምን አሳየኸኝ? የአዛውንቶችን ሰቆቃ ለምን አመለከትኸኝ?
የማልችለውን ለምን አሸከምከኝ? ሆደ ባሻውን ለምን ድንጋጤንና ፍርሃትን የሚያጭር ነገር እጎበኘው ዘንድ ወደድክ? አንተ ለደካሞች
አልተከላከልክላቸውም፤ እኔ ምን እንዳደርግ አመለከትኸኝ ይኾን?
Saturday, 25 July 2020
Sunday, 28 June 2020
የእምነት እንቅስቃሴ አገልጋዮች የክርስቶስን ዘላለማዊ ልጅነት አያምኑም!
(“የእምነት እንቅስቃሴ
- የዛሬዪቱ ቤተ ክርስቲያን
ፈተና”፣ ከሚለው መጽሐፍ ገጽ 61-63
የተወሰደ)
3.1.
ከአምላክነቱ ያልተነጠለ ልጅነቱን መካድ፦ ጌታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ በሰውነቱ የተናገረውንና የተነገረለትን ልክ ለመለኮቱ እንደ ተነገረ ተቈጥሮ ሲካድ እንመለከታለን። ለዚህም እንደ ዋቢ አድርገው የሚጠቅሱት፣ “የክርስቶስን
ከዘላለም የእግዚአብሔር ልጅ አለመኾኑን” ኹለት ሃሳቦችን በአንድነት በመስፋት ነው። እንዲህ በማለት፦
Thursday, 25 June 2020
የእምነት እንቅስቃሴ አገልጋዮች፣ የመጽሐፍ ቅዱስን ሥልጣን አይቀበሉም!
በቃለ አዋዲ የዘመኑ መልክ ላይ የእምነት እንቅስቃሴ አማኝና አገልጋዮች የመጽሐፍ ቅዱስን ሥልጣን የማይቀበሉ መኾናቸውን እንዲህ አውግተን ነበር! ተከታተሉት!
Wednesday, 24 June 2020
Saturday, 20 June 2020
የሐሰት መምህራን የማይነኳቸው ርእሶች (ክፍል ፰ - የመጨረሻ ክፍል)
Please read in PDF
8.
ምስክርነት፦ በሐዋርያት
ሥራ ውስጥ ምስክርነት ከድፍረት ጋር በቀጥታ ተጠቅሶ እንመለከተዋለን፤ ሐዋርያት ሲጸልዩ እንዲህ ብለው ጸለዩ፣ “… ባሪያዎችህም
ቃልህን በፍጹም ድፍረት መናገር እንዲችሉ አድርጋቸው” በማለት፣ “ከጸለዩም በኋላ የነበሩበት ስፍራ ተናወጠ፤ ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ
ተሞሉ፤ የእግዚአብሔርንም ቃል በድፍረት ተናገሩ።” (ሐዋ. 4፥29፡ 31)፤ አስቀድሞም ወንጌልን ይመሰክሩ የነበሩት በድፍረት፤
ያለ አንዳች ፍርሃትና መሸማቀቅ ነበር፤ (2፥29፤ 4፥13)።
Wednesday, 17 June 2020
የሐሰት መምህራን የማይነኳቸው ርእሶች (ክፍል ፯)
Please read in PDF
6. እግዚአብሔርን መምሰል፦ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረን፣ የእነርሱ
መልክ ከበግ ጋር የተቀራረበ የተኩላ መልክ ነው፤ በበጎች መካከል ኾነው ይጸልያሉ፤ ይማራሉ፤ ያስተምራሉ፤ የበግ ጠባይ የያዙ መስለው
ይመላለሳሉ። ዓላማቸው በጉን ለራሳቸው መንጠቅና በእረኛው እንዳያርፍ ማባዘንና ማቅበዝበዝ ነው።
Saturday, 13 June 2020
ባላንጣዎቹ ደቀ መዛሙርት
Please read in PDF
ጌታ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን የጠራቸው እጅግ ከተለያየ ቦታና ከተለያየ
የሥራ ገበታቸው ነው። የአንዳንዶቹ ተግባራት ፈጽሞ የሚያቀራርባቸው ብቻ ያይደለ ደም የሚያቃባቸውም ጭምር እንደ ነበር ታሪካዊ ዳራዎችን
ስናጠና ማስተዋል እንችላለን። ለዚህም በምሳሌነት ከአሥራ ኹለቱ መካከል ኹለቱን ደቀ መዛሙርት በማንሳት እንችላለን።
ከኢየሱስ
ጥሪ በፊት
ቅዱስ
ማቴዎስና ቀናተኛው ስምኦን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከጠራቸው ቅዱሳን ደቀ መዛሙርት መካከል ናቸው፤ ማቴዎስ የተጠራው ከቀራጭነት
ቦታ ሲኾን (ማቴ. 9፥9)፣ ቀናተኛው ስምዖን ደግሞ በቅጽል ስሙ እንደ ተጠራው ቀናተኞች ከኾኑት አይሁድ መካከል ነው። ማቴዎስ
አይሁዳዊ ቢኾንም ለሮማውያን ተቀጣሪ በመኾኑና ግብርን ከአይሁድ ተቀብሎ ለሮማውያም በመሰብሰቡ በአይሁድ ዘንድ ፈጽሞ የተጠላ ነው።
የትኞቹም አይሁድ ለሮማውያን የሚሠሩ አይሁድን የሚመለከቱት እንደ ከዳተኛና ከአሕዛብ ጋር እንደሚተባበሩ ነው።
Friday, 12 June 2020
የሐሰት መምህራን የማይነኳቸው ርእሶች (ክፍል ፮)
Please read in PDf
5. መስቀሉን፦ ኀጢአተኛና የወደውን ዓለም ባለመናቅ፣ ኀጢአትን ፍጹም በመጥላትና በመጠየፍ፣ እግዚአብሔር ዓለምን ለማዳን አንድያ ልጁን በመስቀል አሳልፎ ሰጠ። በአዲስ ኪዳን ምንባባት ውስጥ ከሦስት መቶ በላይ የመስቀልን ትርጉሞችን ያስቀምጥልናል፤ በሌላ ንግግር የኀጢአት መገኘት፣ ፍርድና የኀጢአት ኃይል በተጠቀሰበት የአዲስ ኪዳናት ምንባባት ውስጥ ኹሉ፣ ነገረ መስቀሉ በአብዛኛው ተያይዞ እንደ ተጠቀሰ እናስተውላለን።
5. መስቀሉን፦ ኀጢአተኛና የወደውን ዓለም ባለመናቅ፣ ኀጢአትን ፍጹም በመጥላትና በመጠየፍ፣ እግዚአብሔር ዓለምን ለማዳን አንድያ ልጁን በመስቀል አሳልፎ ሰጠ። በአዲስ ኪዳን ምንባባት ውስጥ ከሦስት መቶ በላይ የመስቀልን ትርጉሞችን ያስቀምጥልናል፤ በሌላ ንግግር የኀጢአት መገኘት፣ ፍርድና የኀጢአት ኃይል በተጠቀሰበት የአዲስ ኪዳናት ምንባባት ውስጥ ኹሉ፣ ነገረ መስቀሉ በአብዛኛው ተያይዞ እንደ ተጠቀሰ እናስተውላለን።
Sunday, 7 June 2020
Friday, 5 June 2020
ድኃ አገልጋዮችና “ሃብታም” አገልጋዮች
ልከኛ አገልጋይ፣ በሰማይና
በምድር ሥልጣን የተሰጠው የጌታ ኢየሱስ ኹነኛ መልእክተኛ ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ደቀ መዛሙርቱን የላከው የሰማይ አምባሳደር
አድርጎ በመሾም ነው፤ (2ቆሮ. 5፥20)። ሰፊው መከር፣ ወንጌል በመስማት የሚድኑ አማንያን እንደ ኾኑ እንዲኹ፣ መከሩን ለማገልገል
የሚያስፈልገው በረከትና አቅም ደግሞ እዚያው በረከት ውስጥ ያለ መኾኑን እናስተውላለን። ጌታ ኢየሱስ፦ “መከሩስ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች
ግን ጥቂቶች ናቸው፤ እንግዲህ የመከሩን ጌታ ወደ መከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት” በማለት ደቀ መዛሙርቱን አዘዛቸው፤ (ማቴ.
9፥፥38)።
Wednesday, 3 June 2020
Subscribe to:
Posts (Atom)

