Please read in PDF
መግቢያ
ጌታችን ኢየሱስ መድኀኒት አስፈላጊነቱ ለበሽተኞች መኾኑን ተናገረ (ማቴ.
9፥12)፤ ስለዚህም ሰዎች ከበሽታ ለመዳን መድኀኒትን መጠቀማቸውን እናስተውላለን፤ “በጥንት ዘመን ሰዎች በመድኃኒት ሲያምኑ
በነፍስ ሊበረቱ ይችላሉ። ጥቅሙ ከእምነት እንጂ ከመድኃኒት አልነበረም። ዛሬ ግን ብዙ ጊዜ በመድኃኒት ቢያምኑም ባያምኑም
መድኃኒቱ ፍቱን ነውና ይሠራል”። ከፊት ዘመን ይልቅ በዛሬ ዘመን ሰዎች በመድኃኒት አብዝተው የሚታመኑ ይመስላል፤ ለዚህም
ይመስላል በምድራችን ላይ እጅግ ዝቅተኛ ከሚባሉት እስከ ቅንጡ መታከሚያ ቤቶች የተበራከቱት። ነገር ግን ይህ ኹሌ ስሙርና የመጨረሻ
መፍትሔ ኾኖ አይታይም።





