Thursday, 12 March 2020

Monday, 9 March 2020

ምኩራብ - ሦስተኛው ቤተ መቅደስ

Please read in PDF

  ያለንበት የዓቢይ ጾም ሳምንት በማኅሌታይ ያሬድ ስያሜ፣ “ምኩራብ” ተብሎአል፤ ምኩራብ አይሁድ በምርኮ ወደ ባቢሎን በተወሰዱ ወራት፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን ለማንበብና የሕጉን ቃሎች ለማሰብ፣ በየጥቂት አባወራ በመሰባሰብ የጀመሩት ነው። ወደ አገራቸው ሲመለሱም ይኸንኑ በመቀጠል፣ ከዋናውና መሥዋዕት ከሚቀርብበት መቅደስ ባሻገር፣ በየመንደራቸው አቅራቢያ ምኩራብ በመሥራት፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን ማጥናትና ማንበብን በዚያ ጀመሩ። እንግዲህ ማኅሌታይ ያሬድ፣ ምኩራብን ለዓቢይ ጾም ሦስተኛው ሳምንት ሲሰይም፣ በሳምንቱ ውስጥ ከሚነበቡት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ደግሞ፣ ዮሐ. 2፥12-22ን በመመደብ ነው። ክፍሉም በቀጥታ በኢየሩሳሌም ከነበረው ቤተ መቅደስ ጋር በማያያዝ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረው ስለ መኾኑ የታመነ ነው።

Sunday, 8 March 2020

በእኔ የተናገርክ … ተባረክ!

Please read in PDF

አገልግሎትን በክብር መጨረስ መታደል ነው። ያለ መንፈስ ቅዱስ ዕርዳታም፣ ማንም አገልግሎቱን በክብር መጨረስ አይቻለውም። ሩጫውን ስለ ጨረሱ ቅዱሳን ስናስብ፣ ልባችን ታላቅ ሐሴት ያደርጋል፤ በመደነቅም ይሞላል፤ ኹላችን እንዲህ ብንኾን፣ በሕይወት ዘመናችን እንደ እነርሱ ባለ ትጋት ጸንተን፣ እርግጠኞች ኾነን፣ “መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤” ማለት ብንችል እንዴት በታደልን?! … አዎን! ለዚህ ተጠርተናል!!!

Wednesday, 4 March 2020

በማንቂያ ደወል አንቅተንስ … ?!

Please read in PDF

  ባለንበት ወር “የማንቂያ ደወል” የሚሉ ጉባኤያት፣ በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን በተደጋጋሚ ከአድባራት እስከ ደብራት ሲደረጉ እያየን ነው። ከተለያዩ ጉባኤያት “መምህራን” አንደበት እንደ ሰማነው፣ የጉባኤያቱ መነሻ ዐሳብ፣ ሕዝቡን ስለ ሃይማኖቱ ማንቃት፣ በተለይ አኹን እየደረሰ ካለው ውጫዊና ውስጣዊ ተጽዕኖ በመከላከል፣ ሃይማኖቱን እንዲጠብቅና ከፍ ሲልም “ሰማዕት” እንዲኾን ማድረግ የሚሉና ሌሎችም ጽኑ አቋሞች አሉት። ነገር ግን ለጉባኤያቱ መደረግ እንደ ሥረ ምክንያት የተነሡትና እንደ ጭብጥ የተያዙት ዐሳቦች፣ ከክርስትና አስተምህሮ እጅግ የራቁና መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ ያላቸው አይመስሉም

Monday, 2 March 2020

ቅድስት - ኢየሱስ ከሰንበት ይበልጣል!

Please read in PDF

  “ሰንበት” የሚለው ቃል፣ በዕብራይስጥ ትርጉሙ ማቆም ወይም መተው ማለት ነው።[1] “ሰንበት … የዕለት ስም ሰባት፣ ሰባተኛ ቀን፤ ሰባተኛ ዓመት ማረፊያ ዕረፍት…”[2] ማለት ነው። በቀደመው ኪዳን ትእዛዝ መሠረት፣ “ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ነው፤ አንተ፥ ወንድ ልጅህም፥ ሴት ልጅህም፥ ሎሌህም፥ ገረድህም፥ ከብትህም፥ በደጆችህም ውስጥ ያለ እንግዳ በእርሱ ምንም ሥራ አትሥሩ፤ …” (ዘጸ. 20፥10) እንዲል፣ ማናቸውም የኪዳኑ አማኝ፣ የዘወትር ሥራውን ትቶ ወይም በማረፍ በኹለንተናዊ መልኩ እግዚአብሔር አምላኩን በአምልኮ ለማክበር የሚጠቀምበት ቀን ነው፤ የሰንበት ቀን ለዕረፍትነት ወይም ለአምልኮ መሰጠቱ ከሕጉ በፊት መኾኑን አለመዘንጋት፣ ለኹሉ የሰው ዘር መሰጠቱን እንድናስተውል ያደርገናል

Wednesday, 26 February 2020

ቤተ ክርስቲያንንም ለ“መደመር”?፤ ተዉ!

Please read in PDF

   በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ነገሥታት “በዶግማና በቀኖና” አንድ ያልነበሩትን “አብያተ ክርስቲያናት”፣ አንድ ለማድረግ እጅግ መጣራቸውን እናስተውላለን።


   “ከኬልቄዶን ጉባኤ በኋላ ለሚቀጥሉት ፩፻፶ ዓመታትያህል የነገሡ የቊስጥንጥንያ ነገሥታት ቤተ ክርስቲያንን ለማዋሐድ ብዙ ጥረት አድርገዋል። ለምሳሌ ከ፬፻፸፬-፬፻፺፩ ዓ/ም የነገሠው ዘይኑን(ዚኖን)፣ ከ፬፻፺፩-፭፻፲፰ዓ/ም የነገሠው እናስታሲዮስ በተዋሕዶ አንድ ባሕርይ የሚለውን የተዋሕዶ እምነት ተቀብለው ቤተ ክርስቲያን በሰላም የምትመራበትን መንገድ ለመፈለግ ተነሳሰተው ነበር። ለዚህም በጎ ፈቃድ መሰናክሉ የኬልቄዶን ጉባኤ ውሳኔና የልዮን ጦማር መኾኑን በመገንዘብ የቊስጥንጥንያው ሊቀ ጳጳስ አባ አጋግዮስ(አካኪዮስ) እና ንጉሡ ዘይኑን ተስማምተው ይህን ለመሰረዝና ቤተ ክርስቲያንንም ወደ ጥንታዊ የተዋሕዶ እምነቷ ለመመለስ ከአንጾኪያና ከእስክንድርያው ፓትርያርኮች ጋር ውይይት ጀመሩ።”[1]

Thursday, 13 February 2020

በነነዌ ማግስት!

Please read in PDF

በነነዌ ምድር …
ኀጢአት ተከተተ፣ ነውር ተከደነ
ዓመጻ ታለለ፣ ምሕረት ገነነ

Thursday, 6 February 2020

ንቀት (ክፍል ፲ እና የመጨረሻ ክፍል)

Please read in PDF
እንኪያስ፦
1.      ትናናቁ፦በማንኛውም የኑሮ ዘይቤ የሚኖሩ ሰዎችን ስታከብሩ፣ ሠሪያቸውን ወይም የፈጠራቸውን ያህዌ ኤሎሂምን ነው የምታከብሩት። እግዚአብሔር ሰውን ወደዚህ ምድር ሲያመጣው በትልቅ ዓላማና ለክብሩ መገለጫ ይኾን ዘንድ ነው። እኛ እንደ ሳይንቲስቶች ወይም እንደዚህ ምድር ጠቢባን በፈጠረው ዓለምና ሰው እጅግ በመደነቅና በመመሰጥ የምንዋጥና በዚህ ብቻ የምንቀር አይደለንም፤ ይልቁንም እግዚአብሔር ዓለምንና ሰውን የፈጠረው ያህዌ ኤሎሂም ከሰው ጋር ግላዊና ኅብረታዊ ግንኙነትን ሊመሠርት እንዳለው እናምናለን።

Wednesday, 5 February 2020

ንቀት (ክፍል ፱)

Please read in PDF

ኢየሱስ ክርስቶስ ዋናው አብነታችን!
ጌታችን ኢየሱስ ፍጹም ተንቆአል!
በአንድ ወቅት በክርስቶስ ኢየሱስ ጉዳይ በአይሁድ ሸንጐና ሕዝብ ክርክር መደረጉን፤ በመካከላቸው መለያየት በተደጋጋሚ መከሰቱንም የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል ይነግረናል፤ (7፥43፤ 9፥16፤ 10፥19)።ለዚህ ምላሽ እንዲኾንም የአይሁድ መሪዎች ኢየሱስን ለማስያዝ ያደረጓቸው ተግባራት ለኢየሱስ የነበራቸውን ንቀት ፍንትው አድርጐ ያሳያል። ዮሐንስ ይህን በሚገባ ይገልጠዋል፤ አስቀድሞ እነርሱ ከሚያከብሩአቸው ሰዎች ታላላቅ ሰዎችን በመላክ ለኢየሱስ ያላቸውን አክብሮት ቢያሳዩም፣ በኋላ ላይ ግልጹ ዐሳባቸው ታውቆአል፤ ይኸውም ለኢየሱስ ያላቸውን ንቀት ለማሳየት ጠባቂዎችንና ዝቅተኛ ሥልጣን ያላቸውን ሰዎች ልከዋል፤ ነገር ግን ከፊተኞቹ የኒቆዲሞስ ማመን ከኋለኞቹም ጠባቂዎች “እንደዚህ ሰው ማንም እንዲሁ ከቶ አልተናገረም” የሚል ምስክርነት መገኘቱ እጅግ የሚደንቅ ነው፤ (ዮሐ. 7፥45-52)።

Sunday, 2 February 2020

ንቀት (ክፍል ፰)

Please read in PDF
1.    በአገራችን አስተዳደጋችን ምንታዌነት አለው
   በመጀመሪያቱ ቤተ ክርስቲያን ቤተሰቦች ውስጥ የነበሩት ባሪያዎች፣ አንዳንዶቹ በጌታ ኢየሱስ ያመኑ ነበሩ፤  ስለዚህም እኒህን ባሪያዎች እንደ ወንድሞቻቸው እንጂ እንደ ቤት አገልጋዮቻቸው እንኳ አይመለከቱአቸውም ነበር፤ ነገር ግን እኒህ ባሪያዎች በተቃራኒው ጌቶቻቸውን መናቅ ጀመሩ፤ የክርስትናው ነጻነት ይበልጥ ሊያከብሩአቸውና ሊሠሩላቸው እንዲገባ ማዘዙን ዘነጉት፣ እነርሱ ግን በተቃራኒው አደረጉ። አንድ አገልጋይ በግዴታ ያገለግል በነበረበት ወራት ይሠራ የነበረውን ሥራ ኹሉ፣ አኹን ግን በፍቅር መሥራት ተሳነው። ለዚህ ነው ቅዱስ ጳውሎስ፦
የሚያምኑም ጌቶች ያሉአቸው፥ ወንድሞች ስለሆኑ አይናቁአቸው፥ ነገር ግን በመልካም ሥራቸው የሚጠቅሙ የሚያምኑና የተወደዱ ስለሆኑ፥ ከፊት ይልቅ ያገልግሉ።” (1ጢሞ. 6፥2)

Saturday, 25 January 2020

“እኔነቴ”ን ልውደድ!

Please read in PDF

ራሴን አልወድም
አንተ ባየኸኝ ልክ “እኔ እኔን” አላይም
እናማ ጌታዬ!

Wednesday, 22 January 2020

ንቀት (ክፍል ፯)

ለምን ግን እንናናቃለን?
   አንዳንዶች በመልካቸው ብቻ ይናቃሉ፤ ለምሳሌ፦ በዓረብ ማኅበረ ሰብ ውስጥ ያሉ ጥቁር ዓረቦች፣ ጥቁር ስለኾኑ ብቻ የተናቁ እንደ ኾኑ ይናገራሉ፤[1] አንዳንድ “ቤተ እምነቶች” ንቀትን የማበረታታት ትምህርቶች አላቸው፤ ለምሳሌ፦ ከእነርሱ ቤተ እምነት ውጪ ያሉትን ወይም የቤተ እምነታቸውን ቀኖናና ዶግማ የማይቀበሉትን ማናቸውንም ቤተ እምነቶች መናቅ እንደሚገባቸው ያምናሉ፤ ልክ አብዛኛዎቹ የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት ወይም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አንዳቸው ሌላውን እንደሚንቁ። እንዲያውም እንደ እስልምና[2]፣ ጅሖቫ፣ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት፣ የእምነት ቃል አገልግሎት፣ ሞርሞንና ተመሳሳይ “ቤተ እምነቶች”፣ ማንኛውም ሰው የእነርሱን ቤተ እምነት ቀኖናና ዶግማ ካልተቀበለና ከእነርሱ ውጭ ካለው ማናቸውም ኅብረት ጋር፣ ኅብረት ቢያደርግ “ከርኩሱ ዓለም ጋር ግንኙነት እንዳደረገ ወይም እንደ ተካፈለ” አጥብቀው ያስተምራሉ።

Sunday, 19 January 2020

በጥምቀቱ ከኀጢአተኞች ጋር ተቈጠረ!

Please read in PDF
 
   ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመጠመቁን ነገር በየዓመቱ በኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት “ታስቦ” ይውላል፤ መታሰቡ “መልካም” ቢኾንም፣ የሚታሰብበት መንገድ ግን ፈጽሞ ከመጽሐፍ ቅዱስ መራቁ፣ እጅግ የሚደንቅ የሚያሳዝንም ነው። በአገራችን “በዓለ” ጥምቀት አብዛኛውን ጊዜ ከመንፈሳዊ ነጸብራቅነቱ ይልቅ፣ ባሕላዊና ʻሃይማኖታዊ ሥርዓት መከናወኛ ብቻ ኾኖ ሲከበርʼ እናስተውላለን። ጭፈራ፣ ሽለላ፣ ʻታቦትʼ እጀባ፣ ሎሚ ውርወራ፣ የአዳዲስ ልብስ ማሳያና … ሌሎችም ተግባራት፣ ልኩንና ገደቡን በጣሰ መልኩ የሚቀርቡት በዚሁ በጥምቀት “በዓል” ቀን ነው። ቤተ ክርስቲያን ወደ ኢየሱሳዊ መንፈሳዊነት ፍጹም አለማዘንበልዋ እንዲህ ላለ ሰፊ ተላላነት ተላልፋ መሰጧን ማስተዋል አያዳግትም።

Thursday, 9 January 2020

ጠላቱን ወዳዱ!

Please read in PDF
አዳም!
የሞተው በኀጢአት የተንኮታኮተው፣
ከሰውነት ማማ አዘቅት የወረደው