Sunday, 19 March 2017

“እነሆ፥ አስቀድሜ ነገርኋችሁ” (ማቴ.24፥25)

                                          Please read in PDF

   ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምድር ሳለ ከተናገራቸው የመጨረሻ ቃሎች መካከል፣ በደብረ ዘይት ለደቀ መዛሙርቱ ስለዳግመኛ መምጣቱ ምልክቶች የተናገረው አንዱና ሠፊውን ክፍል የያዘ ነው፡፡ በውስጡ ብዙ ነገር መናገሩን ወንጌላዊው ጽፎልናል፡፡ በመካከሉም ቅዱስ ማቴዎስ፣ ጌታችን “እነሆ፥ አስቀድሜ ነገርኋችሁ” ብሎ መናገሩን ከጻፈልን የወንጌል ቃል ውስጥ ሁለት መሠረታዊ ጭብጦችን ማውጣት እንችላለን፤ ይኸውም፦
1.      ጌታችን ሁሉንም ነገር የነገረን  በግልጥ ነው፦ ጌታ ለእኛ ከሚያስፈልገን  ቀድሞ ያልተናገረን ምንም ነገር የለም፡፡ በሰማይም ሆነ በምድር ሊሆንና ሊመጣ ያለው ነገር ሁሉ ተነግሮናል፡፡ በዚህ ምድር ሕይወት ስላለው ብርቱ ሰልፍነት፣ ታ ኢየሱስንም አምነን በመከተላችንም ሆነ ሳናምን በመከተላችን ስለሚገጥመን ሕይወትና ሞት፣ ስሙን አምነን በመከተላችንና በመመስከራችን ስለሚያገኘን ነቀፋ፣ ስድብ፣ ግርፋት፣ ስደት፣ ስም ማጥፋት፣ ርስትና ጉልት ማጣት፣ በቤተሰብ ሁሉ ዘንድ ከበሬታና ቦታ መነፈግ፣ መጠላትና መገለል፣ መገደል፣  ... እኒህ ሁሉ አስቀድመው የተነገሩ ናቸው፤ (ማቴ.10፥16 ፤ 24፥9 ፤ ዮሐ.15፥19)፡፡

Monday, 13 March 2017

አትተወን

የትዳር አልጋችን ረከሰ ከየሰ
የኪዳን ቃላችን ሳይውል ፈራረሰ
ከባልንጀራ ጋር በሐሜት ተራኩተን
አንድ ነን እያልን አለቅን ተበላልተን፡፡

Wednesday, 8 March 2017

“የረዳኝን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ”

  
    ልክ ዛሬ፣ የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ በሚለው የጡመራ መድረክና(Blog) በፊት ገጽ(Facebook) መጻፍ ከጀመርኩ አራት ዓመታትን አስቆጠርኩ፤ በእነዚህ ዓመታት ውስጥ በጌታ ጉልበትና ቸርነት፤ በመንፈስ ቅዱስም እርዳታ ሃሳብን በማስፈር ቀስ ብዬ እየዳኽኩ፤  እያደግሁ መጥቻለሁ፤ ገና ወደፊትም ጌታ እንደረዳኝ ብዙ እንደምሠራ መሻቴ ነው፤ ግና ጌታ ብቻ እንደፈቀደ ይሁን፤ አሜን፡፡ ምኞቴና መሻቴ አንዱንና የሞተልኝን ጌታ ኢየሱስን በዘመኔ ሁሉ አክብሬ ማገልገልና ማረፍ ነው፤ ለእርሱ ኖሮ መሞት መታደል፤ እጅግ ወደር የለሽ ክብር ነው!

Sunday, 5 March 2017

ምኩራቡን ለምኩራቡ ጌታ አገልግሎት!

    
Please read in PDf
  የእስራኤል ልጆች በስደት ምድር በባቢሎን ሳሉ፣ በኢየሩሳሌም የነበረው ዋናው ቤተ መቅደስ  ስለፈረሰና በምርኮ ምድር ደግሞ ቤተ መቅደስ መሥራት ስላልተቻላቸው ለጸሎት፣ ቃሉን ለማንበብና ለማጥናት እንዲሁም መንፈሳዊ ሕይወታቸውን ለማሳደግ ምኩራብን በየአቅራቢያቸው ሠሩ፡፡ በምኩራቡ ውስጥም በየቀኑ የሚነበቡ የተለያዩ የሕግና የነቢያት የብራና ጥቅልሎች ቅዱሳት መጻሕፍት ቅጂዎችን አስቀመጡ፡፡
   የእግዚአብሔር እውነተኛ ሕዝብ በየትኛውም ሥፍራና ሁኔታ ሊያስቀድመውና ሊጠነቀቅለት የሚገባው ነገር ከአምላኩ ጋር ያለው ዝምድና፣ ትስስሩና ግንኙነቱ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ይህ ግንኙነት ሊያሳስበው፤ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው በምቹና የተደላደለ ትርፍ ሰዓት ባለው ጊዜ ብቻ አይደለም፡፡ ይልቁን በስደት፤ ፈጽሞ ምንም ዓይነት ዕድል ላይገኝ በሚችልበት መንገዱ፣ የጌታ ነገር ቀዳሚና ትኩረቱን ሳቢ ሊሆን፤ በሕይወቱም ጭምር ሊሰጥለት ይገባል፡፡

Tuesday, 28 February 2017

ቅድስት ሰንበቴ

አልቅበዘበዝም እረኛ እንደሌለው
ከቶ አልጨነቅም ጥጉን እንዳጣ ሰው …

Friday, 24 February 2017

ከኢየሱስ ተኮር - ወደ “አገልጋይ[ስጦታ]” ተኮር ሩጫ (ክፍል ስድስት)

Please read in PDF

5.    ጌታ ኢየሱስ ራሱን እንደአገልጋይ ቆጠረ (ማቴ.20፥28)፤ “እንዲሁ የሰው ልጅም ሊያገለግልና ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም” በማለት፣ እንደአገልጋይ እንጂ “እንደጌታ” አለመምጣቱን ተናገረ፤ (ማር.10፥45 ፤ ፊል.2፥8)፡፡ ስለዚህም መብቱን ሁሉ ለእኛ ሲል ትቶ፣ ሕይወቱንም ጭምር ሊሰጥ መጣ፤ (ዮሐ.10፥11)፡፡ ኢየሱስ በማገልገሉ እኛ ወደድኅነተ ሥጋ ወነፍስ፣ በሞት ጥላ ሥር በጨለማ ውስጥ የነበርን ሕዝቦች በእርሱ መምጣትና መገለጥ፣ ዝቅ ብሎ እንደባርያ  ማገልገል ወደሚደነቅ ብርሃንና ወደበዛ ሕይወት መጣን፤ አገልጋይ ለራሱ እንደማይኖር ጌታ ኢየሱስም ለአባቱ ትእዛዝና ፈቃድ እንጂ ለራሱ አልኖረም፤ ይህንንም በአንደበቱ፥ “አብም እንዳዘዘኝ፥ እንዲሁ አደርጋለሁ” “እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደ ጠበቅሁ በፍቅሩም እንደምኖር ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ” (ዮሐ.14፥31 ፤ 15፥10) ሲል ተናገረ፡፡

Tuesday, 21 February 2017

Friday, 17 February 2017

በችኩል አገልጋይ

Please read in PDf


ስርጓጉጥ ሳይጠራ
መንገዱ ሳይቀና
ኮረብታው ዝቅ ብሎ
ሸለቆው ደልድሎ
ለመረማመጃ ሳይደላ በቅጡ
እሩጫው ወዴት ነው፣ ችኮላው ምንድር ነው፣ ሳያጠባብቁ?

Tuesday, 14 February 2017

ከኢየሱስ ተኮር - ወደ “አገልጋይ[ስጦታ]” ተኮር ሩጫ (ክፍል አምስት)

Please read in PDF
3.    ለክርስቶስ አገልጋዮች የሆንነው በፈቃዳችን ነው፤ ደኅንነት በደመወዝ መልክ አይገኝም፤ ደኅንነት ሁል ጊዜ ከጸጋ ጋር ብቻ የተያያዘ ነው፡፡ ደኅንነት የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ፣ በሠራነውም ሥራና ሰዓት አይወሰንም፡፡ ከጸደቅንና ከዳንን ደግሞ (1ቆሮ.6፥11)፣ ስለጸደቅንበትና ስለዳንንበት ነገር የምናውጀው እውነትና የምንመሰክረው ምስክርነት አለን፡፡
    “ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም” (ኤፌ.2፥8-9) እንዲል አሁንም፣ ዘወትር መርሳት የሌለብን ነገር፣ መዳን ጥረትን አይጠይቅም፤ አገልግሎት ግን ስለዳንንበትና እውነት መመስከርና ማወጅን ይጠይቃልና ጥረትን፣ ድካምን፣ የወዝ ጥሪትን፣ መውጣት መውረዳችንን ይሻል፡፡ የምንለፋው ትሁታን አገልጋዮች ሆነን ነው፤ ዋጋችን በእርሱ እንጂ በሰው ወይም በሌላ አካል ፈጽሞ አይደለም፡፡ ስለዚህም በፈቃድ አገልጋይ ከሆንለት ጌታ እንጂ ዋጋችንን ከማንም አንቀበልም፡፡ ጌታ አገልጋዮቹን የጠራቸው በፈቃዳቸው ነው፤ “ተከተለኝ” በሚል አጭርና ግልጥ ጥሪ፡፡ ለ“ልዩ ሥራ” ካልሆነ በቀር ጌታ ማንንም አስገድዶ ጠርቶ አያውቅም፡፡ ሁሉን በፈቃዱ ስለሚጠራ የሚከፍለውንም ዋጋንም በተመለከተ፣ እንደወደደ መክፈል እንደሚችል በግልጥ ተናግሯል፤ (ማቴ.20፥11-15)፡፡

Thursday, 9 February 2017

ከኢየሱስ ተኮር - ወደ “አገልጋይ[ስጦታ]” ተኮር ሩጫ (ክፍል አራት)

Please read in PDF
2. ራተኛ(አገልጋይ) ባሪያ “ባሪያ ተገዥ፤ አገልጋይ ሰው የተማረከ ወይም የተገዛ ግዝ፤ ውላጅ፡፡ …” [1] በማለት ይተረጉሙታል አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፡፡ “ነጻነትና መብት የሌለው፥ በራሱ ፈቃድ የፈለገውን ማድረግ የማይችል፡፡ በመጀመርያ እግዚአብሔር አንዱን ለሌላው ባሪያ እንዲሆን አድርጎ አልፈጠረም፡፡ ቃሉ ለመጀመርያ ጊዜ በስካር ኃጢአት ከወደቀው ከኖኅ አንደበት ተገኘ፤ ዘፍ.9፥26፡፡” [2]
   ቃሉ በመርገም መልክ ለካም ልጅ ለከነዓን የተነገረ ነው፤ እርግማኑ ከባድ ከመሆኑም ባሻገር እግዚአብሔርን የማይወዱ[ለፈቃዱ የማይታዘዙ] ሁሉ የሚደርስባቸው እርግማን ነው፡፡ የራስን ወላጅ ሆነ የዘመድን ኃፍረተ ሥጋ መመልከት አጸያፊና ነውር ነውና፤ (ዘሌ.18፥4-17) ይህን ያደረገው ከነዓን የባርነቱም እርግማን በትክክል ደርሶበት አይቶታል፤ (ኢያ.16፥10)፡፡ ከዚህ በኋላ በባርነት መያዝና በዚያ መኖር የኃጢአት ውጤት አንዱ መገለጫ ሆኗል፡፡ ለዚህም የእስራኤል ልጆች በመሳፍንት ዘመን በአረማውን እጅ በተደጋጋሚ መውደቃቸውንና በባቢሎንም መማረካቸው በቂ ምስክር ሆኖ በመጽሐፈ መሳፍንት ተጽፎ አለ፡፡

Sunday, 5 February 2017

ጌታ ኢየሱስ ለምን ተጠመቀ? (የመጨረሻ ክፍል)

Please read in PDF
4.   ድቅን ሁሉ ለመፈጸም   ጽድቅ የሚለው ቃል፣ ቀጥታ ከዕብራይስጥ የተቀዳ ሲሆን ትርጉሙ፥ ፍጹም ትክክለኛነት፣ ቀጥተኛ፣ ፍትሓዊ፣ በጐ ምግባር ማለት ነው፡፡  ይኸውም ከእግዚአብሔር ጋር ባለው ግንኙነት “በትክክለኛ ሁኔታ” ላይ ሆኖ መገኘት ማለትን በግልጥ ያሳያል፡፡ እግዚአብሔር ከመጀመርያው ለሰው ያለው ሃሳቡ እንዲህ ነበር፡፡ ፍጹም ጻድቅና መልካም እንዲሆን፥ ሰው ግን በእግዚአብሔር ፊት በመልኩና በአምሳሉ ሊገኝ አልቻለም፡፡ ወደገዛ መንገዱም በማዘንበል በምሳሌው እንደ መልኩ ማንነቱን በመያዝ (ዘፍ.5፥3) በኃጢአት ተሰነካክሎ ወደቀ፤ ከትክክለኛነትም ተሰናከለና በዕድፈት ረከሰ፡፡
    መጥምቁ ዮሐንስ አስቀድሞ ጌታ ኢየሱስን ለማጥመቅ ፈቃደኛ አልነበረም፤ ምክንያቱም ጌታ ኢየሱስ ምንም በደልና ኃጢአት የሌለበት ፍጹም ጻድቅ መሆኑን አስተውሏልና፡፡ ስለዚህም አብረውት ስለኃጢአታቸው ሊጠመቁ ከቆሙት እንደአንዱ ሊቆጥረው አልደፈረም፤ ይልቁንም ጌታ ኢየሱስ ከሁሉ የተለየ ልዩ መሆኑን የአዋጅ ነጋሪው ሰው ተገነዘበ፡፡ “እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን?” በማለት፣ ራሱን ከኢየሱስ ጋር በማስተያየት፣ ዮሐንስ ራሱ መጠመቅ የሚያስፈልገው ፍጹም ኃጢአተኛ መሆኑን መሰከረ፡፡ በእርግጥም፣ ሰው ከሆነው ከኢየሱስ በቀር አንዳች ፍጹምና ጻድቅ ከምድር ስለጠፋ ክርስቶስ ጽድቃችን ሊሆን መጣ፡፡ እርሱ አንዳች በደልና ነውር ያልተገኘበት ነውና ጽድቅን  በመሥራት ለእግዚአብሔር አቀረበን፤ (ዕብ.4፥14 ፤ 1ጴጥ.2፥22-23)፡፡

Wednesday, 25 January 2017

ጌታ ኢየሱስ ለምን ተጠመቀ? (ክፍል ሦስት)

Please read in PDF
3.    ሰው ኃጢአትና ውድቀት ጋር ራሱን ይደምር ዘንድ ይህ ሃሳብ በመንፈስ ቅዱስና በቃሉ ማስተዋል ካልሆንን በቀር፥ ብዙዎች ተሰነካክለው እንደወደቁበት ልንሰነካከልና ልንወድቅበት እንችላለን፡፡ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ትስብእትነት ላይ ብዙዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊውን እውቀት ባለመያዛቸው ምክንያት ከጥንት ዘመን ይስት እንደነበር ዛሬም ብዙዎች ሲስቱ እያየን ነው፡፡

Friday, 20 January 2017

ጌታ ኢየሱስ ለምን ተጠመቀ? (ክፍል ሁለት)

Please read in PDF
2.   ገረ ሥላሴን ለማብራራትና ለዓለም ሁሉ ለመግለጥ፦ ትምህርተ ሥላሴ በመጽሐፍ ቅዱስ በምልዐት የተብራራ ትምህርት ነው፡፡ በተለይም ትምህርቱ በግልጥ የተሰበከው፤ በጉልህ የታየውና የተረዳው በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሲሐዊ መገለጥ[በጥምቀቱ] ጊዜ ነው፡፡

Wednesday, 18 January 2017

ጌታ ኢየሱስ ለምን ተጠመቀ? (ክፍል አንድ)

    ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመሲሕነቱን አገልግሎት በግልጥ የጀመረው በጥምቀቱ ዋዜማ ነው፤ በነቢዩ ኢሳይያስ አንደበት መሲሑ እንደተነገረው፥ “የአዋጅ ነጋሪ ቃል፦ የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ ጥረጉ፥ ለአምላካችንም ጐዳና በበረሀ አስተካከሉ፡፡ ሸለቆው ሁሉ ከፍ ይላል፥ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይላል፤ ጠማማውም ይቃናል፥ ስርጓጕጡም ሜዳ ይሆናል፤ የእግዚአብሔርም ክብር ይገለጣል፥ ሥጋ ለባሹም ሁሉ በአንድነት ያየዋል፥ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና” (ኢሳ.40፥3-5) ተብሎ የተነገረው ትንቢት በተፈጸመ ማግስት ነው፡፡

Friday, 13 January 2017

ከኢየሱስ ተኮር - ወደ “አገልጋይ[ስጦታ]” ተኮር ሩጫ (ክፍል ሦስት)


  6. ውነተኛ ሯጭ ምትክ ሯጮችን ያዘጋጃል፦ እውነተኛ የክርስትና ሕይወት ሯጭ፥ ልክ እንደእርሱ እውነተኛውን ሩጫ የሚሮጡ ምትክ ሯጮችን ማዘጋጀት አለበት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ አለ፥ “መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤ ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፥ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፥ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም፤” (2ጢሞ.4፥7-8)፡፡
    ቅዱስ ጳውሎስ የሮጠበትን የፊተኛውን ዘመን እውነተኛ ሩጫ በትክክል ካስታወሰ በኋላ፥ እርሱ ሮጦ በድል እንዳጠቃለለ እንዲሁ፥ ሌሎቹም እንዲነሣሱና እንዲሮጡ ይጋብዛል፤ ደግሞ የጋበዘ ብቻ አይደለም፤ እንደጢሞቴዎስና ቲቶ ያሉትን እውነተኛ ሯጮችን ተክቶ ሩጫውን ፈጽሟል፡፡ በዚህ ዘመን ከሚታዩ አስከፊ የደቀ መዝሙርነት ገጽታ አንዱ እውነተኛ የሩጫውን ተካፋዮች ለክርስቶስ ከማብዛት ይልቅ ሰዎችን በራስ ዙርያ ወደማከማቸት የሚሮጠው ሩጫ መብዛቱ ነው፡፡