Please read in PDf
የእስራኤል ልጆች በስደት ምድር በባቢሎን ሳሉ፣ በኢየሩሳሌም የነበረው ዋናው ቤተ መቅደስ ስለፈረሰና በምርኮ ምድር ደግሞ ቤተ መቅደስ መሥራት ስላልተቻላቸው ለጸሎት፣ ቃሉን ለማንበብና ለማጥናት እንዲሁም መንፈሳዊ ሕይወታቸውን ለማሳደግ ምኩራብን በየአቅራቢያቸው ሠሩ፡፡ በምኩራቡ ውስጥም በየቀኑ የሚነበቡ የተለያዩ የሕግና የነቢያት የብራና ጥቅልሎች ቅዱሳት መጻሕፍት ቅጂዎችን አስቀመጡ፡፡
የእግዚአብሔር እውነተኛ ሕዝብ በየትኛውም ሥፍራና ሁኔታ ሊያስቀድመውና ሊጠነቀቅለት
የሚገባው ነገር ከአምላኩ ጋር ያለው ዝምድና፣ ትስስሩና ግንኙነቱ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ይህ ግንኙነት ሊያሳስበው፤ ትኩረት ሊሰጠው
የሚገባው በምቹና የተደላደለ ትርፍ ሰዓት ባለው ጊዜ ብቻ አይደለም፡፡ ይልቁን በስደት፤ ፈጽሞ ምንም ዓይነት ዕድል ላይገኝ በሚችልበት
መንገዱ፣ የጌታ ነገር ቀዳሚና ትኩረቱን ሳቢ ሊሆን፤ በሕይወቱም ጭምር ሊሰጥለት ይገባል፡፡


