Wednesday, 11 January 2017
Thursday, 5 January 2017
“ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት … ተወልዶላችኋልና”(ሉቃ.2፥11)
Please read in PDf
የዳዊት ከተማ ቤተ ልሔም ናት፤ የስሟ ትርጓሜም “የእንጀራ ቤት” ማለት ነው፡፡ በያዕቆብ ዘመን “ኤፍራታ” ተብላ ትጠራ ነበር፤ ቤተ ልሔም የብዙ ባለታሪክ ቅዱሳን አባቶች አገር ናት፤ የኢብጻን፣ የቦዔዝ፣ የእሴይና የዳዊት ከተማ ናት፤ (መሳ.12፥8 ፤ ሩት.2፥4 ፤ 1ሳሙ.17፥12)፡፡ ዳዊት ንጉሥ ስለመሆኑ በሳሙኤል እጅ በቤተ ልሔም ተቀባ፤ (1ሳሙ.16፥13)፡፡ በነቢዩ በሚክያስ አንደበትም፥ “አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፤ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል፤”(ሚክ.5፥2) ተብሎ እንደተነገረው በዚህችው በዳዊት ከተማ ቤተ ልሔም ክርስቶስ ኢየሱስ ተወለደ፤ (ሉቃ.2፥4)፡፡
የዳዊት ከተማ ቤተ ልሔም ናት፤ የስሟ ትርጓሜም “የእንጀራ ቤት” ማለት ነው፡፡ በያዕቆብ ዘመን “ኤፍራታ” ተብላ ትጠራ ነበር፤ ቤተ ልሔም የብዙ ባለታሪክ ቅዱሳን አባቶች አገር ናት፤ የኢብጻን፣ የቦዔዝ፣ የእሴይና የዳዊት ከተማ ናት፤ (መሳ.12፥8 ፤ ሩት.2፥4 ፤ 1ሳሙ.17፥12)፡፡ ዳዊት ንጉሥ ስለመሆኑ በሳሙኤል እጅ በቤተ ልሔም ተቀባ፤ (1ሳሙ.16፥13)፡፡ በነቢዩ በሚክያስ አንደበትም፥ “አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፤ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል፤”(ሚክ.5፥2) ተብሎ እንደተነገረው በዚህችው በዳዊት ከተማ ቤተ ልሔም ክርስቶስ ኢየሱስ ተወለደ፤ (ሉቃ.2፥4)፡፡
Monday, 2 January 2017
ከኢየሱስ ተኮር - ወደ“አገልጋይ[ስጦታ]” ተኮር ሩጫ (ክፍል ሁለት)
2. ሩጫውን በአገባቡ ወይም ዓይኑን ከመሙ[ከመሮጫው መስመር] ሳይነቅል መሮጥ፦ የሯጭ የዘወትር
ተግባር ነው፤ ከመስመሩ ዓይኑን ፈጽሞ መንቀል የለበትም፡፡ ከመሙ ወጥቶ ሮጦ ቢያሸንፍ እንኳ አሸናፊነቱ ይሰረዛል፡፡ የዕብራውያን
ጸሐፊ ይህንን ወደክርስትና ሕይወት ሩጫ በመቀየር፥ “የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ
በትዕግሥት እንሩጥ፤”(ዕብ.12፥2) በማለት ገልጦታል፡፡
በሩጫው ዓይናችንን ፈጽሞ ከጌታ ልናነሳና
ምድራዊ ነገሮች ላይ [እጅግ ጠቃሚ ቢሆኑም እንኳ] ልናደርግ አይገባንም፡፡[1] ክርስቶስን በትክክል እያየን ሩጫችንን ልንሮጥ ይገባናል፡፡ አንዳንድ ጊዜ
ክርስቶስን ልክ በፊታችን እንደተሳለ እንዳናየው የሚያደርግ አዚም ሊኖር ይችላል፤ ልክ የገላትያ ክርስቲያኖች፥ “የማታስተውሉ የገላትያ
ሰዎች ሆይ፥ በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ ነበር፤ ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው?”
(ገላ.3፥1) እንደተባሉ፥ እኛም የአዕምሮ ችግር ሳይኖርብን ክርስቶስን መረዳት ሲሳነን፥ ለእርሱ ሥራ ቸለተኞች ስንሆንና ሩጫችንን
እርሱን ፊት ለፊት ባለማየት ስንመላለስ ወዳለማስተዋል አዚም ውስጥ ልንገባ እንችላለን፡፡
Sunday, 25 December 2016
ከኢየሱስ ተኮር - ወደ“አገልጋይ[ስጦታ]” ተኮር ሩጫ (ክፍል አንድ)
Please read in PDF
የዚህ
ጽሁፍ ዋና ጭብጥ፥
1.
ዋናችን ጌታ ኢየሱስን በክርስትና ሕይወታችን ሁሉ ትኩር ብለን እንድንመለከት፤
2.
ዋናችን የሆነውን ጌታ ኢየሱስን ትተን በእርሱ “ሎሌዎች” ላይ ዓይናችንን የተከልን፥ በንስሐ እይታችንን እንድናጠራ፥
ከሰባኪ አድናቂነትና ተከታይነት ወደጸጋ አደላዳዩና ሠጪው ጌታ እንድናተኩር፤
3.
አገልጋዮች የሆንንም፥ “የሚከተሉንን” ምዕመናንና ምዕመናት የተሰጠንን “ስጦታ” ሳይሆን፥ ሰጪውንና ሁሉን አድራጊውን
እንዲመለከቱ፥ በሁላችንም ላይ የሚፈርደውንና የሁላችንን ሥራ ለሚያየው ጌታ ሕይወታቸውንና መንገዳቸውን አሳልፈው በማስጨከን እንዲሰጡ
በማሰብ የተዘጋጀ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምልከታ ነው፡፡
መንደርደርያ
ለብዙ ዘመናት ሰይጣን ሰዎች ዋናውን ጌታ እንዳይመለከቱና
“ሥጦታውን መመልከት ሠጪውን የመመልከት ያህል ነው” ወደሚል ከንቱ ማታለል ብዙዎችን ሲመራ አይተናል፡፡ በተለይም በዘመናችን ይህ
እውነታ ጎልቶና ደምቆ በመካከላችን በሚገባ ይስተዋላል፡፡ ሰዎች ሰባኪ[ሎሌውን] ብቻ መስማትን ልክ እግዚአብሔርን እንደመስማት ሲቆጥሩት፥
ቅዱሱን ወንጌል ከመመርመርና ጌታ ኢየሱስን በትክክል በመመልከት የክርስትና ሕይወት ሩጫቸውን ከመሮጥ ተዘናግተዋል፤ [ይህ በወንጌሉ
ፍጹም እውነትነት ላይ የቆሙትንና ለቃሉ ፍጹም በመታመን በማገልገል ያሉትን የጌታ ታማኝና እውነተኛ አገልጋዮችን አይመለከትም]፡፡
Tuesday, 20 December 2016
Friday, 16 December 2016
Monday, 12 December 2016
ጸሎትና ጾም ለኢትዮጲያ(የመጨረሻ ክፍል)
2.
“እግዚአብሔር ለዚህ ሕዝብ እንዲህ ይላል፦ መቅበዝበዝን ወድደዋል እግራቸውንም
አልከለከሉም፤ ስለዚህ እግዚአብሔር በእነርሱ ደስ አይለውም፥ በደላቸውንም አሁን ያስባል ኃጢአታቸውንም ይቀጣል፡፡ እግዚአብሔርም፦
ለዚህ ሕዝብ ስለ መልካም አትጸልይላቸው፡፡ በጾሙ ጊዜ ጸሎታቸውን አልሰማም፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን ባቀረቡ ጊዜ
አልቀበላቸውም፤ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም አጠፋቸዋለሁ አለኝ፤” (ኤር.14፥10-12)
በኤርምያስ ዘመን የነበሩት ሕዝቦች ወደእግዚአብሔር
በፍጹም ንስሐ ከመመለስ ይልቅ በክፋታቸው በመጨከናቸው ምክንት ሊመጣ ያለውን ቅጣት ነቢዩ ይናገራል፡፡ በልባቸው ወደጣዖት አምልኮ
አዘንብለውና በእግራቸው ወደዚ እየቸኮሉ ነገር ግን ጾምን ቢጾሙ፣ መሥዋዕትን ቢያቀርቡ እግዚአብሔር በዚህ ፈጽሞ አይረካም፡፡ ኤርምያስ
እንዲህ ላለ ሕዝብ ፈጽሞ እንዳይማልድ በተደጋጋሚ ተክልክሏል፤ በክፋቱ የጸና ሕዝብ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይተዋል እንጂ ምንም አይነት
እርዳታ አይደረግለትም፡፡
Thursday, 8 December 2016
Monday, 5 December 2016
ዘረኛነት - ብሔርተኛነት - የዘመናችን ፈተና - (የመጨረሻ ክፍል)
2. ማሕበረ - ሰበ መስቀሉን ማብዛት፤
ክርስቶስ ኢየሱስ በመስቀሉ ሞት መልካሙን ያደርጉ ዘንድ አዲስ ማሕበረሰብን
ፈጥሯል፡፡ ይህን ማሕበረሰብ ያዋቀረው ደግሞ “… ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር አስታርቆ
ነው (ኤፌ.2፥10 ፤ 16)፡፡ “ሁለታቸው” የተባሉት “በሥጋ አሕዛብ የነበሩት፥ በሥጋ በእጅ የተገረዙ በተባሉት ያልተገረዙ የተባሉትና”
(ኤፌ.2፥11)፤ ቤተ እስራኤል ናቸው፡፡ ከእነዚህ ከሁለቱም አንዳች የዘርና ቀለም፤ የቋንቋና የነገድ ልዩነት ሳይኖር ነው፡፡
“ … አይሁድ ብንሆን የግሪክ
ሰዎችም ብንሆን ባሪያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና። ሁላችንም
አንዱን መንፈስ ጠጥተናል”
(1ቆሮ.12፥13)
|
እንደተባለ ክርስቶስ ኢየሱስ ልዩነትን
ሽሮልናል ብቻ ሳይሆን ፍጹም አንድነትን እንኖርበት ዘንድ ሰጥቶናል፡፡
Monday, 28 November 2016
Tuesday, 22 November 2016
ዘረኛነት - ብሔርተኛነት - የዘመናችን ፈተና (ክፍል ስምንት)
ታዲያ ሃይማኖታዊ ብሔርተኝነት ምንድር ነው?
የብሔርተኝነትን ትርጉም ይዘን ሃይማኖታዊ ብሔርተኝነትን ስንተረጉመው፥
“ለአንድ ተመሳሳይ ወይም በአንድ ውስን ሥፍራ ወይም በአንድ መልክአ ምድራዊ
ክልል ውስጥ ለሚኖሩ፥ በሃይማኖታዊ ግንኙነቶች መተሳሰር፥ በአንድ ቋንቋ መጠቀም[በሃይማኖት ጥላ መሰባበሰብ]፥ በጋራ
ታሪካዊ ሂደት ውስጥ የወል ሥነ ልቦናዊ ገጽታዎችና በሃይማኖታዊ አመለካከቶች መያያዝን ያመለክታል ... ” ብለን በአጭሩ መተርጐም ይቻለናል፡፡
ምናልባትም ለሃይማኖታዊ “ብሔርተኝነት” ከዚህ የተሻለ ትርጉምን ልናመጣለትም
አንችልም፡፡ [1]
እንግዲህ የብሔርተኝነትን ትርጉም አንስተን ከሃይማኖት ጋር ለማሻረክ መሞከር፥ በራሱ ብዙ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነገሮችን እንድንፎርሽ
ያደርገናል፡፡ በክርስቶስ የተመሠረተው ክርስትናችን ለጠቅላላው ዓለም[ሰው] መፍትሔ እንጂ “በሃይማኖት ወገንተኝነት” ላይ በማነጣጠር
ወይም እንዲህ ባለው ነገር ላይ መሠረት በመጣል ፈጽሞ አይደለም፡፡
Wednesday, 16 November 2016
ዘረኛነት - ብሔርተኛነት - የዘመናችን ፈተና (ክፍል ሰባት)
ሃይማኖታዊ “ብሔርተኝነት” ምንድር ነው?
“
... የሃይማኖት ብሔርተኝነት መነሻው አገራችን በሰማይ፤ ኑሮዐችን በዓለመ ነፍስ ከመሆኑ ላይ ነው፡፡ የሃይማኖት ብሔርተኝነት
ሲባልም ሃይማኖትን በሃይማኖት እናት፣ አባትና ብሔር አድርጐ መውሰድ ወይም በአጭሩ የሃይማኖት ወገንተኛ ማለት ነው፡፡ ከዚህም
የተነሣ የሃይማኖት “ብሔርተኝነት” ወንዝ- ጐጥና ዘውግ ዘለል መሆኑን ያስፈልጋል፡፡ የሃይማኖት “ብሔርተኝነት” በቤተ ክርስቲያናችን
የነበረና የቆየ ማእከለ አንድነት እንጂ አዲስ ክስተት አይደለም፡፡ [1]
... የሃይማኖት “ብሔርተኝነት” እያጸጸ መምጣቱንና ውስጡ ጥቅመኝነት ሆኖ ሽፋኑ ወንዛዊ- ጎጣዊ- ዘውጋዊ የሆነ
ብሔርተኝነት መሠረት እየያዘ መሆኑን ነው፡፡ እናም መጪውን ጊዜ ለቤተ ክርስቲያን የተሻለና በጐ ከማድረግ አኳያ የጊዜውን አበው፣
ሊቃውንትና ምእመን በሃይማኖት “ብሔርተኝነት” ዋጅቶ ከወንዛዊ- ጐጣዊ- ዘውጋዊ ብሔርተኝነት ደዌ መፈወስ አማራጭ የሌለው መፍትሔ
ነው፡፡
... ቤተ ክርስቲያን በቀጣይ ከባድ ግን ልትወጣው የምትችለው ፈተና አለባት፡፡ በቃላት የሚፈታና የሚነገር ሳይሆን
በተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚፈተነው፡፡ ከዚህ አኳያ ቀጣዩ ጉዞ በሃይማኖት “ብሔርተኝነት” እጅ ለእጅ መያያዝንና ጠንካራ አንድነትን የሚጠይቅ ነው፡፡ ለምን አልተጣሉም? ለምን አልተከፋፈሉም?
የሚሉ አጽራረ ቤተ ክርስቲያን አርፈው የሚቀመጡበትም ሁኔታ እንደሌለ መገንዝብ ይቻላል፡፡ ... ብፁዓን አበውም፣ ሊቃውንተ ቤተ
ክርስቲያንም ምእመናንም ይህን አውቀው በሃይማኖት “ብሔርተኝነት” ጠንክሮ መጓዝ ይጠበቅባቸዋለን እንላለን፡፡” [2]
|
Friday, 11 November 2016
ዘረኛነት - ብሔርተኛነት - የዘመናችን ፈተና (ክፍል ስድስት)
አማኞች፦ ከእኛ ምን ይጠበቃል?
“አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም
ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና”፤ (ገላ.3፥28) የሚለው ቃል ከክርስቶስ ጋር አንድነት በዘር፣ በማኅበራዊ
ኑሮ ደረጃና በጾታ ልዩነት ገደብ የሌለበት መሆኑን በግልጥ ያሳያል፡፡ ክርስቶስ የመሠረታት አዲስ ኪዳናዊት ሕብረት ልዩ የሚያደርጋት
ይህ ነው፤ ምንም ምን ልዩነት በሰው ልጆች መካከል ፈጽሞ አያደርግም፡፡ “በአይሁዳዊና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ
ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው፤ የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና”፤ (ሮሜ.10፥12)፥ የሚለው ቃል ደግሞ፥
ጌታን ለማመንና በእርሱ ለመዳን ምንም የዘር ቅድመ ሁኔታ አለመቀመጡን እናያለን፤ (1ቆሮ.12፥13 ፤ ኤፌ.2፥15 ይመልከቱ)፡፡
Thursday, 3 November 2016
Tuesday, 1 November 2016
“ … የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ”(ኤፌ.4፥3)
ከአንድነት ወደመንፈስ አንድነት
እንመለስ!
ቤተ ክርስቲያን የአይሁድና የሳምራውያን፤ የአሕዛብም
ድምር ውጤት ናት፡፡ ይህ ፍጹም የመንፈስ አንድነት የተገኘው እንዲያው ዝም ብሎ ሳይሆን የወልደ አምላክ የክርስቶስ ኢየሱስን ሞትና
የደም ዋጋ የጠየቀ፥ በእርሱም የደም ቤዛነት በተደረገ ዕርቅ የተገኘ ነው፡፡ አንድነቱ ተራ ወጥነት ያለው አንድነት ወይም ተመሳሳይነት
ማለት አይደለም፡፡ አንድ የመሆን አንድነት በራሱ ከውጫዊ ተጽዕኖ የሚመጣ የጫናና የፍጹም ውጥረት ዳርቻ ነው፡፡ በአንድነት ውስጥ
አንድ ያልሆኑ ልቦች ብዙ ናቸው፡፡
የመንፈስ አንድነት ግን ከመንፈስ ፍሬዎች አንዱ የሆነና
ከአንድነት የተለየ መልካም ነገር ነው፡፡ የብዙዎች አንድነት ቅድመ መርኅን መሠረት ያደረገ ነው፡፡ ስለዚህም አብረው ያሉ፣ የተስማሙ፣
የማይለያዩ፣ የማይከዳዱ፣ የማይነጣጠሉ … ይመስላሉ እንጂ፥ ፈጽመው አንድ አይደሉም፡፡ ትልልቅና የማይፈርሱ የሚመስሉ አንድነቶች
እንዴት እንደፈረሱ እስኪደንቀን ድረስ ፈጽመው ስም አጠራራቸው እስኪጠፋ ፈርሰዋል፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)




