Please read in PDF
መንግሥት ሆይ! እባክህ ከማሰር ፤ ከማጐር ይልቅ፥ ራራ! ይቅር በል!
ማር!!!
በምዕራቡ ዓለም በተደላደለ መኖሪያ ቤታቸው ተቀምጠው እንደሰበኩን፥
“ጨካኝ ፣ እብሪተኛ ፣ አምባገነን ፣ አረመኔ ፣ ጉበኛ ፣ ዘረኛ ፣ ሴሰኛ ፣ አድርባይ ፣ አፋኝ …” ያሉት ይህ የአገር ቤቱ መንግሥት
ወረደ እንበል፤ ግን እኒህ ዲያስፖራ ፖለቲከኞችና ፈሪሳውያን ሃይማኖተኞች ያልመለሱልን ጥያቄ፥ “ማን እንዲመራን ነው ያቀዱት? ፣
ማንን ይሆን ያዘጋጁልን? እነርሱ ራሳቸው ከአውሮፓና ከአሜሪካ ሊመጡና ሊመሩን? ፣ ወይስ ከዚሁ አገር ቤት የሚያሰናዱልን ነገር
ኖሮ ይሆን?”
አንድ ሌላ ጥያቄ አለኝ? እኒህ “ዲያስፖራውያን የፖለቲካና የሃይማኖት
ዲስኩረኞች” ለመሆኑ ስለአንድነትና ስለመንፈስ አንድነት ለማውራት በእውኑ ሞራሉና ብቃቱ አላቸው? በአንድ ነገር አምናለሁ ፤ የአገር
ቤቱ መንግሥት ብዙ ነውር ፣ ዕድፍ ፣ ርኩሰት ፣ ልክፍት ፣ በደል … አለበት ፤ ይህን አምናለሁ፥ አልጠራጠርም፡፡ አንድ ብርቱ
መከራከርያ ግን አለኝ፡፡ ከአገር ቤቱ መንግሥት ይልቅ “የአሁኑን የነውጥ እንቅስቃሴ እየመራ ያለው የዲያስፖራው ጐልማሳ” ግን ነውሩና
ርኩሰቱ ከአገር ቤት መንግሥት ይበልጣል ባይ ነኝ፡፡