Friday, 7 August 2015

ድንግል ማርያም ፥ በድንግል ማርያም አንደበት ስትገለጥ (ክፍል - 1)

    
                                          Please read in PDF

  የዘመኑ ፍጻሜ ሲደርስ (ገላ.4፥4) በገሊላ ግዛት ናዝሬት በምትባለው ከተማ፥ የሚያስደንቅ የምሥራች  ዜና ተሰማ፡፡ ምሥራቹም በኃጢአት የተበከለው ዓለም ሊቀደስ ፣ ለዓለሙ ሁሉ የሚሆን ምሥራችና መድኃኒት ሕጻኑ ኢየሱስ ሊወለድ እንዳለ ፣  መልአኩ ገብርኤል ከመለኮት ዙፋን ችሎት የተቆረጠውን ውሳኔ ሊያሰማ ወደምድር መጣ፡፡ (ሉቃ.1፥26) ናዝሬት በሰው ሕሊና “መልካም ሰው አይወጣባትም ወይም አይገኝባትም” (ዮሐ.1፥47) ብትባልም፥ ዛሬ ግን መልካም ሰው ድንግል ማርያም ተገኝቶባታል፡፡

Monday, 3 August 2015

ክርስቶስን በሚያባብል ቃል ለምን? (የመጨረሻ ክፍል)



ኃጢአትን በማለዘብ አንቃወምም!

       እንኪያስ! ኃጢአትንና ኃጢአተኝነትን በማለዘብ ወይም በማድበስበስ አንቃወምም፡፡ መቃወም ያለብን ፊት ለፊትና በድፍረት ነው፡፡ ወንጌልን ለመስበክ የምንደፍርበትን ድፍረት ኃጢአትን ለመቃውም ካልደፈርንበት ምስክርነታችን በጌታ ፊት የተናቀና የተጣለ ነው፡፡   በተለይም ተመክረው ፣ ተዘክረው ፣ ተወቅሰው ፣ ተገስጸው ፣ ተለምነው ፣ በቁጣም ቃል ብዙ ተብለው አልሰማ ፤ አልመለስ ያሉትን ሐሰተኛ የአዞ እንባ አንቢ አባባዮችን እንደአረመኔና እንደቀራጭ ቆጥሮ (ማቴ.18፥17) ያለፍርሃት መቃወም አገባብ ነው፡፡

Monday, 27 July 2015

“መለከት ድራማ”ና የመጽሐፍ ቅዱስ ይትበሐልን አጠቃቀሙ



                                                    Please read in PDF

“ምነው የ“ጥበብ” መንገድን ከፈጣሪ ቃል ጋር ካልተዘባበታችሁ በ“ጥበብነቷ” ብቻ ማሳየት አይቻላችሁምን? ስለምንስ የማሰናከያን ድንጋይ በትውልድ መንገድ  ላይ  ታስቀምጣላችሁ?”

     “መለከት” ድራማ በተከታታይነት በኢትዮጲያ ብሮድ ካስት ቴሌቪዥን በእሁድ መዝናኛ ፕሮግራም ይቀርባል፡፡  እንደመታደል ጊዜ ሰጥቶ ብዙም ድራማን የመከታተል ልማድ የለኝም ፤ ድንገት ግን እግረ መንገድ ከመጣ አያለሁ፡፡ በተለይ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስንና ጌታዬ ክርስቶስን “የሚዳስስ”ና በዚህም ዙርያ በአሉታዊም ሆነ በአዎንታዊ መልኩ የሚንጸባረቅ ከሆነ ትኩረቴን አሳርፍበታለሁ፡፡ እናም “መለከት”ን እንደዋዛ አየሁት ፤ የመጽሐፍ ቅዱስ ይትበሐልን በአንዱ ተዋናይ አማካይነት ሲጠቀም አየሁትና በማስተዋል አጤንኩት ፥ ከዚያም ሁለት ነገርን ከውስጡ እንዲህ አስተውዬዋለሁ፡፡

Friday, 24 July 2015

አይበቃም እኮ!


                               Please read in PDF                                           

ልንበላላ ፣ ልንነካከስ ፤
ልንቋሰል ፣ ልንቦዳደስ ፤
ላንተዛዘን ፣ ልንከፋፋ፤
ተጨካክነን ፣ ልንጠፋፋ፤

Monday, 20 July 2015

እኛ የክርስቶስን እንጂ የፖፑን (ጳጳሱን) ቃል አንከተልም!!!


                                     

                                                                             Please read in PDF                                                

የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና፤ ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና። (1ጴጥ.2፥21)

    የዘመን ፍጻሜ ደጅ ላይ ነንና ከሐሰተኛው ጠላት ዲያብሎስ (ዮሐ.8፥44) ብቻ ሳይሆን “የክርስትናን ካባና ላንቃ ከደረቡትም አንደበት ቀጥተኛውን የጠላትን ሐሳብ በአደባባይ እየሰማን ነው፡፡ የሮማው ፖፕ “ጌታ እግዚአብሔር አስሩን ሕግጋትና ሌሎችንም ለማሻሻል ሥልጣን እንደሰጣቸውና እንዳሻሻሉም ሰምተናል” ያውም “ግብረ ሰዶምን እንደቅዱስ ተግባር ከመቀበልና ሌሎችም እንዲቀበሉት ከሚያዝ ስብከት ጋር” ፡፡

Friday, 17 July 2015

ክርስቶስን በሚያባብል ቃል ለምን? (ክፍል ሦስት)

      
                            Please read in PDF

      የሐሰት መምህራን እውነትን ጨክኖ በመናገር ከሚመጣ መከራና ስደት ይልቅ (2ጢሞ.3፥12)፤ እውነትን ከሐሰት ጋር ሸቃቅጦ በመናገር የሚገኘውን ሥጋዊ ጥቅምና የሚከተላቸው የበዛ ቁጥር ሊኖር እንደሚችል በሚገባ ያውቃሉ፡፡ ሙሴ ከላካቸው አሥራ ሁለት ሰላዮች ፥ አሥሩ ይዘው የመጡትን የሐሰት ወሬ ሰምተው ሕዝቡ ሁሉ ተገልብጠዋል፡፡ ለብዙ ዓመታት ከመራቸው እግዚአብሔርና ሙሴ ይልቅ አሥሩን ወዲያው ተቀበሏቸው፡፡ (ዘኁል.14፥2) “የእስራኤልም ልጆች ሁሉ በሙሴና በአሮን ላይ አጕረመረሙ ማኅበሩም ሁሉ፦ በግብፅ ምድር ሳለን ምነው በሞትን ኖሮ! ወይም በዚህ ምድረ በዳ ምነው በሞትን ኖሮ! እግዚአብሔርም በሰይፍ እንሞት ዘንድ ወደዚች ምድር ለምን ያገባናል? ሴቶቻችንና ልጆቻችን ምርኮ ይሆናሉ ወደ ግብፅ መመለስ አይሻለንምን?” ብለው እስከመካድ የደረሱት ከሐሰት መምህራን አባባይ ቃል የተነሳ ነው፡፡

Monday, 13 July 2015

መሞቱ ጥቅም ነው!


                      Please read in PDF   

የ“እኔ አልክድህም” ፣ ስሜታዊ ግለት ፤
ቀደም ቀደም የሚል ፣ የእዩኝ ማንነት ፤
አንተ ደግ መምህር !
አትሞትም ይቅር ! …

Thursday, 9 July 2015

ሐዲስ ሕይወት



                                                 Please read in PDF



ምንጭ ፦ ቴዎፍሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ዘኢትዮጲያ መልእክት ፤ ፩ኛ አመት የፓትርያርክነት በዓለ ሢመት መጽሔት ፤ ግንቦት ፩ ቀን ፲፱፻፷፬ ዓ.ም ፤ ገጽ ፯- ፱፡፡

     ሰላም ለክሙ ወጸጋ እግዚአብሔር አቡነ ወእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘአፍቀረነ ወሐደሰ ለነ ፍኖተ ሕይወት በመንጦላዕተ ሥጋሁ ከመ ናንሶሱ ውስተ ሐዲስ ሕይወት ወወሀበነ ፍሥሐ ዘለዓለም ዘሎቱ ክብር ወስብሐት ለዓለም ዓለም፡፡
     የሰው ልጅ ዳግም ልደት ያገኘበት መንፈሱ ፤ ሕሊናው ፤ ሁለንተናው የታደሰበት ሁል ጊዜ በየቀኑ የሚታደስበት የዘለዓለም ፍሥሐ መገኛ የሚሆን የእግዚአብሔር ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን፡፡

      ይህን የሐዋርያውን መልእክት መሠረት በማድረግ የእግዚአብሔር ረቂቅ ጥበብ በየጊዜው ያስነሣቸው አበው ሊቃውንት እየተመራመሩ ያደራጁትን የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት በዘመናችን የቃልና የጽሁፍ ማሰራጫ ዘዴዎች አማካይነት በአዲስ መልክና አቀራረብ ተርጉመን ለማቅረብ ግዴታችንም ምኞታችንም ስለሆነ በልዑል እግዚአብሔር ፈቃድ ግንቦት  ፩ ቀን ፲፱፻፷፫ ዓ.ም የኢትዮጲያ ፓትርያርክ በኢትዮጲያ ምድር ከተሾመበት ጀምሮ በየጊዜው የሚታተም አንድ መጽሔት መሥርተናል፡፡ ስሙንም “ሐዲስ ሕይወት” ብለነዋል፡፡ ይህም ከላይ የጠቀስነውን የሐዋርያውን ቃል መሠረት በማድረግ ነው፡፡

Sunday, 5 July 2015

ክርስቶስን “በሚያባብል ቃል” … ለምን?! (ክፍል ሁለት)



                                       Please read in PDF

እኒህም፦
       ክርስቶስን እንደሌሎች በሚያባብል ቃል አንሰብክም፡፡
       ሐሰተኝነትንም በማለዘብ አንቃወምም፡፡

ክርስቶስን በሚያባብል ቃል ስላለመስበክ

“እምነታችሁም በእግዚአብሔር ኃይል እንጂ በሰው ጥበብ እንዳይሆን፥ ቃሌም ስብከቴም መንፈስንና ኃይልን በመግለጥ ነበረ እንጂ፥ በሚያባብል በጥበብ ቃል አልነበረም።” (!ቆሮ.2፥4-5)

   ወንጌል ስንሰብክ የሰዎችን ነጻነት (የአመለካከትና የማሰብ) አንጋፋም፡፡ ይህንን ላለመጋፋት ዕውቀትን በጥበብ የመግለጥ መንፈስ ቅዱሳዊ ጸጋን እንጂ (ሐዋ.17፥16-17 ፤ 1ቆሮ.12፥8) የማባበልና የመሸቃቀጥን መንገድ አንከተልም፡፡ የተቆረጠን እውነት ለመናገር በእርግጥም የቆረጠ ልብና መንፈሳዊ ጭካኔ ያስፈልጋል፡፡

Wednesday, 1 July 2015

ዲያስፖራዎቻችንን አናምናቸውም!!!

     
                                       Please read in PDF

     ይህንን ፎቶ ሳይ፥ ደንግጬ ክው ብዬ ነው የቀረሁት!!!  ማን ያምናል ኢትዮጲያውያን “ግብረ ሰዶም በመጽደቁ ደስ ብሏቸው ሰልፍ ወጡ ፤ ወይም እንዲጸድቅላቸው እነርሱም ሰልፍ ወጡ” ቢባል?! ግን ይኸው ሆኖ አየን፡፡

   

Sunday, 28 June 2015

ስለግብረ ሰዶማዊነት ከአየርላንድ ስህተት ምን እንማራለን?

     
                            Please raed in PDF                        

   ጌታ እግዚአብሔር የእስራኤል ልጆች ከግብጽ በወጡ ጊዜ እርሱን በማክበርና በመፍራት እንዲያመልኩት በዓላትን ሰጥቷቸዋል፡፡ ከተሰጡት በዓላት መካከል ደግሞ የፋሲካ ፣ የመከርና የዳስ በዓላት የትኛውም እስራኤላዊ ከሚኖርበት ከስደት ምድሩ በመምጣት በእስራኤል ምድር ተገኝተው እንዲያከብሩ አዟቸዋል፡፡ (ዘጸ.23፥14፥17) በእነዚህ የበዓል ወራት የእስራኤል ጎዳናዎች ሁሉ የሚሸቱት እጅግ የተወደደውን የመንፈሳዊነትን ለዛና ዝማሬ ነው፡፡
      ከጥቂት ዓመታት በፊት በካቶሊክና በፕሮቴስታንት ጎራ ክርስትናዋን ከፍላ ጎዳናዎቿን በደም ያጨየቀችው አየርላንድ ፤ አሁን በጎዳናዎቿ የተሰማው ነውር ጆሮን ጭው የሚያደርግ ነው፡፡ ግብረ ሰዶምን በወንጀል ህጓ ጠቅሳ በመከላከልና ለጋብቻ ባላት እሴቷ በአገራችን ካለው ሕግና እሴት ጋር እጅግ የተቀራረበ ነበር፡፡ አየርላንድ በወንጀል ህጓ በግልጥ ግብረ ሰዶምን መከልከል ብቻ ሳይሆን ፈጽመው የተገኙትንም ትቀጣ ነበር፡፡

Sunday, 21 June 2015

ክርስቶስን “በሚያባብል ቃል” … ለምን?! (ክፍል አንድ)

    
                                               Please read in PDF

    ጌታ እግዚአብሔር የነጻነት አምላክ ነው ፤ የወደድነውን ፣ ሕሊናችን የመረጠውን ኃላፊነትን ከሚያስከትለው ውጤት ጋር የመቀበል ሙሉ ነጻነትን ሰጥቶናል፡፡ መንገዳችንን እንደእስራኤል ዘሥጋ ቀድመን ማጥራትና መምረጥ ከእኛ ነው የሚጠበቀው፡፡ መንገዶቹም በረከትና መርገም የሚባሉ እንጂ  ሌላ ሦስተኛ አማራጭ የለም፡፡ ይህንን እውነት ነቢዩ ቅዱስ ሙሴ ምድረ ርስትን ሊወርስ ላለው ፥ ለአዲሱ ትውልድ ሕጉን ለማስተማር ፤ የምክርንም ቃል በተናገረበት አንቀጹ እንዲህ ብሏል፦
“እነሆ፥ እኔ ዛሬ በፊታችሁ በረከትንና መርገምን አኖራለሁ፤ በረከትም፥ እኔ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ብትሰሙ ፣ መርገምም፥ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ባትሰሙ፥ ዛሬም ካዘዝኋችሁ መንገድ ፈቀቅ ብትሉ፥ ሌሎችንም የማታውቋቸውን አማልክት ብትከተሉ ነው፡፡” (ዘዳግ.11፥26-29)

Tuesday, 16 June 2015

በክስ አታዳክሙኝ!


                    Please read in PDF  

ለምን እክዳለሁ ፣ አመንዝራነቴን ፤
ሌባና አመጸኛ ፣ ስግብግብነቴን ፤
አላስተባብልም ፣ ስሁት ሰው መሆኔን … ፤

Wednesday, 10 June 2015

ቅዱስ ሲኖዶስና የመሰብሰቡ ዓላማ (የመጨረሻ ክፍል)



3. በግፍና ያለሥራው የሚወገዝ እንዳይኖር ለመከላከል

      “ … ወደጌታችን ወደኢየሱስ ክርስቶስ በፍጹም ንጽሕና በሚቀርቡ ገንዘብ፡፡ ከካህናት ወገን ወይም ከሕዝቡ ወገን ቢሆን ኤጲስ ቆጶስ አውግዞ የለየውን ሰው ፍርድ ይመረምሩ ቸልታ እንዳይሆን ወይም ይህን በሚመስል ነገር ሁሉ እንደተገለጠላቸው ይፈርዱ ዘንድ፡፡” የሚለው የፍትሐ ነገሥቱ አንቀጽ አድሎዐዊነት እንዳይከሰት በውስጡ ማሳሰቢያ አዘል መልዕክት አለው፡፡ የቱም ጤናማ አባወራ ወይም የቷም ጤናማ እማወራ ልጆቿም የምታሳድገው ባለማበላለጥ በእኩልነት ነው፡፡ ኤጲስ ቆጶስም አማኞችን ሲመራ ልክ ቤተሰቡን እንደሚመራው አይነት ምንም አድሎ በማይኖርበት መልኩ ሊሆን ይገባዋል፡፡ (1ጢሞ.3፥4)

Thursday, 4 June 2015

ጰራቅሊጦስ- መንፈስ ቅዱስ


                             Please Read in PDF


  ከግሪኩ “ፓራክሊቶስ” ወይም ከዕብራይስጡ “ፕራቅሊጥ” ከሚለው ግስ የተገኘው “ጰራቅሊጦስ” የሚለው ቃል ትርጉሙ “ አማላጅ ፣ አስታራቂ ፣ አፍ ፣ ጠበቃ ፣ ትርጁማን ፣ አምጃር ፣ እያጣፈጠ የሚናገር ፣ ስብቅል ካፉ ማር ጠብ የሚል፡፡ … ፤ ናዛዚ ፣ መጽንዒ ፣ መስተፈስሒ ፤ መንፈስ ቅዱስ፡፡” በማለት አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ተርጉመውታል፡፡ (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ/አለቃ/፤ መጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፡፡(1948 ዓ.ም)፤አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፡፡ ገጽ.907)