ከግሪኩ “ፓራክሊቶስ” ወይም ከዕብራይስጡ
“ፕራቅሊጥ” ከሚለው ግስ የተገኘው “ጰራቅሊጦስ” የሚለው ቃል ትርጉሙ “ አማላጅ ፣ አስታራቂ ፣ አፍ ፣ ጠበቃ ፣ ትርጁማን ፣
አምጃር ፣ እያጣፈጠ የሚናገር ፣ ስብቅል ካፉ ማር ጠብ የሚል፡፡ … ፤ ናዛዚ ፣ መጽንዒ ፣ መስተፈስሒ ፤ መንፈስ ቅዱስ፡፡” በማለት
አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ተርጉመውታል፡፡ (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ/አለቃ/፤ መጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፡፡(1948 ዓ.ም)፤አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፡፡ ገጽ.907)
Thursday, 4 June 2015
Sunday, 31 May 2015
ለመኪና ሸላሚዎችና ተሸላሚዎች “አማኞች” ምክር ቢሆን!
“የሚያበራየውን በሬ
አፉን አትሰር” (ዘዳ.25፥4 ፤ 1ቆሮ.9፥9)
ቅዱስ ነቢይ ሙሴ፥ እስራኤል የሚገለገሉባቸውን እንሰሳት በተለይም በሬ እያበራየ
ባለበት ወቅት ጤንነቱ እንዲጠበቅ በቂ ምግብ ማግኘት እንዳለበት ሕዝቡን ያዛል፡፡ ይህም በመራራት ፣ የሚሰጡትን አገልግሎት በማሰብ
እንሰሳቱን መንከባከብ ፣ ተመጣጣኝና የሚበቃቸውን ያህል መብልን ሊሰጣቸው እንደሚገባ ያሳስባል፡፡ ይህ ለእንሰሳት የተነገረው ቃል
፥ በአዲስ ኪዳን ቃል በቃል ለጌታ ወንጌል አገልጋዮች የአገልግሎት መርሕ ተደርጎ ተወስዷል፡፡
Friday, 29 May 2015
ቅዱስ ሲኖዶስና የመሰብሰቡ ዓላማ (ክፍል - 2)
“በበጋና በበልግ ወራት ቸነፈር የድንገት ሞት ይበዛልና ከሞት አስቀድሞ ፍቅር ሰላም ይሆን ዘንድ፡፡” እንዲል “ … ለእርሱ ስለ ሆኑት ይልቁንም ስለ ቤተ ሰዎቹ የማያስብ ማንም ቢሆን፥ ሃይማኖትን የካደ ከማያምንም ሰው ይልቅ የሚከፋ ነው።” (1ጢሞ.5፥8) በሚራራና በፍቅር ስስት ለሃይማኖት ቤተሰብ ማሰብ ከአማኝ ሁሉ የሚጠበቅ መንፈሳዊ ግዴታ ነው፡፡ ከአንደኛው ሃሳብ ጋር ብናስተሳስረው የአምልኮዓችን ጤንነት ያለው ለባልንጀራችን ባለን የርኅራኄ ዕይታ ነው፡፡ ባልንጀራችን ለአደጋ ተጋልጦ (ሉቃ.10፥29-37) ፣ ተርቦ ፣ ተጠምቶ ፣ ታርዞ ፣ ታስሮ (ማቴ.25፥37-40) ፤ በስደትና በመቅበዝበዝ ሲኖር ሳለ እኛ ተቀማጥለን ልብስና ምግብ በማማረጥ ያማሩ ቤቶች ሠርቶ ዕቃዎችን በመገጥገጥ እንድንኖር ክርስቲያናዊ አስተምህሮም ሆነ ትውፊቱ በዝምታ ይነቅፈናል፡፡
Saturday, 23 May 2015
ድል የነሣው ጌታ - አርጓል!
ጌታ ወደሰማያት ያረገው ከአባቱ ዘንድ የተላከበትን ዋናውን ዓላማውን “እኔ ላደርገው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር አከበርሁህ፤” (ዮሐ.17፥4 ፤ 13፥31) በማለት ፈጽሞ (ዮሐ.19፥30) ያከናወነ መሆኑን ተናግሯል፡፡ (ዮሐ.19፥30) ጌታችን ከአባቱ ዘንድ የተላከበት ዋና ዓላማው፥ የሰውን ልጅ ከዘላለም ሞትና ቀንበር ማዳን ነው፡፡ (ሉቃ.9፥56 ፤ 19፥10 ፤ ዮሐ.3፥15 ፤ 17 ፤ 8፥15) ይህንን በመስቀል ላይ በሠራው የፍቅር ሥራው ፈጽሞታል፡፡ ድል መንሳቱንና የሰው ልጆችን መዳን መፈጸሙን ስናነሳ ፥ በጌታ የሆነውን ሁለት ነገሮች ማስታወስ ግድ ይለናል፡፡
Monday, 18 May 2015
ቅዱስ ሲኖዶስና የመሰብሰቡ ዓላማ (ክፍል - 1)
“በየቦታው ሁሉ ኤጲስቆጶሳት በያመቱ ሁለት ጊዜ ከጳጳሳቸው
ወይም ከሊቀ ጳጳሳቸው ዘንድ ይሰብሰቡ፡፡ መጀመርያ ከጾመ ፵ በፊት ይሁን፡፡ ክፉንና ቁጣን በሚያርቁ ገንዘብ ቁርባናቸውም ለእግዚአብሔር
ንጽሕት ክብርት ቅድስት ትሆን ዘንድ፡፡ ሁለተኛውም ከበዓለ መስቀል በኋላ በመከር ወራት ይሁን፡፡ በበጋና በበልግ ወራት ቸነፈር
የድንገት ሞት ይበዛልና ከሞት አስቀድሞ ፍቅር ሰላም ይሆን ዘንድ፡፡ ወደጌታችን ወደኢየሱስ ክርስቶስ በፍጹም ንጽሕና በሚቀርቡ
ገንዘብ፡፡ ከካህናት ወገን ወይም ከሕዝቡ ወገን ቢሆን ኤጲስ ቆጶስ አውግዞ የለየውን ሰው ፍርድ ይመረምሩ ቸልታ እንዳይሆን ወይም
ይህን በሚመስል ነገር ሁሉ እንደተገለጠላቸው ይፈርዱ ዘንድ፡፡”
(ፍትሐ ነገሥት አን.5 ቁ.165 ገጽ
61)
|
Thursday, 14 May 2015
Friday, 8 May 2015
“ … ለደቀ መዛሙርቱ እንደገና ተገለጠላቸው” (ዮሐ.21፥1)
ጌታችን ከሙታን መካከል ከመነሳቱ በፊት ገና በተሰቀለ ጊዜ በደቀ መዛሙርቱ
ልብ የቀረው ነገር እጅግ አስደንጋጭ ነገር ነበር፡፡ እንዲያውም ተስፋ እስከመቁረጥም አድርሷቸው ሉቃስና ቀለዮጳ ወደመጡባት ከተማ
ወደኤማሁስ(ሉቃ.24፥13) ፥ ብዙዎቹም ጥለው እንደሸሹ ያልተመለሱ ሲሆን (ማቴ.26፥56) ፥ ስምዖን ጴጥሮስ ፣ ዲዲሞስ የተባለው
ቶማስ ፣ ናትናኤል ፣ የዘብዴዎስ ሁለቱ ልጆች (ያዕቆብና ዮሐንስ) ደግሞ እጅግ ተስፋ ከመቁረጥ የተነሳ የዕለት ጉርሳቸውንና የዓመት
ልብሳቸውን ለመሸፈን ጌታ እነርሱን ከጠራበትና ትተውት ተከትለውት ወደነበረው (ማቴ.4፥18 ፤ ዮሐ.21፥1) ወደቀደመ ህይወታቸው
አሳ አስጋሪነት(አጥማጅነት) ተመልሰው ተሰማሩ፡፡
Monday, 4 May 2015
ሁለት ብዕርና ምላስ ላላቸው “ሰባኪዎች” ሙግት አለኝ!
ሰሞኑን በISIS ከታረዱት ወገኖቻችን መካከል ኤፍሬም የማነ ስለተባለ
ኤርትራዊ ወንድማችን ቀድሞ ሲወራ የነበረው ጀማል በሚል የእልምና ስም እንደሆነና የእምነቱም ተከታይ እንደሆነ ፤ አብሮ ለመሰዋት
በመወሰኑ ከክርስቲያን ወንድሞቹ ጋር መታረዱን ብዙ ንግግሮችና ጽሁፎችን አድምጠንም ፤ አንብበንም ነበር፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ
ከዚህ ቀደም ሲነገሩም የነበሩ ኢ-መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆኑ አስተምህሯዊ ንግግሮች ስናደምጥም ፤ ስናነብም ታዝበናል፡፡ በተጨማሪም ጥቂት
የማይባሉ ሰባኪዎች የቤተ ክህነቱንና የቤተ መንግሥቱን የሚድያና የስብከት አውደ ምህረትን ተቆጣጥረው “ጀማል ከክርስቲያን ወንድሞቹ
ጋር ሰማዕት ሆነ” በሚለው ዙርያ የተናገሩትንም ሰምተናል ፤ የጻፉትንም አይተናል፡፡ እኒህ ሰባኪዎች ደስ ሲላቸው ራሳቸውን እንደ“ተመራማሪ”
፥ ሲላቸው ደግሞ እንደየ“ፖለቲካ ተንታኝ” ቆጥረው ሳያበቁ “የእግዚአብሔር ቃል እውቀት ሙላት” እንዳላቸውም ደግሞ ለመስበክ ደፍረው
ሲቀርቡም እናያለን፡፡
Monday, 27 April 2015
ደማቸው ድምጽ አለው!
ከሩቅ
የሚሰማ ፣ ከአድማስ ባሻገር፤
ከምድር
ዳርቻ ፣ ከቀላያቱ ዳር፤
ሰው
ከማይኖርበት ፣ ከዚያ ምድረ በዳ፤
በረሃብና
ጥም ፣ ሥጋቸው ቢጎዳ…
Wednesday, 22 April 2015
“ጌታ ሆይ፥ በISIS ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው”
በድጋሚ በግፈኛው ISIS ለተሰው ክርስቲያን ኤርትራውያን ፣ ኢራቃውያን
ቤተሰቦች ጌታ መንፈስ ቅዱስ መጽናናትን እንዲያድላቸው ብርቱ ጸሎታችን ነው!!!
የአንዲት ሕያው ቤተ ክርስቲያን ልዩና የሁል ጊዜ መገለጫ፥ “የእግዚአብሔርን
ቃል ለሁሉ በማዳረስ ማስፋትዋና የደቀ መዛሙርትን ቁጥርና እጅግ የሚታዘዙትንም ማብዛቷ ነው፡፡” (ሐዋ.6፥7) የባለበት ሂድ ወይም
የእየቀጨጩ ዕድገት ጤናማነቱ ተፈጥሮዐዊም ፤ መንፈሳዊም አይደለም፡፡ በብዛትም በጥራትም ማደግ የጤናማ ተፈጥሮዐዊና መንፈሳዊ ዕድገት
መገለጫ ነው፡፡ ወንጌሉ ሕያው ነውና ተበትኖ ፤ ተሰብኮ እንደዋዛ አይቀርም ፤ ሕያው ፍሬንም ያፈራል እንጂ፡፡
ክርስትና
ገና ጉዞውን በጀመረበት ቀደምት ጊዜያት፥ በአንድ የስብከት ርዕስና በአንድ ብርቱ ተአምራት ስምንት ሺህ የሚጠጉ አማኞች ወደአንድ
መቶ ሐያው የጌታ ቤተሰብ ተጨመሩ፡፡ ሥራውን ሠሪው መንፈስ ቅዱስ ስለሆነ የቁጥሩ አጨማመር ከመደመርም ከብዜትም ይልቃል፡፡ እኛ
የቀደምንበት አገልግሎት ጠላትን አለጊዜው ያጎለምሳል ፤ ጌታ የቀደመበት አገልግሎት ግን ጠላት ተኩላ እያለ ሥራውን ያሠራል፡፡(ማቴ.10፥16)
Monday, 20 April 2015
“ISIS” በድርጊቱ እኛን ምን ያስተምረናል?
አስቀድመን በድርጊቱ እጅግ ላዘኑ የሟች ቤተ ሰቦችና ክርስቲያኖች ሁሉ የመጽናናትን መንፈስ
አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ እንዲያድላቸው እንመኛለን፡፡
አለሙ እጅግ
በክፋት እንደተያዘ (1ዮሐ.5፥19) ፤ ክፉዎችም ምድርን ሊያስጨንቋት እንደሚችሉ ታላቁ መጽሐፍ በግልጥ ይነግረናል፡፡ (ማቴ.24፥21)
ክፉዎች ምድርን የሚያስጨንቋት በሦስት ብርቱ ምክንያቶች ይመስለኛል ፦
1. የእግዚአብሔር ሕዝብ ከእግዚአብሔር
ሲለይ፤
2. ህዝቡ መለየቱን ሳያውቅ ንስሐ ሳይገባ
ሲቀር ፤
3. ያመንነው ወንጌል ጠላትን እጅግ
ያስጨነቀው እንደሆን፡፡
Saturday, 18 April 2015
Saturday, 11 April 2015
“የተሰቀለው … ተነስቶአል ፥ በዚህ የለም፤” (ማር.16፥6)
እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ!!!
የሙታን ትንሳኤ ትምህርት ክርስትና ከቆመባቸው መሠረታውያን ዶግማውያን
ትምህርቶች ከሆኑት አንዱና ዋናው ትምህርት ነው፡፡ (1ቆሮ.15፥13
፤ ዕብ.6፥2) መናፍቃን ከሚመዘኑበት መመዘኛ አንዱ ለትንሳኤ ሙታን ባላቸው የአስተምህሮ አቋም ነው፡፡ የትኛውም አማኝም ሆነ የእምነት
አቋም ትንሳኤ ሙታንን በግማሽም ቢሆን ባጠቃላይ ቢክድ በቀደመው ዘመን ከነበሩት መናፍቃን እንደአንዱ መቆጠሩ ምንም የማያሻማ ነው፡፡
ሐዋርያው ለዚህም ነው ፦ “ትንሣኤ ሙታንስ ከሌለ ክርስቶስ አልተነሣማ ፤ ክርስቶስም ካልተነሣ እንግዲያስ ስብከታችን ከንቱ ነው
እምነታችሁም ደግሞ ከንቱ ናት ፤ ደግሞም፦ ክርስቶስን አስነሥቶታል ብለን በእግዚአብሔር ላይ ስለ መሰከርን ሐሰተኞች የእግዚአብሔር
ምስክሮች ሆነን ተገኝተናል፤ ሙታን ግን የማይነሡ ከሆነ እርሱን አላስነሣውም።” (1ቆሮ.15፥13-15) በማለት አጽንቶ የተናገረው፡፡
ቤተ ክርስቲያንም ለዚህ በአንቀጸ ሃይማኖቷ “የሙታንን ትንሳኤ እናምናለን” በማለት በግልጥ የምትመሰክረው፡፡
Wednesday, 8 April 2015
በኢየሱስ ላይ የተሤረ ሤራ (ሉቃ.22፥3-6)
የተወደደው ጌታችን መድኃኒታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ዕውር ስላበራ ፣ ለምጻም ስላነጻ ፣ አንካሶችን ስላስኬደ ፣ ደንቆሮችን እንዲሰሙ ስላደረገ ፣ ሽባ ስለተረተረ
፣ ጉንድሾችን ስላዳነ ፣ ጎባጣ ስላቃና ፣ ሙታንን ስላስነሳ ፣ አጋንንትን ስላወጣ (ማቴ.9፥25 ፤ 11፥5-6 ፤ 15፥30-31)
፣ በድካም መንፈስ ተይዘው ለሚሰቃዩት ዕረፍትን ስላደለ (ሉቃ.13፥11) ፣ ኃጢአተኞችን ስለተቀበለና ከእነርሱም ጋር ስለበላ
(ሉቃ.15፥2)
Sunday, 5 April 2015
ሆሳዕና መባል ይገባዋል!!!
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአባቱና ለእኛ
የታዘዘበትን የገዛ ዘመኑን (1ጢሞ.2፥7) በመፈጸም ወደአባቱ ለመሄድ በመወሰኑ ምክንያት ለመጨረሻ ጊዜ ከኢያሪኮ
(ማቴ.20፥29 ፤ ማር.10፥46 ፤ ሉቃ.19፥1) “ወደ ኢየሩሳሌምም ከደብረ ዘይት
አጠገብ ወዳሉቱ ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታንያ” ሄደ፡፡ ጌታችን ወደኢየሩሳሌም የወጣው አይሁድ እንደሚገድሉት ፤ በእርሱም ላይ እንደተነሳሱ
እያወቀ ነው፡፡ (ማቴ.20፥17-19 ፤ ማር.10፥32 ፤ ሉቃ.9፥22 ፤ 44 ፤ 18፥31) ነፍሱን በፈቃዱ ስለበጎቹ ያኖረው ጌታችን
(ዮሐ.10፥16) ከታላቅ ፍቅሩ የተነሳ ነው ስለእኛ የሞተው፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)









