3. ደቀ መዛሙርትን ወደኋላ ይስባሉ(ቁ.30)
ጌታ ኢየሱስ በወንጌል “መስቀሉንም የማይዝ በኋላዬም የማይከተለኝ ለእኔ
ሊሆን አይገባውም።” ብሏል፡፡ (ማቴ.10፥38) እኛ ሁል ጊዜ ከክርስቶስ
በኋላ ነን፡፡ ተፎካካሪ ስላልሆንን ከጐኑ ፤ ወይም የተሻልን ሆነን ከኋላችን የምናስከትለው አይደለንም፡፡ እርሱ ሰባሪ ነውና ሁል
ጊዜ ከፊት የሚወጣ ነው፡፡ (ሚክ.2፥13) ተመርቆ የተከፈተው አዲስ፤ ህያው መንገድና (ዕብ.10፥19) ቀድሞም በመንገዱ የሄደበት
እርሱ ስለሆነ እኛ የእርሱን ፋናና ፍለጋውን የምንከተል ነን፡፡ (1ጴጥ.2፥21) ይህ ጉዞ የዕለት ተዕለትና ያለምንም ማቋረጥ ልናደርገው
የሚገባን ነው፡፡(ሉቃ.9፥23)


