እንዳልተበጃጀ፣ በእግዜር ምስያ
እንዳልተፈጠረ፣ በመልኩ በአርዓያ
ራሱን ጫፍ ላይ ሰቅሎ፣ ሥጋውን አግንኖ
አስገኚ ነኝ አለ፣ አስገኚን ኮንኖ፡፡
ሚስቱን በቀኝ ክንዱ፣ ታቅፎ እየሳመ
እየበላ እየጠጣ፣ የላመ የጣመ
ቃሉን አመንፍሶ፣ እኔው መንፈስ አለ ...
እኮ እሱ ነው መንፋሽ?
ደግሞ፣ ልክ እንደእግዜሩ፣ እኮ እሱ ነው ነጋሽ?
ይኼ ድኩም ፍጡር፣ ይኼ ሥጋ ለባሽ!?
እንዳትሳሳቱ!
የሰው ጥበብና መንፈስ አትጋቱ!
እንዳትነጠቁ!
ከአመናፋሾች፣ መንፈስ ተጠንቀቁ!
እኔስ ...
ለክፉ ቀን ወዳጅ፣ የማይኾነኝን ሰው
እኮ ለእግዜርነት? ያውም ለጌትነት? መቼም መች አላጨው!!!
እውነትም እንዴት ሊታጭ? ተባረክ አቡ
ReplyDeleteያሳዝናል ትምህርቱ ይህን ያህል ከእግዚአብሔር ጋር ያደፋፍራል ማለት ነው?
ReplyDeleteyetewedede gtm tebarek
ReplyDelete