Please read in PDF
ከብርሃናት
ዙፋን የአህያ ጀርባ
ከወርቅ
ምንጣፍ ይልቅ መናኛ ዘንባባ
ከሊቃውንት
ይልቅ የህፃናት አፍላ
ወዶ
የመረጠ እንደ ማር ወለላ
ዝቅ
ዝቅ ብሎ ውርንጫይቱን ሽቶ
ባማረ
ሰገነት መቀመጥን ትቶ
ሠላማዊ
ነቢይ የሰላም አለቃ
በሚጠቡ
ህፃናት ለመመስገን በቃ፡፡
በፍርድ
ምልክት እሾሀማ ዘንባባ
በፈውስ
ትዕምርት በልስልሱ ወይራ
ታጅቦ
በህጻናት በአላዋቂዎች
ታየ
መድሀኒዓለም ድንቁ የምስራች
ቃል
አካላዊ ቃል ሰማያዊ
ድሀ
የማትረሳ ደግ ሣምራዊ
ሆሳዕና
ላንተ አሁን ለምታድን
ለነፃነት
ጌታ ለምትፈታ እስርን
ርቃችሁ
የምትቆሙ ሊቀ ሊቃውንቱ
ተከፍቶ
ዕልፍኙ የልባችሁ ቤቱ
ምስጋናውን
አብዙ ለከበረ ስሙ
ለትሁቱ
ጌታ በትህትና መንፈስ እናንተም ተቀኙ፡፡
ህፃን
አፍን ከፍቶ
ድንጋይ
ድምጽ ሠጥቶ
ድርቡን
ምስጋና ቅኔ ከተቀኘ
እናንተ
ታላላቅ ምነው ቀኝ ዐይናችሁ ክፉ ተመቀኘ?
ሆሳዕና
ለርሱ ላዳነን መከታ
በክንፎቹ
ጥላ ላሳረፈን ጌታ፡፡
very nice
ReplyDelete