በኹለተኛው ሐዋርያዊ ጉዞው፣ ቅዱስ ጳውሎስና ሲላስ ወንጌል በመመስከር ካለፉባቸው ከተሞች አንዷ ተሰሎንቄ ናት፤ “በአንፊጶልና በአጶሎንያም ካለፉ በኋላ ወደ ተሰሎንቄ መጡ፥ በዚያም የአይሁድ ምኵራብ ነበረ።” (ሐዋ. 17፥1) እንዲል፣ ወደ ተሰሎንቄ እንደ ገቡ ያደረጉት እንደ ልማዳቸው ከቅዱሳት መጻሕፍት እየጠቀሱ ወንጌልን ማስተማር ነበር። የቅዱስ ጳውሎስና ሲላስም የምስክርነታቸው ማዕከል “ይህ እኔ የምሰብክላችሁ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው” የሚል ነው፤ ምክንያቱም “ክርስቶስ መከራ እንዲቀበልና ከሙታን እንዲነሣ ይገባው ነበርና”።
Sunday, 17 February 2019
Monday, 11 February 2019
ቤተ ክርስቲያን ተጐታችና ዘመነኛ ችግሮቿን አስተውላ ይኾንን!? (የመጨረሻ ክፍል)
1.10.
የዘፋኞችንና የአለማውያንን ዝናና ዕውቅና “መቀላወጥ”
ቤተ ክርስቲያን ከአስተማሪዋ መንፈስ ቅዱስ የተማረችው አንድ ትልቅ
እውነት “ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞትን በመካድ … ራስዋን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን መኖርን”
ነው (ቲቶ 2፥12-14)። “እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው
መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ እንጂ፥ በእኛ መልካም ሥነ ምግባር አለመዳናችንንም አውቀን” (ቲቶ 3፥5) መዳናችንን በመልካም
ሥራ መገለጽ እንዳለበት ጸጋን አደላዳዩ መንፈስ ቅዱስ ያስተምረናል። ምክንያቱም ትክክለኛ የኾነ ሥነ ምግባር ምንጩ ትክክለኛ ትምህርት
ነውና።
Tuesday, 5 February 2019
ዘመነኛ “አገልጋዮችን” ሳስብ ትዝ የሚለኝ እንዲህ ነው!
ጌታ አትረፍርፎ ባርኮኛል፣ ዲታና ቱጃር አድርጐ¡ እንዴ ጌታ
ቢባርከኝ አይደል እንዴ የ10 ሚሊየን ብር መኪና ለራሴ፣ የ12 ሚሊየን ብር መኪና ለባለቤቴ መግዛቴ?¡ ጌታማ ልዩነት
ያደርጋል፣ እንኳን በማያምኑትና በእኔ፣ በሚያምኑትና በእኔ መካከል ራሱ ልዩነት ያደርጋል፣ አዎን ያደርጋል፣ ስለሚያደርግም ነው፣
የ200 ሚሊየን ብር መኖሪያ ቤት የሰጠኝ፤ ደግሞ ባርኮቱ እጅግ በጣም ስለተትረፈረፈልኝ፣ ከሰሞኑ ደግሞ የ600 ሚሊዮን ብር
ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ላሠራ ነው፤ ገና ደግሞ በእስቴዲየም ደረጃ የወንጌል ማገልገያ አዳራሽ እናሠራለን፤ ለወንጌልማ ሰማይ
ጠቀስ ሕንጻ ሊገነባለት ይገባል¡¡¡ ለምን ብለን በየመንደሩ፣
ለምን ብለን በየቀዬው፣ ለምን በየገበያው፣ ለምን በየወንዛ ወንዙ እየሄድን እንደ ኢየሱስና ጳውሎስ እንደ ቀደሙት ደቀ መዛሙርት
ለምን “ሳይመቸን እየተንዘላዘልን” እንሰብካለን?¡ ኢየሱስ ራሱ፣ “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና
በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ …” ማለቱ ትክክል
አይደለም፤ እርሱ ዞሮ ያልሰበሰበውን ሕዝብ እኮ እኛ ይኸው ተቀምጠን በቀላሉ ሰብስበን አይደለም ወይ? የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ባይኾኑም
የእኛ ምርጥ ደቀ መዛሙርት ናቸውና ደስ ይለናል?
Tuesday, 29 January 2019
ቤተ ክርስቲያን ተጐታችና ዘመነኛ ችግሮቿን አስተውላ ይኾንን!? (ክፍል 9)
1.8.
ግብረ ሰዶማዊነት
“ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ፤ እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን
ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ …” (ሮሜ 1፥26-27)
“… ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ … የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።” (1ቆሮ. 6፥9-10)
ኀጢአትን አዘውትረው ለሚሠሩ ሰዎች ሁሉ
(ክርስቲያኖችን ጭምር) መንፈሳዊ ሞት የሚያገኛቸው መኾኑን ታላቁ መጽሐፍ ደጋግሞ ተናግሯል (ሮሜ 6፥16፤ 8፥13፤ ገላ. 5፥21፤
ኤፌ. 5፥5-6፤ 1ዮሐ.2፥4፤ 3፥9፤ ያዕ. 1፥15)። ኀጢአትን በተመለከተ ምንም መታለል አይገባም፤ ብዙ ሰዎች በክርስቶስ ሞት
ያገኙትን ነጻነት ለራሳቸው የኃጢአት ሥራ በነጻነት ለመፈጸም እንዲያመቻቸው ሲጠቀሙበት እናያለን። ይህንንም በተመለከተ ታላቁ መጽሐፍ፦
“ወንድሞች ሆይ፥ እናንተ ለአርነት ተጠርታችኋልና፤ ብቻ አርነታችሁ ለሥጋ ምክንያትን አይስጥ፥ … ” (ገላ. 5፥13) እንዲሁም
“አርነት ወጥታችሁ እንደ እግዚአብሔር ባሪያዎች ሁኑ እንጂ ያ አርነት ለክፋት መሸፈኛ እንዲሆን አታድርጉ” (1ጴጥ. 2፥16) በማለት
በግልጥ ያለምንም ማወላወል አርነታችንን ኀጢአትን ለመፈጸም እንደ መሸፈኛ ማቅረብ እንደማንችል ያስቀምጣል።
Tuesday, 22 January 2019
“ከ“መጋቢ”ው የተሻለ መናፍቅ፣ በዚህ ዘመን ይገኝ ይኾንን?”
Please read in PDF
“ … መጽሐፍ ቅዱስ ማኑዋል አይኾንም ወይ? መጽሐፍ ቅዱስ እኮ፣ የኃጢአታችን
ውጤት እንጂ የጽድቃችን ውጤት አይደለም፣ አርፈን ገነት ብንቀመጥ አንድ ሺህ ገጽ መጽሐፍ አይጫንብንም ነበር፣ አዳምና ሔዋን ተንቀዥቅዠው
ከገነት ከወጡ በኋላ ነው፣ አንድ ሺህ ገጽ ጉዳችንን የሚዘረዝር ኀጢአት ተዘርዝሮ፤ እርሱማ የጉዳችን ማኑዋል ነው፣ ጠባያችንን አይገልጥም፤
ለዚህ ነው እኔ የኀጢአት ውጤት ነው፣ በነገራችን ላይ ብሉይ ኪዳንም ኾነ አዲስ ኪዳን፣ ቁርአንም ኾኑ ሌሎቹም መጻሕፍት በጠቅላላ
ከገነት ከተባረርን በኋላ ለስደተኛ የተጻፉ መጻሕፍት ናቸው፤ ስደተኛውን ለማረጋጋት የተጻፉ መጻሕፍት ናቸው እንጂ፣ ማኑዋልማ ሊኾን
አይችልም፤ በግል ልታወራኝ ትችላለህ፣ እኔ የገባኝ ይህ ነው፤”(ጫጫታና ሳቅ፣ ጭብጨባ ከሕዝቡ)
“መጋቢ” [አ]ዲስ ይህን ንግግር የተናገሩት፣ ዶክተር
ምሕረት ደበበ በሚያዘጋጀው፣ “mindset” እየተባለ በሚጠራ መደበኛ ፕርግራም ላይ፣ “ህሊናና ስብዕና” በሚል ርእስ ተዘጋጅቶ
በነበረው የውይይት መድረክ ነው። በውይይቱ ላይ ማናቸውም ሰው መሳተፍ
እንደሚችልና “አእምሮን ለመገንባት” በሚል “ዒላማም”፣ የተለያዩ ዝግጅቶች ጭምር እንደሚቀርቡበት ይታመናል። ለዚህም ይመስላል የተለያየ
ግንዛቤና ዝንባሌ ያላቸው ሰዎች በፕሮግራሙ ላይ በመጋበዝ ሃሳብ ይሰነዝራሉ፣ የውይይት መነሻ ሃሳቦችን ያቀርባሉ፣ ጥናቶችን ያስደምጣሉ፣
ውይይቶች ይደረጋሉ። ከሚቀርቡት ሰዎች መካከል ደግሞ መጋቢ” አዲስ አንዱ ናቸው።
Tuesday, 15 January 2019
ቤተ ክርስቲያን ተጐታችና ዘመነኛ ችግሮቿን አስተውላ ይኾንን!? (ክፍል 8)
Please read in PDF
1.7.
እንደ ወንጌሉ ታላቅ መርሖ አለመኖር
1.7.1.
መርሖ አንድ፦ “ሂዱ”
ከወንጌል ትውፊትና ዋና መርሖ አንዱ ሂዱ የሚለው
ነው። የቤተ ክርስቲያን የዕድሜ ልክ ታላቁ ተልዕኮዋም “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥
ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ …” (ማቴ. 28፥19) የሚለው ነው። ቤተ ክርስቲያን
ተዘልላ ተቀምጣ የሚመጡትን ብቻ መጠበቅ የለባትም። ውኃ በአንድ ቦታ ሲቀመጥ ይሸታል፤ አማኞችም አንድ ቦታ ሰፍረው እንዲቀመጡ አልተባለላቸውም።
እንደ ዘር እንዲበተኑና እየዞሩ ወንጌሉን እንዲሰብኩ እንጂ (ሉቃ.
10፥1፤ ሐዋ. 8፥4 ፤ 13፥1-4)።
Wednesday, 9 January 2019
ቤተ ክርስቲያን ተጐታችና ዘመነኛ ችግሮቿን አስተውላ ይኾንን!? (ክፍል 7)
1.5.
በፍርድ ቤት መክሰስና
መካሰስ
በታሪክ እስከ አኹን ያልተሰማ እንግዳ ሆኖ እየሰማን ካለው ነገር አንዱ፣
የቤተ ክርስቲያን የገዛ ልጆቿን ዓለማዊ ፍርድ ቤት አቁማ፤ ጠበቃ ቀጥራ የመክሰሷ ጉዳይ ነው። እንዲህ ያለ ነገር በቆሮንቶስ ቤተ
ክርስቲያን ተከስቶ እንደ ነበር “… ወንድም ወንድሙን ይከሳል፥ ይህም በማያምኑ ፊት ይደረጋልን? እንግዲህ ፈጽሞ የእርስ በርስ
ሙግት እንዳለባችሁ በእናንተ ጉድለት ነው” (1ቆሮ. 6፥6-7) በማለት ሐዋርያው አስቀምጧል።
Saturday, 5 January 2019
ሕጻኑና እናቱ
Please read in PDF
የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ከቅድስት ድንግል
የመወለዱን ነገር ከጻፉልን ወንጌላውያን አንዱ ቅዱስ ማቴዎስ ነው፤ መሲሑ ተናፋቂው ማስያስ፣ በነቢያት ትንቢትና በአበው ምሳሌ የተነገረለትና
የዘመናት ናፍቆት የነበረው ሕጻንና ጌታ፣ አባትና ልዑል ምጡቅ ከኾነው ከአባቱ ከሰማይ ወጥቶ ወደ ሰው ልጆች ኹሉ[ወደ እኛ] በመምጣቱ
ተገለጠ፤ ቅዱስ ማቴዎስ ይህን እውነታ የመሲሑን ነገረ ልደት ከአይሁድና ከአሕዛብ የትውልድ ሐረግ ቈጥሮ በመምዘዝ፣ በመዘርዘርም
መሲሑን ዘላለማዊ ነገር ግን በሥጋ ዕድሜ የተወሰነ ጊዜ ሊቈጠርለት እንዳለው (1ጢሞ. 2፥6) በመንፈስ ቅዱስ ተነድቶ ጻፈልን።
ወንጌላዊው ቅዱስ ማቴዎስ ስለሕጻኑና እናቱ ሲናገር፣
ሕጻኑን ቀዳሚና አቻ የሌለው በማድረግ ኹል ጊዜ ያቀርበዋል። በምዕራፍ ኹለት ላይ ብቻ ይህን እውነታ በጕልህ መመልከት እንችላለን፤
“ሕፃኑን ከእናቱ
ከማርያም ጋር አዩት”፣ “ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ”፣ “እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን በሌሊት ያዘና …”፣
“ሕፃኑንና እናቱን ያዘና ወደ እስራኤል አገር ገባ”፣ (ማቴ. 2፥11፣ 13፣ 14፣ 21) በማለት በማናቸውም ስፍራ ላይ ከእናቱ
በፊት ሕጻኑን በማስቀደም፣ ፊተኛ በማድረግ፣ በማግነን፣ በማላቅ ያስቀምጠዋል[በእርግጥስ ሕጻኑ ያልላቀ ማን ሊልቅ፣ መሲሑ ያልገነነ ማን ሊገንን፣ ኢየሱስ ፊተኛ ያልኾነ ማን ሊቀድም
…?]።
Friday, 4 January 2019
ቤተክርስቲያን ተጐታችና ዘመነኛ ችግሮቿን አስተውላ ይኾንን!? (ክፍል 6)
·
ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል።
·
ሹም ሲቆጣ ማር ይዞ እደጁ፥
ደስ ሲለው ማር ይዞ እደጁ።
በምሳሌነት ይህን
ተረት አነሳን እንጂ ከዚህ ተመሳሳይነት ያላቸው ተረቶችና ምሳሌያዊ ንግግሮች በተወሰነ መልኩ በባህላችን ውስጥ ተሰንቅረው ለጉበኝነትና
ለመታያ ስጦታ የሚሰጡት ኢ ሥነ ምግባራዊና ሞራላዊ ድጋፍ አለ።
የእግዚአብሔር ቃል
በግልጥ፦ “ፍርድን አታጣምም ፊት አይተህም አታድላ ጉቦ የጥበበኞችን ዓይን ያሳውራልና፥ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና
ጉቦ አትቀበል” (ዘዳግ. 16፥19) በማለት ይናገራል። አንድ ሹም ጉቦ ወይም መማለጃን የሚቀበለው እውነቱን ሐሰት፤ ሐሰቱን እውነት
ለማለት ወይም ለማድረግ ነው። እውነቱን ሐሰት ስንል ጻድቁን ወይም እውነተኛውን እንበድላለን፤ ሐሰቱን ደግሞ እውነት ነው ስልን
ኅጢአተኛውን በጻድቁ ላይ እናሰለጥናለን።
Monday, 31 December 2018
Tuesday, 25 December 2018
Wednesday, 19 December 2018
“ግብረ ሰዶማዊ ሎጐ” በስፖርት መንደር!
Please read in PDF
የሰው ልጅ በኀጢአት ከወደቀ በኋላ፣ ነገሮችን ኹሉ ይቃኝ የነበረው በወደቀውና ከእግዚአብሔር በተለየው የኀጢአት ዝንባሌው ነው።አዳም በኀጢአት ሲወድቅ ከእግዚአብሔር ተለየ፤ በመለየቱ ልክ እንደ እርሱ ያለውን ከእግዚአብሔር የተለየ ልጅን ወለደ፤ (ዘፍ. 5፥3) ከእግዚአብሔር የተለየው ልጅ ቃየል ወንድሙን በመግደሉ (ዘፍጥ. 4፥8) “ኀጢአት በደጁ የምታደባበት፣ ፈቃድዋም ወደ እርሱ” ኾነች፤ (ዘፍጥ. 4፥7)። የኀጢአተኝነት ዝንባሌ በትውልዱ ልክ የጥፋት ውኃ እያየለው እንደ ሄደው እንዲኹ ተንሰራፊና ተስፋፊ እየኾነ ሄደ፤ (ዘፍ. 7፥19)።
የሰው ልጅ በኀጢአት ከወደቀ በኋላ፣ ነገሮችን ኹሉ ይቃኝ የነበረው በወደቀውና ከእግዚአብሔር በተለየው የኀጢአት ዝንባሌው ነው።አዳም በኀጢአት ሲወድቅ ከእግዚአብሔር ተለየ፤ በመለየቱ ልክ እንደ እርሱ ያለውን ከእግዚአብሔር የተለየ ልጅን ወለደ፤ (ዘፍ. 5፥3) ከእግዚአብሔር የተለየው ልጅ ቃየል ወንድሙን በመግደሉ (ዘፍጥ. 4፥8) “ኀጢአት በደጁ የምታደባበት፣ ፈቃድዋም ወደ እርሱ” ኾነች፤ (ዘፍጥ. 4፥7)። የኀጢአተኝነት ዝንባሌ በትውልዱ ልክ የጥፋት ውኃ እያየለው እንደ ሄደው እንዲኹ ተንሰራፊና ተስፋፊ እየኾነ ሄደ፤ (ዘፍ. 7፥19)።
Monday, 17 December 2018
ቤተ ክርስቲያን ተጐታችና ዘመነኛ ችግሮቿን አስተውላ ይኾንን!? (ክፍል 5)
(ቤተ ክርስቲያን ለመንግሥት የፖለቲካ ትርፍ እንጂ፣ እንደ ጌታ ቃል አልታረቀችም)
መለያየት ከሥጋ ሥራዎች አንዱ ነው (ገላ. 5፥21)፤ ቅዱስ ጳውሎስ በልመና
ቃል “ወንድሞች ሆይ፥ ኹላችሁ አንድ ንግግር እንድትናገሩ በአንድ ልብና በአንድ
አሳብም የተባበራችሁ እንድትኾኑ እንጂ መለያየት በመካከላችሁ እንዳይኾን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኋለሁ።” በማለት ይናገራል (1ቆሮ. 1፥10)፤
መለያየት መነሻው የገዛ ምኞትን ከመከተል እንደኾነ ሲገልጥ ጠቢቡ “መለየት
የሚወድድ ምኞቱን ይከተላል፥ መልካሙንም ጥበብ ሁሉ ይቃወማል።” በማለት ገልጦታል።
የታረደው በግ
“ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ከዋጀ” (ራእ. 5፥9) ቤተ ክርስቲያን ከልዩነት ይልቅ
የመንፈስ አንድነት ላይ ትልቅ ሥራ ልትሠራ ይገባታል። የመለያየት መንፈስን ማጥፋት የሚቻለው ማንነታችን በክርስቶስ ኢየሱስ የተወረሰና
የእኛ የኾነ ምንም እንደሌለን መረዳት ሲቻለን ነው። ይህም ዳግመኛ መወለድን ማዕከል ያደረገ ነው፤ “በወንድማማች መዋደድ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ” (ሮሜ 12፥10)
የሚለን ሕያው ቃሉ እንደማይለያይ ወይም መለያየት እንደማይችል ቤተሠብ አንድ መኾናችንን ያገናዝባል።
Thursday, 13 December 2018
ቤተክርስቲያን ተጐታችና ዘመነኛ ችግሮቿን አስተውላ ይኾንን!? (ክፍል 4)
“ …ፍሬምናጦስ አኹን ተገኝቶ ያለውን የቤተ ክርስቲያንን ትውፊትና ድኅነት፣ ወንጌልና ትውፊት መደበላለቅና መተራመስ
ቢመለከት ያዝን ነበር ብዬ አስባለሁ። …”[2]
“በክርስቶስ … ሆኖ” ሃይማኖትንና ምግባርን ሳይለያዩ ሁለቱንም በአንድነት ማወቅና አውቆም መፈጸም ለክርስቲያን ሁሉ
አስፈላጊ ነው። ከሁሉ በፊት ሃይማኖት ይቀድማል። ስለሆነም … እርሱን በቅድሚያ መማርና ማወቅ ይገባናል። ዳሩ ግን ክርስትናችን
ስለሃይማኖት በመማርና በመመራመር፥ በማጥናትና በማወቅ ብቻ አያከትምም። ምክንያቱም ከላይ እንደጠቀስነው “እምነት” ስንል “በክርስቶስ
ኢየሱስ ሆኖ በፍቅር የሚሠራ እምነት እንጂ” እንዲያው እምነት በተናጠል ብቻውን በእውቀትና በትምህርት ደረጃ ብቻ የቆመ ነገር አይደለም።”[3]
Saturday, 8 December 2018
አባይነህ ካሴ ጠቡ ከኢየሱስ እንጂ ከአቡኑ አይደለም!
Please read in PDF
“ … በግድ በብዙ ስም የሚጠራውን ልዑለ ባሕርይ ጌታ በአንዱ ላይ ብቻ ተንጠልጥሎ ኢየሱስ ብቻ ብላችሁ ካልጠራችሁ ብሎ ሙግት ሌላ የተሰወረ ዓላማን ከሚያሳብቅ በቀር ሌላ ትርፍ የለውም። ወይ እኛ ኢየሱስ ማለት ትክክል አይደለም አላልን፤ ይህ ባልተካደበት ሁኔታ ከስሞች መርጦ ለአንዱ ያጋደለ ስሜት እንዲፈጠር ለማድረግ መሞከር አደገኛነትን ያሳያል። …”[1]
በቀን 27/3/2011 በቦሌ መድኀኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ብጹዕ አቡነ በርናባስ
የሰበኩትን ስብከት ከዩቲዩብ አውርጄ አደመጥኹት፤ ከዚያም በዚህ ስብከት ላይ ጥላቻውን ጮኾ በሚያሰማ መንገድ [ለኑፋቄ ግብር የገቡ ልማደኛ … ሐራጥቃዊ “መምህር”… ሰውዬው … እያለ “አዋርዶ” በመጥራት]
አባይነህ ካሴ የተባለ የማኅበረ ቅዱሳን ቀኝ እጅ የኾነ ሰው፣ ስብከታቸውን በመተቸት የጻፈውንም አነበብኹ፤ እናም “ጉዳዩ ኢየሱስ
ኾነና” አንድ ነገር እናገር ዘንድ ተገደድሁ።
Subscribe to:
Posts (Atom)


