ብቻ! የማያሳይ ከወዳጅ አግዝፎ
ብቻ! ማያጎላ ከአዝማድ አልቆ
ኀጢአት አማኞች እንዳያስተውሉት ስለሚፈልግ፣ በጽድቅ
መዝገብ ውስጥ ራሱን መደበቅ ይወዳል። አብዛኛኞቹ አማኞች ግን የተገለጠ ኀጢአትን አይተው ሲሸሹ፣ ራሱን ሊገልጥ የማይወደውንና ስውሩን
ኀጢአትን ግን ሲዘፈቁበት አልያም “ኀጢአት አይደለም” ብለው ሲሞግቱ እንሰማቸዋለን። ከዚህ የተነሣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ተሐድሶ እንዲመጣ
የሚሹ አካላት፣ ዘወትር ሊያመለክቱ ከሚገባቸው ተግባራት አንዱ፣ ራሱን ሸሻጊውን፣ “እድፈት ወይም የፊት መጨማደድ ወይም እንዲህ
ባለ ነገር በነውር ሊይዝ” (ኤፌ. 5፥27) ከሚተጋው ኀጢአት መጠበቅና ማስጠንቀቅ፤ ዘወትር አማኞች እንዳይረሱ ማሳሰብ ነው።
ወደ
ኦርቶዶክስ ተመልሰናል ባዮችና የኦርቶዶክስ “ቀናተኛው ማኅበረ ቅዱሳን”
የቀናተኞቹ
ውይይት ዕጣሬ
በባለፈው ወር ”ወደ ኦርቶዶክስ ተመልሰናል“ ያሉ ወገኖች ብዙ ነጋሪት አስጐስመዋል፤ ከበሮ አስመትተዋል፤ እንቢልታ አስነፍተዋል። ነገር ግን ያስነፉትን እንቢልታ፤ ያስመቱትን ከበሮ፤ ያስጐሰሙትን ነጋሪት ያህል፣ ተቀባይነትን ሳይኾን “ማኅበረ ቅዱሳን የተባለ ‘ኦርቶዶክሳዊ’ ቀናተኛን” በሚገባ አስቀሰቀሰባቸው እንጂ አልጠቀማቸውም። “ተመላሾቹ”፣ እንዲመለሱ መንገድ ያደላደለላቸው ሰው፣ “የማኅበራዊ ሚዲያ አቅም እንዲጠቀሙ በብዙ እንደ መከራቸው ይታመናል፤” ግን ውጤቱን አለመመዘናቸውና በተቀደደ ቦይ መፍሰሳቸው ሊመጣ ያለውን ናዳ አለማስተዋላቸው ወለል አድርጎ ያሳያል።
ካለፈው የቀጠለ …
ከዚህ በታች ያሉት
ዐሳቦች፣ ስለ መንፈስ ቅዱስ ጥምቀት መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምራቸው ታላላቅ እውነቶች ናቸው። የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት፦
1. የመንፈስ ቅዱስን ጥምቀት ከመዳናችን ፈጽሞ ነጥለን ልናየው አንችልም። በቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት እንዳስተዋልነው፣ ከክርስቶስ ጋር የአካል አንድነት የሚኖረን በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አማካይነት ብቻ ነው። በመንፈስ ቅዱስ የሚጠመቀው አማኝ፣ ሕያውና ቅድስት የኾነችውን የቤተ ክርስቲያን አንድነት የሚካፈልና አማኞችን ወደዚህ ፍጹም አንድነት ለመጨመር የሚከናወን ታላቅ መንፈሳዊ ሥራ ነው።
ቤተክርስቲያን የክርስቶስ አካል ናት፤ እርሱ ብቻ ደግሞ ራስዋ ነው። የሚያምርና የተንቆጠቆጠ ካቴድራል አልያም ጽርሐ ወንጌል ላይኖራት ይችላል። አማኞቿ ጥልቅ ድኾች፣ ደምግባት አልባ፣ ያልተማሩ ገበሬዎች አልያም ዶክተሮችና ፕሮፌሰሮች ቢኾኑም፤ በክርስቶስ ፊት እኩልና አንድ፤ ኹሉም ለክርስቶስ በኵራት ናቸው። በጌታ ቤት ታላቅና ታናሽ የለምና!
“ስሕተትን ማን ያስተውላታል? ከተሰወረ ኃጢአት አንጻኝ።” (መዝ. 19፥12)
ሔዋን ከእባብ ጋር በማይጠቅምና በማያንጽ ወሬ መዘግየቷ ዋጋ አስከፍሎአታል (ዘፍ. 3፥1-6)፤ የመጀመሪያው የእስራኤል ንጉሥ የነበረው ሳዖል ውድቀቱ የጀመረው፣ ትንሽ ከምትመስል ነገር ግን አደገኛ ከኾነ ክፉ የባልንጀርነት ቡድን ውስጥ መሳተፉ ነው (1ሳሙ. 14፥2-3)፤ ጅማሮው መልካም የነበረው ያ ንጉሥ በፍጻሜው፣ ጠንቋይ እንደ ፈለገ፣ ለእግዚአብሔር እንዳልታዘዘ ክፉ ሞት ሞተ፡፡ ሳምሶንን የሚያህል ብርቱ አገልጋይ፣ የመውደቁና የመንኮታኮቱ ጅማሮ፣ “ሶምሶንም ወደ ተምና ወረደ፥ በተምናም ከፍልስጥኤማውያን ልጆች አንዲት ሴት አየ።” (መሣ. 13፥1) ከምትል ቀላል ሐረግ ነው፡፡
የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት
የ“መድሎተ ጽድቅ” ጸሐፊ፣ ስለ ነገረ
ድኅነት ያን ያህል ሰፊ ጽሑፍ ሲጽፍ፣ አንድም ቦታ ከውኃ ጥምቀት በስተቀር ስለ መንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አለመጻፉ፣ ምን ያህል
ከመንፈስ ቅዱስ እውነት፣ ከኢየሱስ ትምህርትና ሕይወት መራቁን፣ የቅዱሳት መጻሕፍትን ኃይል ባለማወቅ እንዴት እንደ ሳተ
እንመለከታለን።
መጽሐፍ ቅዱስ ግን፣ በግልጥ ስለ መንፈስ ቅዱስ ጥምቀት በሚገባ ያስተምራል፤ ደግሞም ከነገረ ድኅነት ጋር ተያያዥና ቊልፍ ትምህርት መኾኑን በሚገባ እናስተውላለን። የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች መመልከት እውነታውን እንድናስተውል ይረዳናል።
(ይህ ጽሑፍ፣
በእውነተኛ ልብ ወንጌልን በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ውስጥ ለማድረስና ለሚሽነሪ አገልግሎት በሕይወታቸው ተወራርደው የሚያገለግሉ ታማኝ
አገልጋዮችን አይመለከትም!)
ለምን አንልም?
ክርስቶስ ኢየሱስ፣ ከውስጥ በሚነሳ አሸናፊነትና “ዘገምተኛ” በኾነ ጽኑ የፍቅር መንገድ የሚያሸንፍ እንጂ፣ በግድና በኃይል ማንንም መያዝና አብሮት እንዲኖር አይፈልግም። ጽድቅን ወዳዱ ጌታ፣ ጽድቅን ያደርግ ዘንድ የምድርን የታችኛው ክፍል በትእግሥት ዝግታ ረግጦ መራመዱ ይህን እውነታ በአድናቆት ያሳየናል! ከዚህ በተቃራኒ ግን “ሰሞነኞቹ”፣ እንደ 1980ዎቹ ትውልዶች፣ “‘እስክንድያ እናቴ’ ኦርቶዶክስ ሃይማኖቴ” ብለው መሄዳቸውን ስናይ ምን እንላለን? ምንም!
“ወዳጆች ሆይ፥
በእናንተ መካከል እንደ እሳት ሊፈትናችሁ ስለሚሆነው መከራ ድንቅ ነገር እንደ መጣባችሁ አትደነቁ፤” (1ጴጥ. 4፥12)
ቅዱስ ጴጥሮስ በአማኞች መካከል እንደ እሳት የሚፈትን ፈተናና መከራ ሊነሣ እንደሚችል በግልጥ ያስተምረናል። የፈተናው መነሻ ደግሞ እዚያው መካከላችን መኾኑንም ጭምር፤ አዎን! ከኢየሱስ ጎን ይሁዳ፣ ከጳውሎስ ጎን ዴማስ፣ ከዮሐንስ ጎን ዲዮጥራጢስ፣ ከኤልሳዕ ጎን ግያዝ … መኖራቸው እንግዳና ልዩ ነገር አይደለም። ዛሬ ላይም እንዲህ ያሉ ወገኖች መነሳታቸው ፈጽሞ አይደንቅም፤ አይገርምም። ገንዘብን ለማካበት መጐምጀት፣ ተሰሎንቄን አይቶ ከቅድስና መልፈስፈስ፣ በወንድሞች ላይ የጐበዝ አለቃ ለመኾን መቋመጥ … ያኔም ነበረ፤ አኹንም መኖሩ አይደንቅም፤ አይገርምምም!
ከሰሞኑ ጯኺ መፈክሮች ውስጥ፣ “ወደ ተቋማዊው ኦርቶዶክስ (institutional Orthodox) እንመለስ” የሚለው አንዱ ነው። የሚመለሱበት የአብዛኛዎቹ ምክንያታቸው ደግሞ፣ “‘ተሐድሶ’ ወደ ወንጌላውያን አፍላሽ ኾኖአል እንጂ፣ በራሱ መቆም ያልቻለ ነው፤ ስለዚህም ወደ ተቋማዊው ኦርቶዶክስ ተመልሰን አስቀድመን ከጴንጤነት እንዳን፤ ቀጥለን ደግሞ በኦርቶክሳዊ መንገድ ‘ክርስትናን’ እንስበክ” የሚል ነው። እኒህ ሰዎች፣ አኹን ላይ፣ ወደ ተቋማዊው ኦርቶዶክስ መመለስን ቀለል አድርገው ሲናገሩ፣ በወንጌላውያን “pulpit” ላይ የማርያምን ምልጃ ብንሰብክ፣ ከልካይ የለንም ባይ ፍጹም ተላላዎች ይመስላሉ!
አንድ የምዕራብ ቤተ ክርስቲያን አባባል አለ፤ “በምድር ላይ ፍጽምት ቤተ ክርስቲያን የለችም፤ ምናልባት ካለች፣ አንተ የገባህባት ቀን ፍጽምናዋን ታጣለች” ይላል። ሙሉ ለሙሉ ባልተዋጀው ዓለም ስንመላለስ ፈተናና ውጊያ፤ መሰናክልና ወጥመድ፣ መከራና ተግዳሮት አለብን፤ ጌታችን ኢየሱስ ራሱ፣ “እነሆ፥ እኔ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤” (ማቴ. 10፥16) ብሎ ተናገረን እንጂ፣ ወደ ሰላማውያንና ፍጹማን አማኞች ወይም ማኅበረ ሰቦች ዘንድ እልካችኋለሁ አላለንም። እናም ውጊያችን ፈርጀ ብዙና በዚህች ምድር ላይ እስካለንም ድረስ የማያቋርጥም ነው።
እስጢፋኖሳውያን፣
የወንጌላውያን ተሐድሶ በአውሮፓ ከመጀመሩ ከዓመታት በፊት፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የወንጌል ችቦ እንደ ለኮሱ ይታመናል፤ አንዳንዶች የተሐድሶ
አገልግሎት በኢትዮጵያ ውስጥ አጭር ታሪክ ያለው ይመስላቸዋል። ነገር ግን እስጢፋኖሳውያን በኢትዮጵያ ውስጥ አስደናቂና ወንጌላዊ
የኾነ ተሐድሶ አሥነስተው ለብዙዎች መዳንና ከጨለማው ዓለም ማምለጥ ምክንያት ኾነዋል። የዚህን ዘመን ክስተት፣ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ታላቅ ዕድል እንደ ነበርና እንዳልተጠቀመችበት የደቂቀ እስጢፋኖሳውያንን ገድል በጻፉት መጽሐፋቸው እንዲህ ይላሉ።
ተሐድሶ፣ “ሐደሰ” ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ ሲኾን፣ ትርጕሙ “አዲስ አደረገ” የሚለውን ትርጕም ታሳቢ ያደርጋል። በተገብሮ (Passive) “ተሐድሰ” ከሚለው ቃል ደግሞ፣ “ተሐድሶ” የወጣ ሲኾን፣ ትርጕሙ “አዲስ ኾነ” ማለት ነው። ስለዚህም ስያሜው ድርጊትን እንጂ ተቋማዊነትን ወይም አደረጃጀትን ፈጽሞ አያመለክትም።
ከቅርብ ጊዜያት
ወዲህ፣ በአንገታቸው የመስቀል ምልክትን የሚያስሩ ብዙዎች፣ “ቶ” ምልክት ያለውን በአንገታቸው ማሰርን በአደባባይ እየተመለከትን
ነው። “ቶ” ምልክት ያለው ብቻ ሳይኾን፣ ሌሎችም እንግዳ ድርጊቶች ሲከሰት፣ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶና በሌሎችም አድባራትና አብያተ
ክርስቲያናት ሲከናወን ዝም ማለት አልያም አንዳችም ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቦ፤ ነገሩ ከእንቁላል ወደ ጫጩት እስኪያድግና ብሎም እስኪጐለምስ
ችላ ማለት እንግዳ ተግባርም አይደለም።
ካለፈው የቀጠለ …
ዛሬ ኦርቶዶክስ ማን ነው?
“ተዋሕዶ ሳይኾን ስሙ ሃይማኖቱ
ኦርቶዶክስም ሳይኾን ባህሉና ትምህርቱ
ሰርቆና ቀምቶ የሰው ስም በከንቱ
ሰው ኹሉ አለስሙ ምነው መጠራቱ”[1]
ኦርቶዶክስ[ዊነት] ምንድር ነው?
“ኦርቶዶክስ ማለት ኦርቶ ርቱዕ፤ ዶክስ ባህል ሐሳብ፣ ኅሊና፣ ስብሐት፣ ምስጋና ይኾናል፤ በተገናኝ ርቱዐ ሃይማኖት ማለት ነው። … ኦርቶዶክሳዊ ማለት ደግሞ የኦርቶዶክሳዊ ወገን እውነተኛ ቅን፣ በሃይማኖቱ ሐሰትና ስህተት ጽነት የሌለበት።”[1]
ሳኦል የእግዚአብሔርን መንገድ ባለመከተሉ ምክንያት፣ እግዚአብሔር ዳዊትን “በትይዩ” ንጉሥ አድርጎ ቀባው። ለእግዚአብሔር ቃል ያልታዘዘውና እግዚአብሔርን ፈጽሞ ባለመፈለግ ባዛኙ ሳኦል፣ የዳዊትን መሾም ሲያውቅ፣ ዳዊትን ለመግደል የቻለውን ኹሉ ከማድረግ አላረፈም። በሜዳ፣ በምድረ በዳ፣ በዋሻ፣ በተራራ … ባገኘው ሥፍራ ኹሉ አሳድዶ ሊገድለው እጅጉን ፈለገው። ነገር ግን ዳዊትን መግደል ሳይቻለው፣ “ፍልስጥኤማውያን የሞቱትን ለመግፈፍ በመጡ ጊዜ ሳኦልና ሦስቱ ልጆቹ በጊልቦዓ ተራራ ላይ ወድቀው አገኙአቸው። የሳኦልንም ራስ ቈርጠው የጦር ዕቃውን ገፍፈው ለጣዖታቱ መቅደስ ለሕዝቡም የምስራች ይሰጥ ዘንድ ወደ ፍልስጥኤማውያን አገር ሁሉ ሰደዱ።” በማለት እንዴት ባለ አስቀያሚ ሞት እንደ ሞተ ይነግረናል፤ (1ሳሙ. 31፥8-9)።
በኦርቶዶክስና በካቶሊክ ስለ ማርያም ሞት፣ “ትንሣኤና ዕርገት” የማያልቁ አእላፍ ተረቶች
አሉ፡፡ ምሳሌ፦ ነገረ ማርያም በግልጥ፣ የማርያምን ስም ትርጉም ሲያብራራ እንዲህ ይላል፣ ማርያም በገሃነም ያሉ ኀጢአተኞችን ባየች
ጊዜ፣ “እርሷም እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እነዚህ ነፍሳት ዘለዓለም በገሃነመ እሳት ወርደው ሲቀሩስ እንኳን አንድ ጊዜ ፯ ጊዜ
ልሙት ብላ ሙታለች ኋላም ለፍጥረቱ ኹሉ መጽደቂያ ሁና ተገኝታለችና ወኀብት(ስጥውት) አላት፡፡”[1]
ማርያም ለኀጢአተኞቹ ራርታ ሰባት ጊዜ ልሙትላቸው ብላ ሰባት ጊዜ ሞታላቸዋለች! ከዚህም የተነሣ መጽደቂያቸው ኾናለች! መጽሐፍ ቅዱስ
ግን፣ “አሁን ግን
በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል፥ እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ
በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው፤” (ሮሜ 3፥21-22) በማለት የምንጸድቀው በክርስቶስ ብቻ እንደ ኾነ ይነግረናል!
አንፈራም
የሚሰማው፣ የሚታየው፣
የሚነገረው፣ ጠላት በብሩ የሚጎስመውና የሚያጓራው ማጓራቱ እጅግ ጠንካራና አስፈሪ ነው፤ ነገር ግን እኛ አንፈራም፤ የማንፈራበት
ምክንያት የማንፈራ ኾነን አይደለም፤ ነገር ግን ፍርሃትንና የፍርሃትን ምንጭ የሚሽር አምላክ ስላለን እንጂ። የማንፈራበት ምክንያት፦
1. የሰራዊት አምላክ ከእኛ ጋር ነው፦ ይህ ቃል በዝማሬው ወስጥ እንደ አዝማጅ ተደጋግሞ ተጠቅሶአል (ቊ. 7፡ 11)፤ እርሱ “አምላካችን”፣ የሰራዊት አምላክ”፣ የያዕቆብ አምላክ” ነው። እርሱ በመግቦቱ ለያዕቆብ ወይም ለእስራኤል የተለየ ፍቅር አለው፤ በእርሱ ታምነዋልና። ስለዚህም የእርሱ ከእነርሱ ጋር መኖር ለእነርሱ ክብርና ሞገስ፤ መወደድም እነጂ የፍርሃት ምልክት አይደለም። እርሱ ከእነርሱ ጋር ስለኾነም ለዘላለም መጠጊያና ኀይላቸው፣ በመከራቸው ኹሉ የቅርብ ረዳታቸው (ቊ. 1)፣ መጠጊያቸው (ቊ. 7)፣ ከለላቸው ነው።
በአዲስ ኪዳን ቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ፣ ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የቀረቡ አያሌ ጸሎቶችን እናነባለን። ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቀረቡ አንድ መቶ ሰማንያ ሦስት የሚጠጉ ጸሎቶች መካከል አንዱ ጸሎት፣ “መምህር ሆይ፥ በዚህ መኾን ለእኛ መልካም ነውና አንድ ለአንተ አንድም ለሙሴ አንድም ለኤልያስ ሦስት ዳሶች እንሥራ” (ማር. 9፥5) በማለት ቅዱስ ጴጥሮስ ያቀረበው ጸሎት ነው።
መግቢያ
በዚህ ምዕራፍ፣ መዝሙረኛው የሚዘምረው መዝሙር፣ የቆሬ ልጆችን መዝሙር ነው። የቆሬ ልጆች
ከቆሬ ወገን የኾኑ ሌዋዊ መዘምራን ናቸው። በንጉሥ ዳዊት የተሾሙና በዳዊትም ዘመን የቆሬ መዘምራን አለቃ ኤማን የተባለ ሰው ያገለግል
የነበረ (1ዜና. 6፥31-47) ሲኾን፣ በቅዳሴ ሥርዓት እግዚአብሔርን በአንድነት ያገለግላሉ። በዳዊት መዝሙር ውስጥ፣ በቆሬ ልጆች
ከተሰየሙት ሰባት[1]
መዝሙሮች መካከል፣ አንደኛው ዝማሬ ይህ ዝማሬ ነው። ዝማሬው የጽዮን ዝማሬ ነው፣ ዝማሬውን የሚዘምሩትም ደናግላን በደናግል የዜማ
ስልት ነው። መዝሙሩ የሚዘመረው በኅብረት፣ የመዘምራን አለቆችም እየመሩት ነው።
መዘምራኑ እየዘመሩ በሰልፍ ወደ ቤተ መቅደሱ ሲሄዱ፣ ደናግላኑ ከበሮ እየመቱ በማጀብ ይከተሉአቸዋል። እጅግ ውብና እግዚአብሔርን በሕዝብ ኹሉ ፊት ከፍ የሚያደርጉበት፣ በእርሱ መታመናቸውንም በአደባባይ የሚገልጡበት ዝማሬ ነው።
ሥራ
ካለፈው የቀጠለ
…
ሰዎች ኹሉ ሊድኑ የተጠሩት በክርስቶስ የመስቀል ላይ ሥራ ብቻ ነው፤ መጽሐፍ
ቅዱስ ለዚህ ግልጥና የማያወለዳ ትምህርቶቹን እንዲህ ያስተምራል፤
“ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር
ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።” (ኤፌ. 2፥8-9)
“ኹሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም
ክብር ጎድሎአቸዋል፤ በኢየሱስ ክርስቶስም በኾነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።” (ሮሜ 3፥23-24)
“እንግዲህ ምን እንላለን? ጽድቅን ያልተከተሉት
አሕዛብ ጽድቅን አገኙ፥ እርሱ ግን ከእምነት የሆነ ጽድቅ ነው፤” (ሮሜ 9፥30)
የኦርቶዶክስና የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት የማርያምን፣ “በሦስተኛው ቀን” ሳይኾን፣ በጥር ሞታ ነሐሴ “መነሣቷን” ከዶግማ ትምህርቶቻቸው አንዱ አድርገው ይቀበላሉ። ማርያምን “ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች”ና ፍጹም መካከለኛ አድርገው ለመቀበላቸውም ከሚያቀርቡት ማስረጃዎች አንዱ ይህን፣ “ከሞት ተነሥታለች” የሚለውን ትምህርት በዋቢነት በመጥቀስ ነው።
ካለፈው የቀጠለ …
ሥራ
የክርስትና
ትምህርት ጤናማና መዳን የሚገኝበት ቃል ወይም ትምህርት ተብሎ ተነግሮአል (ሐዋ. 13፥26፤ 1ጢሞ. 6፥3፤ 2ጢሞ. 1፥13፤
2ጢሞ. 3፥15)፤ ትምህርቱ ጤናማ ከኾነ የኑሮ ዘይቤና ጠባዩም ፍጹም ጤናማ መኾኑ አያጠራጥርም። ጤናማው ትምህርት ለእግዚአብሔር
ክብር (Orthopraxy) በሚያመጣ እውነተኛ ሕይወት እንድንመላለስ ያደርገናል፤ ይህ ጤናማ ትምህርት ደግሞ ርትዕት ከኾነች እምነት
(Orthodoxy) ጋር ፈጽሞ ሊነጣጠል የሚቻለው አይደለም። ሕይወት የሚቀዳውና የሚመነጨውም ከእውነተኛ ትምህርትና ከእውነተኛ ፍቅር
(Orthopathy) ነውና።
ሰው እንዴት እግዚአብሔርን እየፈራ፣ ፍጹም እግዚአብሔርን ይቃወማል?! እግዚአብሔርን እየፈሩ እግዚአብሔርን የሚቃወሙ ሰዎች፣ ተቃውሞአቸው ከምድር ኹሉ አደገኛውና ከባዱ ሲኾን ፤ በዚህ ኹሉ ውስጥ ግን የመንፈስ ቅዱስ ደስታ አለ! አሜን፡፡
ካለፈው የቀጠለ …
አንድን እውነት
ማመን ብቻውን እምነት አይኾንም። ለምሳሌ፦ ሰዎች የእግዚአብሔርን መኖር ብቻ ቢያምኑ እርሱ እውነተኛ እምነት አይደለም። እውነተኛ
እምነት ግን ከእግዚአብሔር የሚሰጠውን የዘላለም መዳን ለማግኘት ወይም ለመቀበል በክርስቶስ ኢየሱስ ፍጹም ማመንን የሚጠይቅ ነው።
በልጁ የማያምን እምነቱ ርቱዕና ምሉዕ አይደለም። ስለዚህም የአዲስ ኪዳን እምነት በግልጥ ከዚህ በታች የሚከተሉትን እውነቶችን በውስጡ
የያዘ ነው፤ እኒህም፦
“እምነት ብቻ”ን መጥላት!
ካለፈው የቀጠለ …
ስለ እውነተኛ መዳን ስንናገር፣ ምርጫ አልባ አድርገን የምናቀርባቸው የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች አሉ። ከእነዚህ ምርጫ አልባ እውነቶች መካከል አንዱ፣ “መዳን በእምነት ብቻ ነው” የሚለው የማይለወጥ እውነት ነው። የ“መድሎተ ጽድቅ” ጸሐፊና አብዛኛው ኦርቶዶክሳውያን ግን ይህን ዐሳብ የሚረዱት በተቃራኒው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ፣ “መዳን በእምነት ብቻ ነው” ሲል፣ ሥራን የሚክድና የሚቃወም ወይም ደግሞ በሌላ ጽንፍ፣ “ድነናልና ሥራ ለምኔ!” ለሚሉ አያሌዎች ይኹንታ የሚሰጥ የሚመስላቸው ብዙ ናቸው።
ሃይማኖተኛ
ሲታወር፣ ከዓለማዊ ይልቅ ዓመጸኛ እንደሚኾን አውቃለሁ። ትኵረት ለመሳብና ሰውን ለማስከተል፣ እምነቴና መረዳቴ እንዲህ ነው ብሎ መውረድ እንዴት ያጸይፋል?!
ጌታችን ኢየሱስ፣ “በፍርድ
ቀን ከእናንተ ይልቅ ለጢሮስና ለሲዶና ይቀልላቸዋል።” (ማቴ. 11፥22) ብሎ ተአምራት አይተው የካዱትን ኮራዚዮንና ቤተ
ሳይዳን በጽኑ እንደ ወቀሰው፣ ከደነደነ አማኝ ይልቅ ያላመነ አሕዛብ ተስፋ እንዳለው በግልጥ ነግሮናል።
“ተግሣጽን የሚወድ
ዕውቀትን ይወዳል፤ መታረምን የሚጠላ ግን ደነዝ ነው” (ዐመት)(ምሳ. 12፥1)
አይመጣም እንጂ ቢመጣ፣ ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ ዘመን ካሉ አያሌ አማኞች የሚገጥመው ተቃውሞ እንዲህ የሚል ነው፤ “ምን ነክቶህ ነው ግን፣ ያን ኹሌ የቆሮንቶስን ነውር ፊት ለፊት የተናገርከው? በፍቅር ቀስ ብለህ በግል አትነግራቸውም ነበር? አጉል መተቸት ለምን ትወዳለህ? የሐዋርያት “አለቃ” የነበረውን ቅዱስ ጴጥሮስን ፊት ለፊት ስትቃወምስ ትንሽ ለምን አላፈርክም? ደግሞ የገላትያ አማኞችን አዚም[ጥንቆላ] ማን አደረገባችሁ ትላለህ እንዴ? …
ፖፕ ፍራንሲስ
ከቅርብ ጊዜ በፊት ስለ ሰዶማውያውን፣ “ማኅበራዊ መብቶች” መናገራቸውን አንዘነጋም። ዛሬ ደግሞ በጻፉት ደብዳቤአቸው፣ “ለእግዚአብሔር
ሥራ ሰዶማውያን ጭምር ሊሾሙ እንደሚገባ” መግለጣቸውን ዋሽንግተን ፖስት ደብዳቤአቸውን ዋቢ አድርጎ ዘግቦአል።[1] በእርግጥ በክፋት ከተያዘው ዓለም፣ ቀኖቹ እየባሱ፣
የሚያስቱትም የሚስቱትም እየበዙ እንደሚሄዱ ቅዱስ ቃሉ በማስጠንቀቂያ ጭምር ነግሮናልና፣ ክፉውና ዓመጸኛው ዓለም በክፋቱና በዓመጻው
እጅግ መባሱ አያስደንቅም!
ካለፈው የቀጠለ …
ቅድስና፦ ከመጽሐፍ ቅዱስ፣ ቊልፍ ቃላት መካከል አንዱ ቅድስና የሚለው ነው። በተቃራኒው
ደግሞ፣ “የመድሎተ ጽድቅ ጸሐፊ”፣ ከመጽሐፍ
ቅዱስ ውጭ ትርጕም ከሰጣቸው ቃላት አንዱ ቅድስና ነው። ቅድስና የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ነው፣ “እንደ
እግዚአብሔር ቅዱስ የለምና፥ እንደ አምላካችንም ጻድቅ የለምና፤ ከአንተ በቀር ቅዱስ የለም።” (1ሳሙ. 2፥2)፤ “እኔ እግዚአብሔር
አምላካችሁ ነኝና፤ ሰውነታችሁን ቀድሱ፥ ቅዱሳንም ሁኑ፥ እኔ ቅዱስ ነኝና፤” (ዘሌ. 11፥44)፤“ ጌታ ሆይ፥ የማይፈራህና
ስምህን የማያከብር ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህና፥” (ራእ. 15፥3) ተብሎ እንደ ተጻፈ፣ እግዚአብሔር አምላክ ብቻ ቅዱስ ነው። በዕብራይስጥ (godesh), በግሪክ
(hagiosune) ተብሎ የተጠራው ቅድስና ትርጉሙ፣ መለየት ወይም እግዚአብሔርን መምሰል የሚል ነው። ቃሉ በተለይ በዘሌዋውያን
መጽሐፍ ላይ እጅግ ተደጋግሞ የተጠቀሰ ነው።
በዚህ ወር “ያለ እውነት፣ የእውነት ቃል አገልግሎት!?” ከሚለው መጽሐፍ መታተም
ጋር በተያያዘ፣ ኹለት የእቃአ(ከዚህ በኋላ፣ የእውነት ቃል አገልግሎት ለማለት የሚውል) አገልጋዮች ፊት ለፊት ተገናኝተውኝ አውርተውኝ
ነበር። አንደኛው አገልጋይ መጽሐፍ ተርጓሚያቸው ሲኾን፣ ኹለተኛው ደግሞ ሰባኪያቸው ነበር። አንዱን በሰው መካከለኝነት[በወንድም
ቴዎድሮስ ደመላሽ አማካይነት] ያገኘኹት ሲኾን፣ ሌላው ግን ያገኘኝ ራሱ ደውሎ ለብቻ ነበር።
ኹለቱም በአካል አጊኝተው ሊያወሩኝ በመፈለጋቸው፣ እጅጉን ደስ ብሎኛል።
ሙሉ ስብከቱን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው ያድምጡ! በቅዱስ ቃሉ ይባረኩ፤ ለሌሎችም ያካፍሉ፣ የመንግሥቱ ወንጌል ይሰፋ ዘንድ ላልተወደዱ ለሚመስላቸው ኀጢአተኞችና ዓለም ላገለለቻቸው ጋብዙ! የጌታችን ኢየሱስ መንግሥት ከመንፈስ ቅዱስ ኀይል የተነሣ ትሰፋለች፤ አሜን!
የእውነት ቃል አገልግሎት፣ የእምነት እንቅስቃሴ አጋፋሪ ትምህርት ነው። የእምነት
እንቅስቃሴ ትምህርቶቹ ኹሉ ሰውንና ራስን ወደ ማላቅ፤ ሰውን አምላክና አንዳች ልዩ ኃይል በውስጡ እንዳለ የሚያሞኙ፣ የሚያጃጅሉ፣ በምኞት የሚያስጎመጁና የሚያነኾልሉ
“የከንቱ ከንቱ፤ ከንቱ ከንቱ ስብከቶችና ትምህርቶችን” የታጀለ አስተምህሮ ነው። ትምህርቶቻቸው ማዕከሉ ክርስቶስ መዳረሻውና ፍጻሜው
የእግዚአብሔር መንግሥት መስፋት አይደለም።
ሊቀ ነቢያት ሙሴ እስራኤልን በተናገረው የስንብት ንግግሩ፥ “አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ መካከል ከወንድሞችህ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣልሃል እርሱንም ታደምጣለህ” (ዘዳግ. 18፥16) በማለት፥ ለጊዜው ከእርሱ በኋላ ለሚነሱ ለሌሎች ነቢያት ሲናገር በፍጻሜው ግን በትንቢት መልክ ስለሚመጣው መሲሕና ትንቢቱ በእርሱም የተፈጸመ መኾኑን እናያለን። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ አምስት ሺህ ወንዶችን ባሳመነበት (ሐዋ. 4፥4) የኢየሩሳሌም ስብከቱ በጌታ ኢየሱስን ትንቢቱ በትክክል መፈጸሙን ጠቅሶ አብራርቶታል።
ካለፈው የቀጠለ …
እምነት፦ ሰው፣ በእግዚአብሔር ላይ ያለውን መደገፍ ከሚገልጥበት መንገድ አንዱና ተቀዳሚው
እምነት ነው። እግዚአብሔር ለዘላለም እርሱም፤ ቃሉም ታማኝ ነው (2ጢሞ. 2፥13፤ ቲቶ 3፥8)። አማኝ እግዚአብሔር በተናገረው
ቃሎቹ ላይ ፍጹም መደገፉ እርሱ እምነት ነው። እኛ በእግዚአብሔር ላይ ጥገኞች ነን፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር የፍጥረቱ አካል አይደለም፤
ይልቅ ፍጥረቱን ብቻውን ፈጥሮአልና እርሱ ከፍጥረቱ እጅግ የተለየና ምጡቅ ነው። ፍጥረት በእርሱ ይደገፋል፣ የእርሱን መግቦት ይጠባበቃል፤
እግዚአብሔር ግን በፍጥረቱ ፈጽሞ አይደገፍም።
ከንቱ ትምክህት!
ማኅበረ ቅዱሳንና አንዳንድ የኦርቶዶክስ ሰባክያን፣ ስለ ክርስትና ሲያወሩ፣
ክርስትናን ራሳቸው ጠፍጥፈው የሠሩትና ለዓለም የናኙት ይመስላሉ። እነርሱ በግብዝነት የሚመኩትን ያህል ክርስትና የሰበኩት፣ የመንግሥቱን
ወንጌል ለዓለሙ የናኙት የመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት እንኳ እንደ እነርሱ ፈጽሞ አይመኩም፤ አይገበዙምም። እጅግ በጣም የሚያስደንቀው
ነገር፣ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ አባ ሰላማ፣ ኢትዮጵያዊ እንዳልኾነ የሚያውቁ እጅግ ጥቂቶች ናቸው። እንዲያውም ከታወቁት የቤተ ክርስቲያን
ታሪክ ጸሐፍት አንዱ፣ ቅዱስ ማቴዎስ የተገደለው በኢትዮጵያ ምድር እንደ ኾነ ይነግረናል። ክርስትና አገር በቀል ቢኾን፣ ክርስቲያን
በኢትዮጵያ ምድር ባልተገደለ!
የዛሬ አሥራ ሰባት ዓመት ገደማ፣ ነፍሴ ከግንቦት አንድ አምላኪያን እጅ ያመለጠችበት ቀን ነው። በዚያን ቀን፣ በአርሲ ነጌሌ ሶጊዶ ማርያም ቤተ ክርስቲያን በዓለ ንግሡ ላይ ላገለግል ተጠርቼ በዚያ ነበርኩ። “የተሸሸገ ጣዖት” በሚል ርዕስ፣ የያዕቆብ ሚስት ራሔል ጣዖትን መሸሸጓንና በዚህም የደረሰባትን በማንሳት አንስቼ አገለገልሁ፤ እኛም ይህን ማድረግ እንደሌለብን ብርቱ ማስጠንቀቂያ በማኖር ጭምር። ነገር ግን በዚያን ቀን ሳስተምር፣ ከታቦቱ ጎን ትምህርቴን ቆሞ ይሰማ የነበረ፣ የገጠር ከተማይቱ ጠንቋይ ደም በሰረበ ዓይኖቹ ይመለከተኝ ኖሯል።
እኔ!
በአጭር ቃል፣ እኔ ትላንትና የክርስቶስን መካከለኝነት ነቅፌ የማርያምን መካከለኝነት አስተምር ነበር፤ የክርስቶስን መካከለኝነት ያስተምሩና ይሰብኩ የነበሩትን ነቅፍ፣ ሰድብ፣ በብርቱ ቃል ተች፣ አዋርድ ነበር። እኔ በማደርገው ንግግርና ድርጊት ሰዎች እስኪሸማቀቁ ድረስ ለብዙዎች የመሰናከልና የመውደቅ ምክንያት ነበርኩ። ማርያምን በዝማሬ አምልኬአለሁ፤ ወደ እርሷ ጸልይ፤ በስሟም እማጠን፣ አማልጂኝ ብዬም እለምናት ነበር። ለስእሏ እሰግድ፣ ለስሟም ስዕለት አስገባ፣ በመላእክት፣ ቅዱሳን ተብለው በሚጠሩ ፍጡራን ሰዎችና ቊሳት ኹሉ ስም አምልኮ እፈጽም፣ እግዚአብሔር ሩቅ እንደ ነበር፣ መዳንን በግል ጥረት ማግኘት እንደሚቻል ለዚህም ገዳም ለገዳም እንከራተትም … ነበር።
ነቢዩ ኢሳይያስ ስቁዩንና መከራ ተቀባዩን መሲሕ፣ “ደዌን የሚያውቅ የሕማም ሰው” ብሎ ይጠራዋል (ኢሳ. 53፥3)። መሲሑ መከራን የማይቀበልና ሕመም ተጠያፊ አይደለም፤ ይልቁን ሐዋርያው ጳውሎስ፣ “በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ መኾኑን” (ፊልጵ. 2፥8) በግልጥ ተናገረ። መሲሑ ለመታመም የፈቀደ፣ ለመድቀቅ የወደደ፣ ለመዋረድ ክብሩንና ጥቅሙን ኹሉ በፈቃዱ የተወ፣ እግዚአብሔር ነፍሱ የተደሰተችበት ጻድቅ ባሪያ ነው (ኢሳ. 53፥11)።
"Yommuu bakka Qaraaniyoo jedhamu ga'anitti achitti isa fannisan;" (Luqa. 23:33)
ኒቆዲሞስ፣ ኢየሱስን እጅግ በብዙ ከሚንቁት ፈሪሳውያን ወገንና ከአይሁድ አለቆች መካከል አንዱ የነበረ ሰው ነው። በዚያ ዘመን ፈሪሳዊ መኾን ሕጉን እንጠብቃለን፤ ሕጉን በመጠበቅም እንጸድቃለን ለሚሉ ሃይማኖተኞች ብርቱ ትምክህት ነው። ፈሪሳውያን ለሕጉ እጅግ ቀናተኞች ከመኾናቸው የተነሣም፣ ከመካከላቸው ቀራጮችንና ኀጢአተኞችን ፍጹም በማግለል ራሳቸውን እንደ ፍጹም ጻድቃን ይቈጥሩ ነበር።
ካለፈው የቀጠለ …
ጽድቅ፦ “ጽድቅ” የሚለው ቃል የአማርኛ ተካካይ ትርጉሙ፣ “ሕግን መፈጸም፣ እንደ ሕግ መኖርና መመራት፣ ትክክለኛነት፣ እውነት፣ ቀጥተኛ፣ ፍትሓዊ፣ በጎ ምግባር” ማለት ነው። አለቃ ኪዳነ ወልድም በመዝገበ ቃላቸው ሲተረጕሙ “እውነት፣ ርግጥ፣ ቅንነት”።[1] ይላሉ። ይህም በቀጥታ ከእግዚአብሔር ባሕርይ ወይም ከፍጹም ትክክለኛነቱ ጋር የሚገናኝ ነው። ሰው ኀጢአተኛ ስለ ኾነ የእግዚአብሔርን ጽድቅ መፈጸም አይችልም። በተለይ ደግሞ ከመዳን ትምህርት ጋር አያይዘን ስናነሳው እንዲህ ማለት እንችላለን፤ ሰው መጽደቅ የሚችለው ከእግዚአብሔር ልጅ ከክርስቶስ የቤዝወት ሥራ የተነሣ ብቻ ነው።
የስህተት መምህራን “የክርስቶስን ሐዋርያት እንዲመስሉ ራሳቸውን እየለወጡ ምን ያህል የጽድቅ አገልጋዮች እንደሚመስሉ” (2ቆሮ. 11፥13-14)፣ ምን ያህል ውስጠ ተኵላነታቸውን ደብቀው የበግ ለምድ እንደሚለብሱ (ማቴ. 7፥15) … ጃፒ ከኬፋ ሚደቅሳ ጋር ያደረገው ቃለ መጠይቅ ጥሩ ማሳያ ነው[በእርግጥ እንዲህ ዓይነት አባባይ ቃለ መጠይቆች፣ ከዚህ በፊት ብዙ ተደርገዋል]።
“… ኢየሱስ ክርስቶስም ተቃዋሚ ነበረበት፤ ሙሴም
ተቃዋሚ ነበረበት፤ … ሌሎች ትልልቅ ሰዎችም ተቃዋሚ ነበረባቸው”
ይህን
ቃል የተናገረው ዳንኤል ክብረት(“ቀሲስ”) ነው፤ የተናገረበትም ምክንያት፣ ከፋና ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ፣ “ካንተ ጋር የሚነሡ ክሶችን
በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በተዘጋጁ ሰልፎች ላይ ኹሉ፣ ያንተን ፎቶ ኤክስ ምልክት እያደረጉበት ወይም አንተን
እያወገዙ የተቃውሞ ድምጾችን እየሰማን ነው … ምንድነው ምላሽህ?” ለሚለው የሰጠው መልስ ነው። በርግጥ ዳንኤል ይህን መልስ አስተውሎ
ስለ መመለሱ እርግጠኛ ነኝ።
Jechi “maaraanaataa”
jedhu afaan Araamaayik irraa argame; hiikni isaas “yaa Gooftaa! Koottu!” jechuu
dha. Kana kan jedhe ergamaa qulqullu kan ta’e Paawloos dha. Kanas kan jedhe kadhannaa
isaa keessatti. Ergaa tokkooffaa gara warra Qorontoosiitti barreesse gaafa
goolabu ykn xumuru yoo ka’u; dhufaati Kiristoos hawwudhaan ykn bayyee dheeboochuudhaan
kan kadhatee dha.
“ስለ ምንስ መልካም
እንዲመጣ ክፉ አናደርግም? እንዲሁ ይሰድቡናልና አንዳንዱም እንዲሁ እንድንል ይናገራሉና።” (ሮሜ 3፥8)
ክርስትናና ሳይንሳዊ ግኝቶች
ክርስትናና ሳይንስ እርስ
በርሳቸው ጥዩፋን አይደሉም፤ ሳይንስ በብዙ መንገዱ ከእግዚአብሔር ባገኘው ጥበብ፣ መልሶ እግዚአብሔርን ተቃዋሚና ተጠያፊ ቢኾንም፣
ክርስትና ግን ለሳይንስ ፍጹም ጀርባውን የሰጠ አይደለም። ክርስትና ለሳይንስ ጀርባውን የማይሰጠውና በእግዚአብሔር መግቦታዊና ሉዓላዊ
ጌትነት ሥር ኾኖ የሚቀበለው ግን፣ ሳይንስ ለእግዚአብሔር ፍጥረት አክብሮት ሲሰጥና ራሱ እግዚአብሔርን የሚቃወም እስካልኾነ ድረስ
ብቻ ነው። የእግዚአብሔርን ፍጥረት የሚቃወምና ፍጥረት የሚገዛበትን ሥርዓት የሚቃወም እርሱ እግዚአብሔርን ይቃወማልና።
“ያለ እውነት፥ የእውነት ቃል አገልግሎት!?” በሚል ርዕስ፣ ስለ “እውነት
ቃል አገልግሎት” ማኅበር ከታሪካዊ ዳራቸው ጀምሮ፣ ትምህርቶቻቸውን የሚያስቃኘው መጽሐፌ ታትሞ ከቀን 22/7/2013 ጀምሮ ለንባብ
ይበቃል! እንድታነቡት በፍቅር እየጋበዝኩ፣ አስተያየት እንድትሰጡበት፣ አንብባችሁ የማይረባና የማይጠቅም መስሎ ከታያችሁ “ጊዜያችንን
አቃጥለህብናል፤ የማይገባ ድካም ደክመሃል” ብላችሁ ልትወቅሱኝ፣ ፍሬና ቁም ነገር ካገኛችሁበት ደግሞ “ታንጸንበታል፤ በርታ!” ልትሉኝ
ትችላላችሁ።
(የታማኝ ትዳር ውብ ምሳሌ)
መጽሐፍ ቅዱስ፣ እጅግ
አስደናቂ ስለ ኾኑ ሴቶች ካስቀመጠልን ሕያው ምስክር አንዷ አቢግያ ናት፤ እንዲህም የተመሰከረላት፣ “የሴቲቱም
አእምሮ ታላቅ፥ መልክዋም የተዋበ ነበረ፤” (1ሳሙ. 25፥3)። በተቃራኒው አቢግያ የስሙ ትርጓሜ “ጅል” ተብሎ ለሚጠራው
ለናባል ሚስቱ ነበረች፤ እርሱ በምግባሩ “ባለጌ፥ ግብሩም ክፉ ነበረ፤ ከካሌብም ወገን የኾነና
… ምናምንቴና ባለጠጋም ነበረ” (ቊ. 3፡ 25)። ሰውየው ባለጌ፣ ግብረ ክፉ፣ ካሌብ የስሙ ትርጉም “ውሻ” እንደ ኾነ፣ የውሻ
ጠባይ ያለው ሰው ነበረ፤ ከሚስቱ ፍጹም ተቃራኒ ሰው!
ካለፈው የቀጠለ …
ባለፉት ጊዜያት የ“መድሎተ
ጽድቅ” መጽሐፍን በቀጥታ በመጽሐፍ ቅዱስ ከመመዘናችን በፊት፣ በመጽሐፉ ውስጥ ከቅዱሳት መጻሕፍት ዐሳብ ውጭ በኾነ መንገድ እንደ
ገና ተተርጕመው የቀረቡትን ቃላት መመልከት መጀመራችን ይታወሳል። ቃላቱን በተመለከተ ዛሬም ቀጣዩን ክፍል የምናቀርብ ይኾናል። መልካም
ንባብ።
· መዳን፦ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥና በአጭር ቃል ስለ መዳን ሲናገር እንዲህ ይላል፣ “በእርሱ[በክርስቶስ] የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።” (ዮሐ. 3፥16)። በመጽሐፍ ቅዱስ መዳን የሚለው ዐሳብ፣ ልክ በዚህ ክፍል እንደ ተጠቀሰው የዘላለም ሕይወት፣ አዲስ ልደት (ቲቶ 3፥5)፣ አዲሱን ሰው መልበስ (ቈላ. 3፥10)፣ አለመጥፋት (ዮሐ. 3፥16፤ 2ጢሞ. 2፥11)፣ ልጅነት (ሮሜ 8፥13)፣ ዳግመኛ መወለድ (ዮሐ. 1፥12-13፤ 3፥3-8) በሚሉ ተካካይ ዐሳቦች ገልጦት እንመለከታለን።
በእግዚአብሔር ቸርነትና የተትረፈረፈ
ምሕረት፣ ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት በብሎግ ወይም በጡመራ መድረክ አገልግሎት አገልግያለሁ፤ በእነዚህ ዓመታት ከእግዚአብሔር የሰማኋቸውን፣
የተቀበልኳቸውን፣ ቅዱስ ቃሉን ሳነብብና ሳጠና መንፈስ ቅዱስ የገለጠልኝን፣ በኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች የደረሱትን እጅግ አሳዛኝ
ሰቆቃዎችንና ከፍ ያሉ በደሎችን በአካል በስፍራው ተገኝቼ በመመልከት እግዚአብሔር ምን ይሰማው ይኾን? ብዬ ሙሾ አውርጄአለሁ።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የዓቢይ ጾም የመጀመሪያው ሳምንት ስያሜ “ዘወረደ” ወይም “ጾመ ሕርቃል” ይባላል። የመጀመሪያውን ሳምንት
“ዘወረደ” የሚለውን ስያሜ ያገኘው በባለዜማው ያሬድ ሲኾን፣ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ከሰማያት መውረድና የሰዎችን ልጆች ለማዳን
ያደረገውን የውርደት መንገድ በማሰብ፣ ከቅዱሳት መጻሕፍት ንባባት እየተነበበ አምልኮ የሚቀርብበትም ሳምንት ነው። ይኸው ሳምንት
ከዚህ ከጌታችን ባሕርይ ተቃራኒ በኾነ መንገድ “ጾመ ሕርቃል” ተብሎም ይጠራል።
የጾመ ሕርቃል አጭር ጥንተ ታሪክ[1]
መቼም የሐሰት መምህራንን
ጠባይ መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር እንዲህ ይላል፣ “ክፉዎች
ሰዎችና አታላዮች፥ እያሳቱና እየሳቱ፥ በክፋት እየባሱ ይሄዳሉ” (2ጢሞ. 3፥13)። አንድ የስህተት አስተማሪ ፈጥኖ በቅዱስ ፍርሃትና የቅዱሳት መጻሕፍትን
ሥልጣን በማክበር በመታዘዝ ካልተመለሰ፣ እየባሰ፣ እየከፋ፣ ኀጢአቱን እየጨመረ፣ አሳሳችነቱን ይበልጥ እየገፋበት ይሄዳል።
ዘጠነኛ ክፍል እንግሊዘኛ ያስተምሩን አስተማሪያችን ይኅደጐ ይባላሉ፣ ማስተማር
ከመጀመራቸው በፊት ጥቊር ሰሌዳውን በሚገባ ደጋግመው ያጸዱት ነበር፤ አንድ ቀን አንዱ ተማሪ፣ “ቲቸር ለምን እንዲህ ውልውል አድርገው
በሚገባ ያጸዱታል?” ብሎ ጠየቃቸው፤ እነርሱም፣ “በሚገባ ባልታጠበ ትሪ ምግብ ትበላለህ?” ብለው ጥያቄውን በጥያቄ መለሱለት። እኔም
ዛሬ ሳስተምር፣ እንደ ቀደመው አስተማሪዬ በሚገባ መወልወልን ልማዴ አድርጌ አስቀርቼዋለሁ። ወደ ክርስትና ስመጣ የእኒህ አስተማሪ
“መርህ” በዋዛ የሚታለፍ አይደለም።