Sunday, 27 June 2021

ሰዶማዊነትን፣ ፖፑ ሊፈቅዱ ይችላሉን?

 Please read in PDF

ፖፕ ፍራንሲስ ከቅርብ ጊዜ በፊት ስለ ሰዶማውያውን፣ “ማኅበራዊ መብቶች” መናገራቸውን አንዘነጋም። ዛሬ ደግሞ በጻፉት ደብዳቤአቸው፣ “ለእግዚአብሔር ሥራ ሰዶማውያን ጭምር ሊሾሙ እንደሚገባ” መግለጣቸውን ዋሽንግተን ፖስት ደብዳቤአቸውን ዋቢ አድርጎ ዘግቦአል።[1] በእርግጥ በክፋት ከተያዘው ዓለም፣ ቀኖቹ እየባሱ፣ የሚያስቱትም የሚስቱትም እየበዙ እንደሚሄዱ ቅዱስ ቃሉ በማስጠንቀቂያ ጭምር ነግሮናልና፣ ክፉውና ዓመጸኛው ዓለም በክፋቱና በዓመጻው እጅግ መባሱ አያስደንቅም!



መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ ቃል፣ “ከሴትም ጋር እንደምትተኛ ከወንድ ጋር አትተኛ፤ ጸያፍ ነገር ነውና።” (ዘሌ. 18፥22፤ 20፥13) ደግሞም፣ “እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ። እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤” (ሮሜ 1፥27-28) ይለናል።

በሃይማኖታዊ ግብዝነት የታጀሉ አገልጋዮች፣ ለእግዚአብሔር እውነትና ለወንጌል ጽድቅ ፈጽሞ የሚመቹ አይደሉም፤ በእርግጥ ፖፑ የሚናገሩአቸው ቃሎችና የሚሰጡት ትእዛዛት ልክ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ቃላት፣ ቅቡል ሊኾኑ እንደሚችሉ በቤተ እምነቱ የታመነ ነው። በተለይም ወደ አንድ ቢሊዮን የሚጠጋ አማኞች ያሉአት ካቶሊክ፣ ከቫቲካን የሚወጣው የትኛውም መመሪያ በእኩል መልኩ በካርዲናሎች አማካይነት የሚፈጸምባት “ቤተ ክርስቲያን”፣ የሉሲፈርን ዐሳብ ለማስፈጸም መጨከንዋ እጅግ ያስደነግጣል፤ ምናልባት ጨክነው ይህን ዓመጽ የሚቃወሙና “የድፍረት ዓመጽ ነው!” ብለው ለቅዱስ ቃሉ የሚቆሙ ካርዲናሎች ይነሱ ይኾንን? ጌታ ለምድሪቱና ለ“ቤተ ክርስቲያኒቱ” ምሕረት ያድርግ፤ አሜን።

ዘወትር መዘንጋት የሌለብን እውነት ግን፣ መጽሐፍ ቅዱስ ከቤተ ክርስቲያን በላይ ነው፤ ምክንያቱም ቅዱሳት መጻሕፍት የሥልጣን ምንጫቸው እግዚአብሔር ራሱ እንጂ፣ የትኛውም የፍጡር እጅ ወይም ዐሳብ አይደለምና፤ የእግዚአብሔር ቃሎች የታመኑ ናቸው፤ ቃሉ ጥዩፍና ርኩስ፤ ዓመጽና ክፋት ያላቸውም ኀጢአቶች፣ በምንም መርኅ ትክክልና እውነት ሊኾኑ አይችሉም፤ እግዚአብሔርና ቃሎቹ ብቻ ለዘላለም ትክክልና እውነት ናቸው!

የቤተ ክርስቲያን ቅድስና ለሚገዳችሁ ወገኖች ኹሉ ይህ መልእክቴ ነው፤ ስተው ከሚያስቱ፤ ዓመጻን፣ እውነትና ትክክል ለማድረግ ከሚጥሩ ኀጢአተኛ ደፋር አገልጋዮች ተጠበቁ፤ መሲሑ በመጣ ጊዜ አለነውር ኾናችሁ በፊት መቆም ይኾንላችሁ ዘንድ ራሳችሁን በቅድስና ብቻ አጊጡ!

“ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ባለመጥፋት ከሚወዱ ሁሉ ጋር ጸጋ ይሁን፤ አሜን።” (ኤፌ. 6፥24)


3 comments:

  1. አንተም በወንጌል ስም አዳራሽ በጊታር ስትጨፍር ውለህ እያደርክ ወንጌል ሠበኩ ወንጌል አደረስኩ ትላለህ አራሙቻ።የኚህን አባት ቅንጣት ታክል አገልግሎትም ተቀባይነትም የለህም አንከፍ።

    ReplyDelete
  2. አንተ ክቡር የእግዚአብሔር ሰው ነህ ተባረክልን ያብዛህ በእውነት

    ReplyDelete
  3. እኛ የምናመልከው ከሰማየ ሰማያት የወረደውን ከድንግል ማርያም የተወለደውን በቀራንዮ አደባባይ ተሰቅሎ ያዳነንን፡ነው።
    አንተ የምታመልከው የአሜሪካ ባለሃብቶች ና አውቆ አበዶች የመሰረቱትን እየሱስ ።

    ReplyDelete