የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሐዳስያን ከምትወቀስባቸው “ወቀሳዎች” አንዱ፣
ከፖለቲካው ወይም ከቤተ መንግሥት ጋር የነበራት ግንኙነት ነው። ላለፉት 1600 ዓመታት ያህል ቤተ ክርስቲያኒቱና ቤተ መንግሥቱ
ሊነጣጠሉ እስከማይችሉ በሚመስል መንገድ አንድ ላይ ነበሩ። ይህ ሊስተባበል የማይችል ሐቅ ነው፤ በረጅም ዘመን ታሪኳ
ሳትከፋፈልና ወንጌልና “በመስበክ” መቆየትዋ እየደነቀን፣ ለብዙዎቻችን እግዚአብሔርን ለማክበርም፤ ብሎም ብዙ ዕድፏን እያየን
ደግሞ አንገት ለመድፋት፤ ለመተከዝ የተገደድንበት ብዙ ጊዜም አለ!
Monday, 31 July 2023
ቅልወጣ የማይርቀው “ሃይማኖታችን”ና ፖለቲካ
Tuesday, 25 July 2023
ከእሳት የሚያድን፤ በእሳት የሚጠብቅም አምላክ አለን!
እሳት በመጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ዓይነት መንገድ ተገልጦአል። ለኹላችንም ግልጥ የኾነው እሳት፣ ሰዎች ለመሥዋዕት
አገልግሎት (ዘሌ. 6፥13፤ 1ነገ. 18፥38፤ 2ዜና. 7፥1-3)፣ ለምግብ ማብሰያ (ዮሐ. 21፥9)፣ ለብረት ማቅለጫና
(ዘጸ. 32፥24) ለሌሎችም አገልግሎት የሚውል ነው። ይህን እሳት ዓላውያን ነገሥታት አንዳንድ ጊዜ በእነርሱ ላይ
ለተነሣሱባቸው ሰዎች፣ የፍርድ መቀጣጫ አድርገው ይጠቀማሉ። ንጉሥ ናቡከደነጾር፣ ለእርሱ ምስል ወይም ጣዖት አልሰግድም ያሉትን
ሦስቱን ወጣቶች፣ “… ያስሩ ዘንድ፥ ወደሚነድድም ወደ እቶን እሳት
ይጥሉአቸው ዘንድ በሠራዊቱ ውስጥ ከነበሩት ኃያላን አዘዘ።” (ዳን. 3፥20)።
ነገር ግን ሦስቱን ወጣቶች የእስራኤል አምላክ ያህዌ ኤሎሂም ታደጋቸው፤ አዳናቸውም፤ ከእስራኤል አምላክ ከቅዱሱ እግዚአብሔርም በቀር ሌላ የሚያድን አምላክ እንደሌለ፣ ያ ዓላዊ ንጉሥ እንዲህ ሲል ምስክርነቱን ሰጠ፤ “እኔም እንደዚህ የሚያድን ሌላ አምላክ የለም” (ዳን. 3፥29)፤ በእርግጥም ከእሳት የሚያድን ከእግዚአብሔር በቀር ሌላ እንደሌለና በእሳትም ስለሚያከናውናቸው ተግባራት ቅዱሳት መጻሕፍት በምልአት ይመሰክራሉ፤
Thursday, 20 July 2023
የ“አነቃቂዎቹ” ድንዛዜ!
ዶክተር ወዳጄነህ መሐረነ “አነቃቂ” ንግግር ያቀርባሉ ከሚባሉ ሰዎች መካከል አንዱ ነው። በአነቃቂዎች
ዙሪያ በተደጋጋሚ ለመጻፍ ዐስብና ብዙዎች መልስ በስላቅ፣ በቅኔ፣ በድራማ፣ በ“አሽሙር”፣ በስዕላዊ መንገድ፣ በወግ … መልስ
ስለ ሰጡበት ብዙም መናገር አልፈለግኹም። በእርግጥ “አነቃቂ” እንደ ኾኑ የሚያስቡ አካላት፣ እጅግ በሚያደንቅ መልኩ የሕይወት
ምሳሌነት የሌላቸው (ኹሉም በሚያስብል መልክ ትዳራቸው በፍቺ የተጠናቀቀ፣ ጾታዊ ግንኙነታቸው አኹንም እንኳ ጤናማ ያልኾነ)፣
ነገረ መለኮታዊ ዕሳቤያቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ የማይገጥም፣ ከነባራዊው እውነትና ከማኅበረ ሰቡ መልካም እሴቶች ጋር ፈጽሞ
የማይጣጣም፣ ግለኝነትን የሚያበረታታና መንፈሳዊና ማኅበረ ሰባዊ አንድነትን የሚንድ … አመለካከቶችን በውስጡ ያጨቀ ነው።
Sunday, 16 July 2023
መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፳፬)
ለባለፉት ጥቂት ወራት ያረጋል አበጋዝ የተባለ ሰው በጻፈውና “መድሎተ ጽድቅ” በተባለው መጽሐፉ ላይ፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምላሾችን እየሰጠን መኾናችን ይታወሳል፤ ዛሬም የዚያን ተከታዩን ክፍል እናቀርባለን። በባለፉት ጊዜያት፣ የ“መድሎተ ጽድቅ” ጸሐፊ፣ የመጽሐፍ ቅዱስን ሥልጣን በተደጋጋሚ የሚቃወምበትንና የሚጥስበትን መንገድ እያሳየን መቆየታችን ይታወሳል። አንዳንድ ቦታዎች ላይ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ተቀባይ ቢመስልም፣ ነገር ግን በሌላ ትምህርት ደግሞ ያንኑ የተቀበለውን እውነት መልሶ ሲክድና በሌላ ትምህርት ሲቃወም እንመለከተዋለን፤ ለምሳሌም፦
Monday, 19 June 2023
“ጠላቶቻችሁን ውደዱ” (ማቴ. 5፥43-48)
ጌታችን ኢየሱስ የሚመሠርታት መንግሥት፣ እንደ ሰው ሥርዓትና ትምህርት አይደለችም፤ መንግሥቱ ለፍጹማንና
እርሱን ለሚከተሉ ብቻ የምትገባና የምትሰጥ ናት። ጌታችን ኢየሱስ ስለ መንግሥቱና በመንግሥቱ ውስጥ ተከታዮቹ እንዴትና በምን
መልኩ መመላለስ እንዳለባቸው ሊያስተምራቸው ወደደ፤ ትምህርቱ ባዶ ቃላት አይደሉም፤ ውብና የሕይወት ተስፋዎችን ጭምር የያዙና
በምትመጣውም መንግሥቱ እንዴት መመላለስ እንዳለባቸው በንጉሣዊ ወርቃማ ቃሉ አስተምሮአል።
Sunday, 4 June 2023
የምንጠማው መንፈስ!
“ከበዓሉም በታላቁ በኋለኛው ቀን ኢየሱስ ቆሞ፦ ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ
ይምጣና ይጠጣ። … ይህን ግን በእርሱ የሚያምኑ ሊቀበሉት ስላላቸው ስለ መንፈስ ተናገረ፤ …” (ዮሐ. 7፥37፡ 39)
በአይሁድ ባህል መምህራን የሚያስተምሩት ተቀምጠው ነው፤ ጌታችን ኢየሱስ ግን ከአይሁድ ባህልና ሥርዓት
ወጣ ባለ መንገድ፣ ስለ መንፈስ ቅዱስ ሲናገር፣ ኹሉም ሰው እንዲሰማውና ትኵረት እንዲሰጠው ለማድረግ ፈልጐ ቆሞ ደግሞም “ጮኾ”
(ቍ. 38) ተናገረ። ቆሞና ጮኾ በመናገሩ፣ ከበዓሉ በመጨረሻው ቀን የነበሩት ሕዝቦች ኹሉ እርሱን ለመስማት ችለዋል።
Thursday, 25 May 2023
“ከእነርሱ ተለይቶ ወደ ሰማይ ዐረገ” (ሉቃ. 24፥51)
የጌታችን ኢየሱስ
ክርስቶስን ዕርገት ከዘገቡልን ወንጌላት መካከል ሉቃስ ቀዳሚውና ብቸኛው ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን መካከል ከተነሣ
በኋላ፣ ለአርባ ቀናት ያህል ለደቀ መዛሙርቱ እየተገለጠ ታያቸው፤ በመካከላቸውም ተመላለሰ፤ በመጨረሻም ከሚወዳቸው ደቀ መዛሙርት
ጋር በመኾን ወደሚወዳት ከተማ ቢታንያ ሄደ።
Tuesday, 9 May 2023
ግንቦት ልደታና ቦረንቲቻ አይዛመድ ይኾን?
ቦረንቲቻ፣ በዋቄፈና አስተምህሮ መሠረት፣ በዓመት ኹለት ጊዜ ዋቃን ለማመስገንና ምልጃ ለመጠየቅ (መስከረምና ግንቦት
አከባቢ) በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ የሚከናወን ባህላዊና አምልኮታዊ ሥርዓት[1]
ወይም የሚከበር በዓል ነው። በአርሲ ኦሮሞዎች ዘንድም በቤተሰብ፣ በከብቶቻቸው ላይ የሚመጣቸውን ማናቸውንም ክፉ ነገር
ለማስወገድ ከሚከበሩ በአላት አንዱ ቦረንቲቻ ነው።[2]
ቦረንቲቻ ክብረ ብኵርና ነው፤ የኦሮሞ ኹለቱ የትውልድ ሥርወ ግንዶች ቦረናና በሬንቱ ናቸው። ቦረና ታላቅ እንደ መኾኑ፣ በኦሮሞ
ዘንድ ብኵርና ታላቅ ክብር ስላለው፣ ለቦረና ልዩ ክብር “ቦረንቲቻ” የሚባል በአል ይከበርለታል።[3]
Friday, 21 April 2023
ኀጢአትን ይቅር የማለት ጉዳይ! (ዮሐ. 20፥23)
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ፣ ለደቀ መዛሙርቱ ከሰጣቸው ሥልጣን መካከል አንዱ፣ “ኃጢአታቸውን
ይቅር ያላችኋቸው ሁሉ ይቀርላቸዋል፤ የያዛችሁባቸው ተይዞባቸዋል” (ዮሐ. 20፥23) የሚል ነው፤ ብዙዎች የዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ ዓውዳዊ ትርጕም ለሌላ ነገር ሲጠቀሙበት
ብንመለከትም፣ በቀጥታ ሲተረጐም የሚሰጠን ትርጕም ግን፣ “እናንተ ኀጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ኀጢአታቸው ይቅር ተብሎአል፤
ያላላችኋቸው ግን ይቅር አልተባለም” የሚል ነው።
Saturday, 15 April 2023
የጴጥሮስ ጌታ ዛሬም ይራራል! (ማር. 14፥66-72)
ቅዱስ ማርቆስ፣ ወንጌሉን ሲጽፍ በቅዱስ ጴጥሮስ ላይ ያተኵራል፤ ነገር ግን ከኢየሱስ በላይ አያልቀውም ወይም ከፍ
ከፍ አያደርገውም። ኢየሱስ በተያዘበት ሌሊት ስለ ነበረው ኹኔታ ሲናገር፣ “ጴጥሮስንም፦ ስምዖን ሆይ፥ ተኝተሃልን?
አንዲት ሰዓት ስንኳ ልትተጋ አልቻልህምን?” (ማር.
14፥37) ሲል፣ ሌሎቹ ወንጌላት ግን ኢየሱስ ይህን ጥያቄ ያቀረበው ለኹሉም ደቀ መዛሙርት እንደ ነበር ይናገራሉ (ማቴ.
26፥40፤ ሉቃ. 22፥46)።
Friday, 14 April 2023
Sunday, 9 April 2023
Saturday, 1 April 2023
“የሴት ትሸፈን” ትእዛዝ፣ ለአገልጋዮች ምን መልእክት አለው?
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ከሰጣቸው “ሥርዓታዊ ትእዛዞች” አንዱ፣ “ሴትም ራስዋን
ባትሸፍን ጠጉርዋን ደግሞ ትቆረጥ፤ ለሴት ግን ጠጉርዋን መቆረጥ ወይም መላጨት የሚያሳፍር ከሆነ ራስዋን ትሸፍን።” (1ቆሮ. 11፥6) የሚል ነው። “ሥርዓታዊ ትእዛዙ”፣ በአምልኮ
ሰዓት ሴቶችም “ኾኑ ወንዶች” ተገቢውን ልብስ ለብሰውና የባሕርይ ሥርዓትን መከተል እንዳለባቸው የሚያሳስብ ነው።
Thursday, 30 March 2023
“እርሱ ሊልቅ እኔ ላንስ ይገባል” (ዮሐ. 3፥30)
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኪደተ እግሩ ተመላልሶ ባስተማረበት ወቅት፣ ስለ ራሱ የሰጠውን ምስክርነት የተቀበሉ
ጥቂቶች ናቸው። ምስክርነቱን ያልተቀበሉት እርሱ እውነተኛ ስላልኾነ ሳይኾን፣ ብዙዎች ከኢየሱስ ሕይወትና ትምህርት ይልቅ የጨለማ
ሥራን በመምረጣቸው ነው፤ (ዮሐ. 1፥6-11)። መጽሐፍ እንደሚል፣ ኢየሱስን የደኅንነታቸው ምንጭ አድርገው የተቀበሉ ሰዎች፥
እግዚአብሔር ለዘላለም ለልጆቹ የሚሰጠውን ልዩ ሕይወት ያገኛሉ። ይህን የማይቀበሉ ግን ለዘላለም ፍርድና ቍጣ የሚጠብቃቸው ናቸው።
Saturday, 18 March 2023
ኢየሱስ ጌታ እንደ ኾነ ትመሰክራለህን?
“ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን
እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤” (ሮሜ 10፥9)
ይህን ቃል የተናገረው ታላቁ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ነው፤ የተናገረውም ለሮሜ ቤተ ክርስቲያን
አማኞች ነው። ሐዋርያው ይህን ምስክርነት የሚመሰክረው የመዳንን ታላቅና ብቸኛ መንገድ እያመለከተ ባለበት ክፍል ነው። በሮም ምድር
የቄሳር ጌትነት ገንኖ ይነገር ነበር፣ አማኞች ግን የኢየሱስን ጌትነት በመመስከር ሰማዕታት ኾኑ፤ ምክንያቱም የኢየሱስ ጌትነትን
መቀበልና አለመቀበል፣ ከዘላለም ጉዳያችን ጋር የተያያዘ ነውና።











