ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኪደተ እግሩ ተመላልሶ ባስተማረበት ወቅት፣ ስለ ራሱ የሰጠውን ምስክርነት የተቀበሉ
ጥቂቶች ናቸው። ምስክርነቱን ያልተቀበሉት እርሱ እውነተኛ ስላልኾነ ሳይኾን፣ ብዙዎች ከኢየሱስ ሕይወትና ትምህርት ይልቅ የጨለማ
ሥራን በመምረጣቸው ነው፤ (ዮሐ. 1፥6-11)። መጽሐፍ እንደሚል፣ ኢየሱስን የደኅንነታቸው ምንጭ አድርገው የተቀበሉ ሰዎች፥
እግዚአብሔር ለዘላለም ለልጆቹ የሚሰጠውን ልዩ ሕይወት ያገኛሉ። ይህን የማይቀበሉ ግን ለዘላለም ፍርድና ቍጣ የሚጠብቃቸው ናቸው።
Thursday, 30 March 2023
“እርሱ ሊልቅ እኔ ላንስ ይገባል” (ዮሐ. 3፥30)
Saturday, 18 March 2023
ኢየሱስ ጌታ እንደ ኾነ ትመሰክራለህን?
“ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን
እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤” (ሮሜ 10፥9)
ይህን ቃል የተናገረው ታላቁ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ነው፤ የተናገረውም ለሮሜ ቤተ ክርስቲያን
አማኞች ነው። ሐዋርያው ይህን ምስክርነት የሚመሰክረው የመዳንን ታላቅና ብቸኛ መንገድ እያመለከተ ባለበት ክፍል ነው። በሮም ምድር
የቄሳር ጌትነት ገንኖ ይነገር ነበር፣ አማኞች ግን የኢየሱስን ጌትነት በመመስከር ሰማዕታት ኾኑ፤ ምክንያቱም የኢየሱስ ጌትነትን
መቀበልና አለመቀበል፣ ከዘላለም ጉዳያችን ጋር የተያያዘ ነውና።
Friday, 10 March 2023
የ“ምኵራብ” አገልግሎት ቢቀጥልስ?
የምኵራብ አገልግሎት፣ ባቢሎናዊው ንጉሥ ናቡከደነጾር፣ የአይሁድን መቅደስ አፍርሶ፣ ሕዝቡን ማርኰና አፍልሶ ወደ
ባቢሎን ሲወስድ፣ ሕዝበ እስራኤል ከአምልኮ ማዕከል ከኢየሩሳሌምና ከመቅደሱ ፍጹም በመራቃቸው፣ ለጸሎትና ለማኅበርተኛነት ልዩ
ቤት(ምኵራብ) መሥራትንና በዚያ ጸሎትና ቅዱሳት መጻሕፍትን በማንበብ ለማምለክ ምኵራቦችን አስቀድሞ በባቢሎን ኋላም ደግሞ
በኢየሩሳሌም መሥራት እንደ ጀመሩ ይታመናል፤ (ሕዝ. 11፥16)።[1]
Sunday, 19 February 2023
Saturday, 18 February 2023
የብሔር ተስፋው ምንድር ነው?
እግዚአብሔር አምላክን የምንከተለው ዛሬ የሚታመንና ነገ የሚፈጸም ተስፋ አለው ብለን ስለምናምን ነው። እግዚአብሔርን ብንታመነው የሰጠንን ተስፋ ፈጽሞ ያሳርፈናል፤ “ባናምነው ደግሞ እርሱ የታመነ ሆኖ ይኖራል፤ ራሱን ሊክድ አይችልምና።” (2ጢሞ. 2፥13)፤ እኛ ብንሰናከልና እግዚአብሔርን ብንክድ፣ እግዚአብሔር ጻድቅ ነውና ታማኝ ኾኖ ይኖራል።
Friday, 10 February 2023
“ሰላም ለኹላችሁ ይኹን”
ይህን ቃል
የተናገረው ናዛዜ ኅዙናን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ይህንም ቃል የተናገረው ለተወደዱ ደቀ መዛሙርቱ ነው፤
ጊዜውም ደግሞ እርሱ በሥጋ ሞቱ በአይሁድ እጅ ከተገደለ በኋላና በመቃብር ተቀብሮ፣ ደቀ መዛሙርት ኹላቸውም በፍርሃት ቆፈን
ውስጥ፣ “በመሸ
ጊዜ፥ ደቀ መዛሙርቱ ተሰብስበው በነበሩበት፥ አይሁድን ስለ ፈሩ ደጆቹ ተዘግተው ሳሉ፥ ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቆሞ፦ ሰላም
ለእናንተ ይሁን አላቸው።” (ዮሐ. 20፥19)።
Sunday, 5 February 2023
ለዮናስ ነነዌ፤ ለዮናታን አክሊሉ ኦርቶዶክስ፣ ግድ አይደሉም!
እግዚአብሔር፣ ታላቅ ኀጢአት ሠርታ ስለ ነበረችው ነነዌ ሲናገር እንዲህ ይላል፣ “እኔስ ቀኛቸውንና ግራቸውን የማይለዩ ከመቶ ሀያ ሺህ የሚበልጡ ሰዎችና ብዙ እንስሶች ላሉባት ለታላቂቱ ከተማ ለነነዌ አላዝንምን?” (ዮና. 4፥11)። ዮናስ ምንም እንኳ የእግዚአብሔር ነቢይ የነበረ ቢኾንም፣ ለነነዌ ግን እንጥፍጣፊ ርኀራኄና ሃዘኔታ አለማሳየቱ እጅግ አስደናቂ ነገር ነው። ነቢይነት ሰዎች ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱ በግልጥ የእግዚአብሔርን ዐሳብና ፈቃድ የመናገርን ያህል፣ ስለ ኀጢአት ደግሞ ሲገስጹና ሲቈጡ የእግዚአብሔርን የርኅራኄ ልብ ሳይጥሉና ፍጹም እየሳሱ መኾን ነበረበት።
Friday, 27 January 2023
የአዳዲሶቹ ጳጳሳት ሹመት ስጋት፣ ተስፋዬና ትዝብቴ
ጌታ እግዚአብሔር
በሉዓላዊ አምላክነቱ፣ ክፉውን ነገር ኹሉ ለክብሩ ሊጠቀምበት፣ ወደ በጎ እንደሚያመጣው እናምናለን፤ ኀጢአት እንኳ ከእግዚአብሔር
የሉዓላዊነት ወሰን አልፎ አያውቅም፤ እናም በምድራችን ላይ የምንሰማውን መለያየትና ጥቅመኝነትን ጌታ እግዚአብሔር አጥፍቶ፣
ለሕዝባችን መታነጽና ለክብሩ ታላቅነት እንዲሠራ ከኹሉ በፊት አስቀድመን እንማልዳለን።
አዎን! እግዚአብሔር የፈርዖንን ልበ ደንዳናነት፣ ለሕዝቡ ጥበቃና ትድግና እንደ ተጠቀመበት መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። እግዚአብሔር ሉዓላዊ ነው ስንል፣ በመላለሙ ላይ መጋቢና ሠራዒ፤ አስተዳዳሪና ጌታ ነው እያልን ነው፤ ስለዚህ የምድራችን ነገር የሚገደውና የሚያስብልን ተንከባካቢና ጻድቅ ጌታ አለን ማለታችንም ነው!
Sunday, 22 January 2023
“ጳጳሳቱ”ም እንደ “ጐበዝ አለቃ”
በኢትዮጵያ ፖለቲካ
ታሪክ፣ ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘመናት ለቍጥር በሚታክቱ የጐበዝ አለቆች ሥር ወድቃ ታውቃለች፤ እኒህ የጐበዝ አለቆች “ለሕዝባቸው”
ዘለላ ርኅራኄ የላቸውም፤ ሕዝባቸውን ቆራርሰው ከማስጨነቅ፤ የራሳቸውን ልድልድና ምቹ የዙፋን ሠረገላ ከማመቻቸት የዘለለ፣
ሕዝቡን ሲፈይዱ አልታዩም። እንዲያውም “የሰኞ ገዳይ”፣ “የማክሰኞ መጋቢ” ተባብለው በሳምንቱ ቀናት ላይ ተሿሹመው አስጨናቂ
አስገባሪዎች እንደ ነበሩ ዛሬም ድረስ የምናስተውለው እውነታ ነው።
Wednesday, 18 January 2023
የመንፈስ ቅዱስ እንደ ርግብ መውረድ
በጥምቀት ወራት ከሚነሡት ዐሳቦች መካከል
አንዱ፣ “ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ
በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፤” (ማቴ. 3፥16) የሚለው ቃል ይታወሳል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲጠመቅ፣ መንፈስ ቅዱስ እንደ
ርግብ በጌታችን ላይ ወረደ።
Tuesday, 17 January 2023
መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፳፫)
“በመድሎተ ጽድቅ” መጽሐፍ ውስጥ፣ የመጽሐፍ ቅዱስን ሥልጣን በተመለከተ ጐልተው
የሚታዩትን ስህተቶች በባለፈው ክፍል ከጠቀስናቸው ስህተቶች ባሻገር የሚከተሉትም ይካተቱበታል።
1.2.
የተባለውን በትርጉም በመቃወም፦
የመድሎተ
ጽድቅ ጸሐፊ፣ መዳን በክርስቶስ ብቻ እንዳልኾነና በመዳን ውስጥ እኛም ድርሻ እንዳለን ለማሳየት ከተጠቀመበት ጥቅስ አንዱ እንዲህ
የሚል ነው፤
“ኦርቶዶ ክሳውያን አባቶቻችን የጸጋው ሥጦታ ነጻ(እንዲሁ) የሚሰጥ መኾኑን በአንድ በኩል ፣ የሰውን ነጻ ፈቃድ (ነጻነት)
ደግሞ በሌላ በኩል አስተባብረው በመያዝ ለሰው መዳን የኹለቱ መስተጋብር አስፈላጊ መኾኑን በአጽንዖት ያስተምራሉ። ይህም በቅዱስ
ጳውሎስ ከእርሱ ጋር አብረን የምንሠራ ነንና።” ተብሎ የተገለጸው
ነው(1ቆሮ. 3፥9)”
Friday, 6 January 2023
ጌታዬ ኢየሱስ ለእኔ የተወለደባቸው ምክንያቶች
በምድራችን ላይ
ሲሰሙ ከሚወደዱ ታላላቅ ምሥራቾች ኹሉ፣ የሚልቀውና አቻ የሌለው ምሥራች፣ የጌታችን ኢየሱስ መወለድን የሚያህል ሌላ ምሥራች
የለም! መልአኩ እንዲህ አለ፣ “እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤
ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።”
(ሉቃ. 2፥10-11)፤ ለሰው ኹሉ የሚበቃና ሰውን ኹሉ በእኩል ደስ ማሰኘት የሚችል ምሥራች ከክርስቶስ በቀር አለመኖሩ እንዴት
ይደንቃል!
Saturday, 31 December 2022
“የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባቸው መጻሕፍት ሁሉ - ኒዎኔወስቶስ” (2ጢሞ. 3፥16)
ቅዱስ ጳውሎስ ኹለተኛ ጢሞቴዎስን ሲጽፍ፣ የኑዛዜ ያህል በሞቱ ዋዜማ ነው (4፥6)፤ የሚጽፍለት ደግሞ
“በመንፈስ ለወለደው ልጁ” (1፥2) ቅዱስ ጢሞቴዎስ ነው፤ ለዚህ ተወዳጅ ባላደራ አገልጋይ፣ የቅዱሳት መጻሕፍትን እስትንፋሰ
እግዚአብሔርነት በግልጥ ይጽፍለታል። ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ ክፍል፣ መጽሐፍ ቅዱስን፣ “ቅዱሳት መጻሕፍት” እና የእግዚአብሔር
መንፈስ ያለባቸው መጻሕፍት” በማለት ይጠራቸዋል። “ኒዎኔወስቶስ” የሚለውም የግሪክ ቃል፣ የቅዱሳት መጻሕፍትን የእግዚአብሔር እስትንፋስነት የሚገልጥ ቃል ነው።
Sunday, 25 December 2022
ሄኖክ ኃይሌ(ዲያቆን) ስለ አዋልድ መጻሕፍት ያሳየው ደካማና ጠንካራ ሙግቱ!
ሄኖክ ኃይሌ፣ ስለ ተአምረ ማርያም በጻፈው ኹለተኛ ክፍል ላይ እስካኹን፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ
ቤተ ክርስቲያን፣ አዋልድ መጻሕፍትን (ማለትም ትርጓሜያትን፣ ገድላትን፣ ድርሳናትን፣ መልክዐ መልክዕን፣ ተአምራትን፣ ነገራትን፣
ፍካሬያትን) ለማስተካከልና ለማደስ የተቸገረችበትን ምክንያት ሲጠቅስ እንዲህ ይላል፤
“ … ላለፉት ሠላሳ ዓመታት ያሳተሟቸውና በነጻ ያደሏቸው መጻሕፍት … ክርስቶስን ‘ጨርሶ አታውቂም’
የሚሏትን ከሳሾችዋን በማስታገሥ ሥራ ላይ ተጠምዳ እንድትቆይ ግድ ኾኖባት ቆይቶአል።”
Friday, 16 December 2022
ዮናታዊ ቀበሮነት!
በግልጽ ቃል የዮናታን ዓላማ ቅዱስ ወንጌልን መስበክ አይደለም፤ ዓላማው ቅዱስ ወንጌልን መስበክ ቢኾን
ኖሮ፣ “የቃል እምነት እንቅስቃሴ” ከሚባል ነሁላላ ትምህርት አስቀድሞ ራሱን ባረቀና በጠበቀ ነበር። ነገር ግን ይህ የኑፋቄ
ትምህርቱ እንዳይታወቅበት፣ የኦርቶዶክስን ድርሳንና ገድላት በመንቀፍና በመተቸት “ራሱን ወንጌላዊ አድርጎ ለማቅረብ” ብዙዎችን
ያሞኛል፤ ያጃጅላል።
















