ትምህርተ ሥላሴ የክርስትና ዋነኛ ትምህርት ነው። ጠንቅቀን ካልተረዳን ደግሞ ስተን የምናስትበት ትምህርት ነው። ቅድስት ሥላሴ የእምነት መሠረት እንደ መኾኑ፣ ይህን ትምህርት አለማመን ወይም ከትምህርቱ አንዱን አለመቀበል፣ ከኑፋቄ ያስመድባል። ለዚህ ምሳሌ፦ አርዮስንና መቅዶንዮስን በትምህርተ ሥላሴ ላይ ባመጡት ኑፋቄ መወገዛቸውን የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያስታውሷል።
Friday, 10 November 2023
Saturday, 4 November 2023
Wednesday, 1 November 2023
ነገረ ሥላሴን የምናጠናበት ምክንያት (ክፍል ፭)
ካለፈው ቀጠለ …
4. ስለ ምሥጢረ ሥላሴ ስናጠና ልናስተውላቸው የሚገቡ ቃላት
ቃላትን
በትክክል መረዳት ወይም ትክክለኛ ትርጕማቸውን ማወቅ ወደ እውነተኛ ዕውቀት ያደርሳል። በተለይ ደግሞ ትምህርተ ሥላሴን ስናጠና፣
በጥንቃቄ ልናጠናቸው የሚገቡ ቃላት አሉ። እኒህም፦
4.1.
ሥላሴ፦ በአጭር ቃል፣ “ሥላሴ” የሚለው ቃል በአዲስ
ኪዳን መጻሕፍት ምንባባት ውስጥ የለም። ነገር ግን ለቃሉ ሳይኾን ለትምህርቱ ፍጹም ዕውቅናን እንሰጣለን። ምክንያቱም በቅዱሳት
መጻሕፍት ውስጥ የሥላሴ ትምህርትና መገለጥ በስፋት አለና።
“በግእዝ ቋንቋ ቃሉ “ሦስትነት” ማለት ነውና በትምህርተ
መለኮት ጥቅም ላይ ሲውል በአንዱ በእግዚአብሔር ሦስት አካላት እንዳሉ ያሳስባል። በ2ኛው መቶ ዓመት የአንጾኪያ ጳጳስ የነበረው
ቴዎፍሎስ[1]
በግሪክ ቋንቋ “ትሪአስ” እና ተርቱሊያን[2]
በላቲን ቋንቋ “ትርንታስ” (በእንግሊዘኛ TRINITY) ስለ እግዚአብሔር ሲያስተምሩ፥ አካላት ሦስትነትን ለማመልከት
ተጠቀሙባቸው። ከዚያን ጊዜ ጀምረው የቤተ ክርስቲያን አባቶች በእነዚህ ቃላት እየተጠቀሙ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ለማብራራትና
ለመወሰን ሰፊ ጥረት አደረጉ።”[3]
Tuesday, 24 October 2023
ነገረ ሥላሴን የምናጠናበት ምክንያት (ክፍል ፬)
ካለፈው
ቀጠለ …
3.4. ከሰውም ኾነ ከሌላው ፍጥረት ጋር ያለንን
ግንኙነት የተሻለ ያደርገዋል፤
ሰው ከእግዚአብሔር ጋር በኤደን ገነት በቅድስና ይመላለስ ሳለ፣ ግንኙነቱ ፍጹምና እንከን አልባ ነበር፤ (ዘፍ. 2፥8፡ 15፡ 25)። ነገር ግን ሰው በኀጢአት በወደቀ ጊዜ፣ ኀጢአት የሰውንና የእግዚአብሔርን ግንኙነት አበላሸ። ከዚህም የተነሣ ሰው፣ ወደ ወደቀውና ወደ ተሰበረው ዓለም መጣ፤ እግዚአብሔር ግን ለዘላለም ጸንቶ በሚኖረውና በማይለወጠው የቅድስናና የፍቅር ባሕርይው ጸንቶ አለ፤ (ዘጸ. 3፥14፤ ሚል. 3፥6፤ ኢሳ. 48፥12)።
Friday, 6 October 2023
በአጭሩ፣ ኢሬቻ የዋቄፈታ አማኞች አምልኮአዊ በአል ነው!
በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ የሮማ ቄሳራውያን ያህል፣ ለባህላዊ ሃይማኖት መስፋፋት ታላቅ
አስተዋጽዖ ያደረገ አካልን መጥቀስ አይቻልም። በተለይም እኒህ ነገሥታት ክርስቲያኖችን ለማጥፋት ከተጠቀሙበት መንገድ አንዱ፣
ራሳቸውን እንዲመለኩ በማቅረብና ጣዖታትን እንዲመለኩ አዋጆችን በማውጣት ነው፤ የሚቃወሙአቸውን ኹሉ ደግሞ ያለ አንዳች ርኅራኄ
በመፍጀት ተካካይ የላቸውም።[1]
የኢየሱስን ጌትነት አውጀው፣ የቄሳራውያንን አል ጌትነት መቃወምና ጣዖታትን ፍጹም መጠየፋቸው ለክርስቲያን ወገኖች ብርቱ
የስደትና የሰማዕትነት ዋና ምክንያት ነበር።[2]
በተለይም በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ የቤተ ክርስቲያን የስደት ዘመን ወይም ዘመነ ሰማዕታት በመባል የተጠራበት አንዱ
ምክንያት፣ የክርስቲያኖች ቄሳራዊ አምልኮን፣ ሮማዊና ሌሎችንም ባህላዊ ሃይማኖቶችን መጠየፋቸውና አለመቀበላቸው ነበር።[3]
Wednesday, 4 October 2023
ነገረ ሥላሴን የምናጠናበት ምክንያት (ክፍል ፫)
ካለፈው
ቀጠለ …
3.3. የፍጥረት
ዐላማን መረዳት
እግዚአብሔር፣ በማይቀየረውና ሊለወጥ በማይችለው (ሐ.ሥ. 2፥23)፣ በዘላለም ዕቅዱ (ኤፌ. 3፥10-11)፣ ፍጥረትን የፈጠረው ለራሱ ክብርና ዓላማ ነው። ለራሱ ዓላማ ስለ ፈጠረውም፣ ፍጥረት ክብሩን ያውጃል፤ (ኢሳ. 43፥6-7)። ለዚህም ነው፣ መጽሐፍ ቅዱስ፣ የእግዚአብሔርን ኅልውና ሲያስረዳ፣ “በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።” በማለት ስለ እግዚአብሔር ማብራሪያ ባለመስጠት፣ የፍጥረትን መፈጠር አስደናቂ ተግባር በመተረክ የሚጀምረው። ፍጥረትም የተፈጠረበትን ዓላማ ስለሚያውቅ፣ እግዚአብሔርን ገልጦ ያሳያል፤ ለፈቃዱም በግልጥ ይታዘዛል።
Wednesday, 20 September 2023
ነገረ ሥላሴን የምናጠናበት ምክንያት (ክፍል ፪)
ካለፈው
የቀጠለ …
2.4.
እውነትን በመኖር ለማደግ
እውነተኛ
ዕውቀት አእምሮን ጤናማ ያደርጋል። እውነተኛ ዕውቀትና ጤናማ ትምህርት የሌላቸው ሕይወታቸውና ልምዳቸውም ጤናማ ሊኾን አይችልም።
በክርስትና ትምህርት ስናውቅ እናምናለን፤ ስናምነው ደግሞ የምናውቀው ብዙ አለን። የእምነት ዕድገት የሕይወት፣ የአምልኮና
የመንፈሳዊ ዕድገት ለውጥ ነው።
ቅዱስ ጳውሎስ፣ “የክብር አባት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ።” (ኤፌ. 1፥17) በማለት፣ እግዚአብሔርን በማወቅ እንዲያድጉ የጥበብና የመገለጥ መንፈስ እንዲሰጣቸው ልመና ያቀርባል። ይህም ዕውቀት ከራሱ ከእግዚአብሔር እንጂ ከሌላ ከማንም ሊመጣ እንደማይችልም ጭምር ይናገራል።
Saturday, 16 September 2023
ጥንቆላና ሃይማኖተኝነት!
ከሰሞኑ የስልጤ አከባቢ ጉዳይ አስደምሞኛል። አንድ ቤተ እምነት “በጥንቍልናና መተት፤ በድግምት አማኞቼን ወይም ተከታዮቼን አጥቅተውብኛል” በሚል አስባብ፣ በኦርቶዶክሳውያንና በወንጌላውያን አማኞች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን በምስልም፣ በድምጽም፣ በምስለ ወድምጽም ተመልክቻለሁ።
Monday, 11 September 2023
“ንስሐ ግቡ” (ማቴ. 3፥2)
መጥምቁ ዮሐንስንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን
ከሚያመሳስላቸው የስብከት ርዕሶች ቀዳሚው፣ “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ” የሚለው መንግሥተ ሰማያዊ አዋጅ ነው።
ቅዱስ ማቴዎስ ስለ መጥምቁ ዮሐንስ ሲናገር፣ “በዚያም ወራት … በይሁዳ ምድረ በዳ እየሰበከ መጣ። የስብከቱም ማዕከል
የእግዚአብሔር መንግሥትና ንስሐ ነበር። “ንስሐ” ድርጊታዊ ትርጒሙን ስንመለከት፣ “መመለስ” ማለት ነው። ይህም ከክፉ ድርጊቶች
ኹሉ መመለስ፣ ክፉ ድርጊትን ኹሉ መተው፣ ከክፉ መንገድ ኹሉ ዘወር ማለትና ወደ ክርስቶስ መመለስ የሚል ትርጒምን የያዘ ነው።
Friday, 25 August 2023
ነገረ ሥላሴን የምናጠናበት ምክንያት (ክፍል ፩)
ስመ ሥላሴ ለአማኞች የነገር መጀመሪያም፤ የነገር መጨረሻም ነው፤ “በስመ አብ …” ብሎ የጀመረ አማኝ፣ “ስብሐት ለአብ …” ብሎ መጨረሱ እውነትም፤ እምነትም ነው። ለዚህ ደግሞ ቅዱሳት መጻሕፍት ታላቅ ዋቢ፤ ምስክርም ናቸው። “ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።” (2ቆሮ. 1፥2) ብለው ጀምረው፣ “የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።” (2ቆሮ. 13፥14) ብለው መጨረሳቸው እምነትም፤ የእምነታችን ልምድም ነው።
Wednesday, 23 August 2023
አጵሎሳውያንም፤ ጳውሎሳውያንም ወደ ኢየሱስ ኑ!
በዘመናችን
አገልጋዮችን ማበላለጥ፣ አንዱን አገልጋይ “ጌታ” ሌላውን “ምንዝር” አድርጐ ማቅረብ ልክ እንደ ጳውሎስ ዘመን ያገጠጠ እውነት
ነው። አማኞች የማንም እንዲኾኑ አልተጠሩም፤ በክርስቶስ የተዋጁ አማኞች የክርስቶስ ብቻ እንዲኾኑ የእግዚአብሔር የዘለዓለም
ፈቃዱና ዕቅዱ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ፤ ቀና በሚመስል አመለካከት “እኔ የእገሌ ነኝ” የሚሉትን “እሰይ አበጃችሁ” ሲል
አንመለከትም።
Tuesday, 22 August 2023
የክርስቶስን ትንሣኤ ጥቅሞች
ከሙታን መካከል ስለ መነሣቱ፣ ቅዱሳት መጻሕፍት በምልዓት የሚመሰክሩት ስለ አንዱ
ብቻ ነው፤ እርሱም ክርስቶስ ኢየሱስ። ከክርስቶስ በቀር ከሙታን መካከል የተነሣ እንደ ሌለ ከቅዱሳት መጻሕፍት ባሻገር፣ ሌሎችም
መጻሕፍትም በድፍረት ይመሰክራሉ፤ “ስለዚህም ጌታ … በፈቃዱ ሞተ፤ ከተነሣም በኋላ ዳግመኛ አይሞትም፤
ከትንሣኤው በኋላ ግን ጌታ ይህን አልተናገረም፤ ከሰውም ወገን ማንንም ተነሥ፤ ከመቃብር ውጣ አላለም፤ ዳግመኛ እስከሚመጣባት
ቀን ድረስ ለሰዎች ኹሉ አንድ ኾነው በሚነሡበት ቀን ሙታን ይነሣሉ አላቸው።”
(ሃይማኖተ አበው ዘኤጲፋንዮስ፤ 1988 ዓ.ም፤ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ ምዕ. 59
ክፍል 13 ቊ. 49 ገጽ 209)።
Saturday, 19 August 2023
የጻድቅን ነፍስ የሚሹ ደም አፍሳሾች!
“ዶክተር” መስከረም ትባላለች፤ በደቂቀ እስጢፋኖሳውያን ዙሪያ ስለ ተናገረችው “ፈጠራ ክስ” እጅግ ጥቂት ነገር ማለት ወደድኹ። ... ከጥንት ጀምሮ ደቂቀ እስጢፋኖሳውያን ላይ የማያባራ የስም ማጥፋትና የዓመጽ ውሸት ይሰነዘራል። ምናልባት ግን እንደ ማኅበረ ቅዱሳንና ተከታዮቻቸው፣ ደቂቀ እስጢፋኖስን የሚፈራና በእነርሱ ታሪክ ራሱን አስገብቶ ጻድቅ ሊያደርግ የሚሻ ያለ አይመስለኝም። እስጢፋኖሳውያን ትምህርታቸው የጠራ፣ ሕይወታቸው የተመሰከረ ለመኾኑ ለዘመናት ተዳፍኖ፣ እግዚአብሔር በጊዜው በገለጠው ገድላቸው ላይ በትክክል ሰፍሮ አያሌ አጥኚዎችንና ኦርቶዶክሳውያንን እጅ በአፍ አስጭኖ አስደንቆአል።
Friday, 18 August 2023
Sunday, 6 August 2023
መድሎተ ስሑት ወይስ “መድሎተ ጽድቅ”?! (ክፍል ፳፭)
በባለፉት
ጊዜያት፣ የ“መድሎተ ጽድቅ” ጸሐፊ፣ የመጽሐፍ ቅዱስን ሥልጣን በተደጋጋሚ የሚቃወምበትንና የሚጥስበትን መንገድ እያሳየን መቆየታችን
ይታወሳል። ዛሬም ጸሐፊው እንዴት ባለ መንገድ የመጽሐፍ ቅዱስን ሥልጣን እንደሚጥስና እንደማያከብር ማሳየት እንቀጥላለን።
1.4.
አዋልድ[1] መጻሕፍትን እንደ መጻሕፍተ መለኮታውያት ማቅረብ ወይም ቅዱሳት መጻሕፍትን በአዋልድ መጻሕፍት
ለመተርጐም ማሰብ፦ የ“መድሎተ ጽድቅ” ጸሐፊ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ከዚህ ቀደም እንደ ተናገርነው፣ የሕይወት ቃልን በብቻነቱ መያዙን አይስትም፤
ግን ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ያሉት የሕይወት ቃላት ለማዳን፣ የዘላለም ሕይወት ለመስጠት፣ እውነተኛ የቅድስናና የማናቸውም መልካም
ነገሮች ኹሉ መለኪያና መመሪያዎች ለመኾናቸው በቂዎች ናቸው ብሎ አያምንም።







