Friday, 25 October 2013
Monday, 21 October 2013
ለምን ከደካማው ጋር?
የሰማዩን አለም ቅዱስና ፍጹም
ያደረገው
በዚያ
ያሉ
ሁሉም
ለስሙና
ለፈቃዱ
ብቻ
ስለሚገዙ
ነው፡፡
በቀንና
በሌሊት
ሳያርፉ
የሰማዩን
ዓለም
በምስጋና
ችቦ
የሚያፈኩት
በፊታቸው
የተገለጠች
በጎ
ፈቃዱን
መቀደስ
ምግባቸው
፣ማመስገን
እረፍት
ሆኖላቸው
ነው፡፡በእርግጥም የእግዚአብሔር ፈቃዱ
በሰማይ
የተገለጠች
ናት፡፡"ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች… እንዲል ታላቁ
የህይወት
መዝገብ፡፡(ማቴ.6÷10)
ምድር
ግን
መልካምነትና
በጎነት
የበዛበት
ይህን
ፈቃዱን
፣ከማለዳ
እስከማለዳ
የተዘረጋ
ቅዱስ
ምሪቱን
በኃጢአትዋ
ከመካከልዋ
አሰደደችው፡፡ስለዚህም በክፉዎችና በአስጨናቂዎች ተያዘች፡፡ህይወት የደገሰላትን ትልቁን ጌታ
ትታ
ሞት
የሠረገላትን
ተራ
ባርያ
ዲያብሎስን
ሰምታ
እንዲያስጨንቃት
በላይዋ
ሾመችው፡፡ስለዚህም ሲቻለው በግልጥ አልያ
ደግሞ
የተለያዩ
መንገዶችን
በመጠቀም
ለክፉ
ሐሳቡና
ምኞቱ
ያጠምደናል፡፡
እኛ
ክርስቲያኖች
የጌታ
ፈቃድ
ብቻ
የነገሰባትን
ያቺን
የጽዮን
ተራራ
ለመውረስ
የምንጓዝ
የዘወትር
መንገደኞች
ነን፡፡በተሰፈረ
እድሜ
የማይሰፈርና
መጠኑና
ይዘቱ
ሊለካ
የማይቻለውን
በረከትና
ህይወት
ለመውረስ
በቀንና
ማታ
የምንቃትት
ነን፡፡ክፉ
ገዢ
ካለባት
ከዚህች
ምድር
ወደሚያሰማራን
ጌታ
ለመጓዝ
የምንፋጠን
፣በተስፋ
የምንናፍቅ
ደጅም
የምንጠና
ነን፡፡
ከሁሉ
ይልቅ
ደግሞ
አንድ
ትልቅ
እውነት
ተረድተናል፡፡ጠላታችን መናፍስት መሆናቸውንና ተግዳሮታቸውም ውስብስብ መሆኑን፡፡ደግሞ አለሙ
ሁሉ
በክፋት
እንደተያዘም
በሚገባ
እናውቃለን፡፡
(1ዮሐ.5÷19)
ስለዚህም
ሰልፋችንና
ውጊያችን
ከአጋንንትና
ከጨለማው
አለም
ገዢዎችና
አለቆች
ጋር
ነው፡፡
ከሥጋና
ከደም
ጋር
ሳይሆን
ከነዚህ
በዓይን
ከማይታዩ
አዕላፍና
ልምድ
ካላቸው
መናፍስት
ጋር
ነው፡፡(ኤፌ.6÷12)
Thursday, 17 October 2013
እጅጉን ቀላል ናት
ከባድማ አይደለም የማይቻል ነገር
በፍቅር የታዘዝነው የጌታችን ወንጌል
በጣት 'ማይነካ አስቸጋሪና ጭንቅ
አይደለችም ወንጌል የአምላካችን መንገድ፡፡
ከባዱ ሌላ ነው እጅግ አስጨናቂው
Monday, 14 October 2013
የቱ ይበልጥብናል?
Please read in PDF
ስለመብለጥ ሚዛናችንን ከቅዱስ ቃሉ አንጻር ካላየንና ብልጫነትን ከሌላ ነገር ተነስተን የምንመዝን ከሆነ በቅጽበት እድሜ ቃሉ ያልፈቀደውንና ፈጽሞ የማይወደውን ሚዛን እናበጃለን፡፡በዓለም ላይ ከሚገመተው ቁጥር በላይ የሆነው ሰው የሚዋደቅለትና አብዝቶ የሚመኘው ነገር ቢኖር ብልጫነትን ወይም መብለጥን ነው፡፡መቼም ለመልካምና እግዚአብሔር በሚወደው ነገር በቅዱስ ቅንአት ማደግና መጎልመስን ከዚህ እንደማናያይዘው ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ምክንያቱም በክርስትና ትምህርት ባደግን፣በቤቱ በኖርን ቁጥር መብለጣችንን ሳይሆን በተወደደ ትህትና አለልክ ዝቅ ብለን ሁሉን ማገልገል እንዲገባን እንቆጥራለን እንጂ በአንዳች እንኳ የምንበልጥበት እንዳለን በልባችን ሐሳብ አይገባንም፡፡

በእርግጥ ዛሬ ለምጽፋት "ትንስዬ" ጭብጤ ይህን
ብዬ ተንደረደርኩ እንጂ ዋና ሐሳቤ
ሌላ ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ የመስዋዕትን ህግ ለሙሴ ሲሰጠው
የተናገረውን ብዙ ጊዜ እንዲህ
ሲገለጥ እወደዋለሁ ፦ "ለእንሰሳ ቀንዱ ካልከረከረ፣ጠጉሩ ካላረረ፣ጥፍሩ ካልዘረዘረ
ከንጹህና ከተወደደው መካከል መርጦ" ፣ለእህል ቁርባኑ ደግሞ "ነቀዝ
ካልበላው ፣ወፍ ካልጠረጠረው፣ እንክርዳድ ከሌለው ከሰባውና "ከመልካም ዱቄቱ" መባሉን
አብዝቼ እወደዋለሁ፡፡በእርግጥ ቃሉም ይህን በሚገባ
ይገልጠዋል፡፡
እግዚአብሔር የብሉይ ኪዳኑን የሞትና የኩነኔ አገልግሎቱን እንኳ እንዴት ባለ ክብር
እንደወደደ እዩ!! እንኪያስ በደሙ የከበረውና
የመንፈስና የጽድቅ አገልግሎት የሆነው የምህረቱ ዘመን አገልግሎት እንዴት ባለክብር ይበልጥ ይሆን?እንደከበረው
ምርጡና ውድ መስዋዕት ሆኖ የቀረበውን
ትልቁና ዋናውን ነገር ቅዱስ ጳውሎስ
እንዲህ ብሎ ይገልጥልናል ፦
Wednesday, 9 October 2013
ስውር አገልጋዮች
Please read in PDF
ርዕሰ መምህራን ኢየሱስ ክርስቶስ ህዝብ ወደተሰበሰበበት ቦታ በመሔድ ያስተምር እንደነበር አራቱ ወንጌላውያን በህብረት ዘግበውታል፡፡ በለቅሶ ቤት ፣በገበያ ቦታ ፣በምኩራብና በመቅደስ ፣በባህር ዳርቻ፣በሠርግ ቤትና በሌሎች ስፍራዎች ከሳሾች እስኪገረሙና እስኪደነቁ ፣ኃጥአን እስኪጽናኑና እስኪመለሱ፣ ጻድቃን በልባቸው የመንፈስ ቅዱስ ሐሴትና ደስታ እስኪመላና እስኪበዛ ፣ትዕቢተኞች እስኪገሰጹና በሥራቸው እስኪያፍሩ … ያለከልካይ በግልጥ ያስተምር ነበር፡፡ዛሬ በሚያሳዝን መልኩ ለአብዛኛዎቹ አገልጋዮች እንደክስ ምክንያት የሚሆነው ከቤተ መቅደስ ውጪ የሚሰጡት አገልግሎት ነው፡፡በየቤቱ ተሰባስቦ ለሚደረገው የሥጋ ግብዣና ተራ ወሬ ከልካይ ሳይኖርበት ቃለ ወንጌል ለመነጋገርና ለመወያየት ሲሆን ግን ከሌላ ነገር ጋር በግድ ማያያዝ ጠማማነት እንጂ ሌላ ምንም ትርጉም አይሰጠውም፡፡ በእርግጥ አንዳንዶች ይህን አገልግሎት ለኃጢአት አውለውታል፤ ነገር ግን ከኀጢአተኞች ተነስቶ ጻድቁንም መንቀፍ በእግዚአብሔር ዘንድ አጸያፊ ነው፡፡

የአደባባይ አገልግሎት በነፍስ መወራረድን የሚጠይቅ ፣የተገለጠ የምስክርነት ህይወትን ያዘለና ጥንቃቄና ማስተዋልን የሚሻ
የአገልግሎት አንዱ ክፍል ነው፡፡ የአደባባይ አገልጋዮች የተራቆተ ገላ ናቸው፡፡ ሁለንተናቸው መሰወር የማይችል፡፡ የሰገነት መብራቶች
ናቸው በሁሉም ዘንድ የሚታዩ፡፡ ጌታ ለዚህ አገልግሎት አስራ ሁለት
ደቀ መዛሙርት ሲመርጥ ሌሎች ሰባ ሁለት ረዳት ወንድሞችና ሰላሳ ስድስት ምርጥ እህቶችም አብረው ነበሩ፡፡
Sunday, 6 October 2013
Friday, 4 October 2013
ዮሴፋዊው ጻድቅነት ሲወገዝ
የማቴዎስ ወንጌል ምዕ.1÷19
ስናነብ አንድ ጻድቅ ሰው ሲጨነቅና ለሚበልጠው ለእግዚአብሔር ሐሳብ ሲሸነፍ ፣ሲገዛም እናያለን፡፡እንደኦሪት ህግ አንዲት ሴት ከሌላ
ሰው ባል(ወንድ) ወይም ከባልንጀራዋ ባል ጋር ብታመነዝር ሁለቱም በአንድነት እንዲገደሉ (ዘሌ.20÷10) ህጉ ይፈቅዳል፡፡ ህጉ
በራሱ ከሳሽ ነውና ከሳሾች አስፈልገውታል፡፡ ህጉ አንዳች ኃይል ሳይሰጠን እንድንፈጽመው ያስገድደናል፡፡ በዚህም "በደልም
እንዲበዛ ህግ ጭምር ገባ" (ሮሜ.5÷20) ይለናል ቃሉ፡፡
በህጉ መሰረት የተከሰሰን መክሰስ ኦሪታዊነት ነው፡፡ ምክንያቱም ህጉም
ይህንኑ ይላልና፡፡ የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ቅንና በጎ ብትሆንም ሰዎች ግን ሊፈጽሟት ባለመቻላቸው ኃጢአት የምትጨምርና ሁላችንን ኃጢአተኞች
ብላ ልካችንን የምትነግረን ሆናለች፡፡በአንዱ አዳም ህግ መተላለፍ ምክንያት ሁላችን በእርሱ ክስ ተከሰን ኃጢአተኞች ተብለናል፡፡
ዮሴፍ በህጉ መሰረት በቂ ምክንያት አለው፡፡እመቤታችን ቅድስት ድንግል
ማርያም ያለወንድ ዘር ጌታ ኢየሱስን ጸንሳ ተገኝታለች፡፡በህጉ መሰረት ያለወንድ ዘር የጸነሰች ሴት ፈጽማ ልትገደል ይገባታል፡፡ይህንን
ዮሴፍ ቢያሳውቅ አይሁድ ስራቸው ከቃየል እንደተማሩት ድንጋይ ጨብጦ መንጋጋት መሆኑን ዮሴፍ ያውቀዋል፡፡ስለዚህ "ጻድቅ ሆኖ ሊገልጣት ስላልወደደ
በስውር ሊተዋት አሰበ። "፡፡የክርስቶስ
ደም ሳይፈስና ኦሪት ሳትሻር ከህጉ በላይ ጻድቅ የሆነ ብርቱ ሰው ዮሴፍ ተገኘ፤ የቅድስቲቱን "እንደህጉ" አለመጽነስ
በመግለጥና በመክሰስ ሳይሆን ሊገልጥ ሳይወድ በስውር በመተው፡፡የሐዲስ ኪዳን ታላቅና ልዩ መገለጥ!!!
Tuesday, 1 October 2013
ተፈስሒ ፍስህት
የኢየሱስ እናቱ እጅግ ደስ ይበልሽ
ተወዳጅ አማኑኤል ፀጋ ስለሰጠሽ
ደስ ይበልሽ
ደስታን ጮኸሽ ተናገሪ
ስለመድኃኒትሽ በእልልታ ዘምሪ
አንቺ የእምነት እናት ደገኛ ሙሽራ
የተሠራሽ በእጁ ለቅዱሱ ሥራ
በእምነት ትከሻ አካላዊ ቃልን
በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የማይቻለውን
ይዘሽ የታየሽው ገሊላዊት ድንግል
ደስ ይበልሽ ፍጹም ደስታ ይገባሻል
Subscribe to:
Posts (Atom)