Wednesday, 23 March 2022

ይድረስ ለፓስተር ቸሬ!

 Please read in PDF

“ኢየሱስን መንፈስ ቅዱስ ብቻ እንጂ ሥጋና ደም አይገልጠውም!”

“ኦርቶዶክሶች ማርያም ካለቻቸው እንዴት ኢየሱስ የላቸውም ብለህ አሰብህ? … ።” (ከፓስተር ቸሬ ንግግር የተወሰደ)

ፓስተር ቸሬ፣ “ኤጳፍራ ቤተ ክርስቲያን” በሚባል ከወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት በአንዱ፣ የሚያገለግል አገልጋይ ነው። አገልጋዩ በትዳር እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮችና በስህተት መምህራን ላይ በሚናገራቸው ንግግሮቹ በአብዛኛው ይታወቃል። እኔም በበኩሌ የተወሰኑ ትምህርቶቹን ለመከታተል ጥረት አድርጌ፣ በተወሰነ መንገድ ተጠቅሜበታለሁ። አገልጋዩ በትዳር ጉዳዮች ላይ ባለው ትምህርቱ ቢቀጥል፣ እጅግ ትርፋማ ይኾናል ብዬም ገምታለሁ። ከሰሞኑ ግን “ለኦርቶዶክሳውያን ወንጌል መሰበክ የለበትም፤ ያውቁታል” የሚል መልእክት ያለው ንግግር ማሰማቱን ሰምቼ ይህን ለመጻፍ ተገደድሁ።

ኢየሱስን ያወቅነው በማርያም አይደለም!

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በግልጥ ቃል እንዲህ ይላል፦ “ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፥ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም።” (ማቴ. 11፥27) ይህ ማለት፣ ስለ ጌታችን ኢየሱስ፣ ከአብ በቀር በሰማይም ኾነ በምድር ሊያውቅ የሚችል አንዳችም የሰማይም የምድርም አካል የለም፤ ማርያም ጭምር። ስለ አብም ቢኾን፣ “መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው።” (ዮሐ. 1፥18) ከተባለለት ከኢየሱስ በቀር ያወቀው፤ ሊያውቀውም የሚቻለው ሌላ ማንም የለም። ምክንያቱም፣ አብ የሚያውቀውን ኹሉ ወልድ ያውቃል፤ ወልድ የሚያውቀውንም ኹሉ አብ ያውቃል፤ እነርሱ በመለኮት፣ በፈቃድ፣ በዕውቀት፣ በዐሳብ አንድ ናቸውና (ዮሐ. 10፥30)።

ቅዱስ አብ፣ ስለ ኢየሱስ ካልገለጠለት በቀር፣ ኢየሱስን ማወቅ የሚቻለው ማንም የለም። አብ የገለጠለት ብቻ ኢየሱስን በትክክል ያውቀዋል። ቅዱስ ጴጥሮስ የኢየሱስን የእግዚአብሔር ልጅነት ሲመሰክር፣ ጌታችን ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ።” (ማቴ. 16፥17)፤ አዎን፤ ኢየሱስን ማወቅ የሚቻለው አብ የገለጠለት ብቻ ነው፤ ወይም አብ በገዛ ፈቃዱ የመረጠው ብቻ ነው።

ኢየሱስ፤ አብን የሚያውቀውን ዕውቀት ላመኑት ኹሉ ይገልጣል፤ “ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ለእናንተ አስታውቄአችኋለሁና።” (ዮሐ. 15፥15) እንዲል። እግዚአብሔርን ያወቅነው በእርሱ ዘንድ የነበረው አንድያ ልጁ መጥቶ፣ ስለ ነገረንና ስለ ተረከልን ነው። ያለ ኢየሱስ አብን አናውቀውም፤ ያለ አብም ወልድን ማወቅ የሚቻለው ማንም የለም። ሰዎች ያለ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እናውቃለን ቢሉ፣ በፍጹም ሐሰተኞች ናቸው። እግዚአብሔር ራሱን የገለጠውና እንዲታወቅም የወደደው በልጁ በኩል ብቻ ነውና። መንፈስ ቅዱስ፣ ኢየሱስን ከሚያምኑት ጋር የሚሠራው ታላቁ ሥራ፣ አንድያ ልጅ ኢየሱስን ማስተማርና መግለጥ ነው፤ (ዮሐ. 14፥17፡ 26)፤ ኢየሱስ ወደ ሰማያት ካረገ በኋላ፣ ኢየሱስን የሚገልጠው መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው፤ ይህን ቦታ ማርያም ፈጽሞ ልትተካው አትችልም።

ስለ እግዚአብሔር ከኢየሱስ በቀር እውነተኛ አምላክነቱን የነገረን የለም፤ “በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤” (ቈላ. 2፥9) እንዲል፣ በሥጋ የተገለጠው አምላክ ወልደ አምላክ ወልድ፣ እርሱ የእግዚአብሔር ሙላት ነው። እግዚአብሔርንና ባሕርያቱን ያወቅነው፣ በፍጹሙና እንከን አልባ በኾነው መምህር በክርስቶስ ነው። አዎን፤ በሥጋ የተገለጠው ክርስቶስ፤ እግዚአብሔር ነው፤ ስለዚህም ከእርሱ በቀር በሙላት እግዚአብሔር ያወቀው የሚያውቀውም የለም። ስለ ክርስትናም ቢኾን መሲሑ መጥቶ፣ ባይነግረን ክርስትና የሚባል ሃይማኖት ባልኖረ ነበረ። አዎን፤ “ … የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል እኔም እወደዋለሁ ራሴንም እገልጥለታለሁ።” (ዮሐ. 14፥21) እንዲል፣ ኢየሱስን የሚነግረን ራሱ ኢየሱስና መንፈሱ ብቻ ናቸው።

ከዚህ የተነሣ የማርያም መኖር፣ የክርስቶስን መኖር አይተካም፤ እርስዋ ባልነበረችባቸው ወራት እርሱ ነበረ፤ እርሷንም በሞት አሳልፎ፣ ዛሬም በሕያውነት ያለው ክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ ነው። ደግሞም እርሱ በር በኾነበት እርሷ ፈጽሞ ቁልፍ ልትኾን አትችልም፤ ይልቁን መጽሐፍ በግልጥ ቃል፣ “እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።” (ራእ. 1፥18) ብሎ፣ የሕይወትና የሞት መክፈቻ ያለው እርሱ ብቻ መኾኑን መስክሮአል።

የኦርቶዶክሳውያን ማርያም!

ፓስተር ቸሬ እንደሚለው፣ የኢየሱስ እናት ማርያም ሳትኾን፣ ሌላዋ ማርያማ ናት በኦርቶዶክስ ቤት የምትመለከው። በግልጥ ስለ ማርያምና ስለ መስቀል እንዲህ ይባላል፤ “ለእሉ ክሌቱ ፍጡራን ስብሐተ ፈጣሪ ይደልዎሙ እስመ ተአረዩ በክብሮሙ።” ትርጉም፦ “ለነዚህ ለሁለቱ ፍጡራን ለማርያምና ለመስቀል የፈጣሪ ምስጋና[አምልኮ] ይገባቸዋል። በክብር ከፈጣሪ ጋር እኩል ሆነዋልና” [መስተብቍዕ ዘመስቀል]። ፓስተር ቸሬ፤ እንዲህ የምትመለከው ማርያም ወደ ተወዳጁ መሲሕ ታደርሳለች ብለህ ታምናለህን? ወይስ ይህች ማርያም ከመጽሐፍ ቅዱሷ ማርያም ጋር አንድ እንደ ኾነች ታስባለህን?

በቅርቡ የተመሠረተው ማኅበረ ቅዱሳን የተባለው ድርጅት፣ በሚጽፈው ጽሑፍ ኹሉ መደምደሚያ ላይ እንዲህ ይላል፦ “ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር፤” ትርጉም፦ ለእግዚአብሔር፣ ለማርያምና ለመስቀል ምስጋና ይገባል” ማለት ነው። ፓስተር ቸሬ ይሰማሃል አይደል? እኮ ይህን ነው፤ ማርያም አላቸውና ኢየሱስ አለቻቸው የምትለው? ለመኾኑ በዚያ ቤት፣ ኢየሱስ በወርቀ ደሙ የመሠረተው አዲስ ኪዳን ተሽሮ፣ የማርያም “ኪዳነ ምሕረትነት” እንደሚሰበክ ታውቅ ይኾን?

አዎንታዊ ምልከታ!

በእርግጥ ቤቱ ሙሉውን ጨለማ ነው አንልም፤ በዚያ ጥቂት ብርሃን አለ ብለን ተስፋ እናደርጋለን፤ ያም ብርሃን በመንፈስ ቅዱስና በቃሉ ብርሃን አብዝቶ ቦግ ይልና ይበራ ዘንድ በጸሎት፣ በምልጃ፣ በቅዱስ ቃሉ ምስክርነት እንተጋለን። ነገር ግን በዚያ የቅዱስ ቃሉ ሥልጣን በምልአት አለ፤ የመጽሐፍ ቅዱሷ ማርያም በዚያ አለች፤ የኢየሱስ መካከለኝነት በድፍረት ይሰበካል፤ የተሸቀጠው ወንጌል አይሰበክም፤ የፍጡራን መካከለኝነት(የማርያም፣ የአርሴማ፣ የተክለ ሃይማኖት፣ የጊዮርጊስ …) አልገነነም፤ አይሰበክም ብለን ግን የፈጠጠውን እውነት አንክድም። በዚያ በትክክል ቅዱሱ ወንጌል ተገፍቶአልና!

ማጠቃለያ!

ፓስተር ቸሬ ሆይ፤ ይህን ንግግር በዚያም መንደር ተቀባይነትን ለማግኘት ተናግረኸው ከኾነ እጅግ ያሳዝናል፤ ነገር ግን በተላላነትና ባለመጠንቀቅ ከኾነ ግን ታስተካክላለህ ብለን ተስፋ እናደርጋለን። በዚያ ያለችው ማርያም፤ የማትመለክ እንዳይመስልህ፤ እኩል ከፈጣሪ ጋር በስብሐተ ነግህና በኪዳኑ፤ በሰዓታትና በማኅሌቱ እንክት አድርጋ ትመለካለች፤ ትወደሳለች፤ ከፈጣሪ ጋር አምለኮ ትጋራለች። ይህ ቤተ ክርስቲያኒቱን ያከሰረ የጨለማ መንገድ ነው። ነገር ግን ለመሲሑ እንዲህ ተብሎለታል፤ “መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።” (ራእ. 5፥9-10)። አሜን፤ ብቸኛው በራችንና የሕይወትን ቁልፍና መክፈቻ የያዝኸው አዳኛችን ኢየሱስ ሆይ፤ ብቻህን እናመልክሃለን፤ እንገዛልሃለን፤ አሜን።

3 comments:

  1. ሙሉ መልዕክቱን እንመልከተው!

    https://youtu.be/ddDze3rMFvo

    ReplyDelete
  2. Tewahedo fare enough
    wanaw yemenesemamabet yehnen naw bezih ketmamenene hulum selam naw

    "some so-called reformers mistakenly believe that the problem of our church is the faith itself"

    NO IT'S NOT
    i agree

    ReplyDelete
  3. We need both Christ and the saints because of our weakness and sinful life. Again, the reason we need the saints is not that the blood of Christ is insufficient, but rather because we are sinful/weak and need their help in our struggle against satan. Yes, for those who are always in Christ and follow His words, they don't have any condemnation, but eternal life. Yes, all those who believe in Christ and abide by His words are saints according to the Bible. However, the question is: do you consider yourself equivalent to the saints? Do you think your prayers are heard as much as those of the saints? For example, St George suffered a lot and died multiple times for the sake of Christ. Do you think you and this martyr have equal status in the kingdom of God or in the face of God?
    If you are certain that you are fully and completely following the word of God, then you don't need any saint to pray for you. However, I know my weakness and sinful life, I need the prayers of the saints and their blessings to perfect my salvation. Again, their intercession is not a replacement for the blood of Christ. One of the problems of menafiqans is that they read what is not written while they skip or gloss over what is written. Please re-read what i have written. Even if the saints are not the true medicine, they are sometimes called as the medicine because of their role in bringing us to the true medicine, Christ Jesus. I have given a number of examples from the Bible, but you don't want to read. Another example from our day to day life. People who get healed from a serious disease would always praise the Medical Doctor who may have prescribed the medicine as their healer while we know the healer is the TABLET/MEDICINE that the doctor may have prescribed. The doctor is being praised for the work of the medicine, like a guy who got healed after taking LIPITOR would praise the doc who gave him the LIPITOR that truely did the healing. Similarly, the medicine is Christ and the Doctors are the saints who would prescribe to us Christ as the medicine. Do you think we don't need the doctors, in our case the saints?
    Even the saints request other Christians to pray for them. If you read the epistles of St. Paul, he always asks Christians to pray for him so that he can aggressively disseminate the message of the Gospel. Are you better than St. Paul? You be the judge...
    As to me, I am the weakest of the weaks and always need the support and blessings of the saints. I believe Christ is always there to help me, but I annoy Him with my sins and the prayers of the saints will get me his patience and merci - get saved from judgment. Do you know Christ would spit you out if you fail to abide by His words and become lukewarm? The prayers of the saints would help us not to be spit out or not to be lukewarm... I would have wanted to write a longer piece, but few words are enough for a believing heart and a wise person....

    ReplyDelete