Tuesday, 2 September 2025

ማደግ ነዉ!

 Please read in PDF

አንድ ናፍቆት አለኝ ከውስጤ ʻማይወጣ፣

ማለዳ ስነቃ ታድሶ ʻሚመጣ፣

በፊህ ስንጓደድ ዓይኖቼን ሳቀና፣

በልቤ ተቀምጦ ላንደበቴ የቀና!

አለኝ የማልረሳው ቀና ስል ወዳንተ፣

ሌላ እንዳልቀላቅል ልቤን የከተተ፤

የፀሎቴ ርዕስ ዘወትር ምናፍቀው

ዕለት ዕለት ጌታ ወደ አንተ ማደግ ነው።

(ምንጭ - ሰላም ሰላም ከሚል ከፊት ገጽ የተወሰደ)

No comments:

Post a Comment